አጠቃላይ ጉባኤ
በመስቀል ላይ ተሰቀለ
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


በመስቀል ላይ ተሰቀለ

የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ መሆን አንዳንድ ጊዜ ሸክምን መሸከም እና መስዋዕትነት የግድ ወደሚሆንበት እንዲሁም መከራ ወደማይቀርበት ቦታ መሄድን ይጠይቃል።

ከዓመታት በፊት በአሜሪካ የሀይማኖት ታሪክ ላይ የማስተርስ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውይይትን ተከትሎ፣ አንድ ተማሪ “ለምንድን ነው ሌሎች ቤተክርስቲያናት እንደ የእምነታቸው ምልክት የሚጠቀሙትን መስቀል የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የማይጠቀሙት?” ብሎ ጠየቀኝ።

እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎች ብዙውን ጊዜ ለክርስቶስ ስላለን ቆራጥነት ጥያቄ ስለሚሆን፣ ወዲያውኑ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ እንደ መአከላዊ እውነታ፣ ወሳኙ መሰረት፣ ዋናው ትምህርት እና እግዚአብሔር ለልጆቹ ደህንነት ባለው ታላቅ ዕቅድ ውስጥ መለኮታዊ ፍቅር መገለጫ እንደሆነ እንደምታስብ ነገርኩት።1 በዚያ ተግር ውስጥ ያለው የደህንነት ፀጋ ጠቃሚ እንደነበር እና ለመላ የሰው ዘር ከአዳም እና ሔዋን ጀምሮ እስከ ዓለም መጨረሻ በስጦታ እንደተሰጠ ገለፅኩኝ።2 ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝን እንዲህ ጠቀስኩኝ፣ “ሀማኖታችንን የሚመለከቱት ሁሉም ነገሮች” ለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ “ቅጥያዎች ናቸው”።3

ከዚያም ኔፊ ከኢየሱስ ወልደት ከ600 ዓመታት በፊት የፃፈውን አነበብኩለት። ፦ መልአኩ እንዲህ ሲል ተናገረ ተመልከት!“ እኔም ተመለከትኩ እናም የእግዚአብሄርን በግ፣ , … “ለዓለም ኃጢያት በመስቀል ላይ ሲሰቀልና ሲገደል ተመለከትኩ።”4

በእኔ “ውደድ፣ አካፍል፣ እና ጋብዝ” ከፍተኛ ፍላጎት፣ ማንበቤን ቀጠልኩኝ! ከሞት የተነሳው ክርስቶስ በአዲሱ ዓለም ይኖሩ ለነበሩት ኔፋውያን እንዲህ አላቸው “አባቴም በመስቀል እሰቀል ዘንድ ልኮኛል፤… ሁሉን ሰዎች ወደ እኔ አመጣ ዘንድ፣ … እናም ለዚህም ምክንያት ተሰቀልኩኝ።”5

ሐዋርያው ጳውሎስን ልጠቅስ ስል የጓደኛዬ አይኖች እየደከሙ ሲመጡ ተገነዘብኩኝ። የእጅ ሰዓቱን በፍጥነት መመልከቱ የሆነ ቦታ ማንኛውም ቦታ መሆን እንዳለበት አስታወሰው—እና ወደ ምናባዊ ቀጠሮው ገሰገሰ። ስለሆነም ንግግራችን ተቋጨ።

በዚህ ጠዋት ከ50 ዓመታት በኋላ፣ ያንን ገለፃ ለመጨረስ ቆርጬ ተነስቻለው—ምንም እንኳን እያንዳንዳችሁ የእጅ ሰዓታችሁን ብትመለከቱም። መስቀሉን ለምን እንደማንጠቀም ስገልፅ፣ በእምነት መሞላት እና ህይወታቸውን በመለገስ ይህን ለሚጠቀሙ ሰዎች ያለንን ጥልቅ ክብር እና ከፍተኛ አድናቆት ግልፅ ማድረግ እፈልጋው።

መስቀሉን እንደ ምልክት የማናተኩርበት አንዱ ምክንያት የመጣው ከመጽሐፍ ቅዱስ የተነሳ ነው። ስቅለት በሮሜ ግዛት ከነበሩት ታላቅ አሰቃቂ ቅጣቶች አንዱ ስለነበር፣ ብዙዎቹ ቀደምት የኢየሱስ ተከታዮች በዚያ አሰቃቂ መሳሪያ ላይ ላለማተኮር መረጡ። የክርስቶስ ሞት ትርጉም ለእምነታቸው በእርግጥ ማዕከላዊ ነበር፣ ነገር ግን ለተወሰኑ ሶስት መቶ ዓመታት የወንጌል ማንነታቸውን በተለየ መልክ ለመግለፅ ፈለጉ።6

በአራተኛው እና በአምስተኛው መቶ አመታት፣ መስቀል እንደ አጠቃላይ ክርስቲያንነት ምልክት ተዋወቀ፣ ነገር ግን የእኛ “አጠቃላይ ክርስቲያንነት” አይደለም። ካቶሊክ ወይም ፕሮቴስታንት ሳንሆን፣ እኛ በዳግም የተመለሰ ቤተክርስቲያን፣ በዳግም የተመለሰ የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ነን። ስለሆነም፣ መነሻችን እና ስልጣናችን ከሸንጎዎች፣ ከሀይማኖቶች እና አዶዎችን በፊት የነበሩ ናቸው።7 በኋላ እየተለመደ የመጣው ምልክት አለመኖሩ፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ትክክለኛ የክርስቲያን መጀመሪያዎች መመለሻ እንደሆነች ሌላኛው ማረጋገጫ ነው።

የአዶ መስቀሎችን የማንጠቀምበት ሌላኛው ምክንያት በክርስቶስ ሙሉ ታማራታዊ ተልዕኮ፣ እንዲሁም ግርማዊው ትንሳኤው እና የስቃዩ መስዋዕትና ሞት ስለምናተኩር ነው። ያን ግንኙነት ላይ በማተኮር፣ ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለት ሐዋርያት ምልዓተ ጉባኤ በየሐሙስ ቀን በሶልት ሌክ ከተማ በቅዱስ ሳምንታዊ የቤተመቅደስ ስብሰባቸው ውስጥ እንደ ምስል በስተጀርባ የሚጠቀሙትን ሁለት የስነ ጥበብ ስራዎችን አመለከታለሁ8። እነዚህ ገላጭ ምስሎች የእርሱ አገልጋዮች ለሆንነው የተከፈለውን ዋጋ እና በእርሱ ስለተገኘው ድል ለእኛ የማያቋርጥ ማሳሰቢያ ሆነው ያገለግላሉ።

ምስል
ስቅለት፣ በሃሪ አንደርሰን
ምስል
ትንሳኤው፣ በሃሪ አንደርሰን

ከሞት የተነሳው ክርስቶስ ስቅለቱን የሚያረጋገጥ ቁስልን በማሳየት ከመቃብር በክብር የወጣውን ትንሳኤ በሚያሳየው በዚህች ትንሽ የቶርቫልድሰን ምስል መጠቀማችን የክርስቶስን ባለሁለት ክፍል ድል የበለጠ ህዝባዊ ውክልናችን ነው።9

ምስል
የቤተክርስቲያን አርማ

በመጨረሻም፣ ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ አንድ ጊዜ ያስተማሩትን እናስታውስ፣ “የህዝባችን ህይወቶች የእምነታችን ምሳሌ መሆን አለባቸው።”10 እነዚህ እይታዎች--በተለይም የመጨረሻው--ስለ መስቀል በጣም አስፈላጊ ወደሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ይወስደኛል። በአንገት ጌጥ ወይም ጌጣጌጥ፣ ከቤተክርስቲያኗ ጉልላት ወይም ከመንገድ ምልክቶችን የተያያዘ አይደለም። ክርስቲያኖች ኢየሱስ ለእያንዳንዱ ደቀመዛሙርቱ የሰጠውን ጥሪ የሚያመጡበትን ታማኝነት እና ቆራጥነት ይመለከታል። በየትኛውም አገር እና የእድሜ ክልል ውስጥ ለምንገኝ ለሁላችንም እንዲህ ብሏል “በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።”11

ይህ የሚናገረው ስለምንሸከመው መስቀሎች እንጂ ስለምንለብሰው አይደለም። የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ መሆን አንዳንድ ጊዜ የራሳችሁን ወይም የሌላውን ሸክም መሸከም እና መስዋዕትነት የግድ ወደሚሆንበት እንዲሁም መከራ ወደማይቀርበት ቦታ መሄድን ይጠይቃል። እውነተኛ ክርስቲያን እሱ ወይም እሷ በሚስማሙበት ነገሮች ብቻ መምህርን መከተል አይችሉም። አይደለም። በሁሉም ቦታ፣ አንድ አንድ ጊዜ ብቻችን ልንቆም በምንችልበት ቦታም፣ አስፈላጊ ከሆነ በለቅሶ እና ችግር በተሞላበት ስፍራ ጭምር እንከተለዋለን።

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እና ውጪ ክርስቶስን በአማኝነት እየተከተሉ ያሉ ሰዎችን አውቃለው። ብዙ የአካል ጉድለት ያለባቸውን ልጆች አውቃለው እና እነሱን የሚንከባከቡ ወላጆቻቸውንም አውቃለው። አንዳንዴ ሁሉም እስኪደክሙ ድረስ ሲሰሩ፣ ጥንካሬን፣ ደህንነትን፣ እና በሌላ መንገድ የማይመጣን ደስታ ሲሹ አያለው። አፍቃሪ አጋርን፣ ድንቅ ትዳርን እና በልጅ የተሞላ ቤትን የሚፈልጉ እና የሚገባቸው ብዙ ያላገቡ ጎልማሶችን አውቃለሁ። ከዚህ የበለጠ ምንም ፍላጎት ፃድቅ አይሆንም፣ ነገር ግን ከዓመት ወደ ዓመት ይህ መልካም እድል አይመጣም። ቃል ለተገባው ለስሜታዊ መረጋጋት በመጸለይ እርዳታን የሚለምኑ በብዙ ዓይነት የአዕምሮ በሽታን የሚታገሉ ሰዎችን አውቃለው። በአድካሚ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ነገር ግን ተስፋ ሳይቆርጡ፣ ለሚወዱት እና በዙሪያቸው ላሉ ሰዎች ህይወትን የተሻለ ለማድረግ እድል የሚጠይቁ ሰዎችን አውቃለው። በማንነት፣ በፆታ እና የፆታ ፍላጎት ጉዳዮች ላይ የሚታገሉ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ። የውሳኔዎቻቸው ውጤቶች መም ያህል አስፈላጊ ሊሆኑ እንደሚችሉ በማወቅ ለእነርሱ ከእነሱ ጋር አነባለው።

እነዚህ በህይወታችን ውስጥ ሊያጋጥሙን ከሚችሉት በርካታ ፈታኝ ሁኔታዎች መካከል ጥቂቶቹ፣ የደቀመዝሙርነት ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንካራ ማሳሰቢያዎች ናቸው። ንጉሥ ዳዊት፣ ለሚቃጠል መስዋዕት በሬዎች እና እንጨት በነጻ ሊሰጠው ለሞከረው ለኦርናን እንዳለው፣ “እንዲህ አይደለም፣ ነገር ግን በዋጋ ከአንተ እገዛለው፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መስዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም።”12 ስለሆነም ሁላችንም እንዲህ እንላለን።

መስቀላችንን ስንሸከም እና እርሱን ስንከተል፣ የፈተናዎቻችን ክብደት ሌሎች ለተሸከሟቸው ሸክሞች የበለጠ አዛኝ እና በቅርበት ትኩረት የምንሰጥ ካላደረገን በእርግጥ አሳዛኝ ይሆናል። የአዳኙ እጆች ተዘርግተው በምስማር መመታታቸው የስቅለቱ ከፍተኛ ተፃራሪ ነገር ነው፣ ነገር ግን ሁሉም በመላው የሰው ዘር ውስጥ ያለ ሰው፣ ሴት እና ልጅ በእርሱ የቤዛነት እቅፍ ውስጥ ተቀባይነት ያላቸው መሆኑ ብቻ ሳይሆን እንደተጋበዙም በግልፅ የሚያሳይ ምልክት ነው።13

ክብራማው ትንሳኤ አሰቃቂውን ስቅለቱን ሲከተል፣ ፍቃደኛ በሆኑ ሰዎች ላይ በረከቶች በየአይነቱ ፈሰሱ፣ የመጽሐፈ ሞርሞን ነብይ ያዕቆብ እንደሚለው “በክርስቶስ እመኑ እና ሞቱን ተገንዘቡ እና የመስቀሉን ስቃይ ተቀበሉ።”15 አንዳንድ ጊዜ እነዚህ በረከቶች ቶሎ ይመጣሉ፣ አንድ አንድ ጊዜ ደግሞ ይዘገያሉ፣ ነገር ግን ለግላዊ አስቸጋሪ መንገዳችን14 አስደናቂው መደምደሚያ መምህሩ ራሱ እንደሚመጡ የሰጠን የተስፋ ቃል ነው። እነዚህን በረከቶች ለመቀበል፣ ተስፋ ሳንቆርጥ፣ ሳንደክም ወይም ሳንሸሽ፣ በስራ ላይ ሳናሾፍ፣ መስቀሎቻችን ቢከብዱ እና መንገዱ ለትንሽ ጊዜ ቢጨልምም እንኳን እርሱን እንከተለዋለን። ለጥንካሬያችሁ ታማኝነታችሁ አእና ፍቅራችሁ ጥልቅ የሆነ ግላዊ ምስጋና እሰጣለው። በዚህ ቀን ስለ “ተሰቀለው” 15 እናም ከእርሱ ጋር “ለተሰቀሉት” ስለ ሰጣቸው የዘላለም በረከቶች ስለ እርሱ የሐዋርያ ምስክርነቴን እመሰክራለው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ጀፍሪአር ሆላንድ፣ “Encyclopedia of Mormonism፣” (1992 እ.አ.አ)፣ “Atonement of Jesus Christ፣” 1፥83

  2. አሙሌቅ ስለ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ እንደ “ታላቅ እና የመጨረሻ መስዋትነት” እና “ማለቂያ የሌለው እና ዘላለማዊ” እንደሆነ ይናገራል (አልማ 34፥10)። ምክንያቱም “ሁሉም ወድቀዋልና ጠፍተዋል፣ እናም መፈጸሙ አስፈላጊ ከሆነው ከኃጢያት ክፍያ በቀር መጥፋት አለባቸው” (አልማ 34፥9፤ እንዲሁም ቁጥሮች 8–12 ይመልከቱ)። ፕሬዘደንት ጆን ቴይለር እንዲህ ጨመሩ፦ “ ኢየሱስ የኃጢያትን ሸክም ለመላ ዓለም ተሸከመ፣ ለአዳም ብቻ ሳይሆን ለትውልዶቹ በሙሉ እናም ያንን በማድረግ የሰማይን መንግስት ከፈተ፣ ለአማኞች እና የእግዚአብሔርን ህግ ለሚታዘዙት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከግማሽ በላይ ለሚሆኑ ከማደጋቸው በፊት ለሞቱት የሰው ዘር፣ እንዲሁም ህግ ሳይኖራቸው ለሞቱት እና በእርሱ አማላጅነት ከሞት ካለ ህግ ለተነሱት እና ካለ ህግ ለተዳኙት በሙሉ በኃጢያት ክፍያው ተባርከዋል” (An Examination into and an Elucidation of the Great Principle of the Mediation and Atonement of Our Lord and Savior Jesus Christ [1892 (እ.አ.አ)]፣ 148–49; የቤተክርስቲያኗ ፕሬዝዳንቶች ትምህርቶች፦ ጆን ቴይለር [2001 (እ.አ.አ)]፣ 52–53)።

  3. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [2007 (እ.አ.አ)]፣ 49።

  4. 1 ኔፊ 11፥32–33

  5. 3 ኔፊ 27፥14–15

  6. በእርግጥ በጳውሎስ ትምህርቶች ውስጥ ስለ መስቀሉ ተጠቅሷል (ለምሳሌ 1 ቆሮንጦስ 1፥17–18ገላትያ 6፥14ፊልጵስዮስ 3፥18)፣ ነገር ግን እነዚህ ስለ ሁለት እንጨቶች በጋራ በሚስማር ከመመታታቸው በበለጠ ይናገራሉ። ስለሆነም፣ ጳውሎስ ስለ መስቀሉ ሲናገር፣ ስለ የሃጢያት ክፍያውን ታላቅነት ለመናገር ትምህርት እየተጠቀመ ነው፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የሚስማሙበት እና የሚጠቅሱት ቦታ ነው።

  7. የቀደምት እና ባህላዊ ክርስቲያኖች እንደ ማርቲን ሉተርን አንድሪያስ ካርለሰታድት (1486-1541 እ.አ.አ) ጨምሮ “ስቅለቱ” የክርስቶስን ስቃይ ብቻ እንደሚያሳይ እና የእርሱን የትንሳኤ እና የቤዛነት ኃይሎች ችላ እንደሚል ተከራክረዋል። (in John Hilton III, Considering the Cross: How Calvary Connects Us with Christ [2021], 17).

  8. ሄሪ አንደርሰን፣ The Crucifixion፤ እና ሄሪ አንደርሰን፣ Mary and the Resurrected Lord.

  9. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ሰማያትን ለእርዳታ መክፈት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣70-74 ይመልከቱ።

  10. ጎርደንቢ. ሂንክሊ፣ “The Symbol of Christ፣” ኢንሳይን፣ ግንቦት 1975 (እ.አ.አ)፣ 92።

  11. ማቴዎስ 16፥24

  12. 2 ሳሙኤል 24፥24

  13. “ንስሃ ለሚገቡ ሰዎችና በስሙ ለሚያምኑት ህዝብ ሁሉ ክንዱ ተዘርግቷል” (አልማ 19፥362 ኔፊ 26፥33አልማ 5፥33)።

  14. Via dolorosa የላቲን ሃረግ ነው ትርጉሙም “በጣም አስቸጋሪ ጉዞ፣ መንገድ፣ ወይም ቀጣይነት ያላቸው የልምዶች” ማለት ነው” (Merriam-Webster.com መዝገበ ቃላት፣ “via dolorosa፣” ነሐሴ 16 ቀን 2022 (እ.አ.አ) ብዙውን ጊዜ በጲላጦስ እጅ ለመሰቀል ከተፈረደበት አንስቶ እስከ በቀራንዮ ስቅለቱ ካለው የኢየሱስ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ነው።

  15. 3ኛ ኔፊ 27፥14–15 ይመልከቱ።

አትም