ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ህዳር 24–30 (እ.አ.አ)፦ “እርሱ ‘ተልዕኮውን እና ስራዎቹን በደሙ አስሯል’”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች135–136


“ህዳር 24–30፦ ‘እርሱ “ተልዕኮውን እና ስራዎቹን በደሙ አስሯል’”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135–136፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135–136፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ካርቴጅ እስር ቤት

ካርቴጅ እስር ቤት

ህዳር 24–30፦ እርሱ “ተልዕኮውን እና ስራዎቹን በደሙ አስሯል”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135–136

ሰኔ 27 ቀን 1844 (እ.አ.አ) ከሰዓት በኋላ፣ ጆሴፍ እና ኃይረም ስሚዝ ከጆን ቴይለር እና ዊለርድ ሪቻርድ ጋር በድጋሚ እስር ቤት ገቡ። ከማንኛውም ወንጀል ንጹህ እንደሆኑ ያምኑ ነበር፣ ነገር ግን በናቩ ውስጥ ያሉትን ቅዱሳን ደህንነት ለመጠበቅ ሲሉ ራሳቸውን ለእሥር አሳልፈው ሠጡ። የቤተክርስቲያኗ ጠላቶች ነቢዩ ጆሴፍን እስር ቤት ሲያስገቡት ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አልነበረም፣ ነገር ግን በዚህ ጊዜ በህይወት እንደማይመለስ የተገነዘበ ይመስል ነበር። እርሱ እና ጓደኞቹ መፅሐፈ ሞርሞንን በማንበብ እና መዝሙር በመዘመር አንዳቸው ሌላውን ለማጽናናት ሞከሩ። ከዚያም የተኩስ ድምጽ ተሰማ፣ እንዲሁም በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የጆሴፍ ስሚዝ እና የወንድሙ ኃይረም ምድራዊ ህይወት ተፈጸመ።

ነገር ግን ይህ የተቀበሉት መለኮታዊ ሥራ መጨረሻ አልነበረም። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዳግም መመለስ መጨረሻም አልነበረም። የሚሠራ ተጨማሪ ስራ ነበር እንዲሁም ቤተክርስቲያኗን ወደ ፊት እንድትቀጥል የሚመራት ተጨማሪ ራዕይም ነበር። የነቢዩ ህይወት ፍፃሜ የእግዚአብሔር ሥራ መጨረሻ አልነበረም።

Saints [ቅዱሳን]1፥521–52 ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135136፥37–39

ጆሴፍ እና ሃይረም ስሚዝ ምስክርነታቸውን በደማቸው አተሙ።

ጆሴፍ እና ሃይረም ስሚዝ በተገደሉበት ጊዜ ናቩ ውስጥ የምትኖሩ ብትሆኑ ኖሮ ምን ሊሰማችሁ ይችል እንደነበር ገምቱ (Saints [ቅዱሳን] 1፥554–55 ተመልከቱ)። ለዚህን አሳዛኝ ክስተት ምን ትርጉም ትሠጡት ነበር? ከሶስት ወራት በኋላ የታተመው ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135 ረድቶ የነበረ ሊሆን ይችላል። በዚህ ክፍል ውስጥ ስትመረምሩ ምን መረዳት እና ማረጋገጫ አምጥቶላችችሁ ሊሆን እንደሚችል አስቡ። “እግዚአብሔር ነቢዩ እንዲገደል ለምን ፈቀደ?” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136፥37–39 ተመልከቱ) ብሎ ለሚጠይቅ ሰው ምን ትሉታላችሁ?

እንዲሁም በክፍል 135 ውስጥ እንደ ጆሴፍ እና ሃይረም ለክርስቶስ ታማኝ እንድትሆኑ የሚያነሳሷችሁን ቃላት ወይም ሀረጎች ልትፈልጉም ትችላላችሁ።

በተጨማሪም፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥21–22፤ “Remembering the Martyrdom [ሰማዕትነትን ማስታወስ]፣” Revelations in Context [ራዕያት በአገባብ] 299–306፤ Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርት፦ ጆሴፍ ስሚዝ]፣ (2011)፣ 529–40529–40 ተመልከቱ።

4:39

Testimony of the Book of Mormon

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥3

የሴሚናሪ ምልክት
ጆሴፍ ስሚዝ ነቢይ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ነበር

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥3 “አጭር በሆነ በሀያ አመት ጊዜ ውስጥ” ጆሴፍ ስሚዝ ከፈጸማቸው ታላላቅ ነገሮች መካከል አንዳንዶቹን ይዘረዝራል። እነዚህ ነገሮች በእናንተ ላይ እንዲሁም ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባላችሁ ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩት እንዴት ነው? እንደዚህ ያለውን ዓረፍተ ነገር እንዴት እንደምታሟሉ አስብቡ፦ ጌታ በጆሴፍ ስሚዝ በኩል ባደረገው ነገር፣ እኔ … እናንተም የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ምስክርነታችሁን መመዝገብ እና ለሌሎች ማካፈል ትችላላችሁ።

ስለ ጆሴፍ ስሚዝ ተልዕኮ የምንማርበት ሌላው መንገድ ለእሱ አጭር የሀዘን መግለጫ ወይም መወድስ ለመጻፍ መሞከር ነው። በክርስቶስ እና ዳግም በተመለሠው ወንጌሉ ላይ እምነትን ለመገንባት ምን ልትሉ ትችላላችሁ? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135 ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ክስተቶችን ወይም ስኬቶችን ወይም ከታች ባሉት ግብዓቶች ውስጥ የተጠቀሱትን ለማካተት ትፈልጉ ይሆናል።

ኢየሱስ ክርስቶስ በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ስለራሱ እና ስለኃጢያት ክፍያው ብዙ እውነቶችን ገልጧል። በዚህ ዓመት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን በማጥናታችሁ ያገኛችሁትን ተሞክሮ ማሰላሰልን አስቡ። ለእናንተ ጎልተው የታዩዋችሁ እውነቶች የትኞቹ ናቸው? በዚህ ሣምንት ስታጠኑ፣ እነዚህን ለቤተሠባችሁ፣ ለክፍል ወይም ለቡድን አባላት ወይም ለሌሎች ማካፈል ልትፈልጉ ትችላላችሁ። እነዚህ እውነቶች አዳኙን እንድትገነዘቡት እና ወደእርሱ እንድትቀርቡ የሚረዷችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም፣ “Joseph Smith: The Prophet of the Restoration [ጆሴፍ ስሚዝ፦ የዳግም መመለስ ነቢይ]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ፣ ታድ አር. ካሊስተር፣ “Joseph Smith—Prophet of the Restoration [ጆሴፍ ስሚዝ—የዳግም መመለስ ነቢይ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2009 (እ.አ.አ)፣ 35–37፤ “Praise to the Man [ሰውየው ይሞገስ]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 27፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “ጆሴፍ ስሚዝ፣” የወንጌል ላይብረሪ።

62:4

Joseph Smith: The Prophet of the Restoration

ተዛማጅ ሙዚቃዎች

የሚከተሉትን መዝሙሮች መዘመር ወይም ቪዲዮዎቹን መመልከት መንፈስ ቅዱስን ሊጋብዝ ወይም ስለ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ሥራ እና ከእርሱ በኋላ የነበሩት ቅዱሳን ስለከፈሏቸው መስዋዕትነቶች የሚዳሥ ውይይት ሊያነሳሳ ይችላል።

A Poor Wayfaring Man of Grief [ድሀ መንገደኛ፣ የሀዘን ሰው]” (መዝሙር፣ ቁጥር 29)። ጆን ቴይለር በካርቴጅ እስር ቤት ውስጥ እያለ ይህንን መዝሙር ዘመረ።

Praise to the Man [ሰውየው ይሞገስ]” (መዝሙር፣ ቁጥር 27፤ በተጨማሪም ቪዲዮ ተመልከቱ)። የዚህ መዝሙር ፅሁፍ የተፃፈው ለጆሴፍ ስሚዝ ጥልቅ አድናቆት ለመሥጠት ነበር።

6:16

Praise to the Man – The Tabernacle Choir at Temple Square

Come, Come, Ye Saints [ኑ፣ ኑ፣ ቅዱሳን]” (መዝሙር፣ ቅጥር 30፤ በተጨማሪም ቪዲዮ ተመልከቱ)።

2:3

Come, Come, Ye Saints - Mormon Tabernacle Choir

“Faith in Every Footstep [በእያንዳንዱ እርምጃ፣ እምነት]” (ቪዲዮውን ተመልከቱ)።

2:3

Faith in Every Footstep - Mormon Tabernacle Choir

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136

ምክሩን ስከተል የጌታን ፈቃድ በመፈፀም ለመርዳት እችላለሁ።

ጆሴፍ ስሚዝ ከሞተ በኋላ ቅዱሳኑ ከናቩ ተባረሩ። አሁን 1,300 ማይል (2,100 ኪሜ) የሚሸፍን አስቸጋሪ ምድረበዳ ገጠማቸው። የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን ፕሬዚዳንት የነበሩት ብሪገም ያንግ፣ ቅዱሳኑ ከጉዞው እንዴት በህይወት መትረፍ ይችላሉ በማለት ተጨነቁ። ዊንተር ኳርተር በተባለ ጊዜያዊ ሰፈር መመሪያ ለማግኘት ተማጸኑ። የጌታ መልሶች በክፍል 136 ውስጥ ተመዝግበዋል። “ይህ ራዕይ፣ ቅዱሳን በጉዞ ላይ የሚያሣዩት ባህርይ የመዳረሻውን ያህል አስፈላጊ መሆኑን እንዲያስታውሱ በመርዳት፣ ወደ ምዕራብ የሚደረገውን ፍልሰት ከአሳዛኝ አስፈላጊነት ወደ ጠቃሚ የጋራ መንፈሳዊ ተሞክሮ እንዲለወጥ ረድቷል” (“This Shall Be Our Covenant [ይህም ቃል ኪዳናችን ይሆናል]፣” በRevelations in Context [ራዕያት በአግባብ]፣ 308 ውስጥ)።

ክፍል 136ን በምታጠኑበት ጊዜ ይህንን በአዕምሯችሁ ያዙ። በህይወታችሁ ውስጥ አስቸጋሪ ፈተናን ወደ “አስፈላጊ … መንፈሳዊ ተሞክሮ” ለመቀየር የሚረዳችሁን ምን ምክር አገኛችሁ? ይህ ምክር ቀደምት ቅዱሳንን በጉዟቸው ላይ እንደረዳቸው፣ የጌታን ፈቃድ በራሳችሁ ህይወት ውስጥ ለመፈፀም እንዴት እንደሚረዳችሁ ልታሰላስሉ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም፣ “This Shall Be Our Covenant [ይህም ቃል ኪዳናችን ይሆናል]፣” በRevelations in Context [ራዕያት በአገባብ]፣ 307–14 ውስጥ፤ “Come, Come, Ye Saints [ኑ፣ ኑ ቅዱሳን]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 30፤ Church History Topics [የቤተክርስቲያኗ ታሪክ ርዕሶች]፣ “Succession of Church Leadership [የቤተክርስቲያኗ መሪነት እንዴት እንደሚተላለፍ]]፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ዊንተር ኳርተርስ ሥዕል

ዝርዝር ከWinter Quarters [ዊንተር ኳርተርስ]፣” በግሬግ ኦልሰን

የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥1–2፣ 4–5

ጆሴፍ እና ሃይረም ስሚዝ ህይወታቸውን ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ለወንጌሉ ሰጡ።

  • ለልጆቻችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥1ን አሳጥራችሁ አቅርቡ ወይም “Chapter 57: The Prophet Is Killed [ምዕራፍ 57፦ ነቢዩ ተገደለ]” (በDoctrine and Covenants Stories [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 201–5፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን ከወንጌል ቤተመጻህፍት) አካፍሉ። ይህም ጆሴፍ እና ሃይረም ለአዳኙ እና ለወንጌሉ ስለከፈሉት መስዋዕትነት እናንተ እና ልጆቻችሁ ያላችሁን ስሜት ለማካፈል ጥሩ አጋጣሚ ሊሆንላችሁ ይችላል።

    3:21

    Chapter 57: The Prophet Is Killed: June 1844

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥4–5 ሃይረም ስሚዝ ወደ ካርቴጅ እሥር ቤት ከመሄዱ በፊት ከመፅሐፈ ሞርሞን አንድ ምንባብ እንዳነበበ ይገልፃል። እናንተ እና ልጆቻችሁ ይህንን ምንባብ አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ (ኤተር 12፥36–38 ተመልከቱ)። እነዚህ ጥቅሶች ሃይረምን እንዴት አፅናንተውት ሊሆን ይችላል? ጭንቀት ወይም ሃዘን በሚሰማችሁ ጊዜ የሚያጽናኗችሁን ጥቅሶች ማካፈልም ትችላላችሁ።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ የነቢያትን ፎቶዎች ልትመለከቱና (የወንጌል ስዕሎች መፅሐፍ፣ ቁጥር 71467 ተመልከቱ) እግዚአብሔር ነቢያትን ስለጠየቃቸው አንዳንድ ነገሮች ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። እነዚህ ነቢያት ለአዳኙ ሲሉ ምን መስዋዕትነት ከፍለዋል?

    The Old Testament prophet Noah standing on a log as he preaches to a group of assembled people. The people are laughing and mocking Noah. The partially completed ark is visible in the background.

በቤት ውስጥ፣ መማር እና መኖር አይነጣጠሉም። “በቤት ውስጥ የወንጌል አግባብነት ወዲያውኑ ይታያል። እዚያ ወንጌሉን አብራችኋቸው የምትማሩት ሰዎች፣ በየቀኑ በወንጌሉ ስትኖሩ አብረዋችሁ የሚሆኑት ሰዎች ናቸው። በእርግጥ፣ ብዙውን ጊዜ በወንጌል መኖር ወንጌልን የምንማርበት መንገድ ነው (በአዳኙ መንገድ ማስተማር31)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥3

ጆሴፍ ስሚዝ ነቢይ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ምሥክር ነበር።

  • ልጆቻችሁ፣ ጌታ በጆሴፍ ስሚዝ ተልዕኮ አማካኝነት እንዴት እንደባረከን እንዲያስታውሱ እና አድናቆት እንዲኖራቸው ለመርዳት፣ እንደ መፅሐፈ ሞርሞን፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች፣ ወይም የቤተመቅደስ ምሥል ያሉ ጆሴፍ ያደረጋቸውን ነገሮች የሚወክሉ ነገሮችን ልታሳዩ ትችላላችሁ (በተጨማሪም የዚህን ሣምንትየአክቲቪቲ ገፅ ተመልከቱ)። ከዚያም ልጆቻችሁ ጆሴፍ ስሚዝ ወደ ሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንቀርብ ያደረጋቸውን አንዳንድ ነገሮች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 135፥3 ውስጥ ልትፈልጉ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ለእነዚህ ነገሮች ለምን አመስጋኞች እንደሆኑ እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ

American Prophet [የአሜሪካ ነቢይ]፣ በዴል ፓርሰን

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136

ችግር ውስጥ በምሆንበት ጊዜ ጌታ ሊባርከኝ ይችላል።

  • የናቩ ቤተመቅደስን ምሥል በክፍሉ በአንድ በኩል ማስቀመጥን እንዲሁም በሌላኛው በኩል ደግሞ ቀላል መጠለያ ማዘጋጀትን አስቡ። ልጆቻችሁ በሥዕሉ አጠገብ እንዲሰበሰቡ ጋብዟቸው እንዲሁም ጆሴፍ ስሚዝ ከሞተ በኋላ ናቩን ለቀው መውጣት ስለነበረባቸው ቅዱሳን ንገራቸው (ምዕራፍ 5860፣ እና 62ን በDoctrine and Covenants Stories [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 206–8፣ 211–16፣ 222–24 ውስጥ፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ)። እነዚህ ቅዱሳን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ለነበራቸው እምነት አጽንኦት ስጡ፣ እንዲሁም ልጆቻችሁ ወደ ዊንተር ኳርተርስ የተደረገውን ጉዞ ለመወከል ወደ መጠለያው እንዲሄዱ ጋብዟቸው። እንደ “To Be a Pioneer [መስራች ለመሆን]” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 218–19) ዓይነት መዝሙርን ሊዘምሩም ይችላሉ።

    1:31

    Chapter 58: A New Leader for the Church: July–August 1844

    3:51

    Chapter 60: The Saints Leave Nauvoo: September 1845–September 1846

    2:29

    Chapter 62: The Saints Establish Winter Quarters: 1846–1847

  • በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 136 ውስጥ፣ ቅዱሳን ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ አድርገውት በነበረው ጉዞ ለመርዳት ጌታ ምክር እንደሰጣቸው አብራሩ። ልጆቻችሁ ለዚህ ጉዞ ድፍረት ሊሰጣቸው የሚችልን ነገር በዚህ ራዕይ ውስጥ እንዲፈልጉ እርዷቸው (ቁጥር 4፣ 10–11፣ 18–30 ተመልከቱ)። ዛሬ በሚያጋሙን ፈተናዎች ውስጥ ይህ ምክር እንዴት ሊረዳን ይችላል?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ህገ ወጥ የሰዎች ስብስብ ጆሴፍን እና ሌሎችን በካርቴጅ እስር ቤት እያጠቁ

Greater Love Hath No Man [ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ማንም የለውም] በኬሲ ቻይልድስ

የአክቲቪቲ ገጽ ለልጆች