ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ህዳር 17–23 (እ.አ.አ)፦ “ለሙሽራው ምጻት ተዘጋጁ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133–134


ህዳር 17–23 (እ.አ.አ)፦ ‘ለሙሽራው ምጻት ተዘጋጁ‘፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133–134፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133–134፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

የአስሩ ደናግላን ሥዕል

አስሩ ደናግላን፣ በጆርጅ ኮኮ

ህዳር 17–23፦ “ለሙሽራው ምጻት ተዘጋጁ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133–134

በ1833 (እ.አ.አ) የህገ ወጥ ሠዎች ስብስብ በቤተክርስቲያኗ ማተሚያ ቤት ላይ ጥቃት ፈፀመ እንዲሁም አወደመ። በዚያን ጊዜ በሂደት ላይ ከነበሩት የህትመት ስራዎች መካከል የእግዚአብሔርን የኋለኛው ቀናት ራዕዮች በአንድ ቅፅ የማሳተም የቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያ ሙከራ የነበረው የትዕዛዛት መጽሃፍ ይገኝበታል። የህገ ወጥ ሠዎቹ ስብስብ ያልተጠረዙ ገጾችን በታተኑ፣ ምንም እንኳን ደፋር የሆኑ ቅዱሳን ጥቂቶቹን ቢያተርፉም፣ ጥቂት ያልተሟሉ የትዕዛዛት መጽሃፍት ቅጂዎች ብቻ እንደተረፉ ይታወቃል።

አሁን ክፍል 133 ሲባል የምናውቀው የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል የትዕዛዛት መጻህፍት አባሪ እንዲሆን፣ ማለትም በታተሙ የጌታ ራዕዮች መጨረሻ ላይ ልክ እንደ ትእምርተ–አንክሮ እንዲሆን የታሰበ ነበር። የፍርድ ቀን እየመጣ እንደሆነ ያስጠነቅቃል እንዲሁም በመላው የዘመኑ ራዕይ ውስጥ የሚገኘውን በባቢሎን ከተመሠለው ዓለማዊነትን ሽሹ የሚለውን ጥሪ በድጋሚ ያቀርባል። ፅዮንን ገንቡ። ለዳግሞ ምፅዓት ተዘጋጁ። እንዲሁም ይህንን መልዕክት “ለእያንዳንዱ ህዝብ፣ ለነገድ፣ ቋንቋ፣ እና ወገንም ሁሉ” አሠራጩ (ቁጥር 37)። ለትዕዛዛት መጻህፍት የነበሩት የመጀመሪያ ዕቅዶች የተሳኩ ባይሆንም፣ ይህ ራዕይ የጌታ ሥራ መከናወኑን እንደሚቀጥል፣ በዚህም “የተቀደሰውን ክንዱን … [እንደሚገልጥ]፣ እና በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካቸውን መድኃኒት [እንደሚያዩ]፣” (ቁጥር 3) አስታዋሽ እና ምስክር ነው።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥4–14

ኢየሱስ ክርስቶስ ባቢሎንን እንድተውና ወደ ጽዮን እንድመጣ ጠርቶኛል።

በመንፈሳዊ የጽዮን ተቃራኒ የሆነችው በቅዱሳት መጻህፍት ሁሉ ክፋትንና መንፈሳዊ እሥራትን የምትወክለው ጥንታዊቷ ከተማ ባቢሎን ናት። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥4–14 ስታነቡ አዳኙ “ከባቢሎን [እንድትወጡ]” (ቁጥር 5) እና “ወደ ፅዮን … [እንድትሄዱ]” (ቁጥር 9) ጥሪ ያደረገላችሁ እንዴት እንደሆነ አሰላስሉ። ላቀረበው ጥሪ ምላሽ እየሰጣችሁ ያላችሁት እንዴት ነው? “Come to Zion [ወደ ፅዮን ኑ]” ከሚለው የሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን መልዕክት ሌላ ስለፅዮን ምን ትማራላችሁ? (ሊያሆና፣ ህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 37–40)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥1–19፣ 37–39

የሴሚናሪ ምልክት
ለአዳኙ ዳግም ምፅዓት አሁን መዘጋጀት እችላለሁ።

የጌታ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መቅድም የሆነው ክፍል 1 እና የመጽሐፈ ትዕዛዛት የመጀመሪያው አባሪ የነበረው ክፍል 133፣ ሁለቱም፣ “የቤተክርስቲያኔ ህዝብ ሆይ፣ አድምጡ፣” ((ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥1)133፥1) በሚሉት ተመሳሳይ የጌታ ተማፅኖዎች ይጀምራሉ። ምናልባት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133–19፣ 37–39ን ልታጠኑ እና ለዳግም ምጽዓቱ በምትዘጋጁበት ጊዜ ጌታ “[እንድታደምጡ]” (ለመስማት እና ለመታዘዝ) የሚጋብዛችሁን መልዕክቶች ዘርዝሩ። በተለይም፣ ተመልሶ ለሚመጣበት ጊዜ (1) ራሳችሁን ለማዘጋጀት እና (2) ዓለምን ለማዘጋጀት እንድታደርጓቸው የሚፈልጋቸውን ነገሮች ልትዘረዝሩ ትችላላችሁ። ከእነዚህ ዝርዝሮች ምን ትማራላችሁ?

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ አዳኙ ተመልሶ ሲመጣ ዓለም ምን እንደምትመስል እንዲሁም እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል ጠቃሚ እውነቶችን አካፍለዋል። “The Future of the Church: Preparing the World for the Savior’s Second Coming [የቤተክርስቲያን የወደፊት ሁኔታ፦ ዓለምን ለአዳኙ ዳግም ምጽዓት ማዘጋጀት]፣” (ሊያሆና፣ ሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ)፣6–11) በተሠኘው መልዕክታቸው ውስጥ እነዚህን እውነቶች ፈልጉ። “ዓለምን ለአዳኙ ዳግም ምፅዓት ለማዘጋጀት” ምን ለማድረግ—ወይም በማደረግ ለመቀጠል ትነሳሳላችሁ? “Aaronic Priesthood Quorum Theme[የአሮናዊ ክህነት ቡድን ጭብጥ]፣” ወንጌል ላይብረሪ)።

በተጨማሪም ማቴዎስ 25፥1–13፤ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Embrace the Future with Faith [ወደፊትን በእምነት መቀበል]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 73–76፤ “Come, Ye Children of the Lord [ኑ፣ እናንተ የጌታ ልጆች]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 58፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “Second Coming of Jesus Christ [የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት]፣” ወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥19–56

የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ለጻድቃን አስደሳች ይሆናል።

ስለ አዳኙ ምፅዓት የሚናገረውን በቁጥር 32–56 ውስጥ ያለውን መግለጫ ስታነቡ፣ በጉጉት የምትጠብቁት ምን ታገኛላችሁ? ጌታ ለህዝቡ ያለውን ፍቅር የሚገልፁት ቃላት ወይም ሀረጎች የትኞቹ ናቸው? “[የጌታችሁን] አፍቃሪ ደግነትን፣ እና በመልካምነቱም መሰረት፣ … [በእናንተ] ላይ ስላፈሰሰው” (ቁጥር 52) ያላችሁን የግል ተሞክሮዎች መመዝገብን አስቡ።

ኢየሱስ ለአንዲት ሴት ደግነት እያሳየ

ዝርዝር ከHealer [ፈዋሽ]፣ በኬልሲ እና ጀሲ ላይትዌቭ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 134

“መንግስታት እግዚአብሔር ለሰው ጥቅም የመሰረታቸው [ናቸው]።”

ቀደምት ቅዱሳን ከመንግስት ጋር የነበራቸው ግንኙነት ውስብስብ ነበር። ቅዱሳኑ ከጃክሰን ካውንቲ፣ ሚዙሪ በ1833 (እ.አ.አ) ተገድደው ሲወጡ፣ ከአካባቢው ወይም ከብሔራዊ መንግሥቱ እርዳታን ለማግኘት ቢጠይቁም አላገኙም። በተመሳሳይ ጊዜም፣ ከቤተክርስቲያኗ ውጭ ያሉ አንዳንድ ሰዎች የፅዮን አስተምህሮ፣ ቅዱሳን የምድራዊ መንግስታትን ስልጣን አይቀበሉም ማለት እንደሆነ ተረጎሙት። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 134 በከፊል የተጻፈው ቤተክርስቲያኗ ስለመንግስት ያላትን አቋም ለማብራራት ነበር። ይህ ክፍል የጌታ ቅዱሳን ስለ መንግስት ሊሰማቸው ስለሚገባው ነገር ምን ይጠቁማል?

ክፍል 134ን ስታጠኑ፣ የመንግስትን መርሆዎች እና የዜጎችን ኃላፊነቶች መፈለግን አስቡ። እነዚህ ሀሳቦች ለቀደምት ቅዱሳን እንዴት ጠቃሚ ይሆኑ ነበር? እናንተ በምትኖሩበት ቦታስ ተግባራዊ የሚሆኑት እንዴት ነው?

በተጨማሪም፣ የእምነት አንቀፆች 1፥11–12፤ “Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “Religious Freedom [የሃይማኖት ነፃነት]፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥4–5፣ 14

ጌታ በዓለም ውስጥ ካሉ ክፋቶች እንድርቅ ይፈልጋል ።

  • አናንተ እና ልጆቻችሁ ጌታ እንድንርቃቸው የሚፈልጋቸውን አንዳንድ ቦታዎች እና ሁኔታዎች ልትዘረዝሩ ትችላላችሁ። ከዚያም፣ እነዚያን ቦታዎች እና ሁኔታዎች በቅዱሳት መፃህፍት መመሪያ (ወንጌል ቤተመጻህፍት) ውስጥ ካለው የ“Babel, Babylon [ባቢሎን]” ፍቺ ጋር አነፃፅሩት። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥4–5ን ሊያነቡ ይችላሉ። “ከባቢሎን…[መውጣት]” ማለት ምን ማለት ነው? (ቁጥር 5)። ጌታ እንድንሄድባቸው የሚጋብዘንን የቦታዎች እና የሁኔታዎች ዝርዝር ልታዘጋጁ እና ያንን ዝርዝር በቅዱሳት መፃህፍት መመሪያ ውስጥ ካለው ፅዮን ከሚለው ቃል ፍቺ ጋር ልታነፃፅሩት ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥19–21፣ 25

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና ይመጣል።

  • ልጆቻችሁ እንደ ስፖርት ውድድር፣ አስፈላጊ ጎብኚ፣ ወይም ተወዳጅ የበዓል ቀን ለመሠለ ነገር መዘጋጀት ምን እንደሚመስል መተወን ያስደስታቸው ይሆናል። ዝግጅት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥17–19፣ 21ን አብራችሁ ልታነቡና ጌታ እንድንዘጋጅበት የሚጋብዘዘን እንዲፈልጉ ልጆቻችሁን ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። በዚህ ሳምንት መዘርዝር ውስጥ ያለውን ሥዕል ልታሳዩዋቸውና ልጆቻችሁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ምን እንደሚያውቁ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ከቁጥር 19–25፣ 46–52 ሌላ ምን እንማራለን? ለዚህ አስደሳች ቀን ለመዘጋጀት ምን ልናደርግ እንችላለን?

  • ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ለመዘጋጀት ማድረግ የምንችላቸውን ቅዱሳት መጻህፍትን እንደ ማንበብ፣ ወንጌልን እንደማካፈል ወይም ቤተሰባችንን እንደማገልገል የመሠሉ ነገሮችን የሚያሳዩ የተለያዩ ሥዕሎችን ወይም እቃዎችን ልትደብቁ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ሥዕሎቹን ወይም ዕቃዎቹን እንዲፈልጉ አድርጉ፣ ከዚያም እነዚህን ነገሮች ማድረጋችን አዳኙ ሲመለስ ለመገናኘት እንዴት ዝግጁ እንድንሆን እንደሚረዳን ተነጋገሩ።

  • እንደ “Follow the Prophet [ነቢዩን ተከተሉ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 82–83) የመሠለ ስለዳግም ምጽዓት የሚያወሣ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ። ለአዳኙ ስላላችሁ ፍቅር እና ስለዳግም መመለሡ የሚሰማችሁን አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥52–53

ኢየሱስ ክርስቶስ አፍቃሪ እና ደግ ነው።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ ኢየሱስ አፍቃሪ እና ደግ መሆኑን የሚያሳዩ ሥዕሎችን ልትመለከቱ ትችላላችሁ። (ለምሳሌ፣ የወንጌል ስዕሎች መፅሐፍቁጥር 4247ን ተመልከቱ።) ኢየሱስ ፍቅር እና ደግነቱን ለማሣየት ሌላ ምን አድርጓል? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥52ን አብራችሁ አንብቡ፣ ከዚያም ልጆቻችሁ ለሌሎች “የጌታቸውን አፍቃሪ ደግነት … [የሚናገሩበትን]” መንገድ እንዲያስቡ እርዷቸው።

    Christ Healing the Sick at Bethesda
ኢየሱስ እና አንድ ልጅ

ዝርዝር ከIn His Light [በብርሀኑ]፣” ግሬግ ኦልሰን

ግልፅ እና ቀላል ትምህርትን አስተምሩ። ጌታ ወንጌሉን “በግልጽ እና በቀላል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 133፥57) መንገድ ያስተምራል። እነዚህ ቃላት ወንጌልን ለቤተሰቦቻችሁ ወይም ለክፍላችሁ ስለማስተማር ምን ይጠቁሟችኋል?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 134፥1–2

ጌታ ህጉን እንድታዘዝ ይፈልጋል።

  • ልጆቻችሁ የሚታዘዟቸውን ደንቦች እና ህጎች ሊዘረዝሯቸው ይችላሉ። ማንም እነዚህን ህጎች ባይጠብቅ ኖሮ ህይወት ምን ሊመስል ይችል ነበር? ከዚያም፣ ያልገቧቸውን ቃላት ወይም ሀረጎች እንዲገነዘቡ እየረዳችኋቸው ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 134፥1–2ን ከእነርሱ ጋር ልታነቡ ትችላላችሁ ። ጌታ ህጎችን እንድንታዘዝ የሚፈልገው ለምንድን ነው? (በተጨማሪም የእምነት አንቀጾች 1፥12 ተመልከቱ)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።

ኢየሱስ ቀይ ካባ ለብሶ

ክርስቶስ ቀይ ካባ ለብሶ፣ በሚኔርቫ ቲቸርት

የአክቲቪቲ ገጽ ለልጆች