“የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
1817–1820 (እ.አ.አ)
የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ
ለትሕትና ጸሎት የሚሰጥ መልስ
የጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰቦች በሚኖሩበት ቦታ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያስተምሩ ብዙ ቤተክርስቲያኖች ነበሩ። ሁሉም ስለ እርሱ የተለያዩ ነገሮችን አስተማሩ። ጆሴፍ ማንኛቸው ትክክል እንደሆኑ እርግጠኛ አልነበረም። አዳኝ እንደሚያስፈልገው አወቀ፣ ነገር ግን የትኛውን ቤተክርስቲያን መቀላቀል እንዳለበት አላወቀም።
ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥5–6፣ ቅዱሳን፣ 1፥9
ጆሴፍ ስለዚህ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ አሰበ። ኃጢአቱ ይቅር እንዲባልለት ፈለገ። በርካታ ቤተ ክርስቲያኖችን ቢጎበኝም ግራ እንደተጋባ ሆኖ ተሰማው።
ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥8–10፣ ቅዱሳን፣ 1፥9–12
አንድ ቀን ጆሴፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያዕቆብ 1፥5ን አነበበ። ጥበብን ከፈለግን አምላክን መጠየቅ እንደምንችል ይናገራል። ጆሴፍ ማድረግ የሚፈልግው ይህን እንደነበር በልቡ አውቀ።
በ1820 (እ.አ.አ) ወብ ጸደይ ወር ጠዋት ላይ ጆሴፍ ከቤቱ አቅራቢያ ወዳሉት ጫካዎች ገባ። ብቻውን ሆኖ ለሰማይ አባት ለመጸለይ በሚችልበት ቦታ መሆን ፈለገ ።
ጆሴፍም ተንበርክኮ መጸለይ ጀመረ። ልክ በመጸለይ ላይ ሳለ አንድ ክፉ ኃይል ሲይዘው ተሰማው። ዙሪያውን ጨለማ ተሰማው። አንድ ነገር ከአምላክ ጋር እንዳይነጋገር ለማገድ እየሞከረ ያለ ይመስላል። ጆሴፍ፣ አምላክ እንዲያድነው ለመጠየቅ ኃይሉን ሁሉ ተጠቀመ።
በድንገት ጆሴፍ የሚያምር ደማቅ ብርሃን ከሰማይ ሲወርድ ተመለከተ። ጨለማው እራቀው እናም ሰላም ተሰማው። በብርሃን ውስጥ፣ ጆሴፍ የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ በአየር ላይ ቆመው አየ። የሰማይ አባት የጆሴፍን ስም ጠራ። የሰማይ አባት ወደ ኢየሱስ በመጠቆም እንዲህ አለ፣ “ይህ የምወደው ልጄ ነው፡፡ አድምጠው!” አለው።
ኢየሱስ ጆሴፍን ኃጢአቱ ይቅር እንደተባለለት ነገረው። ጆሴፍ ኢየሱስን የትኛውን ቤተ ክርስቲያን መቀላቀል እንዳለበት ጠየቀው። ኢየሱስ አንዳቸውንም ቢሆን መቀላቀል እንደሌለበት ነገረው።
ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥18–19፣ ቅዱሳን፣ 1፥16
ኢየሱስ ስለ ወንጌሉ አስፈላጊ እውነቶች እንደጠፉ ተናገረ። እነዚህን እውነቶች ለጆሴፍ እንዲያስተምሩትና እርሱም ለዓለም እንዲያካፍል መላዕክትን ወደ እሱ እንደሚልክ ተናገረ።
ቅዱሳን፣ 1፥16–17
ራዕዩ ካለቀ በኋላ ጆሴፍ በፍቅርና በሀሴት ተሞልቶ ነበር። ከዚህ በኋላ ግራ አልተጋባም። አምላክ እንደሚወደው አወቀ። ምንም እንኳን የሰማይ አባትንና ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳየ በመናገሩ አንዳንድ ሰዎች ቢጠሉትም ጆሴፍ ይህ እውነት እንደሆነ ያውቅ ነበር።
ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥20–26፣ ቅዱሳን፣ 1፥16