“ትምህትና ቃል ኪዳኖች 15፟–21፦ ‘ቤተሰብ ፈጣሪው ላለው እቅድ … ዋና ክፍል [ነው]’፦ ቤተሠብ፦ ለዓለም የተላለፈ ዓዋጅ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]
“ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ ዓዋጅ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፦ 2025 (እ.አ.አ)
“ቤተሰብ ፈጣሪ ላለው እቅድ … ዋና ክፍል [ነው]”
ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ ዓዋጅ
ከመወለዳችን በፊት እንኳን የቤተሰብ አካል ነበርን—የሰማይ ወላጆቻችን ቤተሰብ አካል ነበርን። ያ ንድፍ በምድር ላይ ቀጥሏል። እዚህ ያሉት ቤተሠቦች፣ የተሣካላቸው በሚሆን ጊዜ፣ በሰማይ የነበረውን ፍጹም የሆነውን ንድፍ እንዲያንፀባርቁ የታሰቡ ናቸው።
ምድራዊ ቤተሰቦች ፍፁም እንደሚሆኑ ወይም የታለመላቸውን ዓላማ ለማሳካት እንኳን የሚጠቅሙ እንደሚሆኑ ዋስትና የለም። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ እንዳስተማሩት፣ ቤተሰቦች፣ “በሰማይ ሣለን ይሰማን ከነበረው ጋር በሚቀራረበው በምድር ባለው ብቸኛው ፍቅር—የወላጅ ፍቅር፣ ወደዚህ ዓለም በጥሩ ሁኔታ ለመቀበል ከሁሉ የተሻለውን እድል ለእግዚአብሔር ልጆች ይሰጣሉ።” [“የእግዚአብሔርን ቤተሰብ መሰብሰብ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 20]። ቤተሰቦች ፍጽምና የጎደላቸው እና ለጠላት ጥቃቶች የተጋለጡ መሆናቸውን አውቆ፣ እግዚአብሔር ውድ ልጁን ቤዛችን እንዲሆን እና ቤተሰቦቻችንን እንዲፈውስ ልኳል። እንዲሁም ቤተሰቦችን ለመጠበቅ እና ለማፅናናት የኋለኛውን ቀን ነቢያትን ከአዋጅ ጋር ልኳል። ነቢያትን ከተከተልን እና እምነታችንን በአዳኛችን ላይ ካደረግን፣ ምንም እንኳን ምድራዊ ቤተሰቦች መለኮታዊ ፍፅምና ባይኖራቸውም፣ በምድርም በሰማይም ለቤተሰቦች ተስፋ አለ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
“ቤተሰብ ፈጣሪ ላለው እቅድ … ዋና ክፍል [ነው]።”
“ቤተሰብ፥ ለዓለም የተላለፈ አዋጅ” በግልፅ ስለቤተሰቦች ነው። ነገር ግን በእኩል ደረጃ ስለ እግዚአብሔር የደህንነት ዕቅድ ነው። አዋጁን የማጥኛ አንደኛው መንገድ ቅድመ ምድራዊ ህይወት፣ ምድራዊ ህይወት እና ከምድራዊ ህይወት በኋላ ያለ ህይወት የሚሉትን ሀረጎች በቁራጭ ወረቀት ላይ መፃፍና አዋጁ ስለእነዚህ ስለእያንዳንዱ ርዕስ የሚያስተምረውን መዘርዘር ነው። አዋጁን በዚህ መንገድ ስታጠኑ ምን ትማራላችሁ? ጋብቻ እና ቤተሰብ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑት ለምን እንደሆነ እንድትገነዘቡ የሚረዳችሁ እንዴት ነው? በአዋጁ ውስጥ ያሉት እውነቶች በምርጫዎቻችሁ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩት እንዴት ነው?
በተለያዩ ምክንያቶች ጋብቻን ወይም ልጆች ማሳደግን የሚፈሩ ብዙ ሰዎች አሉ። አንድ ጓደኛችሁ “ትዳር መመሥረት ወይም ቤተሰብ እንዲኖረኝ አልፈልግም” ቢላችሁ ምን ምላሽ ትሠጣላችሁ? ምናልባት ጓደኛችሁ በእግዚአብሔር እቅድ ላይ ተስፋ ይኖረው ዘንድ የሚረዳውን ነገር ለማግኘት በአዋጁ ውሥጥ ልትፈልጉ ትችላላችሁ።
ሌላው ልትጠየቁ የምትችሉት ጥያቄ ወይም እራሳችሁን ልትጠይቁ የምትችሉት ጥያቄ የሚከተለውን የመሠለ ነው፦ “የቤተሰቤ ሁኔታ በቤተሰብ አዋጁ ውሥጥ ከተገለጸው ጋር የማይመሳሰል ቢሆንስ?”። ነቢያዊ ምክር ልታገኙ የምትችሉባቸው ሁለት ቦታዎች እነሆ፦ “A Mighty Change [ታላቅ ለውጥ]” በሚለው በሽማግሌ ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ መልእክት ክፍል ውስጥ“Jesus Christ Is the Strength of Parents [ኢየሱስ የወላጆች ጥንካሬ ነው]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 55–59) እና “Why Marriage, Why Family [ጋብቻ፣ ቤተሰብ ለምን ያስፈልጋል]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 52) በተሰኘው የሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን መልዕክት የመጨረሻ አራት አንቀፆች ውስጥ።
ባጠናችሁት ጥናት ምክንያት ምን ለማድረግ መነሣሣት ይሰማችኋል?
በተጨማሪም ዳለን ኤች. አኦክስ፣ “The Plan and the Proclamation [እቅዱ እና አዋጁ]፣” ሊያሆና፣ Nov. 2017 (እ.አ.አ)፣ 28–31፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “Family [ቤተሰብ]፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።
“እያንዳንዱም [ግለሠብ] በሰማይ ወላጆች የተወደዱ … ሴት [ወይም] ወንድ ልጆች ናቸው።”
ብዙውን ጊዜ የቤተሰብ አዋጁ የቤተሰብ ህይወት መመሪያ እንደሆነ እናስባለን። ነገር ግን ስለሰማያዊ ቤተሰባችን እና ስለዘለዓለማዊ ማንነታችን ጠቃሚ እውነቶችንም ያስተምራል። ሁላችንም የዚህ ቤተሰብ አካል መሆናችንን ማወቃችሁ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህ እውነት በምርጫዎቻችሁ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?
በተጨማሪም “I Am a Child of God [እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ]፣” መዝሙር፣ ቁ. 301 ተመልከቱ።
“በቤተሰብ ህይወት ውስጥ ደስታ የሚገኘው ቤተሰብ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ላይ ሲገነባ ነው።”
የቤተሰብ አዋጁን አንቀጽ ስድስት እና ሰባት “ለቤተሰብ ህይወት ደስታን” እንደሚያስገኝ ንድፍ አድርጋችሁ አስቡት። እነዚህን አንቀጾች በምታነቡበት ጊዜ “የተሳኩ ጋብቻዎች እና ቤተሰቦች” መርሆዎችን ለዩ። በቤተሰባችሁ ውስጥ ወይም በሌሎች ቤተሰቦች ውስጥ ስላያችኋቸው የእነዚህ መርሆዎች ምሳሌዎች ታስቡ ይሆናል። እነዚህ መርሆዎች፣ ኢየሱስ ክርስቶስን የቤተሰብ ህይወት መሠረት ለማድረግ የሚረዱት እንዴት ነው?
ከዚያም ልታጠናክሩት ስለምትፈልጉት የቤተሰብ ግንኙነት አስቡ። በተቀበላችኋቸው ግንዛቤዎች ላይ ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ በአዳኙ እርዳታ እቅድ አውጡ።
በተጨማሪም ኤል. ዊትኒ ክሌይተን “The Finest Homes [ከሁሉም በላይ መልካም የሆኑ ቤቶች]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 107–19ን ተመልከቱ።
“ሀላፊነት [የሚሠማቸው] ዜጎች… ቤተሰብ … እንዲጠናከር እርምጃዎች እንዲወስዱም ጥሪ እናቀርባለን”።
የቤተሠብ አዋጁ የመጨረሻ አንቀፅ ተግባራዊ እርምጃ የመውሰድ ጥሪን ያካትታል። ለዚህ ጥሪ እንዴት ምላሽ እንደምትሰጡ ስታስቡ የአዋጁን ርዕስ ማጥናት ሊረዳ ይችላል። ለምሣሌ፣ አዋጅ ምንድን ነው? ይህ ቃል ሰነዱ ስለያዘው መልዕክት ለእናንተ ምን ያመለክታል? የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን ቤተሰብን አስመልክቶ ለአለም አዋጅ ለማውጣት ብቁ ያደረጋቸው ምንድን ነው? የአዋጁ ዋና መልእክቶች ናቸው የምትሏቸውን ዝርዝር ልታዘጋጁም ትችላላችሁ። እነዚህን መልዕክቶች በህይወታችሁ፣ በቤታችሁ እና በማህበረሰባችሁ ውስጥ ማስተዋወቅ የምትችሉት እንዴት ነው?
በተጨማሪም ቦኒ ኤል. ኦስካርሰን፣ “Defenders of the Family Proclamation [የቤተሰብ አዋጅ ጠባቂዎች]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 14–17፤ “Defenders of the Faith [የእምነት ጠባቂዎች]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ቤተሰቦች ለሠማይ አባት እቅድ አስፈላጊ ናቸው።
-
ለእነርሱ በጣም አስፈላጊ በመሆናቸው ምክንያት፣ ስለእነሱለሁሉም ለመንገር የሚፈልጓቸውን ነገሮች እንዲያስቡ ልጆቻችሁ እርዷቸው። “ቤተሰብ፦ ለዓለም የተላለፈ ዓዋጅ” የሚለውን ፅሁፍ አንድ ቅጂ ለልጆቹ አሳዩዋቸው እንዲሁም ነቢያት እና ሐዋርያት፣ ቤተሰቦች ለሰማይ አባት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ ለሁላችንም ለመንገር የፃፉት እንደሆነ አስረዱ። ቤተሠቦች ለእርሱ በጣም አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? (በተጨማሪም፣ “What Is the Purpose of Family? [የቤተሰብ አላማ ምንድን ነው?]” [ChurchofJesusChrist.org] የሚለውን ቪዲዮ ተመልከቱ)።
-
ሁላችንም ልናውቀው እንደሚገባን የሚሠማችሁን ነገር ከዓዋጁ በማውጣት ለልጆቻችሁ አካፍሉ። ልጆቻችሁ ስለእነዚያ እውነታዎች የሚሠማቸውን እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። እነዚህን ነገሮች ባናውቃቸው ኖሮ ህይወታችን የተለየ ሊሆን ይችል የነበረው እንዴት ነው? እንደ “I Will Follow God’s Plan [የእግዚአብሔርን እቅድ እከተላለሁ]” (የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 164–65) ከመሠሉ በአዋጁ ውስጥ ከሚገኙ እውነቶች ጋር የሚዛመድ መዝሙር አብራችሁ ልትዘምሩ ትችላላችሁ።
-
ፕሬዚዳንት ዳለን ኤች. ኦክስ “The Plan and the Proclamation [እቅዱ እና አዋጁ]” (ሊያሆና፣ ህዳር. 2017(እ.አ.አ)፣ 30) በተባለው መልዕክት ክፍል 4 ውስጥ፣ የቤተሰብ አዋጁ እንዴት እንደተጻፈ ገልፀዋል። ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ የእርሳቸውን መግለጫ አብራችሁ ልትከልሡና ጌታ ስለቤተሰብ እውነቶችን እንዲያስተምሩን አገልጋዮቹን ስላነሳሳ ለምን አመሰጋኝ እንደሆናችሁ ማውራት ትችላላችሁ።
-
የቤተሰብ አዋጁ ውስጥ የሚገኙትን እውነቶች የሚያሳዩ ሥዕሎችን(ወይም የተወሰኑ ሥዕሎችን እንዲስሉ ጋብዟቸው) ለልጆቻችሁ ማሳየትም ትችላላችሁ። እነዚህም፣ የቤተመቅደስ ምስሎች፣ ቤተሰብ እየፀለዩ ወይም አብረው እየተጫወቱ ወይም ጥንዶች ጋብቻቸውን እየፈፅሙ ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚያም ልጆቻችሁ ከምስሎቹ ጋር የሚዛመዱ ዓረፍተ ነገሮችን በቤተሰብ አዋጁውስጥ ሊፈልጉ ይችላሉ። ጌታ በአዋጁ ውስጥ ስለእነዚህ ነገሮች ምን ያስተምረናል?
እኔ “[የ]ሠማይ ወላጆች [ውድ] የመንፈስ ወንድ ልጅ ወይም መንፈሣዊ ሴት [ልጅ ነኝ]።”
-
“I Am a Child of God [እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ]” (የልጆች መፅሐፍ፣ 2–3) የሚለውን መዝሙር አብራችሁ ስትዘምሩ፣ “[የልጁ ሥም].የሚባል የእግዚአብሔር ልጅ አውቃለሁ” በማለት ለአንድ ልጅ ኳሷን መወርወር ትችላላችሁ። ከዚያም ያ ልጅ የዚያን ሰው ስም በማስገባት ተመሳሳይ ቃላትን በመናገር እቃውን ወደ ሌላ ሰው ሊወረውር እና ይችላል። ልጆቻችሁ በቤተሰብ አዋጁ ውስጥ “የሰማይ ወላጆች የተወደዱ የመንፈስ ሴት ወይም ወንድ ልጆች” የሚለውን ሐረግ እንዲያገኙ እርዷቸው እንዲሁም የዚህን እውነታ ምስክርነት ስጡ።