ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የካቲት 17–23 (እ.አ.አ)፦ “አገልጋይ ባልንጀሮቼ … ለእናንተ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 12–17፤ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥66–75


“የካቲት 10–23 (እ.አ.አ)፦ ‘አገልጋይ ባልንጀሮቼ … ለእናንተ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 12–17፣የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥ 66–75፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 12–17፤ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥66–75፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2025 (እ.አ.አ)

ሰስኮሀና ወንዝ

ሰስኮሀና ወንዝ በፔንሲልቫኒያ ሃርመኒ አቅራቢያ

የካቲት 17–23፦ “አገልጋይ ባልንጀሮቼ … ለእናንተ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች12–17የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥66–75

በዓለም ዙሪያ ያሉ አብዛኞቹ ሰዎች ሃርመኒ፣ ፔንሲልቫንያ ስለሚባል ቦታ ሰምተው አያውቁም ይሆናል። አብዛኛውን ጊዜ፣ ጌታ በመንግሥቱ ውስጥ ለሚፈጸሙ ጉልህ ክስተቶች አነስተኛ ግምት የሚሰጣቸውን ስፍራዎች ይመርጣል። ግንቦት 15፣ 1829 (እ.አ.አ) በሃርመኒ አቅራቢያ በሚገኝ በደን የተሸፈነ ስፍራ መጥምቁ ዮሃንስ ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለኦሊቨር ካውድሪ ተገለጠላቸው። “አገልጋይ ባልንጀሮቼ” ብሎ ከጠራቸው በኋላ፣ እጁን በጭንቅላታቸው ላይ በመጫን የአሮናዊ ክህነት ስልጣንን ሰጣቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥1)።

መጥምቁ ዮሃንስ ኢየሱስ ክርስቶስን ያጠመቀውና ለመምጣቱ መንገዱን የጠረገለት የታመነ አገልጋይ ነበር (ማቴዎስ 3፥1–6፣ 13–17 ተመልከቱ)። እነዚህ ገና በሃያዎቹ የእድሜ ክልል የነበሩት ሁለቱ ወጣቶች የዮሐንስ አገልጋይ ባልንጀራ ተብለው መጠራታቸው በትህትና ዝቅ የሚያደርግና ምናልባትም ከአቅማቸው በላይ የሆነባቸው ሳይሆን አይቀርም። በወቅቱ፣ እንደ ሃርመኒ ሁሉ፣ ጆሴፍን እና ኦሊቨርንም በንፅፅር ማንም አያውቃቸውም ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር ስራ ውስጥ ማገልገል ሁልጊዜ እንዴት እናገለግላለን የሚለው ነው እንጂ ማን ያስተውለናል የሚለው አይደለም። ምንም እንኳን አስተዋዕጿችሁ አንዳንድ ጊዜ ትንሽ ወይንም የማይታይ ቢመስልም፣ እናንተም በጌታ “በታላቅ እና ድንቅ ስራ” ውስጥ ከእስሩ ጋር አገልጋይ ባልንጀሮች ናችሁ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥1)።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1214

በእግዚአብሔር “ታላቅ እና ድንቅ ስራ” ላይ ተሳታፊ መሆን እችላለሁ።

ጆሴፍ ናይት እና ዴቪድ ዊትመር በጌታ ስራ ላይ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ለማወቅ ፈለጉ። ጌታ የሰጠውን መልስ ስታነቡ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1214) “የፅዮንን እንቅስቃሴ [መፈፀም እና መመሥረት]” ምን ማለት እንደሆነ አስቡ (12፥6፣ በተጫማሪም 14፥6 ተመልከቱ)። በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ ይህን ለማድረግ የሚረዷችሁ ምን መርሆዎች እና የክርስቶስ መሰል ባህርያት አገኛችሁ?

በተጨማሪም “The Knight and Whitmer Families [የናይት እና የዊትመር ቤተሰቦች]፣” ራዕያት በአገባብ፣ 20–24 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13

ኢየሱስ ክርስቶስ የአሮናዊ የክህነት ስልጣንን ዳግም እንዲመልስ መጥምቁ ዮሐንስን ላከው።

መጥምቁ ዮሐንስ፣ ጆሴፍ ስሚዝን እና ኦሊቨር ካውድሪን “አገልጋይ ባልንጀሮቼ” ሲል ጠራቸው። ከመጥምቁ ዮሐንስ ጋር አገልጋይ ባልንጀራ መሆን ማለት ምን ይመስላችኋል? (ማቴዎስ 3፥13–17ሉቃስ 1፥13–173፥2–20 ተመልከቱ)።

በክፍል 13 ውስጥ መጥምቁ ዮሐንስ የተናገረውን ስታነቡ፣ የክህነት ቁልፎቹ የጌታን መንገድ የማዘጋጀት የነበረውን የዮሐንስ ተልዕኮ ለማከናወን እንዴት እንደሚረዱት አሰላስሉ። ለምሳሌ፦

እንደ ጥምቀት እና ቅዱስ ቁርባን ያሉ የአሮናዊ ክህነት ሥርዓቶች አዳኙን በህይወታችሁ ለመቀበል መንገዱን ለማዘጋጀት የሚረዷችሁ እንዴት ነው?

የክህነት ቁልፎች ምንድን ናቸው?

ዴል ጂ. ረንላንድ እና ባለቤታቸው ስለክህነት ቁልፎች የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፦

“የክህነት ቁልፎች የሚለው ቃል በሁለት የተለያዩ መንገዶች ጥቅም ላይ ይውላል። የመጀመሪያው፣ የአሮናዊ ወይም የመልከ ጼዴቅ ክህነት ለተቀበሉት ሁሉ የተሰጠውን ልዩ መብት ወይም ዕድል ያመለክታል። ለምሳሌ፣ የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች የመላእክት አገልግሎት ቁልፎችን እና የንስሐ እንዲሁም ለኃጢያት ስርየት በውሃ ውስጥ በመጥለቅ የሚከናወን ጥምቀት ወንጌል ዝግጅት ቁልፎችን ይቀበላሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥184፥26–27 ተመልከቱ)። የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች የመንግስቱን ሚስጥሮች ቁልፍ፣ የእግዚአብሔርን እውቀት ቁልፍ እንዲሁም የሁሉንም የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ በረከቶች ቁልፎች ይቀበላሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19107፥18 ተመልከቱ)።

“ሁለተኛው፣ የክህነት ቁልፎች የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የሚውልበት መንገድ አመራርን ለማመልከት ነው። የክህነት መሪዎች ተጨማሪ የቤተክርስቲያኗን ወይም የቡድን ድርጅት ክፍልን በበላይነት የመምራት የክህነት ቁልፎችን ይቀበላሉ። በዚህ ረገድ፣ የክህነት ቁልፎች በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የመምራት እና የማስተዳደር ስልጣን እና ሀይል ይሰጣሉ” (The Melchizedek Priesthood: Understanding the Doctrine፣ Living the Principles [የመልከ ጼዴቅ ክህነት፦ አስተምህሮቱን መረዳት፣ በመርሆዎቹ መኖር] [2018 (እ.አ.አ)]፣ 26)።

ጆሴፍ ስሚዝ ኦሊቨር ካውድሪን ሲያጠምቀው

ጆሴፍ ስሚዝ ኦሊቨር ካውድሪን አጠመቀ በዴል ፓርሰን

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥66–75

የሴሚናሪ ምልክት
ሥርአቶች የእግዚአብሔርን ሃይል እንዳገኝ መንገድ ይሰጡኛል።

በዳግም መመለሱ ዋና ዋና ክንውኖች ወቅት ከጆሴፍ ስሚዝ እና ከኦሊቨር ካውድሪ ጋር መሆን ምን ሊመስል ይችል እንደነበር አስባችሁ ታውቃላችሁን? የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥66–75 እና በቁጥር 71 መጨረሻ ላይ ያለውን ማስታወሻ ስታነቡ፣ ቢያንስ የተወሰነውን የተሰማቸውን ልትገነዘቡ ትችላላችሁ። ከተናገሩት ቃላት ያስደነቀቃችሁ ምንድን ነው? ክህነትን ስለተቀበሉ እና ስለተጠመቁ የተቀበሏቸውን በረከቶች በተለይ አስተውሉ። አዳኙ፣ በክህነት ሥርዓቶች በኩል ምን በረከቶችን ሰጥቷችኋል?

የበለጠ ለመማር፣ ሥርዓቶች እና በረከቶች የሚሉ ርዕሶች ያሉት ሰንጠረዥ መስራትን አስቡ። ከዚያም ከእነርሱ የሚገኙትን ሥርዓቶች እና በረከቶች ለመዘርዘር እንደዚህ ያሉ የቅዱሳት መሳህፍት ጥቅሶችን ልትፈልጉ ትችላላችሁ፦ ዮሐንስ 14፥26ሥራ 2፥38ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19–22131፥1–4የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥73–74። በዚህ ዝርዝር ላይ ምን ሌሎች በረከቶች ትጨምራላችሁ? የተቀበላችኋቸው ሥርዓቶቹ የአዳኙን ሃይል ወደ ህይወታችሁ ያመጡት እንዴት ነው?

በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “With the Power of God in Great Glory [በእግዚአብሔር ኃይል በታላቅ ክብር]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021(እ.አ.አ)፣ 28–30፤ ቅዱሳን1፥65–68፤ “God of Power፣ God of Right [የሀይል አምላክ፣ የትክክል አምላክ]፣” መዝሙር፣ ቁ. 20፤ ርዕሶች እና ጥያቄዎች፣ “ቃል ኪዳኖች እና ሥርዓቶች፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15–16

ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ማምጣት ታላቅ ዋጋ አለው።

እንደ ዮሐንስ እና ጴጥሮስ ዊትመር በህይወታችሁ “ታላቅ ዋጋ ያለው” ምን ሊሆን እንደሚችል አስባችሁ ታውቃላችሁን? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15፥416፥4)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15–16ን ስታነቡ፣ ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ማምጣት ትልቅ ዋጋ ያለው ለምን እንደሆነ አሰላስሉ። “ነፍሳትን [ወደ ክርስቶስ] ለማምጣት” ምን እያደረጋችሁ ናችሁ?

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥68–71 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 17

ጌታ ቃሉ ይፈጸም ዘንድ ምስክሮችን ይጠቀማል።

ምስክር ምንድን ነው? ጌታ በስራው ምስክሮችን የሚጠቀመው ለምንድን ነው? (2 ቆሮንጦስ 13፥1ን yመልከቱ)። እግዚአብሔርን ለሶስቱ ምስክሮች የተናገረውን ቃል በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 17 ውስጥ ስታነቡ እነዚህን ጥያቄዎች አሰላስሉ። (እንዲሁም በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ያለውን “የሶስቱ ምስክሮች ምስክርነት” ተመልከቱ።) ምስክሮች እንዴት አድርገው ነው የእግዚአብሔርን “የጽድቅ አላማ” ለማምጣት የሚረዱት? (ቁጥር 4)።

ስለ ምን መመስከር ትችላላችሁ?

በተጨማሪም “ቅዱሳን1፥73–75፤ “Days of Harmony [ስምምነት ቀናት]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

23:9

A Day for the Eternities

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13; ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥68–74

መጥምቁ ዮሐንስ የአሮናዊ የክህነትን ዳግም መለሰ።

  • በዚህ መዘርዝር ውስጥ ያለው የስዕል ሥራ ልጆቻችሁ የአሮናዊ ክህነትን ዳግም መመለስ በአእምሯቸው ማየት እንዲችሉ ሊረዳቸው ይችላል (በተጨማሪም “Chapter 6፥ Joseph Smith and His Family [ምዕራፍ 6፦ ጆሴፍ ስሚዝ እና ቤተሰቡ]፣” በበትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች ውስጥ፣ 26–27፣ ወይም የሱን ተዛማጅ ቪዲዮ በወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ)። እነርሱ በጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥68–74 ውስጥ አብራችሁ ካነበባችሁት በመነሳት ስለሁኔታው ሰዕል በመሳል ይደሰቱ ይሆን?

    2:12

    Angels Restore the Priesthood: Power to do God's work

  • ማቴዎስ 3፥13–17ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥68–70 በአንድነት ስታነቡ፣ የመጥምቁ ዮሐንስን ምሥል ልታሳዩ ትችላላችሁ። ለጆሴፍ ስሚዝ የማጥመቅ የክህነት ስልጣን እንዲሰጠው ጌታ መጥምቁ ዮሐንስን መላክ ያስፈለገው ለምን ነበር?

ልጆቻችሁ ለእድሜ ልክ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ እንዲሆኑ ማዘጋጀት። ልጆቻችሁ ስለክህነት ሃይል፣ ሥልጣን እና ቁልፎች እንዲማሩ ለመርዳት ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት አባሪ ሀ ወይም አባሪ ለን ተመልከቱ።

መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያጠምቅ

ኢየሱስ ሲጠመቅ የሚያሳይ ስዕል በዳን በር

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13

የሰማይ አባት በአሮናዊ ክህነት አማካኝነት ይባርከኛል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13 ላይ ስለተጠቀሱት ቁልፎች ውይይት ለመጀመር እናንተ እና ልጆቻችሁ የቁልፎች ሥብሥብን ልትመለከቱ እና ቁልፎች ምን ማድረግ እንደሚያስችሉን መነጋገር ትችላላችሁ። ምናልባት በክፍል 13 ውስጥ ቁልፎች የሚሉትን ቃላት እንዲያገኙ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13 ውስጥ የአሮናዊ ክህነት በረከቶችን የሚገልጹት ሌሎች ቃላት ወይም ሀረጎች የትኞቹ ናቸው? ልጆቻችሁ፣ “የክህነት በረከቶች” (የወንጌል ላይብረሪ) በሚለው ቪዲዮ ውስጥ ያሉትን የሰማይ አባት በክህነት አማካኝነት እኛን የሚባርክበትን መንገዶች ሊለዩም ይችላሉ።

3:4

Blessings of the Priesthood

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15፥4–616፥4–6

ሌሎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጡ መርዳት “ትልቅ ዋጋ ያለው” ነገር ነው።

  • ጆን እና ፒተር ዊትመር በህይወታቸው “በጣም ትልቅ ዋጋ” ሊኖረው የሚችለው ምን እንደሆነ ማወቅ ፈለጉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15፥416፥4)። ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ ለእናንተ በጣም ትልቅ ዋጋ ስላላቸው ነገሮች ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15፥4–6 ወይም 16፥6ን ስታነቡ ጌታ “በጣም ትልቅ ዋጋ” ያለው ነገር ነው ስላለው ነገር ሲሰሙ ልጆቻችሁ እጃቸውን እንዲያወጡ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ።

  • “ነፍሳትን ወደ [ኢየሱስ ክርስቶስ] ማምጣት” ማለት ምን ማለት ነው? ልጆቻችሁ፣ ከሌሎች ጋር ጓደኛ እንደመሆን፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ለጓደኛ እንደማካፈል ወይም እርዳታ ለሚያስፈልገው ሰው እንደመጸለይ ያሉ ሃሳቦችን ዝርዝር እንዲያዘጋጁ እርዷቸው። ልጆቻችሁ እነዚህን ነገሮች በቤተክርስቲያን መጽሔቶች ወይም በየወንጌል የአርት መፅሐፍ ውስጥ መፈለግ ይችላሉ። ወይንም የራሳቸውን ሥዕል መሳልም ይችላሉ። ከዝርዝራቸው ውስጥ የሚሰሩትን አንድ ነገር እንዲመርጡ ጋብዟቸው። “I Feel My Savior’s Love [የአዳኜ ፍቅር ይሰማኛል]” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 74–75) የሚለውን መዝሙር አራተኛ ስንኝ አብራችሁ መዘመርም ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 17

የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክር መሆን እችላለሁ።

  • Chapter 7፥ Joseph Smith and Oliver Cowdery [ምዕራፍ 7፦ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ]” (በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 31–33፣ ወይም በወንጌል ላይብረሪ ባለው ተዛማጅ ቪዲዮ ውስጥ) ልጆቻችሁ ስለሶስቱ ምስክሮች እንዲማሩ ሊረዳቸው ይችላል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 17፥5–6ን ስታነቡ፣ መፅሐፈ ሞርሞን እውነት መሆኑን እንዴት እንዳወቃችሁ ንገሯቸው። የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክሮች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

    4:58

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ጆሴፍ እና ኦሊቨር አሮናዊ ክህነትን ከመጥምቁ ዮሃንስ ተቀበሉ።

አገልጋይ ባልንጀሮቼ … ለእናንተ በሊንዳ ከርሊ ክሪስቸንሰን

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ