ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የካቲት 3–9 (እ.አ.አ)፦ “ይህ የራዕይ መንፈስ ነው”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–9


“የካቲት 3–9 (እ.አ.አ)፦‘ይህ የራዕይ መንፈስ ነው’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–9፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ኦሊቨር ካውድሪ በላባ ብዕር እየፃፈ የሚያሳይ ምሥል

የካቲት 3–9 (እ.አ.አ)፦ “ይህ የራዕይ መንፈስ ነው”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–9

በ1828 (እ.አ.አ) ክረምት ወቅት ኦሊቨር ካውድሪ የተባለ አንድ ወጣት የትምህርት ቤት አስተማሪ በማንቸስተር፣ ኒው ዮርክ የአስተማሪነት ስራን ተቀጠረ፣ እንዲሁም ከሉሲ እና ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ ቤተሰብ ጋር ይኖር ነበር። ኦሊቨር ስለልጃቸው ጆሴፍ እና ስለአስደናቂ ተሞክሮው ሰምቶ ነበር፣ እናም እራሱን እንደ እውነት ፈላጊ የሚመለከተው ኦሊቨር ስለዚህ ተጨማሪ ለማወቅ ፈለገ። የስሚዝ ቤተሰቦችም ስለመላእክት ጉብኝቶች፣ ስለአንድ ጥንታዊ ጽሁፍ፣ እና ከእግዚአብሔር በመጣ ሃይል ስለመተርጎም ስጦታ ገልጸው ነገሩት። ኦሊቨርም በጣም ተደነቀ። እውነት ሊሆን ይችላልን? ሉሲና ጆሴፍ፣ ቀዳማዊ እውነትን ለሚፈልግ ሁሉ የሚሰራውን ምክር ለገሱት፦ ፀልይና ጌታን ጠይቅ።

ኦሊቨርም እንደተባለው አደረገ፣ እናም ጌታ ለኦሊቨር “አእምሮ ሰላምን” በመስጠት መለሰ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥23)። ኦሊቨርም ራዕይ እንደ ጆሴፍ ላሉት ነቢያት ብቻ እንዳልሆነ አወቀ። ለሚፈልጉትና በቅንነት ለሚሹት ሁሉ ነው። ኦሊቨር ገና ብዙ መማር ነበረበት ነገር ግን ቀጣዩን እርምጃውን ለመውሰድ በቂ ነገር አውቋል። ጌታ በጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት በጣም ጠቃሚ ነገር እያደረገ እንደነበር አወቀ፣ ስለዚህ ኦሊቨርም የዚሁ አካል ለመሆን ፈለገ።

በተጨማሪም “ቅዱሳን1፥58–64፤ “Days of Harmony [የስምምነት ቀናት]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68–9

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
የሰማይ አባት እኔን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ያናግረኛል።

በ1829 (እ.አ.አ) ጸደይ ወቅት፣ ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን መተርጎሙን በቀጠለ ጊዜ ኦሊቨር ካውድሪ እንደጸሃፊ ለማገልገል በጎ ፈቃደኛ ሆነ። ተሞክሮው እጅጉን አስደነቀው፣ እንዲሁም እርሱም ራዕይን የመቀበል እና የመተርጎም ስጦታን ሊያገኝ ይችል እንደሆን አሰበ። ሆኖም የመጀመሪያ ሙከራው አልተሳካም ነበር።

ራዕይን መቀበል ወይም መረዳት አዳጋች ከሆነባችሁ ምናልባት ከኦሊቨር ተሞክሮ ጋር ማገናኘት እና ከእርሱ መማር ትችላላችሁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፣ እና 9ን ስታነቡ፣ ጌታ ኦሊቨርን ስለግል ራዕይ ምን እንዳስተማረው አስተውሉ። ለምሳሌ፦

የኦሊቨር ተሞክሮዎች ጌታ እንዳናገራችሁ የተሰማችሁን ጊዜ “[እንድታስታውሱ]” ሊያደርጋችሁ ይችላል ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥22)። ስለእነዚህ ተሞክሮዎች ያሏችሁን ሃሳቦች ወይም ሥሜቶች መዝግባችሁ ታውቃላችሁን? ከሆነ፣ የፃፋችሁትን ማንበብን አስቡ። ካልሆነ፣ የምታስታውሱትን ለመጻፍ ጊዜ መድቡ። ከእነዚህ ተሞክሮዎች ጥንካሬ ማግኘታችሁን መቀጠል የምትችሉት እንዴት እንደሆነ አስቡ። ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣(ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “Spiritually Defining Memories [መንፈሳዊነትን ትርጉም የሚሰጡ ትዝታዎች]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 18–22 ተመልከቱ።)

በርካታ የቤተክርስቲያን መሪዎች ራዕይን የተመለከቱ ልምዶቻቸውን በ“እርሱን ስሙት!” የቪዲዮ ሥብሥቦች ውስጥ አካፍለዋል። ከእነዚህ ቪዲዮዎች ውስጥ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ካያችሁ በኋላ፣ ጌታ እንዴት እንደተናገራችሁ ለማካፈል የራሳችሁን ተሞክሮዎች የመመዝገብ መነሳሳት ሊሰማችሁ ይችላል።

በተጨማሪም ርዕስ እና ጥያቄዎች “የግል ራዕይ፣” ወንጌል ላይብረሪ፤ “Oliver Cowdery’s Gift [የኦሊቨር ካውድሪ ስጦታ]፣” በራዕያት በአገባብ፣፣ 15–19 ውስጥ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥18–21፣ 29–37

በሃሳባችሁ ሁሉ ወደ ክርስቶስ ተመልከቱ።

በመጪዎቹ አመታት ጆሴፍ ስሚዝ “አስቸጋሪ ሁኔታዎች” እንደሚገጥሙት ጌታ ያውቅ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥18)። በእናንተም ቀጣይ ህይወት ላይ ስለሚመጡት ፈተናዎችም ያውቃል። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥18–21፣ 29–37 ውስጥ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር ከተሰጠው ምክር ውስጥ እናንተም በእርሱ እንድትታመኑ ሊረዳችሁ የሚችል ምን አገኛችሁ?

“ባሰባችሁት ነገር ሁሉ ወደ [ክርስቶስ] ተመልከቱ” ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? (ቁጥር 36)። በጥሩ እና “በአስቸጋሪ ሁኔታዎች” ውስጥ ይህን ይበልጥ ሳታቋርጡ ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? ይህን የፕሬዚዳንት ራስል ኤም.ኔልሰንን ምክር አስቡ፦ “በሁሉም አስተሳሰብ ወደ እርሱ ለመመልከት መጣር በአእምሮ ጠንካራ መሆንን ይጠይቃል። ነገር ግን እንደዚያ ስናደርግ፣ ጥርጣሬዎቻችን እና ፍርሃቶቻችን ይጠፋሉ።” (“Drawing the Power of Jesus Christ into Our Lives፣” ሊያሆና፣ 41)።

በተጨማሪም ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “አዕምሮዬ በዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ሀሳብ ላይ ተያዘ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ) 91–91ን ተመልከቱ።

ምስል
በተከፈተ መዳፉ ላይ የምስማር ጠባሳ ያለበት የአዳኙ እጅ ምሥል

እጄን ተመልከቱ ዝርዝር፣ በ ጀፍሪ ዋርድ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥29–37

“መልካምን ለማድረግ አትፍሩ።”

አንዳንድ ጊዜ “መልካምን ለማድረግ የምንፈራው” (ቁጥር 33) ለምንድን ነው? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥29–37 ውስጥ መልካምን ለማድረግ ድፍረት የሚሰጣችሁን ምን ታገኛላችሁ? በክርስቶስ ድፍረት እንዲኖራችሁ የሚያነሳሳችሁ እንደ “Let Us All Press On [ወደፊት እንግፋ]” (መዝሙር፣ ቁ. 243) ያለ መዝሙር መዘመርን ወይም ማዳመጥን አስቡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6–79፥3፣ 7–14

“ላደርግልህ እንደምትሻው እንዲሁ ይደረግልሃል።”

“መሻት” ወይንም “መፈለግ” የሚሉት ቃላት በክፍል 6 እና 7 ውስጥ ምን ያህል ጊዜ እንደሚገኙ ልብ በሉ። እግዚአብሔር ለመሻታችሁ ስለሚሠጠው አስፈላጊነት ከእነዚህ ክፍሎች ምን ትማራላችሁ? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 7፥1 ውስጥ ያለውን “ምን ትሻህ” የሚለውን የጌታ ጥያቄ እራሳችሁን ጠይቁ።

ከኦሊቨር ካውድሪ የፅድቅ መሻቶች አንዱ የሆነው—ልክ እንደ ጆሴፍ ስሚዝ የመተርጎም ፍላጎቱ—አልተሟላለትም ነበር። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 9፥3፣ 7–14ን ስታነቡ፣ የተቀደሱ ፍላጎቶቻችሁ አሁን ሳይሟሉ ሲቀሩ ሊረዷችሁ የሚችሉ ምን ግንዛቤዎችን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥8፤ ዳለን ኤች. ኦክስ “እሹ፣” ሊያሆና ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 42–45 ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥5፣ 15–16፣ 22–238፥29፣7–9

የሰማይ አባት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ያናግረኛል።

  • ኦሊቨር ካውደሪ ስለግል ራዕይ የተማራቸው እውነቶች፣ ልጆቻችሁ መንፈስ ቅዱስን የመለየት ችሎታቸውን በሚያዳብሩበት ጊዜ ሊረዳቸው ይችላል። ልጆቻችሁን ስለኦሊቨር እና ስለተማራቸው ነገሮች ለማስተማር “Chapter 5: Joseph Smith and Oliver Cowdery [ምዕራፍ 5፦ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ]” (በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 22–25፣ ውስጥ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን ከወንጌል ላይብረሪ) ልትጠቀሙ ትችላላችሁ። የምትወዱትን የታሪኩን ክፍል አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ። ይህንን ስታደርጉ፣ የእግዚአብሔርን ድምጽ እንዴት እንደሚሰማ ጌታ ለኦሊቨር ባስተማራቸው ነገሮች ላይ አፅንዖት ስጡ እንዲሁም እንደ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥23 ወይም 9፥7–9 ያሉ ተዛማጅ ጥቅሶችን አንብቡ።

    ምስል
    ኦሊቨር ካውድሪ እየፃፈ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እየተመለከተ

    ኦሊቨር ካውድሪ ስለ ራዕይ የተማረው ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን ሲተረጉም እየረዳው በነበረበት ጊዜ ነበር።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፥2 ውስጥ “አእምሮ” እና “ልብ” የሚሉትን ቃላት በምታነቡበት ጊዜ ልጆቻችሁ ጭንቅላታቸውን እና ደረታቸውን እንዲነኩ ልትጋበዟቸውም ትችላላችሁ። መንፈስ ቅዱስ በአእምሮአችሁ እና በልባችሁ በሚናገርበት ጊዜ ምን እንደሚመስል ያሏችሁን ተሞክሮዎች ለልጆቻችሁ ንገሯቸው። “መንፈስ ቅዱስ የሚነጋግረን እንዴት ነው?” ለሚለው ጥያቄ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ መልሶችን እንዲያገኙ እርዷቸው፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥15–16፣ 22–238፥29፣7–9

ታሪኮችን ተጠቀሙ። ታሪኮች፣ ልጆች የወንጌልን መርሆዎች እንዲረዱ ያግዟቸዋል ምክንያቱም ሌሎች ሰዎች እነዚህን መርሆዎች እንዴት እንደሚኖሩ በገሃዱ ዓለም በተግባር ያሳያሉ። ስታስተምሩ፣ ከቅዱሳት መፃህፍት፣ ከቤተክርስቲያን ታሪክ ወይንም ከራሳችሁ ህይወት ውስጥ በቅዱሳት መፃሕፍት ውስጥ ያሉ መርሆዎችን ምሣሌ የሚያቀርቡ ታሪኮችን ለማካተት መንገዶችን ፈልጉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥34

በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት “[አለመፍራት]” እችላለሁ።

  • ጌታ፣ ጆሴፍን እና ኦሊቨርን “አትፍሩ፣ እናንት ትንሽ መንጋዎች” ብሏቸዋል (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 6፥34)። ልጆቻችሁ ይህን ሐረግ ከእናንተ ጋር ብዙ ጊዜ እንዲደጋግሙት ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ፍርሃት የያዛቸው የበጎች መንጋ እንደሆኑ በመምሰልም ሊደሰቱ ይችላሉ። በግ ሊፈራ የሚችለው ምን ሊሆን ይችላል? ከዚያም እናንተ እና ልጆቻችሁ አዳኙ እንደ እረኛ ሆኖ የሚያሳይን ምስል (አንዱ በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ይገኛል) ልትመለከቱ እንዲሁም እረኛ በጎቹን እንደሚጠብቅ እርሱም እኛን እንደሚጠብቅ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ።

  • እንደ “Dare to Do Right [ትክክለኛውን ለማድረግ ድፈሩ]” (የልጆች መዝሙር፣ 158) ወይም “Let Us All Press On [ወደፊት ግፉ]” (መዝሙር፣ ቁጥር 243) የመሰሉ በክርስቶስ ድፍረት ስለማግኘት የሚያወሱ መዝሙሮችን ማጫወትን ወይም መዘመርን አስቡ። አዳኙ እንዳንፈራ እኛን ስለሚረዳበት መንገድ መዝሙሩ ምን ያስተምራል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥36

በሃሳቤ ሁሉ ወደ ክርስቶስ መመልከት እችላለሁ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥36ን በአንድነት ካነበባችሁ በኋላ እናንተ እና ልጆቻችሁ “በሃሳባችሁ ሁሉ ወደ [ኢየሱስ ክርስቶስ] መመልከትን” እንድታስታውሱ የሚረዳችሁን ሥዕል መሳል ትችላላችሁ። ሥዕሎቻችሁን እርስ በእርሳችሁ ተለዋወጡ እንዲሁም ሁልጊዜ ሊያዩዋቸው ይችሉ ዘንድ ሊያስቀምጧቸው የሚችሉባቸውን ቦታዎች እንዲያስቡ ልጆቻችሁን እርዷቸው።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ከበጎች መንጋ ጋር

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፣ በዮንግሱንግ ኪም

ምስል
የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ

አትም