“መላዕክት ክህነት ሥልጣን በዳግም መለሱት፣” የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች [2024 (እ.አ.አ)]
“መላዕክት ክህነት ሥልጣን በዳግም መለሱት፣” ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች
1829 (እ.አ.አ)
መላዕክት የክህነት ሥልጣንን ዳግም መለሱት
የእግዚአብሔርን ሥራ የማከናወን ኃይል
ጆሴፍና ኦሊቨር የወርቁን ሰሌዳዎች ሲተረጉሙ፣ ኢየሱስ እያንዳንዱ ሰው እንዲጠመቁ እንደሚፈልግ ተገነዘቡ። በተጨማሪም ሰዎችን እንዲያጠምቁ ሥልጣንን ሰጣቸው። ጆሴፍ አልተጠመቀም ነበር። ስለጥምቀት ይበልጥ ማወቅ ፈለገ።
ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥68፣ ቅዱሳን፣ 1፥65–66
ጆሴፍና ኦሊቨር ሰዎችን አሁን የማጥመቅ ሥልጣን ያለው ማን እንደሆነ ማወቅ ፈለጉ። እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወሰኑ። ወደ ጫካ ገብተው ለመጸለይ ተንበረከኩ።
ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥68፣ ቅዱሳን፣ 1፥66
ሲጸልዩም አንድ መልአክ ተገለጠ። ኢየሱስ ክርስቶስን ከረጅም ጊዜ በፊት ያጠመቀው መጥምቁ ዮሐንስ እንደሆነ ተናገረ። ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር የአሮናዊ ክህነትን ሰጣቸው። ክህነት የእግዚአብሔር ኃይል ነው። የእግዚአብሔርን ልጆች ለመባረክ ያገለግላል።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፤ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥69፣ 72፣ ቅዱሳን፣ 1፥66–67
መጥምቁ ዮሐንስ የአሮናዊ ክህነት ስልጣን ያለው ሰው፣ ሰዎች ንስሀ እንዲገቡ ማስተማር እና እነሱን ማጥመቅ እንደሚችል ተናገረ። ዮሐንስ ለጆሴፍና ለኦሊቨር እንዲጠመቁ ነገራቸው። ከዚያም ወደ አንድ ወንዝ ሄደው አንዱ ሌላውን አጠመቀ። ከውኃውም በወጡ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። በጣም ተደሰቱ!
ከጊዜ በኋላ ሌሎች መላዕክት መጡ። ሦስቱ የኢየሱስ ሐዋርያት—ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ—ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ሰጡ። አሁን ጆሴፍና ኦሊቨር የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መስጠት ይችላሉ። ጆሴፍና ኦሊቨር ሐዋርያትም ሆኑ። ቤተክርስቲያኑን ሊመሩ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ ምስክሮች ሊሆኑ ቻሉ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥12፤ ቅዱሳን፣ 1–84