ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የዳግም መመለስ ድምጾች፦ የጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ


“የዳግም መመለስ ድምጾች፦ የጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“የጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
የዳግም የመመለስ ድምጾች

የዳግም የመመለስ ድምጾች

የጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ

እያንዳንዳችን በቤተሰባችን ህይወት ጥልቅ ተጽዕኖ ስር ነን፣ እና ጆሴፍ ስሚዝም ከዚህ የተለየ አልነበረም። ቤተሰቦቹ የነበራቸው የኃይማኖት ጽናት እና ልምዶች ዳግም መመለሱ እንዲሳካ ያደረጉ የእምነት ዘሮችን ዘርተዋል። የጆሴፍ የግል ማስታወሻ ይህንን የምስጋና ቃል ይዟል፦ “[ይህን] ያህል የተከበሩ ወላጆችን ለሰጠኝ ለእግዚአብሔር ያለኝን ምስጋና ለመግለጽ ቃላት እና ቋንቋ በቂ አይደሉም።”

እናቱ ሉሲ ማክ ስሚዝ፣ ወንድሙ ዊሊያም ስሚዝ እና ነቢዩ ራሱ የተናገሯቸው የሚቀጥሉት ጥቅሶች በስሚዝ ቤተሰብ ውስጥ ስለነበረው የኃይማኖት ተጽዕኖ የጨረፍታ ግንዛቤ ይሰጡናል።

ምስል
የጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ ቤተሰብ ምስል

የጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ፣ በዳን ባክስተር

ሉሲ ማክ ስሚዝ

ምስል
A painting depicting Lucy Mack Smith, mother of Joseph Smith.

[በ1802 (እ.አ.አ) አካባቢ] ታምሜ ነበር። … ለራሴም እንዲህ አልኩኝ፣ የክርስቶስን መንገድ ስለማላውቅ ለመሞት የተዘጋጀሁ አይደለሁም፣ ለእኔ እንደሚሰማኝ ከሆነ በእኔ እና በክርስቶስ መካከል ለመሻገር የማልደፍረው ጨለማ እና ብቸኝነት እንዲሰማ የሚያደርግ ጥልቅ ልዩነት እንዳለ ይሰማኛል። …

“ወደ ጌታ ተመለከትኩና ልጆቼን ለማሳደግ እና የባለቤቴን ልብ ለማጽናናት እችል ዛንድ ህይወቴን እንዲያድን ለመንኩት እንዲሁም ተማጸንኩት፤ ሌሊቱን ሙሉ በዚህ ሁኔታ ተኝቼ አሳለፍኩኝ። … በህይወት እንድኖር የሚፈቅድልኝ ከሆነ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወይም ሊገኝ በሚችልበት በሌላ በማንኛውም ቦታ፣ በእምነት እና በጸሎት ከመንግስተ ሰማያት የሚገኝ ቢሆንም እንኳን እርሱን በአግባቡ እንዳገለግለው የሚያስችለኝን ኃይማኖት ለማግኘት እንደምጥር ከእግዚአብሔርም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ። በመጨረሻም አንድ ድምጽ አናገረኝ፣ እንዲህም አለኝ፣ ‘ፈልጊ፣ ታገኚማለሽ፤ መዝጊያውን አንኳኪ፣ ይከፈትልሻል። ልብሽ ይጽናና። በእግዚአብሔር ታምኛለሽ፤ በእኔም ደግሞ እመኚ።’ …

“ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ ብርታትን አገኘሁ። ምንም እንኳን መላ አእምሮዬን ቢቆጣጠረውም፣ በሃይማኖት ርዕሰ ጉዳይ ላይ የምናገረው በጣም ጥቂት ነበር፣ እንዲሁም ወዲያው እንደተቻለኝ የእግዚአብሔርን መንገድ የሚያውቅ እና ስለሰማያዊ ነገሮች የሚያስተምረኝ ሃይማኖተኛ ሰው ለማግኘት በፍጥነት ጥረቴን አደርጋለሁ ስል አሰብኩ።”

ዊሊያም ስሚዝ

ምስል
Portrait of William Smith in latter years of his life.

“በጣም ሃይማኖተኛ እንዲሁም በዚህ ምድር እና በመጪው ህይወት ልጆቿ ስለሚኖራቸው ህይወት በጣም ትጨነቅ የነበረችው ሴት፣ እናቴ፣ የወላጅነት ፍቅሯ የፈቀደውን ያህል የነፍሳችንን ደህንነት እናገኝ ዘንድ ፍላጎት እንድናሳድር ወይንም (በወቅቱ ይባል እንደነበረው) ‘ሃይማኖተኛ እንድንሆን’ ያለውን መንገድ ሁሉ ተጠቅማለች። በስብሰባዎቹ እንድንሳተፍ አሳመነችን፣ እናም ቤተሰቡ በሙሉ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ለጉዳዩ ፍላጎት አሳየን እንዲሁም እውነትን የምንፈልግ ሆንን።”

“ማስታወስ እስከምችልበት ጊዜ ጀምሮ ሁልጊዜ የቤተሰብን ጸሎት እናደርግ ነበር። አባቴ መነጽሩን በሰደርያው ደረት ኪስ ውስጥ ያስቀምጠው እንደነበረ በደንብ አስታውሳለሁ፣ … እንዲሁም መነጽሩን መዳበስ ሲጀምር ለጸሎት የመዘጋጀት ምልክት እንደሆነ እኛ ወንዶች ልጆች እናውቅ ነበር፣ ካላስተዋልነው ደግሞ እናታችን፣ ‘ዊሊያም፣’ ወይም ቸል ያለውን ልጅ፣ ‘ለጸሎት ተዘጋጅ’ ትል ነበር። ከጸሎቱ በኋላ የምንዘምረው መዝሙርም ነበረን።”

ምስል
የተከፈቱ ቅዱሳት መጻህፍት

ጆሴፍ ቀዳማዊ እና ሉሲ ስሚዝ፣ ቤተሰባቸው ቅዱሳት መጻህፍትን እንዲያጠኑ አስተምረዋል።

ጆሴፍ ስሚዝ

ምስል
One drawing in pencil, charcoal and ink on paper. A left profile, head/shoulders portrait of Joseph Smith; drawn basically in charcoal, highlighted with white paint and black ink. titled at bottom "Jospeh Smith the Prophet." Signed at left shoulder "Drawn from the most authentic sources by Dan Weggeland" A drawn border surrounds it. No date apparent.

“አሁን እንዲህ እላለሁ፣ [አባቴ] እኔ እስከማውቀው ድረስ በህይወቱ ደግነት የጎደለው ሊባል የሚችል የጭካኔ ድርጊት ፈጽሞ አያውቅም። አባቴንና ስለእርሱ ያሉኝን ትውስታዎች እወዳቸዋለሁ፤ ድንቅ የሆኑ ተግባሮቹ ትውስታም በአዕምሮዬ በግዝፈት ሰፍረዋል፤ እንዲሁም የእርሱ መልካምና የወላጅ ቃሎች በልቤ ማህተም ተጽፈዋል። ከተወለድኩ ጀምሮ ያየኋቸው በአዕምሮዬ የሚመላለሱት በዚያም ሰፍረው የሚገኙት የምወዳቸው የእርሱ የህይወት ታሪክ ሃሳቦች ለእኔ የተቀደሱ ናቸው። … እናቴም እንዲሁ ከሁሉም የበለጠች ጨዋና ከሁሉም ሴቶች ምርጧ ናት።”

አትም