ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ህዳር 10–16 (እ.አ.አ)፦ “ታዛዥ በመሆን ያደረከውን መስዋዕትነት አይቻለሁ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 129–132


“ህዳር10–16 (እ.አ.አ)፦ ‘ታዛዥ በመሆን ያደረከውን መስዋዕትነት አይቻለሁ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 129–132፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 129–132፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ እያስተማረ

ዝርዝር ከJoseph Smith in Nauvoo, 1840 [ጆሴፍ ስሚዝ በናቩ፣ 1840 (እ.አ.አ)]፣ በቴውዶር ጎርካ

ህዳር 10–16 (እ.አ.አ)፦ “ታዛዥ በመሆን ያደረከውን መስዋዕትነት አይቻለሁ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 129–132

ጌታ አንዳንድ ሚስጢሮችን በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ከዘለአለማዊነት ውስጥ አወጣ። የእግዚአብሔር ታላቅነት፣ የሰማይ ክብር እና የዘለአለማዊነት ትልቅነት ዳግም በተመለሰው የወንጌል ብርሃን፣ እኛ እንዳለን ዓይነት ውስን ለሆነ አዕምሮ እንኳን የሚታወቅ ሊመስል ይችላል። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 129–32 ውስጥ የሚገኙት ራዕዮች ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው። እግዚአብሔር ምን ይመስላል? “እንደ ሰው ሊዳሰስ እና ሊጨበጥ የሚችል … አካል አለው።” ሰማይ ምን ይመስላል? “በዚህ በመካከላችን የሚገኘው ማህበራዊ ግንኙነት … በዚያም እናገኘዋለን” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥22፣ 2)። በእርግጥ፣ በጣም አስደሳች ከሆኑት የመንግሥተ ሰማይ እውነቶች አንዱ፣ ተገቢ ሥልጣን ባለው ሠው የታተምን ከሆነ ውድ የቤተሰብ ግንኙነታችንን ሊያካትትም ይችላል። እንደእነዚህ ያሉ እውነቶች ሰማይ በቅርበት ያለ ያህል እንዲመስል ያደርጉታል—ታላቅ ቢሆንም ግን ተደራሽ የሆነ።

ነገር ግን በዚያን ጊዜ፣ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር የማይመቹ እና በቀላሉ የማይደረሥባቸው የሚመስሉ ነገሮችን እንድናደርግ ሊጠይቀን ይችላል። ለብዙዎቹ ቀደምት ቅዱሳን፣ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ከእንደዚህ ዓይነት ትዕዛዛት አንዱ ነበር። ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ለሚስቱ ኤማ እና ይህን ለተቀበሉት ለሁሉም ሰዎች ከባድ የእምነት ፈተና ነበር። በዚህ ፈተና ውስጥ ለማለፍ፣ ዳግም ስለተመለሰው ወንጌል አዎንታዊ ስሜቶችን ብቻ አልነበረም የሚያስፈልጋቸው፤ ከዚያ የበለጠ በጣም ጥልቅ የሆነ የእግዚአብሔር እምነት ያስፈልጋቸው ነበር። ይህ ትዕዛዝ ዛሬ የጸና አይደለም፣ ነገር ግን ይህን አክብረው የኖሩት ሠዎች የታማኝነት ምሳሌ አሁንም ይኖራል። “ታዛዥ በመሆን [የምናደርገውን] መስዋዕትነት” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥50) እንድናቀርብ ስንጠየቅ ይህ ምሳሌ ያነሣሣናል።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130–132

እግዚአብሔር፣ ልጆቹ በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ እንዲሉ ይፈልጋል።

በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ ስለመደረግ ወይም በሰለስቲያል መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ስላለው ህይወት ብዙ የማናውቃቸው ነገሮች አሉ። አብዛኛው ነገር አሁን ካለን የመረዳት አቅም በላይ ሊሆን ይችላል። ሆኖም እግዚአብሔር ጥቂት ውድ ፍንጮችን ገልጧል፣ እንዲሁም ከእነርሱ ውስጥ ብዙዎቹ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130–32 ውስጥ ይገኛሉ። ለምሳሌ፣ እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎችን በአዕምሮአችሁ በመያዝ ማንበብ ትችላላችሁ፦ ስለ እግዚአብሔር ምን እማራለሁ? ከምድራዊ ህይወት በኋላ ስላለው ህይወት ምን እማራለሁ? ይህ የዘለአለም ህይወት መረጃ አሁን ህይወቴን የሚባርከው እንዴት ነው?

በተጨማሪም “Our Hearts Rejoiced to Hear Him Speak [ልባችን እርሱ ሲናገስ ስንሰማ ይደሰታል] ፣” Revelations in Context [ራዕያት በአገባብ]፣ 277–80 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥20–21132፥5

እግዚአብሔር ህጎቹን የሚያከብሩትን ይባርካል።

ጌታ በትምህርቶች እና ቃል ኪዳኖች 130፥20–21 እና 132፥5 ውስጥ የሚያስተምረውን በራሳችሁ አባባል የምትገልፁት እንዴት ነው? ይህ መርህ በህይወታችሁ ውስጥ በተግባር የታየው እንዴት እንደሆነ አሠላስሉ።

አንዳንድ ጊዜ፣ ለእግዚአብሔር እየታዘዝንም እንኳን፣ ተስፋ የምናደርጋቸው በረከቶች ወዲያውኑ አይመጡም። ይህ በሚሆንበት ጊዜ እምነታችሁን ይዛችሁ መቆየት የምትችሉት እንዴት ነው? “Our Relationship with God [ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት]” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 78–80) የተሠኘውን የሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን መልዕክት ውስጥ ሃሳቦችን ፈልጉ።

በተጨማሪም 1 ኔፊ 17፥35ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥10 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥13–21

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
የሰማይ አባት ቤተሰቦች ዘለዓለማዊ እንዲሆኑ አስችሏል።

ጋብቻ እና የቤተሰብ ግንኙነቶች ዘለአለማዊ መሆን የመቻላቸውን እውነት ጌታ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ዳግም መልሷል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥13–21ን በምታነቡበት ጊዜ፣ ለዘለዓለም “በሚቀረው” እና በማይቀረው መካከል ያለውን ልዩነት እንድትገነዘቡ የሚረዷችሁን ሀረጎችን ፈልጉ። የጋብቻ ግንኙነት “[በጌታ]” ነው ሲባል ምን ማለት ይመስላችኋል? (ቁጥር 14).

ፕሬዚዳንት ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ “In Praise of Those Who Save [የሚያድኑትን በማሞገስ]I ” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2016(እ.አ.አ)፣ 77–78) በሚለው መልዕክታቸው ዘለዓለማዊ የጋብቻ ግንኙነቶችን “ከሚጣሉ” ነገሮች ጋር አነጻጽረዋቸዋል። ይህ ንጽጽር የጋብቻ ግንኙነትን ስለመንከባከብ ወይም ለጋብቻ ስለመዘጋጀት ምን ያስተምራችኋል? የሽማግሌ ኡክዶርፍን መልዕክት በምታነቡበት ጊዜ፣ አሁን ስላላችሁ እና ወደፊት ስለሚኖራችሁ የቤተሰብ ግንኙነት አስቡ። በዚያ ውስጥ ስለቤተሰብ ግንኙነቶቻችሁ በክርስቶስ ተስፋ የሚሰጣችሁ ምን ታገኛላችሁ?

ፕሬዚዳንት ሄነሪ ቢ. አይሪንግ በቤተሰባቸው ውስጥ ስላለው ስለዚህ ጉዳይ በተጨነቁ ጊዜ የተቀበሉትን ምክር አካፍለዋል፦ “እናንተ ለሰለስቲያል መንግስት ብቁ በመሆን ብቻ ኑሩ፣ እናም የቤተሰብ አደረጃጀታችሁ ከምትገምቱት በላይ አስደሳች ይሆናል” (“የጌታ መንፈስ የሚኖርበት ቤት፣” ሊያሆና ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 25)። ይህ ምክር እናንተን ወይም አንድ የምታውቁትን ሠው የሚረዳው እንዴት ነው?

በተጨማሪም Families Can Be Together Forever [ቤተስቦች ለዘለአለም ለመሆን ይችላል]መዝሙር፤ ቁጥር 300፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “ጋብቻ፣” የወንጌል ላይብረሪ፣ ተመልከቱ።

ምስል
አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ከቤተመቅደስ ውጪ

ጋብቻ በጌታ ቤት ውስጥ ለዘለዓለም ሊታተም ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥1–2፣ 29–40

ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው እሱ ሲያዝ ብቻ ነው።

ብሉይ ኪዳንን ያነበቡ ብዙ ሠዎች ከአንድ በላይ ሚስቶችን ስላገቡት ስለ አብርሐም፣ ስለ ያዕቆብ፣ ስለ ሙሴ እና ስለሌሎችም ይደነቃሉ። እነዚህ መልካም ሰዎች እያመነዘሩ ነበር? እግዚአብሔር ለጋብቻቸውን ፈቃድ ሰጥቶ ነበር? ጆሴፍ ስሚዝ ተመሣሣይ ጥያቄዎች ነበሩት። እግዚአብሔር በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥1–2፣ 29–40 ውስጥ የሠጣቸውን መልሶች ፈልጉ።

በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ያለው ጋብቻ፣ የእግዚአብሔር የጋብቻ መስፈርት ነው (አስተዳደራዊ አዋጅ 1 የክፍል መግቢያን፤ ያዕቆብ 2፥27፣ 30 ተመልከቱ)። ሆኖም፣ እግዚአብሔር ከአንድ በላይ እንዲያገቡ ልጆቹን ያዘዘባቸው ጊዜያት አሉ።

ዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያን የመጀመሪያዎቹ ዓመታትም ለየት ካሉት ጊዜያት ውስጥ የሚመደቡ ነበሩ። በቀደምት ቅዱሳን ዘንድ ስለነበሩት ከአንድ በላይ ጋብቻዎች የበለጠ ለማወቅ ከፈለጋችሁ፣ “Mercy Thompson and the Revelation on Marriage [መርሲ ቶምሰን እና የጋብቻ ራዕይ]” (በRevelations in Context [ራዕያት በአገባብ]፣ 281–93)፤ Saints [ቅዱሳን]1፥290–92432–35482–92502–4፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “Plural Marriage in The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints [በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአንድ በላይ ጋብቻ]፣” ወንጌል ላይብረሪ፤ “Why Was It Necessary for Joseph Smith and Others to Practice Polygamy? [ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች ከአንድ በላይ ጋብቻ ልምምድ አስፈላጊ የነበረው ለምንድን ነው?]” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥18–19132፥13፣ 19

የሰማይ አባት በዘለዓለማዊ ነገሮች ላይ እንዳተኩር ይፈልጋል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥20–21132፥21–23

እግዚአብሔር ህጎቹን ሳከብር ይባርከኛል።

  • ምናልባት አንድ ቀላል ንፅፅር የእግዚአብሔርን ህግጋት ስለማክበር ልጆቻችሁን ሊያስተምራቸው ይችላል። ለምሳሌ፣ ወደ ትምህርት ቤት ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ህንጻ ወይም ወደ ሆነ አንድ ቦታ ለመሄድ የሚረዳ አቅጣጫን እንዲሰጧችሁ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። አቅጣጫዎቹን ካልተከተልን ምን ይሆናል? ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥21ን ልታነቡ እና እነዚህን አቅጣጫዎች እግዚአብሔር ከሠጠን ትዕዛዛት ጋር ልታነፃፅሯቸው ትችላላችሁ።

  • ስለ መታዘዝ የሚያወሱ እንደ “Keep the Commandments [ትእዛዛቱን ጠብቁ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣፣ 146–47) የመሠሉ መዝሙሮችን አብራችሁ መዘመር እና በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥20–21 እና 132፥5 ውስጥ፣ በመዝሙሩ ውስጥ ካሉት ጋር ተመሣሣይነት ያላቸውን ቃላት ልትፈልጉ ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ ስንጥር የሚባርከን እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥22

የሠማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ የማይሞት አካል አላቸው።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥22ን አብራችሁ ካነበባችህ በኋላ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ የኢየሱስ ክርስቶስን ምሥል ልትመለከቱ እና ወደ ዓይኖቹ፣ ወደ አፉ እና ወደ ሌሎች የሰውነቱ ክፍሎች መጠቆም ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ወደራሳቸው ተመሳሳይ የአካላቸው ክፍል ሊያመለክቱ ይችላሉ። ሰውነታችን የሰማይ አባትን እና የኢየሱስን አካላት እንደሚመስሉ ማወቃችሁ ለእናንተ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ንገሯቸው።

ምስል
አንድ ወንድ እና አንዲት ወጣት ሴት ከቤተመቅደስ ውጪ

በጌታ ቤት ውስጥ በሚደረጉ ሥርዓቶች ምክንያት ቤተሰቦች ዘለዓለማዊ ሊሆኑ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥19

የሰማይ አባት ቤተሰቦች ለዘለዓለም አንድ ላይ እንዲሆኑ አስችሏል።

  • ልጆቻችሁ እንደሚበላሽ ምግብ፣ የሚረግፍ አበባ እና የመሳሰሉ ለዘለአለም የማይቆዩ ነገሮችን ምሳሌ እንዲፈልጉ እርዷቸው። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥19ን አብራችሁ ተመልከቱና እንደ “ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን”፣ “እትመት”፣ “በዘለዓለም ሁሉ” እና “ለዘለዓለም” የሚሉ ቃላትን ፈልጉ። (በተጨማሪም “Chapter 55: A Revelation about Marriage [ምዕራፍ 55፦ ስለጋብቻ የተሰጠ ራዕይ]፣” በDoctrine and Covenants Stories [የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 198፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ ተመልከቱ። የቤተሰባችሁን ምስሎች ልትመለከቱና ጌታ በቤተመቅደስ ሥርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች አማካኝነት ቤተሰቦች ዘለዓማዊ እንዲሆኑ እንዳደረገ ልትመሠክሩም ትችላላችሁ።

ለቤተሠብ ሁኔታዎች ጥንቃቄ አድርጉ። “በአሁኑ ጊዜ፣ ልጆች ብዛት ባላቸው የተለያዩ እና ውስብስብ በሆኑ የቤተሰብ ሁኔታዎች ውስጥ ይኖራሉ። … [እኛ] ብቸኝነት የሚሰማቸውን፣ የተተዉትን ወይም ከአጥሩ ውጭ ያሉትን ልንረዳቸው ይገባል፣” Whoso Receiveth Them, Receiveth Me [ማንም የሚቀበላቸው እኔን ይቀበለኛል]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 49፣ 52)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ምስል
የእትመት ክፍል

የጋብቻ እትመት ክፍል በፓሪስ ፈረንሳይ ቤተመቅደስ ውስጥ።

ምስል
የአክቲቪቲ ገጽ ለልጆች

አትም