ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የዳግም መመለስ ድምጾች፦ ለቅድመ ዓያቶቻችን መጠመቅ፣ “ታላቅ ትምህርት”


“የዳግም መመለስ ድምጾች፦ ለቅድመ ዓያቶቻችን መጠመቅ፣ ‘ታላቅ ትምህርት፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ለቅድመ ዓያቶቻችን መጠመቅ፣ ‘ታላቅ ትምህርት፣”” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
የዳግም መመለስ ድምጾች ምልክት

የዳግም መመለስ ድምጾች

ለቅድመ ዓያቶቻችን መጠመቅ፣ “ታላቅ ትምህርት”

ምስል
በናቩ ቤተመቅደስ ውስጥ የሚገኝ የጥምቀት ገንዳ ንድፍ

ይህ ንድፍ የናቩ ቤተመቅደስ የጥምቀት ገንዳ በአሥራ ሁለት በሬዎች ላይ አርፎ ያሳያል።

ፊቢ እና ውልፈርድ ውድረፍ

ምስል
Portrait engraving of Orson Pratt

ፊቢ ውድረፍ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ከዚህ በፊት ለሞቱ መጠመቅ እንደሚቻል ማስተማር በጀመረበት ጊዜ በናቩ አቅራቢያ ትኖር ነበር። በእንግሊዝ በሚስዮን እያገለገለ ለነበረው ለባልዋ ለዊልፎርድ ስለዚህ ጉዳይ ጻፈችለት፦

“ወንድም ጆሴፍ … ይህንን ወንጌል የመስማት ዕድል ሣይኖራቸው ለሞቱት ዘመዶቻቸው፣ ለልጆቻቸው፣ ለወላጆቻቸው፣ ለወንድሞቻቸው፣ ለእህቶቻቸው፣ ለአያቶቻቸው፣ ለአጎቶቻቸው እና ለአክስቶቻቸው በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ መጠመቅ እንደሚችሉ በራዕይ ተምሯል። … ለጓደኞቻቸው እንደተጠመቁ ከእስር ወዲያው ይለቀቃሉ እናም በትንሳኤ ጊዜ የእነርሱ ያደርጓቸዋል እንዲሁም ወደ ሰለስቲያል መንግሥትም ያመጧቸዋል—ይህ ትምህርት በቤተክርስቲያን ውስጥ በጥሩ ሁኔታ ተቀባይነት አግኝቷል እንዲሁም ወደ ብዙ ህዝብ ውስጥ እየሠረገ ነው፣ አንዳንዶች በአንድ ቀን እስከ 16 ጊዜያት ተጠምቀዋል።”

በኋላ ውልፈርድ ውድረፍ ስለዚህ መርህ እንዲህ ብሏል፦ “ይህን በሰማሁበት ቅጽበት ነፍሴ በደስታ ዘለለች። … ላስታወስኳቸው የሞቱ ዘመዶቼ ሁሉ መጠመቄን ቀጠልኩኝ። … ለሞቱት ስለመጠመቅ የሚገልጥ ራዕይ ለእኛ ሲገለጥ ሃሌሉያ እንድል የሚገፋፋ ሥሜት ተሠማኝ። በመንግሥተ ሰማይ በረከቶች የመደሰት መብት እንዳለን ተሰማኝ።”

ቪሌት ኪምባል

ምስል
Portrait of Vilate Kimball.

እንደ እህት ውድረፍ፣ ቪሌት ኪምባል ባለቤቷ ሒበር ወንጌልን ለመስበክ ሄዶ በነበረበት ጊዜ ስለ ውክልና ጥምቀት ሰማች። እንዲህ ስትል ጻፈችለት፦

“ፕሬዚዳንት ስሚዝ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ታላቅ መነቃቃት እንዲፈጠር ያደረገ አዲስ እና ታላቅ ርዕሰ ጉዳይ ግልፅ አድርጓል። ያም፣ ለሞቱ ሠዎች መጠመቅ ነው። ጳውሎስ ስለዚህ ጉዳይ በአንደኛ ቆሮንቶስ 15ኛ ምዕራፍ 29ኛ ቁጥር ውስጥ ተናግሯል። ጅሴፍም በራዕይ የበለጠ የተሟላ ማብራሪያ ተቀብሏልል። … ይህ ወንጌል ከመታወጁ በፊት ለሞቱት ዘመዶቻቸው ሁሉ፣ እስከ ወንድ እና ሴት ቅድመ አያቶቻቸው ድረስ እንኳን መጠመቅ በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ ልዩ መብት ነው።… እንዲህ በማድረግ ለእነርሱ ወኪሎች እንሆናለን፤ እንዲሁም በመጀመሪያው ትንሳኤ የመነሳት ዕድልን እንዲያገኙ እናደርጋለን። እርሱ ወንጌል እንደሚሰበክላቸው ተናግሯል … ግን ነፍሳት ይጠመቃሉ የሚል ምንም ነገር የለም። … ይህ ትዕዛዝ እዚህ ከተሰበከ ጀምሮ፣ ወንዞቹ ያለማቋረጥ በሥራ ተጠምደዋል። በጉባኤው ወቅት አንዳንድ ጊዜ ከስምንት እስከ አስር ሽማግሌዎች በአንድ ጊዜ በወንዙ ውስጥ ያጠምቁ ነበር። … ለእናቴ መጠመቅ እፈልጋለሁ። ወደ ቤት እስክትመለስ ድረስ ለመጠበቅ አስቤ ነበር፣ ነገር ግን ጆሴፍ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ በተናገረ ጊዜ፣ እያንዳንዳቸው በንቃት እንዲያከናውኑት፣ እንዲሁም ጓደኞቻቸውን በተቻለ ፍጥነት ከባርነት ነፃ እንዲያወጡ መክሯል። ስለዚህ ብዙ ጎረቤቶች ይህን ስለሚያደርጉ እኔም በዚህ ሳምንት አደርገዋለሁ ብዬ አስባለሁ። አንዳንዶች አስቀድመው ብዙ ጊዜ ተጠምቀዋል። … ስለዚህ ለሁሉም ዕድል እንዳለ ታያለህ። ይህ ታላቅ ትምህርት አይደለምን?”

ፊቢ ቼዝ

ምስል
Picture of Phoebe Carter Woodruff, wife of Wilford Woodruff, circa 1840.

የናቩ ቤተመቅደስ የጥምቀት ገንዳ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ የውክልና ጥምቀት የሚከናወነው በወንዙ ውስጥ ሳይሆን በዚያ ነበር። የናቩ ነዋሪ የነበረችው ፊቢ ቼዝ ስለ ቤተመቅደስ ሥትፅፍ የጥምቀቱ ገንዳ “ለሞቱብን የምንጠመቅበት እና በፅዮን ተራራ አዳኞች የምንሆንበት ቦታ” በማለት ለእናቷ ገልፃለች። እንዲህም በማለት ማብራራቷን ቀጥላለች፦ በዚህ ገንዳ ውስጥ “ለውዱ አባቴና ለተቀሩት የሞቱት ጓደኞቼ በሙሉ ተጠምቄያለሁ። … አሁን እነርሱን ለማስፈታት ስለምፈልግ የአባትሽ እና የእናትሽ ስም ማን እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ፣ ለሙታን እፎይታ መሥጠት እፈልጋለሁና። … ጌታ እንደገና ተናግሯል እናም የጥንቱን ሥርዓት ዳግም መልሷል።”

ሳሊ ራንዳል

ከዚህ በፊት ኖረው ላለፉት የቤተሰብ አባላት ስለሚከናወን ጥምቀት ለጓደኞቿ እና ለቤተሰቦቿ ስትጽፍ፣ ሳሊ ራንዳል የልጇን የጆርጅን ህልፈት አስታውሳለች፦

“አቤት ለእኔ ምንኛ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር እንዲሁም እንደዚያ እንደሆነ አሁንም ልቀበለው የምችል አይመስልም ነበር፣ ነገር ግን … አባቱ ለእርሱ ተጠምቋል፤ አሁን የሚሰበከውን የወንጌል ሙላት ማመናችን እና መቀበላችን እንዲሁም ለሞቱ ጓደኞቻችን ሁሉ ልንጠመቅላቸው እና ስለእነርሱ መረጃ ልናገኝ እስከምንችለው ድረስ በመሄድ ልናድናቸው መቻላችን ምንኛ ታላቅ ነገር ነው።

“ከእኛ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የሞቱትን እስከ ወንድ አያቶች እና ሴት አያቶች ድረስ የሁሉንም ሠዎች ስም እንድትፅፉልኝ እፈልጋለሁ። ጓደኞቼን ለማዳን የቻልኩትን ሁሉ ለማድረግ አስቤአለሁ እንዲሁም አንዳንዶቻችሁም ብትመጡና ብትረዱኝ በጣም ደስ ይለኛል፣ ይህንን አንድ ሰው ብቻውን ለማድረግ የማይችለው ትልቅ ስራ ነውና። … ይህ እንግዳ የሆነ ትምህርት ነው ብላችሁ ታስቡ ይሆናል ነገር ግን እውነት ሆኖ ታገኙታላችሁ ብዬ እጠብቃለሁ።”

ማስታወሻዎች

  1. Phebe Woodruff letter to Wilford Woodruff፣ Oct. 6፣ 1840 [ፊቢ ውድሩፍ ለውልፈርድ ውድረፍ የጻፈችው ደብዳቤ፣ ጥቅምት 6 ቀን 1840 (እ.አ.አ)]፣ የቤተክርስቲያኗ ታሪክ ቤተመጻህፍት፣ ሶልት ሌክ ሲቲ፤ የሆሄ አጻጻፉ እና ሥርዓተ-ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል።

  2. ውልፈርድ ውድረፍ፣ “ንግግሮች፣” Deseret News [ዴዘረት ኒውስ፣ ግንቦት 27፣ 1857 (እ.አ.አ)፣ 91፤ ሥርዓተ-ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል።

  3. ቪሌት ኪምቦል ለሂበር ሲ. ኪምቦል የፃፈችው ደብዳቤ፣ ጥቅምት 11፣ 1840 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያኗ ታሪክ ቤተመጻህፍት፣ ሶልት ሌክ ስቲ፤ የፊደል አጻጻፍ እና ሥርዓተ-ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል።

  4. የፊቢ ቼዝ ደብዳቤ፣ ቀኑ ያልታወቀ፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻህፍት፣ ሶልት ሌክ ሲቲ፤ የፊደል አጻጻፍ እና ሥርዓተ-ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል። ቅዱሳኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙታን ጥምቀቶችን ሲያከናውኑ፣ ግለሰቦች አንዳንድ ጊዜ የሁለቱንም ጾታዎች ቅድመ አያቶች በመወከል ይጠመቁ ነበር። ከዚያ በኋላ ለወንዶች ወንዶች እንዲሁም ለሴቶች ደግሞ ሴቶች መጠመቅ እንዳለባቸው ተገለጠ።

  5. የሳሊ ራንዳል ደብዳቤ ሚያዝያ 21፣ 1844 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተመጻህፍት፣ ሶልት ሌክ ስቲ፤ የሆሄ አጻጻፉ እና ሥርዓተ-ነጥቡ ዘመናዊ ተደርጓል።

አትም