“እግዚአብሔር ኦሊቨር ካውደሪን ላከ፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“እግዚአብሔር ኦሊቨር ካውደሪን ላከ፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
1828–1829 (እ.አ.አ)
እግዚአብሔር ኦሊቨር ካውድሪን ላከ
እግዚአብሔር እንዴት እንደሚናገረን መማር
ጆሴፍና ኤማ መፅሐፈ ሞርሞንን መተርጎማቸውን ቀጠሉ። ሥራው በጣም ከባድ ነበረ በእርሻቸው ላይ መስራትም ነበረባቸው። መፅሐፈ ሞርሞንን ለመተርጎም የሚረዳውን ሰው እንዲልክለት ጆሴፍ ወደሰማይ አባት ጸለየ።
ቅዱሳን፣ 1፥56፣ 58
ኦሊቨር ካውድሪ የሚባል ወጣት አስተማሪ በኒው ዮርክ ውስጥ ራቅ ወዳለ ቦታ ከጆሴፍ ስሚዝ ወላጆች ጋር ይኖር ነበር። ኦሊቨር የጆሴፍን ታናሽ ወንድሞችና እህቶች አስተማረ።
ቅዱሳን፣ 1፥58–59
ኦሊቨር ስለ ጆሴፍና ስለ የወርቅ ሰሌዳዎች ሰማ። የማወቅ ጉጉት አደረበት። የጆሴፍን ወላጆች አነጋገራቸው። ጆሴፍ የእግዚአብሔርን ሥራ እየሠራ እንደሆነ ለኦሊቨር ነገሩት።
ቅዱሳን፣ 1፥59
ኦሊቨር ከዚህም ይበልጥ ጉጉት አደረበት። የጆሴፍ ወላጆች ኦሊቨር እንዲጸልይና የእግዚአብሔር ሥራ መሆኑን በራሱ እንዲያውቅ ነገሩት። ስለዚህ አንድ ምሽት ኦሊቨር በሙሉ ልቡ ጸለየ። እግዚአብሔር የአእምሮ ሰላምን ሰጠው። ኦሊቨር ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደሆነ አወቀ። ጆሴፍን መርዳት እንዳለበት ተሰማው።
ቅዱሳን፣ 1፥60
የትምህርት ዓመት ሲያበቃ፣ ኦሊቨር ጆሴፍን እና ኤማን ለማግኘት ሄደ። ጆሴፍና ኦሊቨር ስለ ወርቁ ሰሌዳዎች እና ስለ እግዚአብሔር ሥራ ሲያወሩ ቆይተው አመሹ።
ቅዱሳን፣ 1፥60።
ኦሊቨር ጆሴፍ ሲተረጎም እሱ እንደሚጽፍ ተናገረ። ስለ ኢየሱስ እየተማረ የነበረውን ነገር ወደደው። በተጨማሪም ጥያቄዎች ነበሩት እንዲሁም ጠንካራ እምነት እንዲኖረው ይፈልግ ነበር።
ቅዱሳን፣ 1፥61።
በነቢዩ ጆሴፍ አማካኝነት ጌታ ለኦሊቨር መልእክት ሰጠ። የጸለየበትን ሌሊት እንዲያስታውስ ለኦሊቨር ነገረው ። እግዚአብሔር ሰላምን ሰጠው። ስለዚህ ጸሎት የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነበር። የኦሊቨር እምነት ጠነከረ። ጆሴፍን ማገዙን ቀጠለ፣ ጌታም ለእኛ በምን ዓይነት መልኩ እንደሚናገረን ብዙ ነገሮችን እንዲያውቅ አደረገው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥14–24፤ 8፥1–3፤ 9፥7–9፤ ቅዱሳን፣ 1፥62–64