ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥር 13–19 (እ.አ.አ)፦ “የብርሃን አምድ … ተመለከትኩ”፦ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥1–26


“ጥር 13–19 (እ.አ.አ)፦ “የብርሃን አምድ … ተመለከትኩ”፦ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥1–26፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥1–26፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ቅዱስ ጥሻ

ቅዱስ ጥሻ፣ በግሬግ ኬ. ኦልሰን

“ጥር 13–19 (እ.አ.አ)፦ “የብርሃን አምድ … ተመለከትኩ”

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥1–26

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች የጸሎቶችን መልስ የያዘ መጽሃፍ ነው ልትሉ ትችላላችሁ፦ በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ የተቀደሱ ራዕዮች የተገኙት ለጥያቄዎች ከተሰጠ ምላሽ ነው። የኋለኛውን ቀን የራዕይ ፍሰት የቀሰቀሰውን ይህንን ሁሉ የጀመረው ጥያቄ የተጠየቀው በ14 ዓመት ልጅ ነው። “የቃላት ጦርነት እና የአስተያየቶች ሁካታ”፣ (የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥10) ጆሴፍ ስሚዝ በሃይማኖት እና ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት ግራ እንዲጋባ አድርገውት ነበር። ምናልባት፣ ይህ እናንተንም ሊመለከት ይችላል። በዘመናችን የሚጣረሱ ሃሳቦችን እና አሳማኝ ድምጾችን እንሰማለን። እነዚህን መልዕክቶች በመፈተሽ እውነትን ለማግኘት በምንፈልግበት ጊዜ፣ ጆሴፍ እንዳደረገው ማድረግ እንችላለን። ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት፣ ማሰላሰል፣ እና በመጨረሻም እግዚአብሔርን መጠየቅ እንችላለን። ለጆሴፍ ስሚዝ ጸሎት ምላሽም የብርሃን አምድ ከሰማይ ወረደ። እግዚአብሔር አብ እና ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጡና ጥያቄዎቹን መለሱ። የጆሴፍ ስሚዝ ተዓምራዊ ተሞክሮ ምስክርነት ማንም “ጥበብ [ቢጎድለው] እግዚአብሔርን [መጠየቅ] [እንደሚችል] እናም [እንደማይነቀፍ]” (የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥26) በአፅንዖት ያውጃል። በሰማያዊ ራዕይ መልክ ባይሆንም እንኳን፣ ሁላችንም በሰማይ ብርሃን የተሞላ የላቀ ግንዛቤን ልንቀበል እንችላለን።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥5–26

ጆሴፍ ስሚዝ የዳግም መመለሱ ነቢይ ነው።

የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ አላማ ለእኛ “ተጨባጭ ነገሮችን ለመስጠት” ነበር፣ ምክንያቱም ስለ ጆሴፍ ያለው እውነታ ብዙውን ጊዜ የተዛባ ስለሆነ ነው (ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥1)። የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥1–26ን ስታነቡ፣ ስለእርሱ መለኮታዊ ጥሪ ያላችሁን ምስክርነት የሚያጠነክረው ምንድን ነው?

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥3–19ን ተመልከቱ።

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥5–25

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
ለፀሎቶቼ መልሶችን ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?

“ጥበብ ጎድሏችሁ” ወይንም ልታደርጉ ስለሚገባችሁ ውሳኔ ግራ ተጋብታችሁ ታውቃላችሁ? (የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥13)። ጆሴፍ ስሚዝ በ1820 (እ.አ.አ) የነበረው ተሞክሮ የራሳችሁን የግል ራዕይ ለመቀበል ጥሩ መንገድ በመሆን ሊያገለግል ይችላል። ለምሳሌ፣ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥5–25ን ስታነቡ፣ ከእናንተ ጋር የሚዛመዱ ተሞክሮዎችን ፈልጉ። ስለሚከተሉት ነገሮች ምን ትማራላችሁ፦

  • ጆሴፍ እንዴት ለቅዱስ ተሞክሮው በፀሎት እንደተዘጋጀ? (ቁጥር 8፥11፣14–15ን ተመልከቱ)።

  • ራዕይን በመፈለግ ውስጥ የቅዱሳት መፃህፍት ጥናት ስላለው ሚና? (ቁጥር 11–12ን ተመልከቱ)።

  • ተቃውሞ በሚገጥም ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባ? (ቁጥር 15–1621–26ን ተመልከቱ)።

  • የመጡላችሁን መልሶች መቀበል እና ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ (ቁጥር18–25ን ተመልከቱ)።

ማካፈልን ጋብዙ ቅዱሳት መፃህፍትን መመርመር ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጣን ግንዛቤ ይጋብዛል። እነዚህን ግንዛቤዎች ማጋራት፣ መንፈስ ቅዱስ ለሌሎች እንዲሁም ለሚያካፍለው ግለሰብ እንዲመሰክር ሊጋብዘው ይችላል።

The First Vision: A Pattern for Personal Revelation [የመጀመሪያው ራዕይ፦ የግል ራዕይ ንድፍ]” ከተሰኘው የፕሬዚዳንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ ፅሁፍ ምን ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ? (ሊያሆና፣ የካቲት፣ 2020 (እ.አ.አ)፣ 12–17)።

በተጨማሪም በቅዱሳት መፃህፍት ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስለተነጋገሩ ሰዎች ሌሎች ምሳሌዎችን ልትፈልጉም ትችላላችሁ። በየወንጌል የአርት መፅሐፍ ወይንም በሌላ የኑ፣ ተከተሉኝ መፃህፍት ውስጥ ያሉ ምስሎች ሃሳቦችን ሊሰጧችሁ ይችላሉ። ላገኛችሁት ለእያንዳንዱ ምሳሌ ከዚህ በፊት የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ። ለፀሎት መልሶችን የመቀበል ምን ተሞክሮዎች ነበሯችሁ? ሌሎችም ጥሩ ተሞክሮ እንዲያገኙ ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

እንዲሁም ራስል ኤም ኔልሰን፣ “እርሱን ስሙት!፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 88–92፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች “የግል ራዕይ፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥15–20

ጆሴፍ ስሚዝ እግዚአብሔር አብን እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ተመለከተ።

ጆሴፍ ስሚዝ እግዚአብሔር ጸሎቱን እንደሚመልስለት አመነ፣ ነገር ግን ያ መልስ የእርሱን ህይወት እና አለምን እንዴት ሊቀይር እንደሚችል አልገመተም ነበር። ስለ ጆሴፍ ተሞክሮ ስታነቡ፣ የመጀመሪያው ራዕይ ውጤቶች እንዴት አድርገው ህይወታችሁን እንደቀየሩ አሰላስሉ።

ለምሳሌ፣ የመጀመሪያው ራዕይ በጆሴፍ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ብዙ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር አብ እና ስለ ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ያምኗቸው ከነበሩት የተለዩ ብዙ እውነቶችን ገልጿል። የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥15–20ን ስታነቡ “የመጀመሪያው ራዕይ በመምጣቱ ምክንያት … አውቃለሁ” የመሰሉ ዓረፍተ ነገሮችን ለማሟላት በተለያዩ መንገዶች ለመፃፍ አስቡ።

የጆሴፍን ተሞክሮ እና በእሱ ምክንያት የተከሰቱትን ነገሮች ሁሉ ስታሰላስሉ ምን ይሰማችኋል?

በተጨማሪም “እግዚአብሔርን ጠይቁ፥ የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያው ራዕይ፣” (ቪድዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ፤ “Joseph Smith’s First Prayer፣” መዝሙር፣ ቁ. 26።

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ በቅዱስ ጥሻ ውስጥ

ዝርዝር ከIf Any of You Lack Wisdom [ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው]፣ በዋልተር ሬን

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥15–20

ስለመጀመሪያው ራዕይ የተለያዩ ጽሁፎች ያሉት ለምንድን ነው?

ጆሴፍ ስሚዝ በህይወት ሳለ በቅዱስ ጥሻ ውስጥ ያጋጠመውን ተሞክሮ አብዛኛውን ጊዜ ጸሀፊዎችን ተጠቅሞ ቢያንስ አራት ጊዜ ያህል ጽፏል። በተጨማሪም፣ ጆሴፍ ስለ ራዕዩ ሲናገር በሰሙ በሌሎች ሰዎችም ብዙ ፅሁፎች ተጽፈዋል። ምንም እንኳን እነዚህ ጽሁፎች ከፀሃፊዎቹ፣ ከአዳማጮቹና ከሁኔታዎቹ አንጻር በአንዳንድ ዝርዝሮቻቸው ቢለያዩም፣ በጠቅላላው ተመሳሳይ ናቸው። ልክ አራቱ የአዲስ ኪዳን ወንጌሎች የአዳኙን ተልዕኮ በደንብ እንድንገነዘብ እንደሚረዱን ሁሉ፣ እያንዳንዱ ጽሁፍ የጆሴፍ ስሚዝን ተሞክሮ በደንብ እንድንገነዘብ የሚረዱ ዝርዝሮችን ይጨምራል።

በተጨማሪም ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “First Vision Accounts [የመጀመሪያው ራዕይ ታሪኮች]፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥21–26

ሌሎች ባይቀበሉኝም እንኳን፣ ስለማውቀው ነገር በታማኝነት መፅናት እችላለሁ።

ከአስደናቂ የመጀመሪያ ራዕዩ በኋላ ጆሴፍ ስሚዝ ተሞክሮውን ለሌሎች ለማካፈል ፈለገ። የገጠመው ተቃውሞ አስደነቀው። ፅሁፉን ስታነቡ፣ ለምስክርነታችሁ ታማኝ ሆናችሁ እንድትቆዩ የሚያነሳሳችሁ ምንድን ነው? ከቅዱሳት መጻህፍት፣ ከቅድመ ዓያታችሁ ወይም ከምታውቋቸው ሰዎች ላገኛችሁት መንፈሳዊ ተሞክሮ ታምናችሁ እንድትቆዩ ድፍረትን የሚሰጧችሁ ሌሎች ምሳሌዎች ምን ምን ናቸው?

በተጨማሪም ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን፣ “Nourishing and Bearing Your Testimony [ምስክርነታችሁን መንከባከብ እና መካፈል]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 111–14 ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥3–14

ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚአብሔር ነቢይ ለመሆን ተዘጋጅቶ ነበር።

  • ልጆቻችሁ ስለጆሴፍ ስሚዝ የወጣትነት ጊዜ ማወቃቸው ከእርሱ ተሞክሮ በሚማሩበት ጊዜ እንዲያውቁት እና እንዲያደንቁት ሊረዳቸው ይችላል። ምናልባት የጆሴፍ ስሚዝን ምስል ሊይዙና ስለእርሱ የሚያውቁትን ሊያካፍሉ ይችላሉ። አስፈላጊ ከሆነ፣ ስለእርሱ አንዳንድ እውነቶችን ከየጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥3–14 ውስጥ ልትጨምሩ ትችላላችሁ (በተጨማሪም “Chapter 1: Joseph Smith and His Family [ምዕራፍ 1፦ ጆሴፍ ስሚዝ እና ቤተሰቡ]፣” በDoctrine and Covenants Stories [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 6–8 ውስጥ፣ ወይም የሱን ተዛማጅ ቪዲዮ በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ)። ጆሴፍ ነቢይ ለመሆን እንዲዘጋጅ የረዳው ምን ተሞክሮ አገኘ? እግዚአብሔር ምን እንድናደርግ እያዘጋጀን ሊሆን ይችላል?

ምስል
የጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ እና የመጀመሪያው ራዕይ ሥዕል

ዝርዝር ከJoseph Smith’s First Prayer [የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ጸሎት]፣” ግሬግ ኦልሰን

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥10–13

እግዚአብሔር በቅዱሳት መፃህፍት አማካኝነት ለጥያቄዎቼ መልስ መስጠት ይችላል።

  • ቅዱሳት መፃህፍትን ጨምሮ የተለያዩ መፃህፍትን ለልጆቻችሁ ማሳየትን አስቡ። እነዚህ መፃህፍት ሊመልሷቸው የሚችሏቸውን ጥያቄዎችን እንዲያስቡ እርዷቸው። ጆሴፍ ስሚዝ ስለነበሩት ጥያቄዎች እና በቅዱሳት መፃህፍት ውስጥ ስላገኛቸው መልሶች ለማወቅ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥10–11ን አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ።

  • ልጆቻችሁ ያዕቆብ 1፥5ን ማንበብ በጆሴፍ ላይ ምን ተጽዕኖ እንዳሳደረ የሚገልጹ ቃላትን በቁጥር 12 ላይ ማግኘት ይችሉ ይሆናል። ከዚያም፣ አንድ የቅዱሳት መፃህፍት ምንባብ በእናንተ ላይ ሃይለኛ ተፅዕኖ ያሳደረበትን ተሞክሮዎች አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። እንዲሁም ቅዱሳት መፃህፍትን ስለማንበብ የሚናገር እንደ “Follow the Prophet [ነቢዩን ተከተሉ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 109) ያለ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ። መዝሙሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስለምናነብበት ምክንያት ምን ያስተምራል?

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥10–17

የሰማይ አባት ጸሎቴን ይሰማል እንዲሁም ይመልሳል።

  • ከሰማይ አባት ጋር መነጋገር ስለምንችልበት መንገድ ውይይት ለመጀመር፣ ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ እንደ ፅሁፍ መልዕክት፣ ስልክ ጥሪ ወይም በእጅ የተፃፈ ማስታወሻ ያሉ የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም እርስ በርሳችሁ ጥያቄዎችን መጠያየቅ ትችላላችሁ። የሰማይ አባትን ጥያቄዎች የምንጠይቀው እንዴት ነው? እርሱን እንደምንወደው እና እንደምናከብረው በፀሎታችን የምናሳየው እንዴት ነው? የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥10–17ን በጋራ አንብቡ እና የሰማይ አባት የጆሴፍ ስሚዝን ፀሎት እንዴት እንደመለሰ ተወያዩ። ከዚያም፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ እግዚአብሔርን እርዳታ የጠየቃችሁበትን እና መልስ የተቀበላችሁበትን ተሞክሮዎች ማካፈል ትችላላችሁ።

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥17–19

ጆሴፍ ስሚዝ የሰማይ አባትን እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን አየ።

  • ትንንሽ ልጆችን ስለመጀመሪያው ራዕይ በምትነግሯቸዉ ጊዜ እጆቻቸውን በቅዱስ ጥሻ ውስጥ እንዳሉ ዛፎች አስመስለው በመዘርጋት መቆም ሊያስደስታቸው ይችላል። ስለጆሴፍ መፀለይ በምትናገሩበት ጊዜ ልጆቹ በነፋሱ እንደተገፉ እንዲወዘወዙ ጠይቋቸው። ከዚያም የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ለጆሴፍ እንደተገለጡለት ስትነግሯቸው ባሉበት እንዲቆሙ እና ፀጥ እንዲሉ ጠይቋቸው።

  • ትልልቅ ልጆች ስለመጀመሪያው ራዕይ የሚያውቁትን ለመናገር በዚህ መዘርዝር ውስጥ ካሉት ሥዕሎች ውስጥ አንድ ወይም ከዚያ በላይ መጠቀም ያስደስታቸው ይሆናል። የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥3–14ን እንዲያጣቅሱ እና ስለጆሴፍ ተሞክሮ ያሏቸውን ሃሳቦች እና ስሜቶች እንዲያካፍሉ አበረታቷቸው (በተጨማሪም “Chapter 2: Joseph Smith’s First Vision [ምዕራፍ 2፦ የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ]፣” በDoctrine and Covenants Stories [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 9–12 ውስጥ፣ ወይም የሱን ተዛማጅ ቪዲዮ በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ምስል
የመጀመሪያው ራዕይ ሥዕል

Truth Restored [እውነት በዳግም ተመልሶ]፣ በሌዮን ፓርሰን

ምስል
የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ

አትም