በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ስለ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች


“ስለ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች (2024 [እ.አ.አ])

“ስለ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

መግቢያ

ስለ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች

ጌታ በድጋሚ ይናገራል።

ኢየሱስ ክርስቶስ በጥንቷ አሜሪካ ይኖሩ ለነበሩ ሰዎች ታይቷል።

የሰማይ አባታችን ይወደናል! እርሱ እንዲባርከን፣ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳኖችን እንድንገባ ይፈልጋል። አዳኛችን እንዲሆን እንዲሁም ወደ እርሱ ለመመለስ እንችል ዘንድ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ላከው።

በጥቅልል ወረቀት ላይ እየጻፈ ያለ አንድ የጥንት ነቢይ።

በተጨማሪም እግዚአብሔር ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ትእዛዛቱ እንዲያስተምሩን ነቢያትን ይልካል። ነቢያት ኢየሱስ ክርስቶስን ያገለግላሉ እንዲሁም ቤተክርስቲያኑን በመምራት ያግዛሉ።

ሙሴ አሥርቱ ትእዛዛትን ይዞ።

ኢየሱስ፣ ነቢያት እኛን ምን እንደሚያስተምሩን ይነግራቸዋል። ከረጅም ጊዜያት በፊት የነበሩ የነቢያት ቃላት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እና መፅሀፈ ሞርሞን ባሉ መፃህፍት የተጻፉ ናቸው።

ጆሴፍ ስሚዝ የትኛውን ሃይማኖታዊ ወግ መከተል እንዳለበት እያሰበ።

ኢየሱስ በምድር ላይ ከኖረ በኋላ ባሉት ብዙ ዓመታት ነቢያት አልነበሩም። ሰዎች ከአምላክ ጋር ቃል ኪዳን አይፈጽሙም እንዲሁም አይጠብቁም ነበር። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ አልነበረችም።

የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ለጆሴፍ ስሚዝ ሲገለጡለት።

ከዚያ በኋላ ግን ጆሴፍ ስሚዝ ነቢይ እንዲሆን ጌታ ጠራው። ጆሴፍ ገና ወጣት ነበር፣ ቢሆንም አምላክ እርሱ እንዲሰራው ያዘጋጀለት በጣም አስፈላጊ ነገር ነበር።

ሰዎች ጆሴፍን እና ኦሊቨርን እንደ ቤተክርስቲያኗ መሪ አድርገው ለመደገፍ እጃቸውን እያነሱ።

ጆሴፍ ስሚዝ ስለ ኢየሱስ አስተምሯል። የኢየሱስን ቤተክርስቲያን በማደራጀት ረድቷል። ኢየሱስ ለጆሴፍ ስሚዝ ስለወንጌሉ እና ቤተክርስቲያኑን እንዴት መምራት እንደሚችል አስተማረው።

አንድ ቤተሰብ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን እያነበበ።

ኢየሱስ ለጆሴፍ ስሚዝ የነገራቸው ብዙ ነገሮች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ተፅፈዋል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እና እንደ መፅሐፈ ሞርሞን አይነት የቅዱሳት መፃህፍት መፅሃፍ ነው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች በሰዎች ላይ ምን ተጽዕኖ እንዳሳረፈ የሚያሳይ አንድ ምሳሌያዊ ስዕል።

የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች ኢየሱስ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና በሌሎች ሰዎች እርዳታ ቤተክርስቲያኑን እንዴት ዳግም እንደመለሰ ይናገራል። የቤተክርስቲያኗ አባላት ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ። እነዚህ ታሪኮች አምላክ በመላው ዓለም ያሉትን ልጆቹን እንደሚወዳቸው ያሳያሉ። ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ስንገባ ሊባርከን ይፈልጋል።