ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ታህሣስ 1–7 (እ.አ.አ)፦ “ስለሙታን ቤዛነት [ራዕይ]”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137–138።


ታህሣስ 1–7 (እ.አ.አ)፦ ‘ስለሙታን ቤዛነት [ራዕይ]’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137–138፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137–138፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ዓለም እያስተማረ

ዝርዝር ከChrist Preaching in the Spirit World [ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ዓለም እያስተማረ]፣ በሮበርት ቲ.ባሬት

ታህሣስ 1–7 (እ.አ.አ)፦ “ስለሙታን ቤዛነት [ራዕይ]”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137–138

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137 እና 138 ውስጥ የተመዘገቡት ራዕዮች በ80 ዓመት ርዝመት እና በ 1 ሺህ 500 ማይሎች (2,400 ኪሜ) ርቀት ይለያዩ ነበር። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ክፍል 137ን የተቀበለው በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ በ1836 (እ.አ.አ) ሲሆን፣ ክፍል 138ን የተቀበሉት ደግሞ ስድስተኛው የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ በ1918 (እ.አ.አ) በሶልት ሌክ ሲቲ ውስጥ ነበር። ነገር ግን በትምህርት፣ እነዚህ ሁለት ራዕዮች ጎን ለጎን የሚሄዱ ናቸው። የእግዚአብሔር ነቢያትን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ለሚያነሷቸው ከሞት በኋላ ያለውን ህይወት የተመለከቱ ጥያቄዎች ሁለቱም መልስ ይሰጣሉ። ጆሴፍ ስሚዝ ሳይጠመቅ የሞተው የወንድሙ አልቪን እጣ ፈንታ ያስጨንቀው ነበር። ሁለቱንም ወላጆቻቸውን እና 13 ልጆቻቸውን ያለጊዜው በሞት ያጡት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ስለ መንፈሳዊው ዓለም ብዙ ጊዜ ያስቡ ነበር እንዲሁም በዚያ ስለሚከናወነው የወንጌል ስብከት ያስቡ ነበር።

ክፍል 137 የእግዚአብሔር ልጆች በሚቀጥለው ህይወት በሚኖራቸው ዕጣ ፈንታ ላይ የተወሰነ የመጀመሪያ ብርሃን ይሰጣል፣ እንዲሁም ክፍል 138 መጋረጃዎቹን ይበልጥ በስፋት ይከፍታል። ሁለቱ ራዕዮች በአንድነት፣ “አብ እና ወልድ ያሳዩትን ታላቅ እና አስደናቂ ፍቅር” ይመሰክራሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥3)።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137138፥30–37፣ 57–60

የሴሚናሪ ምልክት
ሁሉም የሰማይ አባት ልጆች ዘለዓለማዊ ህይወትን የመምረጥ እድል ይኖራቸዋል

የነቢዩ ጆሴፍ ውድ ወንድም የሆነው አልቪን ስሚዝ እግዚአብሔር የማጥመቅ ሥልጣንን ዳግም ከመመለሱ ከስድስት ዓመታት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በ1836 (እ.አ.አ) በተውሰኑ ክርስቲያኖች ዘንድ የነበረው የጋራ መግባባት፣ አንድ ሠው ሳይጠመቅ ቢሞት፣ ያ ሰው ወደ ሰማይ መሄድ እንደማይችል ነበር። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137 ውስጥ የሚገኘውን ራዕይ እስከተቀበለበት ጊዜ ድረስ፣ ጆሴፍ ለብዙ ዓመታት የአልቪን ዘለዓለማዊ ደህንነት ያስጨንቀው ነበር።

ዛሬ ብዙ ሰዎች ተመሣሣይ ጥያቄዎች አሏቸው። ብዙ ሰዎች ሥርዓቶችን እና ቃል ኪዳኖችን ለመቀበል ዕድል ባላገኙበት ሁኔታ እግዚአብሔር ለምን አስፈላጊ ያደርጋቸዋል? ይህ ለሚያሳስበው ግለሠብ ምን ትሉታላችሁ? በእግዚአብሔር እና ለመዳን እንደሚያስፈልጉ ባስቀመጣቸው መሥፈርቶች ላይ ያላቸውን እምነት የምትገነቡት እንዴት ነው? በክፍል 137 እና በክፍል 138፥30–37፣ 57–60 ውስጥ ልታካፍሏቸው የምትችሏቸውን እውነቶች ፈልጉ። እነዚህን እውነቶች በተገለፁባቸው“The Glorious Gospel Light Has Shone [የወንጌሉ ታላቅ ብርሀን በርቷል]” (መዝሙር፣ ቁጥር. 283) በሚለው መዝሙር ውስጥ እና “Gathering the Family of God [የእግዚአብሔርን ቤተሰብ ሰብስቡ]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2017፣ 19–22).በተሠኘው የፕሬዚዳንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ መልዕክት ውስጥ ልትፈልጓቸውም ትችላላችሁ።

በምታጠኑበት እና በምታሰላስሉበት ጊዜ፣ እንደሚከተሉት ያሉ ዓረፍተ ነገሮችን በማሟላት ግንዛቤያችሁን ልትመዘግቡ ትችላላችሁ፦

  • በእነዚህ ራዕዮች ምክንያት፣ የሠማይ አባትአውቃለሁ

  • በእነዚህ ራዕዮች ምክንያት፣ የአብ የደህንነት ዕቅድአውቃለሁ

  • በእነዚህ ራዕዮች ምክንያት፣እፈልጋለሁ

በተጨማሪም Saints [ቅዱሳን]1፥232–35ን ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥1–11፣ 25–30

ቅዱሳት መጻህፍትን ማንበብ እና ማሰላሰል ራዕይን እንድቀበል ያዘጋጀኛል።

አንዳንድ ጊዜ ባልፈለግንበትም ጊዜ እንኳን መገለጥ ይመጣል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ የሚመጣው በትጋት በመፈለጋችን እና ለዚያ በመዘጋጀታችን ምክንያት ነው። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥1–11፣ 25–30ን ስታነቡ፣ “ [የእርሳቸው] የመረዳት አይኖች ሲከፈቱ” ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ምን እያሠላሠሉ እንደበሩ አስተውሉ። እርሳቸው የነበራቸውን ተሞክሮ ከ1 ኔፊ 11፥1–6ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥12–19 ጋር ማነፃፀርም ትችላላችሁ። ከዚያም የፕሬዚዳንት ስሚዝን ምሳሌ እንዴት መከተል እንደምትችሉ አስቡ። ለምሳሌ፣ የበለጠ የግል ራዕይን ትቀበሉ ዘንድ በቅዱሣት መፃሃፍት ጥናታችሁ ላይ ምን አይነት ለውጦችን ለማድረግ ትነሳሳላችሁ?

ፕሬዚዳንት ኤም. ራስል ባላርድ “The Vision of the Redemption of the Dead [የሙታን የመዳን ራዕይ]” (ሊያሆና ህዳር 2018 (እ.አ.አ) 71–74) በተሠኘው መልዕክታቸው ውስጥ፣ ፕሬዚዳንት ስሚዝ ይህንን ራዕይ ለመቀበል የተዘጋጁባቸውን ሌሎች መንገዶችን ጠቁመዋል። ከእርሳቸው ተሞክሮ ምን ትማራላችሁ? ጌታ አሁን ላሏችሁ ተሞክሮዎች እንዴት እንዳዘጋጃችሁ ወይም ወደፊት ለሚያጋጥሟችሁ ተሞክሮዎች እንዴት እያዘጋጃችሁ እንደሆነ አስቡ።

በተጨማሪም Saints [ቅዱሳን]3፥202–5፤ “Ministry of Joseph F. Smith: A Vision of the Redemption of the Dead [የጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ አገልግሎት፦የሙታን የመዳን ራዕይ]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት ተመልከቱ።

2:3

Ministry of Joseph F. Smith: A Vision of the Redemption of the Dead

ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ

ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ በአልበርት ኢ. ሳልዝብረነር

መንፈስ ቅዱስን ጋብዙ። “ለወንጌል ትምህርት መንፈሳዊ ሁኔታ አስተዋጽዖ የሚያደርግ ምን ነገር አይታችኋል? የእሱን መገኘት የሚቀንሰውስ ምንድን ነው?” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር18ን ተመልከቱ)። ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ስለነበራቸው ተሞክሮ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፡1–11 ውስጥ ስታጠኑ፣ ማሰላሰልን እንዴት እንደምታበረታቱ እና መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን ለራሳችሁ እንዲሁም አስተማሪ ከሆናችሁ ደግሞ ለምታስተምሯቸው ሰዎች መጋበዝ እንደምትችሉ አስቡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥25–60

የአዳኙ ሥራ በመጋረጃው ሌላኛው ክፍል ቀጥሏል።

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “ለአለም ያለን መልእክት ቀላል እና ልባዊ ነው፦ በመጋረጃው በሁለቱም በኩል ያሉትን የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ወደ አዳኛቸው እንዲመጡ፣ የቅዱስ ቤተመቅደስ በረከቶችን እንዲቀበሉ፣ ዘላቂ ደስታ እንዲያገኙ፣ እንዲሁም ለዘለአለም ህይወት ብቁ እንዲሆኑ ሁሉንም እንጋብዛለን” (“ወደፊት እንግፋ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 118–19)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥25–60ን ስታነቡ ይህንን መግለጫ አሰላስሉ። እንዲሁም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከግምት ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ፦

  • በመንፈሳዊው አለም ውስጥ የአዳኙ ሥራ እንዴት እየተከናወነ እንደሆነ ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ትማራላችሁ? ይህ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ማወቃችሁ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • በመንፈሳዊው አለም ውስጥ ስላሉት የጌታ መልዕክተኞች ያስገረማችሁ ምንድን ነው?

  • ይህ ራዕይ በእግዚአብሔር የማዳን ዕቅድ ላይ ያላችሁን እምነት ያጠናክረው እንዴት ነው?

ስለመንፈሳዊው አለም የበለጠ ለማወቅ “Small and Simple Things [ትንሽ እና ቀላል ነገሮች]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 26–29) የተሰኘውን የፕሬዚዳንት ዳልን ኤች. ኦክስ መልዕክት ልታጠኑ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም፣ “Susa Young Gates and the Vision of the Redemption of the Dead [ሱሳ ያንግ ጌትስ እና የሙታን የመዳን ራዕይ]፣” Revelations in Context [ራዕያት በአግባብ]፣ 315–22፤ “A Visit from Father [የአባት ጉብኝት]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

3:20

A Visit from Father

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137፥5–10138፥18–35

ሁሉም የሰማይ አባት ልጆች ወንጌልን የመስማት ዕድል ይኖራቸዋል።

  • ጆሴፍ ስሚዝ ብዙ የቤተሰብ አባላቱን በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ማየት መቻሉ ለእርሱ ምን ትርጉም እንደነበረው ለመማር፣ ልጆቻችሁ “Ministry of Joseph Smith: Temples [የጆሴፍ ስሚዝ አገልግሎት፦ ቤተመቅደሶች” የተሠኘውን ቪዲዮ (የወንጌል ላይብረሪ) ሊመለከቱ ወይም Doctrine and Covenants Stories [የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]152–53 ልታካፍሉ (ወይንም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ማየት) ይችላሉ። ምናልባትም ለመጠመቅ እድሉ ሳይኖረው ስለሞተ ስለ አንድ ሰው ማውራትም ትችላላችሁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137፥5–10 ስለዚያ ሰው ምን ያስተምረናል?

    2:3

    Ministry of Joseph Smith: Temples

    2:17

    Chapter 39: The Kirtland Temple Is Dedicated: January–March 1836

  • የአዳኙን መቃብር ሥዕል (የወንጌል ስዕሎች መጽሐፍ ቁ. 58፣ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ፎቶዎች፣ ቁ. 14 ተመልከቱ) እንዲሁም በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ የሚገኘውን ሥዕል ተጠቅማችሁ፣ ሥጋው በመቃብር ውስጥ በነበረበት ጊዜ የኢየሱስ መንፈስ የት እንደሄደ ማስተማርን አስቡ። ከዚያም ኢየሱስ እዚያ በነበረበት ጊዜ ምን እንዳደረገ ለማወቅ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥18–19፣ 23–24፣ 27–30ን አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። ማንን ጎበኘ? ምን እንዲያደርጉ ጠየቃቸው? ይህንን ያደረገው ለምንድን ነው?

    The body of the crucified Christ being wrapped in white burial cloth (presumably by Joseph of Arimathaea and Nicodemus) in preparation for entombment. Several men and women are gathered around the crucified body. They are mourning the crucifixion.
  • የዚህን ሣምንት የአክቲቪቲ ገፅ በመጠቀም፣ በዚህኛው የመጋረጃው በኩል ሚስዮናውያን የሚያስተምሩትን (ለምሳሌ፣የእምነት አንቀፆች1፥4ን ተመልከቱ)፣ ሚስዮናውያን በመንፈሥ ዓለም ከሚያስተምሩት (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥33 ተመልከቱ) ጋር እንዲያነፃፅሩ ልጆቻችሁን ለመርዳት ትችላላችሁ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ምን ተመሣሣይ ነገር አለ፣ የሚለይስ? ይህ ስለሠማይ አባት እና ስለዕቅዱ ምን ያስተምረናል?

አንድ ልጅ ቅዱሳት መጻህፍትን እያነበበ

በቅዱሳት መፃህፍት ላይ ማሰላሠል መንፈስ ቅዱስን ይጋብዛል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥1–11

በቅዱሳት መጻህፍት ላይ ሳሰላስል፣ መንፈስ ቅዱስ እንድገነዘባቸው ሊረዳኝ ይችላል።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥1–11ን አብራችሁ ስታነቡ፣ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝን እንደሆኑ ሊያስመስሉ እና በቁጥር 6 እና 11.ውስጥ ካሉት ቃላቶች ጋር አብረው የሚሄዱ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። እንዲሁም የፕሬዚዳንት ስሚዝን አንድ ምስል (በዚህ መዘርዝር ውስጥ አለ) ልታሣዩዋቸው እና የቤተክርስቲያኗ ስድስተኛ ፕሬዚዳንት እንደነበሩ ልታስረዷቸው ትችላላችሁ። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ያለን አንድ ነገር ስላሰላሰላችሁበት ጊዜ እና መንፈስ ቅዱስ እንድትገነዘቡት ስለረዳችሁ ጊዜ ልትናገሩም ትችላላችሁ።

  • ቅዱሳት መፃህፍትን ስለማንበብ የሚያወሳ እንደ “Search, Ponder, and Pray [ፈትሽ፣ አሰላስል፣ እንዲሁም ጸልይ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 109) ያለ መዝሙር አብራችሁ መዘመርን አስቡ። ይህ መዝሙር ቅዱሳት መፃህፍትን ለመገንዘብ ምን ማድረግ እንዳለብን ይናገራል?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ዓለም

The Commissioned [ሀላፊነት የተሰጠው]፣ በ ሃሮልድ አይ. ሆፕኪንሰን

የአክቲቪቲ ገፅ ለልጆች