“ታህሳስ 8–14፦ ‘እናምናለን’፦ የእምነት አንቀጾች እና አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2፦” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]።
የእምነት አንቀጾች እና አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2፦” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 8-14፦ “እናምናለን”
የእምነት አንቀጾች እና አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2
ከጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ ጀምሮ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኑን በራዕይ አማካኝነት መምራቱን ቀጥሎ ነበር። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ያ ራዕይ በቤተክርስቲያኗ ፖሊሲዎች እና ልምዶች ላይ ለውጦችን አካትቷል። አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2 እንደዚህ አይነት ራዕዮችን ይወክላሉ—አንደኛው ከአንድ ሚስት በላይ ጋብቻ እንዲያበቃ ያደረገ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ የክህነት በረከቶች ለሁሉም ዘሮች እንዲገኝ አድርጓል። እንደነዚህ ያሉ ለውጦች፣ እውነተኛ እና በህይወት ያለ ነቢይ ያላት፣ በእውነተኛ እና በህያው እግዚአብሔር የምትመራ “እውነተኛ እና ህያው ቤተክርስቲያን” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥30) የመኖር ትርጉም አካል ናቸው።
ነገር ግን ዘለዓለማዊ እውነት አይለወጥም፣ ምንም እንኳን ስለእሱ ያለን ግንዛቤ ቢለወጥም። ስለዚህም፣ አንዳንድ ጊዜ ራዕይ በእውነት ላይ ተጨማሪ ብርሃን ይፈነጥቃል። የእምነት አንቀጾች የዚህ አይነት የማብራራት ዓላማ አላቸው። ቤተክርስቲያኗ በዘለዓለም እውነት ላይ የተመሰረተች ናት ነገር ግን “እንደ ጌታ ፈቃድ፣ እንደ ሰው ልጆች ሁኔታዎች ምህረቱን በማመቻቸት” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥15) ማደግ እና መለወጥ ትችላለች ። በሌላም አባባል፣ “እግዚአብሔር እስካሁን በገለጣቸው ሁሉ፣ አሁንም በሚገልጣቸው ሁሉ እናምናለን፣ እናም የእግዚአብሔርን መንግስት በተመለከተ ወደፊትም እርሱ በሚገልጣቸው ታላቅና አስፈላጊ ነገሮችም እናምናለን” (የእምነት አንቀጾች 1፥9)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
የእምነት አንቀጾች ዳግም የተመለሰውን ወንጌል መሠረታዊ እውነቶች ይዘዋል።
የእምነት አንቀጾችን ለማጥናት የሚረዳውን ይህን መንገድ አስቡ፦ ለእያንዳንዱ የእምነት አንቀጽ፣ የምታምኑበትን ነገር ለማስረዳት “ትንሽ ትምህርት” አዘጋጁ። ትንሽ ትምህርታችሁም ተዛማጅ የሆኑ የቅዱሣት መፃህፍት ጥቅስን፣ ሥዕልን፣ መዝሙርን ወይም የልጆች መዝሙርን፣ ወይም የእምነት አንቀፁ የሚያስተምረውን እውነት ስለመኖር የሚገልፅ የግል ተሞክሮን ሊያካትት ይችላል።
እነዚህ እውነቶች ከሠማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባላችሁ ግንኙነት ላይ ምን ልዩነት ያመጣሉ? የእምነት አንቀጾች የወንጌል ጥናታችሁን ያሻሻሉት ወይም ወንጌልን ለሌሎች እንድታካፍሉ የረዷችሁ እንዴት ነው?
በተጨማሪም የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያን፣ “የእምነት አንቀጾች፣” ወንጌል ላይብረሪ፤ ኤል ቶም ፔሪ፣ “The Doctrines and Principles Contained in the Articles of Faith [በእምነት አንቀጾች ውስጥ ያሉት ትምህርቶች እና መርሆዎች]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 46–48፤ “Chapter 38: The Wentworth Letter [ምዕራፍ 38፦ የዌንትወርዝ ደብዳቤ]፣” በየቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፦ ጆሴፍ ስሚዝ፣ (2011 [እ.አ.አ])፣ 435–47 ተመልከቱ።
የእምነት አንቀጾች 1፥9፤ አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2
የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በራዕይ ትመራለች።
“የእግዚአብሔርን መንግስት በተመለከተ እርሱ ወደፊትም በሚገልጣቸው ብዛት ያላቸው ታላላቅና አስፈላጊ ነገሮችም እናምናለን” (የእምነት አንቀጾች 1፥9)። ይህንን መርህ በዓእምሯችሁ በመያዝ፣ አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና2 ገምግሙ፣ እንዲሁም በራዕይ ቀጣይነት ላይ ያላችሁን እምነት የሚያጠናክሩ ቃላትን እና ሀረጎችን ፈልጉ። እነዚህ ራዕያት በህይወታችሁ ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩት እንዴት ነው? የሰማይ አባት መንግሥት ሥራ እንዲያድግ የረዱት እንዴት ነው?
ቤተክርስቲያኗ ዛሬ “ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በሚሠጠው መነሳሳት” እንደምትመራ ምን ማስረጃ ታያላችሁ? (አስተዳደራዊ አዋጅ 1)። ምናልባት ጌታ የእርሱን ቤተክርስቲያን እና የእናንተን ህይወት እየመራ ስላለበት መንገድ በመፈለግ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የቅርብ ጊዜ አጠቃላይ የጉባኤ መልእክቶችን ልትከልሱ ትችላላችሁ። የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንትን እጅግ የቅርብ ጊዜ መልዕክት ለመጀመር ጥሩ ቦታ ሊሆን ይችላል።
እናንተ ወይም የምትወዱት አንድ ሠው ጌታ በነቢያቱ በኩል የሚያስተምረውን ለመገንዘብ ወይም ለመቀበል ብትቸገሩ ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ? ስለነቢያት አመስጋኝ የሆናችሁት ለምንድን ነው?
በተጨማሪም፣ አሞፅ 3፥7፤ 2 ኔፊ 28፥30፤ አለን ዲ. ሄይኒ፣ “A Living Prophet for the Latter Days [በህይወት ያለ የኋለኛው ቀን ነቢይ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 25–28፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “ነቢያት፣” ወንጌል ላይብረሪ፤ “We Thank Thee, O God, for a Prophet አምላክ ሆይ፣ ስለነቢዩ እናመሰግንሀለን]፣” መዝሙር፣ ቁ. 19 ተመልከቱ።
የእግዚአብሔር ሥራ እያደገ መሄድ አለበት።
“ፕሬዚዳንት ዊልፈርድ ዉድረፍ ማኒፈስቶውን አስመልክተው ከሰጡት ሶስት ንግግሮች የተወሰደ ምንባብ” (በአስተዳደራዊ አዋጅ 1 መጨረሻው ላይ) ውስጥ፣ ጌታ በቤተክርስቲያኗ ከአንድ በላይ ጋብቻ የመፈፀም ልምድን ለማቆም ስለሠጣቸው ምክንያቶች ነቢዩ ምን ተናገሩ? ይህ ስለ እግዚአብሔር ሥራ ምን ያስተምራችኋል?
ስለ አስተዳደራዊ አዋጅ 1፣ ታሪካዊ መነሻ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ “Saints [ቅዱሳን]” 2፥602–15፤ “The Messenger and the Manifesto [መልዕክተኛው እና ማኒፈስቶው]፣” በRevelations in Context [ራዕያት በአገባብ]፣ 323–31 ውስጥ፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “Plural Marriage and Families in Early Utah [ከአንድ በላይ ጋብቻ እና ቤተሰቦች በቀድሞው ዩታ]፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።
ፍጹም የሆነ መረዳት በማይኖረንም ጊዜ እንኳን በጌታ ላምን እችላለሁ።
የክህነት ሹመት እና የቤተመቅደስ ሥርዓቶች የአፍሪካ ዝርያ ላላቸው የቤተክርስቲያኗ አባላት ለምን እንዳልተፈቀዱ አናውቅም። ስለዚያ ፖሊሲ ያልተመለሱ ከባድ ጥያቄዎች ባጋጠሟቸው ጊዜም እንኳን፣ ብዙ ጥቁር የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በጌታ ታምነዋል (ምሳሌ 3፥5 ተመልከቱ) እንዲሁም በህይወታቸው ሙሉ ለእርሱ ታማኝ በመሆን ቆይተዋል። ስለእምነታቸው እና ስለተሞክሯቸው መማር የሚያነሳሳችሁ ሊሆን ይችላል። ከታሪኮቻቸው ውስጥ የተወሰኑት፣ በhistory.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ ይገኛሉ፦
-
“In My Father’s House Are Many Mansions [በአባቴ ቤት ውስጥ ብዙ መኖሪያዎች አሉ]” (የግሪን ፍሌክ ታሪክ)
-
“You Have Come at Last [በመጨረሻ መጥታችኋል]” (የአንቶኒ ኦቢያን ታሪክ)
-
“Break the Soil of Bitterness” (የጁሊያ ማቪምቤላ ታሪክ)
-
“I Will Take It in Faith [በእምነት ይህን እወስዳለሁ]” (የጆርጀ ሪከፎርድ ታሪክ)
-
“Long-Promised Day [ለረጅም ጊዜ በተስፋ የተሰጠ ቀን]” (የጆሴፍ ደብልዩ. ቢ. ጆንሰን ታሪክ)
አስተዳደራዊ አዋጅ 2ን ስታነቡ፣ ጌታ የቤተክርስቲያኑን ፖሊሲዎች ስለሚመራበት ሂደት ምን ትማራላችሁ? ፍጹም የሆነ መረዳት ባይኖራችሁም እንኳን በጌታ ላይ እንዴት መታመንን መማር እንደቻላችሁ አሰላስሉ።
በተጨማሪም፣ 2 ኔፊ 26፥33፤ “Witnessing the Faithfulness [ታማኝነትን መመሥከር]፣” በRevelations in Context [ራዕያት በአገባብ] ውስጥ፣ 332–41፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “Race and the Priesthood [ዘር እና ክህነት]፣” ወንጌል ቤተመጻህፍት፤ አህመድ ኮርቢት፣ “A Personal Essay on Race and the Priesthood [በዘር እና በክህነት ስልጣን ላይ ያተኮረ የግል ጥናታዊ ጽሁፍ]፣” ክፍል 1–4፣ history.ChurchofJesusChrist.org፤ BeOne.ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አምናለሁ።
-
ልጆቻችሁ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የእምነት አንቀጾችን እንዲገነዘቡ የሚረዱ መዝሙሮችን ወይም የልጆች መዝሙሮችን መፈለግን እንዲሁም መዘመርን አስቡ። ምናልባት መዝሙሮቹን እና የልጆች መዝሙሮቹን በመምረጥ ሊረዷችሁ ይችላሉ። ልጆቻችሁ፣ መዝሙሮቹ ከእምነት አንቀፆቹ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ እንዲያዩ እርዷቸው።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ወይም ስለእርሱ ቤተክርስቲያን ሊኖሯቸው የሚችሉትን ጥያቄዎች በመጻፍ አብራችሁ ልትሰሩ ትችላላችሁ። ከዚያም የእምነት አንቀፆችን በመጠቀም ለእነዚያ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት አብራችሁ ልትሠሩ ትችላላችሁ። ስለወንጌል ጥያቄዎች በሚኖሩን ጊዜ ሌላ ወዴት መሄድ እንችላለን?
የእምነት አንቀጾች 1፥9፤ አስተዳደራዊ አዋጆች 2
ጌታ ቤተክርስቲያኗን በነቢዩ አማካኝነት ይመራታል።
-
ልጆቻችሁ ዘጠነኛውን የእምነት አንቀፅ እንዲገነዘቡት ለመርዳት፣ ምናልባት የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶችን እና በህይወት ያለውን ነቢይ ምስል (ወይንም የሊያሆና የቅርብ ጊዜ የጉባኤ ዕትም) ልትሰጧቸው ትችላላችሁ። “እግዚአብሔር እስካሁን የገለጣቸውን ሁሉ” የሚለውን ስታነቡ ቅዱሳት መጻህፍትን ከፍ አድርገው እንዲይዙ እንዲሁም “አሁን የሚገልጣቸውን ሁሉ” (የእምነት አንቀጽ 1፥9) የሚለውን ስታነቡ ደግሞ ስዕሉን ወይም መጽሔቱን ከፍ አድርገው እንዲይዙ ጠይቋቸው። የጥንት እና የዘመኑ ነቢያት የሚያስፈልጉን ለምንድን ነው?
-
እንደ ምግብ ወይም አሻንጉሊት የመሠሉ ነገሮችን ለመሥራት የሚረዱ መመሪያዎችን በመከተል፣ ልጆቻችሁ የነቢያት ቃል እንዴት እንደሚመራን ሊማሩ ይችላሉ። ይህንንም ኢየሱስ ክርስቶስ በነቢዩ በኩል ከሰጠን መመሪያዎች ጋር ልታነፃፅሩት ትችላላችሁ። ዛሬ በህይወት ባለው ነቢዩ በኩል ጌታ ያስተማረን አንዳንድ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
አስተዳደራዊ አዋጆች 1 እና 2
ነቢያት የሰማይ አባት ፈቃድ ምን እንደሆነ እንድናውቅ ይረዱናል።
-
ምናልባት የጥንት ቅዱሳት መጻህፍት ከዘመኑ ራዕይ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ ማየታችሁ ልጆቻችሁ አስተዳደራዊ አዋጆቹን እንዲገነዘቡ ሊረዳቸው ይችላል። የሐዋርያት ሥራ 10፥34–35ን እና ያዕቆብ 2፥27–30ን እንዲያነቡ ልትጠይቋቸው እና የትኛው የቅዱሳት መፃህፍት ጥቅስ ከአስተዳደራዊ አዋጆች 1 (ከአንድ በላይ ጋብቻን ወደማብቃት የመራው) እንዲሁም የትኛው የቅዱሳት መፃህፍት ጥቅስ ከአስተዳደራዊ አዋጆች 2(የክህነት ሹመት እና የቤተመቅደስ ሥርዓቶች ለሁሉም የሠው ልጆች ዘር እንደሚገኙ ያስታወቀው) ጋር እንደሚዛመድ እንዲወስኑ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ጌታ ፈቃዱን ለጥንት እና ለዘመናችን ነቢያት እንደሚገልጥ ያላችሁን ምስክርነት ስጡ።