በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
መልአኩ ሞሮኒ ጆሴፍ ስሚዝን ጎበኘው


መልአኩ ሞሮኒ ጆሴፍ ስሚዝን ጎበኘው፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“መልአኩ ሞሮኒ ጆሴፍ ስሚዝን ጎበኘው፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

1823 (እ.አ.አ)

መልአኩ ሞሮኒ ጆሴፍ ስሚዝን ጎበኘው

ስለ ቅዱስ መጽሐፍ መማር

ጆሴፍ ስሚዝ በቤቱ መስኮት ወደ ውጪ ሲመለከት።

ጆሴፍ ስሚዝ የተመለከተው የመጀመሪያው ራእይ ሦስት ዓመታት አለፉት። ጆሴፍ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሠራቸው አንዳንድ ስህተቶች በጣም አዘነ። አምላክ ስለ እሱ ምን እንደሚሰማው አሰበ።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥28–29ቅዱሳን1፥20

ጆሴፍ ስሚዝ በአልጋው አጠገብ ሲጸልይ።

አንድ ቀን ማታ ሁሉም ተኝተው ሳለ ጆሴፍ ለመጸለይ ወሰነ። እግዚአብሔር ከዚህ በፊት ጸሎቱን መልሶ ነበር እናም እርሱ በድጋሜ ጸሎቶቹን እንደሚመልስ አወቀ።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥29ቅዱሳን1፥21–22

ሞሮኒ ለጆሴፍ ስሚዝ ተገለጠ።

ጆሴፍ እየጸለየ ሳለ ብርሃን ክፍሉን ሞላው። ጆሴፍ አንድ መልአክ ከአልጋውአጠገብ በአየር ላይ ቆሞ አየ። መልአኩ ስሙ ሞሮኒ እንደሆነ ተናገረ። እግዚአብሄር ላከው። እግዚአብሄር ጆሴፍን ይቅር እንዳለውና የሚሠራው ሥራ እንዳለው ነገረው። በመላው ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ስለ ጆሴፍና አምላክ ስለሰጠው ሥራ ያውቃሉ።

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥30–33

ሞሮኒ ለጆሴፍ ስሚዝ ከወርቅ ሰሌዳ ስለተሠራ አንድ መጽሐፍ ነገረው።

ሞሮኒ ከወርቅ ገጾች ወይም ሰሌዳዎች የተሠራ መጽሐፍ መኖሩን ተናገረ። የተቀበረውም በጆሴፍ ቤት አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ኮረብታ ላይ ነበር። መጽሐፉ ከረጅም ጊዜ በፊት በአሜሪካ አገር ስለኖሩ ሰዎች የሚናገር ነበር። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ ወንጌሉ ያውቁ ነበር። ሰዎች መጽሐፉን እንዲያነቡት ጆሴፍ መጽሐፉን እንዲተረጉም እግዚአብሔር እንደሚረዳው ሞሮኒ ተናገረ።

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥34፣ 46

ጆሴፍ ስሚዝ ከሞሮኒ ስለተደረገው ጉብኝት ለአባቱ ነገረው።

ሞሮኒ በዛ ቀን ማታ ሶስት ጊዜ እና በንጋታውም ጎበኘ። ጆሴፍ ያየውን ነገር ለአባቱ ነገረው። የጆሴፍ አባት በጣም ተደሰተ። “ይህ ራእይ ከእግዚአብሄር የመጣ ነው” በማለት ለጆሴፍ ነገረው።

ጆሴፍ ስሚዝ - ታሪክ 1፥35–50ቅዱሳን1፥22–25

ጆሴፍ ስሚዝ ከዐለት ሥር ያለውን የወርቅ ሰሌዳዎች አገኘ።

ጆሴፍም ወደ ኮረብታው ሄዶ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ከከባድ ዓለት ስር አገኘ። እጆቹንም ዘርግቶ ሊያነሳቸው ሳለ፣ ምን ያህል ገንዘብ ሊያወጡ እንደሚችሉ አሰበ። ሞሮኒ መጥቶ ለጆሴፍ ሰሌዳዎቹን ለመውሰድ ዝግጁ አለመሆኑን ነገረው። ጆሴፍ ዝግጁ እስከሚሆን ድረስ ወደዚህ ስፍራ በየዓመቱ እንዲመለስ ነገረው።

ጆሴፍ ስሚዝ - ታሪክ 1፥51–54ቅዱሳን1፥25–27