“የጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“የጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
1805–1817 (እ.አ.አ)
የጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ
የእምነት ቤተሰብ
ጆሴፍ ስሚዝ ታኅሣሥ 23፣ 1805 (እ.አ.አ) በሰሜን ምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ተወለደ። አባቱም ጆሴፍ ይባል ነበር። የእናቱ ስም ሉሲ ነበር። ብዙ ወንድሞች እና እህቶች ነበሩት። የጆሴፍ ቤተሰብ ገበሬዎች ነበሩ። በእግዚአብሔር ያምኑ ነበር እንዲሁም እርስ በርሳቸው ይዋደዱ ነበር።
ጆሴፍ ትንሽ ልጅ ሳለ እግሩ ላይ ችግር የሚፈጥር በሽታ ይዞት ነበር ። በጣም ያመው ነበር። የጆሴፍ ቤተሰቦች እንዲሻለው ሊረዱት ቢሞክሩም እግሩ ግን በጣም ያመው ነበር። ሐኪሞች እግሩን ለማሻል ቢሞክሩም አልቻሉም።
ቅዱሳን፣ 1፥7
ሐኪሞቹ የጆሴፍን ሕይወት ለማትረፍ እግሩን መቁረጥ እንደሚያስፈልጋቸው ተናገሩ። እናቱ ግን አልፈቀደችላቸውም። ጆሴፍን ለመርዳት ሌላ መንገድ ይኖር እንደሆነ ጠየቀችው። ዶክተሮቹ በምትኩ ከእግሩ ውስጥ የአጥንት ክፍሉን ቆርጠው ለማውጣት ወሰኑ። ጆሴፍ ይህ እንደሚያም ቢያውቅም አምላክ እንደሚረዳው እምነት ነበረው።
ቅዱሳን፣ 1፥7
ሐኪሞቹ ጆሴፍ ሕመሙን ለማደንዘዝ አልኮል እንዲጠጣ ፈለጉ። ጆሴፍ ግን አምቢ አለ። አባቱ እንዲይዘው ብቻ ፈለገ።
ቅዱሳን፣ 1፥7
ጆሴፍ እናቱን ወደ ውጭ እንድትወጣ ጠየቃት። ሐኪሞቹ እግሩን ሲቀዱት ብዙ ሥቃይ ሲደርስበት እንድታየው አልፈለገም።
የጆሴፍ አባት እሱን ይዞት ዶክተሮቹ ደግሞ በእግሩ ያለውን መጥፎ የአጥንቱን ክፍል ቆርጠው አወጡት። ይህ በጣም ያማል፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ጆሴፍ ደፋር እንዲሆን እረዳው። ከጥቂት ዓመታት በኋላ የጆሴፍ እግር ዳነ፣ ነገር ግን ሲራመድ ያመው ነበር።
ቅዱሳን፣ 1፥6-7
ጆሴፍ በዕድሜ ከፍ ሲል ቤተሰቡ ወደ ኒው ዮርክ አመሩ። የጆሴፍ ቤተሰብ ድሃ ነበሩ። ለቤተሰባቸው የሚሆን በቂ ምግብ ለማግኘት ጠንክረው ይሠሩ ነበር። ጆሴፍ ጥሩ ልጅ ነበር። ደስተኛ ነበር እናም መሳቅና መደሰት ይወድ ነበር።
ቅዱሳን፣ 1፥5-9።
የጆሴፍ ቤተሰቦች ኢየሱስ ክርስቶስን ይወዱ ነበር። በአንድነት መጽሐፍ ቅዱስን ያነቡ እና ይጸልዩ ነበር። ነገር ግን የጆሴፍ ወላጆች የትኛውን ቤተክርስቲያን መቀላቀል እንዳለባቸው እርግጠኛ አልነበሩም። አንድ ቀን ማታ የጆሴፍ እናት ሉሲ ወደ አምላክ ጸለየችና እውነተኛውን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ለማግኘት እንደምትፈልግ ነገረችው። እግዚአብሔር ለጸሎቷ መልስ በመስጠቱ እንደምታገኘው ቃል ገባላት።
ቅዱሳን፣ 1፥10-11