በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ጆሴፍ እና ኤማ


“ጆሴፍ እና ኤማ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]

“ጆሴፍ እና ኤማ፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

1825–1828 (እ.አ.አ)

ጆሴፍ እና ኤማ

መፅሐፈ ሞርሞን ዓለምን ለማምጣት በጋራ መስራት

ኤማ ሄል በቤቷ አቅራቢያ ወንዝ አጠገብ ተቀምጣ።

ኤማ ሄል ያደገችው ጆሴፍ ስሚዝ ይኖርበት ከነበረው ከኒው ዮርክ ብዙም ሳይርቅ በፔንሰልቬንያ በሚገኝ አንድ ትልቅ ቤተሰብ ውስጥ ነው። ኤማ እና ቤተሰቧ በእግዚአብሄር ያምኑነበር። ኤማ ማንበብ፣ መዘመር፣ ፈረሶችን መጋለብ እና በቤቷ አጠገብ ባለው ወንዝ ላይ ጀልባ መቅዘፍ ትወዳለች።

ቅዱሳን1፥31–32

ጆሴፍ ስሚዝ እና አባቱ በኤማ ሄልስ ቤት አጠገብ ሲሄዱ። ኤማ በመስኮት ወደ ውጪ በመመልከት ጆሴፍን አየችው።

ኤማ 21 ዓመት ሲሞላት፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና አባቱ ከኤማ ጎረቤቶች ለአንዱ ለመስራት መጡ። የኤማ አባት በእሱ ቤት እንዲቆዩ ጋበዛቸው።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥56–57ቅዱሳን1፥31–32

ጆሴፍና ኤማ ከኤማ ቤት ውጭ ሲነጋገሩ። የኤማ ወላጆች በበሩ ደጃፍ ላይ ሆነው።

ጆሴፍና ኤማ ተዋወቁ። አንድ ላይ መሆናቸውን ወደዱት። የኤማ ወላጆች ግን ጆሴፍን አልወደዱትም። መልአክ እንዳየ አላመኑም።

ቅዱሳን1፥32–33

ኤማ እና ጆሴፍ ስሚዝ በፈረስ ጋሪ ላይ አብረው ሲጓዙ።

ከአንድ ዓመት ገደማ በኋላ ጆሴፍ ኤማ እንድታገባው ጠየቃት። ኤማ እና ጆሴፍ በጣም ተዋደዱ። ከተጋቡ በኋላ በኒው ዮርክ ውስጥ ከጆሴፍ ወላጆች ጋር ለመኖር ሄዱ።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥57–54=8ቅዱሳን1፥34–35

ኤማ እና ጆሴፍ ስሚዝ በፈረስ የሚጎተት ጋሪን በጫካ ውስጥ እየነዱ።

ሞሮኒ ለጆሴፍ ስለ ወርቁ ሰሌዳዎች ከነገረው አራት ዓመት አለፉት። ሰዓቱ ሲደርስ ኤማና ጆሴፍ ሰሌዳዎቹ ወደ ተደበቁበት ኮረብታ ሄዱ።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥59ቅዱሳን1፥36–37

ሞሮኒ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ለጆሴፍ ስሚዝ ሰጠው።

መልአኩ ሞሮኒ ጆሴፍን ከኮረብታው ላይ አግኝቶ ሰሌዳዎቹን ሰጠው። ጆሴፍ ሰሌዳዎቹን ለመንከባከብ አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ካደረገ ሰሌዳዎቹ ምንም እንደማይሆኑ ነገረው።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥59ቅዱሳን1፥37–38

ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ይዞ። አንድ ሰው ሰሌዳዎቹን ለመውሰድ እያባረረው።

ሰዎች ጆሴፍ የወርቅ ሰሌዳዎቹ እንዳሉት ሰሙ እናም አንዳንዶቹ ሰሌዳዎቹን ከእሱ ሊሰርቁ ሞከሩ። ጆሴፍ መደበቂያ ቦታ ማግኘት ነበረበት። ጆሴፍ ሰሌዳዎቹን ጫካ ውስጥ ከተደበቁበት ቦታ ሲያወጣ አንዳንድ ሰዎች ጥቃት አደረሱበት። ገፍትሮ ጣላቸው እና ወደ ወላጆቹ ቤት ሮጠ።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥60ቅዱሳን1፥38፣ 40–41

ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ወደ ቤቱ አምጥቶ ሰሌዳዎቹን ቤተሰቡ እንዲነኳቸው አደረገ።

ጆሴፍ ሰሌዳዎቹን ወደ ቤቱ ሲያስገባ እህቱ ጠረጴዛው ላይ እንዲያስቀምጥ ረዳቸው። ሞሮኒ ሰሌዳዎቹን ለማንም ሰው እንዳያሣያቸው ለጆሴፍ ነግሮት ነበር፤ ሆኖም በጨርቅ ተጠቅልለው እንዳሉ ቤተሰቦቹ ሰሌዳዎቹን ነክተዋቸውቸው ነበር።

ቅዱሳን1፥41

ኤማ እና ጆሴፍ ወደ አዲስ ቤት ሲገቡ።

ሶዎች ያነብቧቸው ዘንድ ጆሴፍ ወርቃማ ሰሌዳዎቹን እንዲተረጉም እግዚአብሔር ፈለገ። ይሁን እንጂ በኒው ዮርክ የሚኖሩ ሰዎች ሰሌዳዎቹን ለመስረቅ መሞከራቸውን ቀጠሉ። ጆሴፍ ሰሌዳዎቹን በጥንቃቄ ለመጠበቅ በተደበቁበት እንዲቆዩ ማድረግ ነበረበት። ስለዚህ ጆሴፍና ኤማ ለኤማ ወላጆች ወደሚቀርብ ቤት ተዘዋወሩ። ሰሌዳዎቹን በሰላም ለመተርጎም ቢችሉ ተመኝተው ነበር።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥61–62ቅዱሳን1፥43 ፣ 45–46

ጆሴፍ ስሚዝ ኤማን ግንባሯ ላይ ሲስማት። የወርቅ ሰሌዳዎቹን እንዲተረጉም ስትረዳው።

ጆሴፍ ሰሌዳዎቹን መተርጎም ጀመረ። እግዚአብሄር እሱን ለመርዳት ያዘጋጃቸውን ልዩ መሣሪያዎች ተጠቀመ። ጆሴፍ ሲተረጎም ኤማ የሚናገረውን ጻፈች። ለረዥም ሰዓታት አብረው ሠሩ። ኤማ ተገረመች። ባሏ በእግዚአብሔር ኃይል ሲተረጎም እንደነበር አወቀች።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥35ቅዱሳን1፥49