ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የዳግም መመለስ ድምጾች፦ የሴቶች መረዳጃ ማህበር


“የዳግም መመለስ ድምጾች፦ የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
የዳግም መመለስ ድምጾች ምልክት

የዳግም መመለስ ድምጾች

የሴቶች መረዳጃ ማህበር

በ1842 (እ.አ.አ)፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር በናቩ፣ ኢሊኖይ ውስጥ ከተደራጀ በኋላ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ “ሴቶቹ እንደዚህ እስከተደራጁበት ጊዜ ድረስ ቤተክርስቲያኗ በፍፁም አልተደራጀችም” ብሏል።” በተመሳሳይም፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የሴቶች ደቀመዛሙርት “የጥንት ንድፍ ዳግም መመለሥ” የሆነውን የሴቶች መረዳጃ ማህበር ጥናት እስኪያካትት ድረስ የጌታ ቤተክርስቲያን እና የክህነቱ ዳግም መመለሥ አይጠናቀቀም።

እላይዛ አር. ስኖው በዚያ ዳግም መመለስ ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውታለች። የሴቶች መረዳጃ ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ በተደራጀበት ጊዜ ተገኝታ ነበር እንዲሁም፣ እንደማህበሩ ጸሐፊ፣ በስብሰባዎቹ ወቅት ማስታወሻዎችን ትይዝ ነበር። የሴቶች መረዳጃ ማህበር “በክህነት ንድፍ” የተደራጀ መሆኑን በቀዳሚነት መስክራለች። ከዚህ በታች የቀረቡት፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሁለተኛ አጠቃላይ ፕሬዚዳንት ሆና በማገልገል ላይ በነበረችበት ጊዜ፣ እህቶቿ ለእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሴት ልጆች በአደራ የሰጣቸውን መለኮታዊ ስራ እንዲገነዘቡ ለመርዳት የተፃፉ የእርሷ ቃላት ናቸው።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር እንዴት እንደተደራጀ የበለጠ ለማወቅ፣ Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society [ሴት ልጆች በመንግሥቴ፡ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ታሪክ እና ስራ] [2017 (እ.አ.አ)]፣ 1–25The First Fifty Years of Relief Society [የሴቶች መረዳጃ ማህበር የመጀመሪያ አምሳ ዓመታት] [2016(እ.አ.አ)]፣ 3–175ን ተመልከቱ፡።

ምስል
ኤማ ስሚዝ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባን እየመራች

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ድርጅት ሥዕል በፖል ማን

እላይዛ አር. ስኖው

“ምንም እንኳን [የሴቶች መረዳጃ ማህበር] የሚለው ሥም ዘመናዊ ሊሆን ቢችልም፣ ተቋሙ ጥንታዊ አመጣጥ አለው። ይህ ድርጅት በቤተክርስቲያን ውስጥ በጥንት ዘመን እንደነበረ [በጆሴፍ ስሚዝ] ተነግሮናል፣ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተመዘገቡት በአንዳንድ ደብዳቤዎች ውስጥም “ለተመረጠች ሴት” የሚል መጠሪያ በመጠቀም ተገልጿል [2 ዮሀንስ 1፥1ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥3 ተመልከቱ]።

“ይህ ድርጅት ያለ ክህነት መኖር አይችልም፣ ምክንያቱም ስልጣኑን እና ተፅዕኖውን ሁሉ የሚያገኘው ከዚያ ምንጭ ነውና። ክህነት ከምድር በተወሰደ ጊዜ፣ ይህ ተቋም እንዲሁም በምድር ላይ ያሉት የእርሱ ቅጥያ የሆኑት የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ሥርዓቶች ሁሉ ጠፍተዋል። …

“‘የናቩ የሴቶች መረዳጃ ማህበር’ በተቋቋመበት ጊዜ ተገኝቼ የነበርኩኝ በመሆኔ፣ … እንዲሁም በዚያ ማህበር ውስጥ ትልቅ ተሞክሮ ያገኘሁኝ በመሆኔ፣ ምናልባት፣ የጽዮን ሴት ልጆች በአዲስ እና ብዛት ባላቸው ሀላፊነቶች ወደተሞላው ወደዚህ በጣም አስፈላጊ ወደ ሆነ ቦታ ለመምጣት የሚረዷቸውን ጥቂት ፍንጮች ላካፍል እችላለሁ። በእስራኤል ውስጥ ካሉ ሴቶች ልጆች እና እናቶች መካከል አንዳቸውም አሁን ባሉበት አነስተኛ ቦታ ላይ እንደተገደቡ የሚሰማቸው ቢሆን፣ አሁን መልካም ነገርን ያደርጉ ዘንድ በነፃ የተሠጣቸውን ሁሉንም ሃይል የማግኘት ሠፋ ያለ ወሠን እና በቂ አቅም ያገኛሉ።…

ምስል
የቀይ ሸክላ ሱቅ ናቩ፣ ኢለኖይ

የሴቶች መረዳጃ ማህበር የተደራጀው በቀይ ሸክላ ሱቅ ፎቅ ላይ በነበረ አንድ ክፍል ውስጥ ነበር።

“በማንኛውም አእምሮ ውስጥ ጥያቄ የሚነሳ ከሆነ እንዲህ የሚል ይሆናል፦ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ዓላማ ምንድን ነው? ድሆችን ለመርዳት ብቻ ሳይሆን፣ ነፍሳትን ለማዳን ይቻል ዘንድ መልካም ለማድረግ ያለን አቅም ሁሉ ከአንድ ቦታ ወደሚሠጡበት ሥርዓት ለማምጣት—መልካም ለማድረግ—በማለት እመልሣለሁ። የተባበረ ጥረት፣ እጅግ በጣም ውጤታማ የሆነ የግለሠብ ሃይል ከሚያከናውነው የበለጠ እጅግ ብዙ ነገርን ያከናውናል። …

“ድሆችን በመርዳት፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣ አካላዊ ፍላጎቶችን ከማስታገስ በላይ የሚያከናውነው ሌላ ሀላፊነት አለበት። የአእምሮ ድህነት እና የልብ ህመምም ትኩረትን ይጠይቃሉ፤ እንዲሁም ብዙ ጊዜ የደግነት ንግግር—ጥቂት የምክር ቃላት ወይም ሞቅ ያለ እና በፍቅር የሚሰጥ የእጅ መጨበጥም እንኳን ይበልጥ ይጠቅማል እንዲሁም ከአንድ ቦርሳ ወርቅ የተሻለ ዋጋ ይቸረዋል። …

“ቅዱሳን፣ ለሁሉም ሠዎች እንግዶች በመሆን፣ በመዋሸት እና በማታለል ከእምነታቸው ሊያስወጧቸው ለሚጠባበቁ ሰዎች በመጋለጥ ከውጭ አገር በሚሰባሰቡበት ጊዜ፣ [የሴቶች መረዳጃ] ማህበር [እነርሱን] ለመንከባከብ አፋጣኝ እርምጃ የሚወስድ መሆን አለበት እንዲሁም እነሱን ወደሚያነጻ እና ከፍ ከፍ ከሚያደርግ፣ እንዲሁም ከሁሉም በላይ እነርሱን በወንጌል እምነታቸው ከሚያጠናክራቸው ማህበረሰብ ጋር ማስተዋወቅ ይገባዋል፣ እና ይህን በማድረግም ብዙዎችን ለማዳን ጠቃሚ መሳሪያ ሊሆን ይችላል።

በማኅበሩ የተፅዕኖ ወሠን ውስጥ የሚካተቱ ተግባራትን፣ መብቶችን እና ሀላፊነቶችን ለመግለፅ ብዙ የመጻህፍት ቅፆች ያስፈልጋሉ። … (በኤጲስ ቆጶሳችሁ አመራር) በመረጋጋት፣ ሆን ብሎ፣ በኃይል፣ በአንድነት እና በጸሎት መንፈሥ ሂዱ እናም እግዚአብሔር ጥረቶቻችሁን ስኬታማ ያደርገዋል።”

ማስታወሻዎች

  1. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፦ ጆሴፍ ስሚዝ] [2007(እ.አ.አ)]፣ 451

  2. Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society [ሴት ልጆች በመንግሥቴ፦ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ታሪክ እና ስራ] (2017 ( እ.አ.አ))፣ 7

  3. ጆሴፍ ስሚዝ፣ በሳራ ኤም. ኪምባል “የግል–የህይወት ታሪክ፣” ውስጥ የተጠቀሰው Woman’s Exponent፣ መሥከረም 1፣ 1883 (እ.አ.አ)፣ 51።

  4. “የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣” Deseret News[ዲዘረት ኒውስ]፣ ሚያዝያ 22፣ 1868 (እ.አ.አ)፣ 81።

አትም