ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 30፟–ጥር 5 (እ.አ.አ)፦ “ቃል የተገባው ዳግም መመለስ ይቀጥላል”፦ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት ዳግም መመለስ


“ታህሳስ 30፟–ጥር 5 (እ.አ.አ)፦‘ቃል የተገባው ዳግም መመለስ ይቀጥላል’፦ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት ዳግም መመለስ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት ዳግም መመለስ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ፀሃይዋ በስማይ ላይ ስትወጣ

ታህሳስ 30፟–ጥር 5 (እ.አ.አ)፦ “ቃል የተገባው ዳግም መመለስ ይቀጥላል”

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት ዳግም መመለስ

ዓለምን የለወጠውን ክስተት 200ኛ ዓመትን የምትዘክሩት እንዴት ነው? ሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) እየተቃረበ በነበረበት ጊዜ፣ ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን፣ ጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕዩን ያየበትን 200ኛ ዓመት ስለማክበር እያሰላሰሉ ነበር። “የመታሰቢያ ሐውልት ማቆም ይኖርብን ይሆን ስንል አሰብን፣” በማለት ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ያስታውሳሉ። “ነገር ግን የዚያን ራዕይ ልዩ መገለጫ—እና የመጀመሪያውን ራዕይ ታሪክ አለም አቀፋዊ ተፅዕኖ—ስናስብ፣ የተከበረ እና የተቀደሰ አዋጅ ቃላት፣ “በድንጋይ ፅላት” ላይ ለመቀረፅ የተጻፉ ሳይሆን፣ ይልቁኑ በሰው ልጆች ልቦች “የስጋ ፅላት” ላይ ሊቀረፁ የሚችሉ የቃላት መታሰቢያ ሀውልትን ለማቆም የሚገፋፋ ስሜት ተሰማን [2 ቆሮንቶስ 3፥3]” (“እርሱን ስሙት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 90)።

የቆመው የቃላት ሃውልት ርዕስ “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት በዳግም መመለስ፦ የሁለት መቶኛ አመት መታሰቢያ ለአለም የተላለፈ አዋጅ ነው። የመታሰቢያ ሐውልቱ ስለመጀመሪያው ራዕይ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስላደረገው —አሁንም እያደረገ ስላለው—ነገር ሁሉ ነው። የእርሱ ወንጌል ዳግም መመለስ የጀመረው አንድ ሰው ወደ እግዚአብሔር በተመለሰበት እና እርሱን በሰማበት ጊዜ ነበር። በዚያው ተመሳሳይ መንገድ ይቀጥላል፦ የእናንተን ጨምሮ አንድ ልብ፣ አንድ ቅዱስ ተሞክሮ በአንድ ጊዜ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

“እግዚአብሔር በሁሉም አገሮች የሚኖሩ ልጆቹን ይወዳል።”

በእናንተ አስተያየት የዳግም መመለስ አዋጅ በእግዚአብሔር ፍቅር መግለጫ የሚጀምረው ለምንድን ነው አዋጁን ስታጠኑ፣ እግዚአብሔር “በሁሉም አገሮች ለሚኖሩ ልጆቹ” ስላለው ፍቅር መግለጫዎች ፈልጉ። የወንጌሉ ዳግም መመለስ የእርሱ ፍቅር እንዲሰማችሁ የረዳችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም ጌሪት ደብሊው. ጎንግ፣ “All Nations, Kindreds, and Tongues፣” ሊያሆና ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 38-41 ተመልከቱ።

ዳግም መመለሱ የተጀመረው ለአንድ ጥያቄ በተሰጠ መልስ ነበር።

አዳኙ የወንጌሉን ዳግም መመለስ ያስጀመረው ለአንድ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ነበር ማለት ይቻላል። አንድ ግለሰብ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለወንጌል ወይንም “ስለእርሱ [ወይም ስለእርሷ] ነፍስ ደህንነት” ስላለው ጥያቄ የዳግም መመለስ አዋጅ ምን መልዕክት እንደያዘ ይሰማችኋል? በተጨማሪም፣ ለወንጌል ጥያቄዎች መልስ ማግኘትን በተመለከተ ከጆሴፍ ስሚዝ ምን መማር እንደምትችሉ ለማየት የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥5–20 ማጥናት ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ርዕሶች እና ጥያቄዎች “Seeking Answers [መልሶችን መፈለግ]፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

ጆሴፍ ስሚዝ በዛፎች ቁጥቋጦ ውስጥ ወደ ላይ እየተመለከተ የሚያሳይ ስዕል

ዝርዝር ከThe Desires of My Heart፣ በዋልተር ሬን

የሴሚናሪ ምልክት
ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን ዳግም መልሷል።

አዳኙ በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት በዳግም ስለመለሰው “ስለክርስቶስ አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን” ምን ታውቃላችሁ? እነዚህን የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች ማጥናትንና የእርሱን ቤተክርስቲያን አንዳንድ ገፅታዎች መዘርዘርን አስቡ።

ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተክርስቲያኑን ገፅታዎች በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት እንዴት እንደመለሰ የሚገልጹትን ከላይ ያሉትን የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች ከታች ካሉት ጋር ማዛመድ ትችላላችሁ፦

ስለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዳግም መመለስ አመስጋኝ የሆናችሁት ለምንድን ነው?

ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እና ባለቤታቸው አንድ ጊዜ ወንጌሉ ዳግም ከመመለሱ በፊት ኖረው ቢሆን ኖሮ እንዴት ይሰማቸው እንደነበረ ለመገመት ሞክረው ነበር። “ቢኖረን ኖሮ ብለን እንመኝ የነበው ምንድን ነው?” ሲሉ ራሳቸውን ጠይቀዋል። ስለነበራቸው ተሞክሮ በ “A Perfect Brightness of Hope [ፍጹም የተስፋ ብርሀን]፣” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 81-82) ውስጥ አንብቡ። ዳግም መመለሱ መንፈሳዊ ተስፋችሁን እንድታሟሉ የረዳችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም ርዕሶች እና ጥያቄዎች “Apostasy and the Restoration of the Gospel [ክህደት እና የወንጌል ዳግም መመለስ]፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

“ቃል የተገባው ዳግም መመለስ ይቀጥላል።”

ራሳችሁን የወንጌል ዳግም መመለስ አካል አድርጋችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? በፕሬዚዳንት ዲየተር ኤፍ ኡክዶርፍ የተናገሯቸውን እነዚህን ቃላት አስቡ፦ “አንዳንድ ጊዜ የወንጌል ዳግም መመለስን እንደ አንድ የተጠናቀቀ ነገር፣ እንዳለፍነው ነገር አድርገን እናስበዋለን። … እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ዳግም መመለሱ በመካሄድ ላይ ያለ ሂደት ነው፤ አሁን ራሱ የምንኖረው በዚያው ውስጥ ነው” (“Are You Sleeping through the Restoration? [ዳግም መመለስ ሲካሄድ እያንቀላፋችሁበት ናችሁን?]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2014፣ (እ.አ.አ) 59)።

ወንጌሉ በ1800ዎቹ.ዓመታት ወንጌሉ ዳግም ስለተመለሰበት መንገድ ለማጥናት ስትዘጋጁ፣ በህይወታችሁ ውስጥ እንዴት ዳግም እንደተመለሰ በማሰላሰል ልትጀምሩ ትችላላችሁ። የሚቀጥሉትን አይነት ጥያቄዎችን በአዕምሯችሁ በመያዝ የዳግም መመለስ አዋጅን አንብቡ፦ ይህ እውነት መሆኑን እንዴት አወቅሁ? ዛሬ በዳግም መመለሱ የምሳተፈው እንዴት ነው?

“ሰማያት ተከፍተዋል”

“ሠማያት ተከፍተዋል” የሚለው ሃረግ ለእናንተ ምን ትርጉም አለው? በዳግም መመለስ አዋጅ ውስጥ ዛሬ በቤተክርስቲያን፣ በቅዱሳት መፃህፍት እና በህይወታችህ ውስጥ በእርግጥ ሠማያት እንደተከፈቱ የሚያሳይ ምን ማስረጃ ታያላችሁ?

የጥናታችሁ አካል አድርጋችሁ “The Morning Breaks [ጠዋቱ ሲነጋ]” (መዝሙር፣ ቁ.1) ልታካትቱም ትችላላችሁ። በዚህ መዝሙር ውስጥ “ሠማያት ተከፍተዋል” የሚለውን ሃረግ የመረዳት ግንዛቤያችሁን የሚጨምር ምን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ክዉንተን ኤል. ኩክ፣ “The Blessing of Continuing Revelation to Prophets and Personal Revelation to Guide Our Lives [ለነቢያት በመቀጠል የሚመጣ ራዕይ እና ህይወታችንን ለመምራት የሚመጣ የግል ራዕይ በረከት]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 96–100 ተመልከቱ።

በጋራ ተማሩ። ፕሬዚዳንት ኔልሰን “[የዳግም መመለስ አዋጁን] በግል እንዲሁም ከቤተሰባችን አባላት እና ከጓደኞች ጋር እንድናጠናው” ጋብዘውናል (“እርሱን ስሙት፣” 92) በጥናታችሁ ውስጥ ሌሎችን እንዴት እንደምታካትቱ አስቡ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

“በክብር እናውጃለን።”

  • ከልጆቻችሁ ጋር የዳግም መመለስ አዋጁን ስታነቡ (ወይንም ፕሬዚዳንት ኔልሰን ሲያነቡት የሚያሳየውን ቪዲዮ ስትመለከቱ)፣ “እናውጃለን፣” ወይም “እንመሰክራለን” በሚሉ ሃረጎች የሚጨርሱ ዓረፍተ ነገሮችን እንዲፈልጉ እርዷቸው። ነቢያቶቻችን እና ሐዋርያቶቻችን ምን እውነቶችን እያወጁ ናቸው? ምናልባት እናንተና ልጆቻችሁ የእነዚህን አንዳንድ እውነቶች የራሳችሁን ምስክርነቶች ልታጋሩ ትችላላችሁ።

    6:0

    The Restoration of the Fulness of the Gospel of Jesus Christ

“ጆሴፍ ስሚዝ … ጥያቄዎች ነበሩት።”

  • ወደ አዳኙ ወንጌል ዳግም መመለስ የመሩትን ጆሴፍ ስሚዝ የነበሩትን አንዳንድ ጥያቄዎች መፈለግ ለልጆቻችሁ አስደሳች ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ምሳሌዎችን በጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥10፣ 29፣ 68 ውስጥ እንዲያገኙ እርዷቸው። እግዚአብሔር የጆሴፍ ስሚዝን ጥያቄዎች በመመለሱ ምክንያት የተባረክነው እንዴት ነው?

  • ልጆቻችሁ ያሏቸውን ጥያቄዎች እንዲያነሱ ዕድል ልትሰጧቸውም ትችላላችሁ። መልሶችን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ከጆሴፍ ስሚዝ ምን እንማራለን? (ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥8–17፤ በተጨማሪም “This Is My Beloved Son [ይህ ውዱ ልጄ ነው]፣” ቁጥር 3 እና 4 ተመልከቱ የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 76 ተመልከቱ)።

“የሰማይ መልእክተኞች ጆሴፍን ለማስተማር … [መጡ]።”

  • “[ጆሴፍን ሊያስተምሩት የመጡት የሰማይ መልዕክተኞች]” እነማን ነበሩ? ልጆቻችሁ የወንጌል የአርት መፅሐፍ ውስጥ የእነርሱን ምስሎች በመፈለግ ሊደሰቱ ይችላሉ (ቁጥር 91939495 ተመልከቱ)። እነዚህ እያንዳንዱ መልዕክተኞች “የኢየሱስ ክርስቶችን ቤተክርስቲያን ዳግም ለመመስረት” የረዱት እንዴት ነበር? በዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገፅ ውስጥ የተጠቆሙት የቅዱሳት መፃህፍት ጥቅሶች ልጆቻችሁን ሊረዷቸው ይችላሉ።

The Prophet Joseph Smith sitting on his bed in the Smith farm house. Joseph has a patchwork quilt over his knees. He is looking up at the angel Moroni who has appeared before him. Moroni is depicted wearing a white robe. The painting depicts the event wherein the angel Moroni appeared to the Prophet Joseph Smith three times in the Prophet's bedroom during the night of September 21, 1823 to inform him of the existence and location of the gold plates, and to instruct him as to his responsibility concerning the plates.

ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን ዳግም መልሷል።

  • ልጆቻችሁ ስለአዳኙ ቤተክርስቲያን ዳግም መመለስ እንዲገነዘቡ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው? ምናልባት በጡቦች ወይም በስኒዎች ቀለል ያለ ግንብ ሊገነቡ እና “ዳግም ሊመልሱት” ወይም እንደገና ሊገነቡት ይችሉ ይሆናል። ወይንም ልጆቻችሁ አንድን የጠፋ ወይም የፈረሰ ነገር እንደነበረ መመለስ የነበረባቸው ጊዜ ከነበረ፣ ያንን ተሞክሮ አዳኙ የእርሱን ቤተክርስቲያን ዳግም እየመለሰ ካለበት ሁኔታ ጋር ማነፃፀር ትችላላችሁ። በዳግም መመለስ አዋጁ ውስጥ የተጠቀሱ አዳኙ ዳግም የመለሳቸው የተወሰኑ ነገሮችን እንዲያገኙ እርዷቸው።

አባት እና ልጆች በጡቦች እየተጫወቱ

“ሰማያት ተከፍተዋል።”

  • “ሰማያት ተከፍተዋል” የሚለውን ሃረግ ትርጉም በምሳሌ ለማሳየት፣ ምናልባት በመጀመሪያ በሩ እንደተዘጋ ከዚያም በሩን ክፍት አድርጋችሁ አንድን መልዕክት ለልጆቻችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። እነርሱም ተራ በተራ መልዕክት እንዲያካፍሉ ፍቀዱላቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ምን መልዕክቶች አሉት? ሰማያት እንደተከፈቱ እንድናውቅ የረዱን የትኞቹ ተሞክሮዎች ናቸው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።