ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 22–28 (እ.አ.አ)፦ “ወደር የለሽ ለሆነው መለኮታዊ የእግዚአብሔር ልጅ”፦ ገና


“ታህሳስ 22፟–28 (እ.አ.አ)፦ ‘ወደር የለሽ ለሆነው መለኮታዊ የእግዚአብሔር ልጅ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]።

“ገና፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ማርያም እና ህፃኑ ኢየሱስ

ዝርዝር ከNativity in Copper and Umber በጄ. ከርክ ሪቻርድስ

ታህሳስ 22–28 (እ.አ.አ)፦ገ ወደር የለሽ ለሆነው መለኮታዊ የእግዚአብሔር ልጅ

ገና

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ “የሐይማኖታችን መሰረታዊ መርሆች ቢኖሩ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን በተመለከተ፣ እንዲሁም እርሱ እንደሞተ፣ እንደተቀበረ፣ እና በሶስተኛውም ቀን እንደተነሳ፣ እንዲሁም ወደ ሰማይ እንዳረገ የሚመሰክሩት የሐዋርያትና የነቢያት ምስክርነቶች ናቸው፤ እናም ሁሉም ሐይማኖታችን የሚመለከቱ ሌላ ነገሮች በሙሉ የዚያ አካል ቅጥያዎች ብቻ ናቸው” (Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፦ ጆሴፍ ስሚዝ [2011 (እ.አ.አ)]፣ 49) ብሎ ተናግሯል። ከ160 ዓመታት በኋላ፣ ይህ ንግግር የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን፣ የአዳኙን 2 ሺህ ዓመት የልደት በዓል ለመዘከር “The Living Christ: The Testimony of the Apostles[ህያው ክርስቶስ፦ የሐዋርያት ምስክርነት”” እንዲያሳትሙ አነሳስቷል (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Drawing the Power of Jesus Christ into Our Lives [የኢየሱስ ክርስቶስን ሀይል ወደህይወታችን መሳብ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017፣ 40 ተመልከቱ)።

እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ በዘመናችን ነቢያት እና ሐዋርያት በኩል ቀጣይነት ባለው መልኩ በሚመጣው የመገለጥ በረከት እንደሰታለን። በመንፈስ አነሳሽነት ለሚሰጡት የምክር፣ የማስጠንቀቂያ እና ማበረታቻ ቃላት አመስጋኞች ነን። ነገር ግን ከሁሉም በላይ፣ በገና እና ዓመቱን በሙሉ፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰጡት ጠንካራ ምስክርነታቸው ተባርከናል። እነዚህ፣ ከተካኑ ጸሐፊዎች ወይም ከህዝብ ተናጋሪዎች ቃላት ወይም ከቅዱሳት መጻህፍት ሊቃውንት ከሚገኙ ግንዛቤዎች የላቁ ናቸው። እነርሱ፣ “ለዓለም ሁሉ የክርስቶስ ስም ልዩ ምስክሮች” (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 107፥23) እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ከተመረጡ፣ ከተጠሩ እና ስልጣን ከተሠጣቸው የመጡ ቃላት ናቸው።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

“ይህን ያህል ተጽዕኖ ያሳደረ ሌላ ማንም የለም።”

“ከዚህ በፊት ከኖሩት እና በዚህ ምድር ላይ ከሚኖሩት ሁሉ በላይ [እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ] ትልቅ ተጽዕኖ ያሳደረ ማንም የለም” የሚለውን ንግግር በመደገፍ ምን ትላላችሁ? በ“ህያው ክርስቶስ” ውስጥ የአዳኙን ትልቅ ተጽዕኖ የሚመሠክሩ አንቀፆችን ፈልጉ። በእናንተ ላይስ ተፅእኖ ያሳደረው እንዴት ነው?

ስለክርስትና የማያውቅ አንድ ሰው ገናን ለምን ታከብራላችሁ ብሎ እንደጠየቃችሁ አስቡ። ምላሽ የምትሰጡት እንዴት ነው? ይህንን ጥያቄ በአዕምሯችሁ ይዛችሁ፣ “ህያው ክርስቶስን” ከልሱ፤ ከዚያም የሚመጡላችሁን ማናቸውንም ሐሳቦች ወይም ግንዛቤዎች መፃፍን አስቡ።

በተጨማሪም “Why We Need a Savior [አዳኝ ለምን ያስፈገናል]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት ተመልከቱ።

“[እሱ] ከመቃብር ተነስቷል።”

በ“ህያው ክርስቶስ” ውስጥ፣ ሐዋርያቱ ከሞት የተነሳው ጌታ ከተገለጠባቸው ቦታዎች ሦስቱን በመጥቀስ ስለ አዳኙ ትንሳኤ መስክረዋል (አንቀጽ 5ን ተመልከቱ)። የእነዚህን ጉብኝቶች የተወሰኑ ታሪኮች በዮሐንስ 20–213 ኔፊ 11–26፤ እና ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥14–20 ውስጥ ማንበብን አስቡ። በእነዚህ በተገለጠባቸው ጊዜያት ከተናገራቸው ቃላት እና ካደረጋቸው ተግባራት ስለአዳኙ ምን ትማራላችሁ?

በአዳኙ ላይ ትኩረት አድርጉ። “‘ህያው ክርስቶስን’ በጸሎት መንፈሥ ማንበብ የማቴዎስን፣ የማርቆስን፣ የሉቃስን፣ የዮሐንስን እና የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢያትን ምስክርነቶች እንደማንበብ ነው። በአዳኙ ላይ ያላችሁን እምነት ይጨምራል እንዲሁም በእርሱ ላይ ትኩረት እንድታደርጉ ይረዳችኋል” [ኤም. ራስል ባለርድ፣ “ተመለሱ እና ተቀበሉ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ) 65]።

”የእርሱ ክህነት እና ቤተክርስቲያኑ … ዳግም [ተመልሰዋል]።”

በዚህ ዓመት የትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን ጥናታችሁ ወቅት፣ የአዳኙ “ክህነት እና ቤተክርስቲያኑ እንዴት ዳግም [እንደተመለሱ]” የበለጠ ለመማር እድል አግኝታችኋል። ዳግም ከተመለሱት እውነቶች ወይም መርሆዎች ውስጥ በተለይ ለእናንተ ትርጉም ያላቸው የትኞቹ ናቸው? ከሚከተሉት ውስጥ የተወሰኑትን ስለዳግም መመለስ የሚያስተምሩ ጥቅሶች መከለስን አስቡ፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥17–231320፥1–1265110112፥30–32124፥39–42128፥19–21። ዳግም የተመለሰው ወንጌል እውነቶች ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅና ለመውደድ እንዴት እንደሚረዷችሁ አሰላስሉ።

“አንድ ቀን ወደ ምድር [ይመለሳል]።”

የገና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበትን ቀን የምናስብበት እና እንደገና የሚመጣበትን ቀን በጉጉት የምንጠባበቅበት ጊዜ ነው። “በህያው ክርስቶስከመጨረሻው አንቀፅ በፊት ከሚገኘው አንቀፅ ስለእርሱ እንደገና መምጣት ምን ትማራላችሁ? እንደ “Joy to the World [ደስታ ለዓለም]” ወይም “It Came upon the Midnight Clear [ግልጽ በሆነው ሌሊት ላይ መጥቷል]” (መዝሙር፣ ቁጥር 201፣ 207) አይነት ስለዳግም ምፅአቱ የሚያስተምሩ የገና መዝሙሮችን ማንበብን፣ መዘመርን ወይም ማዳመጥን ልታስቡ ትችላላችሁ።

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
“እርሱ የአለም ብርሀን፣ ህይወት እና ተስፋ ነው።”

በህያው ክርስቶስየመጨረሻው አንቀጽ ውስጥ፣ ለአዳኙ የተሰጡትን ባህሪያት እና መጠሪያዎች አስተውሉ። ስለአንዳንዶቹ በመማር ጊዜ ማሳለፍን አስቡ። ለምሳሌ፦

ብርሃን፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናንተ እንደ ብርሃን የሆነው እንዴት ነው? ለእናንተ የሚሰጠውን ብርሃን የሚወክልን ሥዕል ለመሳል ወይም ፎቶግራፍ ለማንሳት ልታስቡ ትችላላችሁ። የእርሱን ብርሃን ለማካፈል ምን ለማድረግ የመነሳሳት ሥሜት ይሰማችኋል? (በተጨማሪም፣ ዮሐንስ 8፥123 ኔፊ 18፥24ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥24 ተመልከቱ።)

ህይወት፦ ህይወት ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግለፅ ጥሩ ቃል የሆነው ለምን ይመስላችኋል? ህይወት የሚሠጣችሁ በምን መልኩ ነው? ያለ እርሱ እና ያለ ወንጌሉ ህይወታችሁ የተለየ የሚሆነውእንዴት ነው? (በተጨማሪም፣ ዮሐንስ 10፥101 ቆሮንቶስ 15፥19–23ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 66፥24 ተመልከቱ።)

ተሥፋ፦ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ ምክንያት ምን ተሥፋ የታደርጋላችሁ? ስለ ወደፊቱ ጊዜ ተስፋ የማይታየው ሠው ታውቃላችሁ? በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት የሚሠማችሁን ተሥፋ ለዚያ ሠው እንዴት ልታካፍሉ እንደምትችሉ አሰላስሉ። (በተጨማሪም ምሳሌ 8፥24–25ኤተር 12፥4ሞሮኒ 7፥41ን ተመልከቱ።)

በተጨማሪም Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች] “ኢየሱስ ክርስቶስ፣” በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ

“ወደር የለሽ ለሆነ … ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።”

በ“ህያው ክርስቶስ፣” ውስጥ ሐዋርያት፣ አዳኙን ከሠማይ አባታችን የተሠጠ “ሥጦታ” ብለው ጠርተውታል። “በህያው ክርስቶስ” ውስጥ በምታገኙት መሠረት፣ ይህንን ዓረፍተ ነገር እንዴት ታሟላላችሁ፦ “በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት እግዚአብሔር የ … ሥጦታ ሰጥቶኛል።” እነዚህን ሥጦታዎች ይበልጥ ሙሉ በሆነ ሁኔታ ለመቀበል ምን ማድረግ እንደምትችሉ አሰላስሉ።

ህያው ክርስቶስን” ማጥናት በአዳኝ ላይ ባላችሁ እምነት እና ፍቅር ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው?

በተጨማሪም፣ ራስል ኤም ኔልሰን፣ “Four Gifts That Jesus Christ Offers to You [ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጣችሁ አራት ስጦታዎች]” [የቀዳሚ አመራር የገና የሃይማኖት ትምህርት፣ ታህሳስ፣ 2 ፣ 2018 (እ.አ.አ)]፣ የወንጌል ላይብረሪ፤ “Excerpts from ‘The Living Christ: The Testimony of the Apostles’ [ከህያው ክርስቶስ፦ የሐዋርያት ምስክርነት የተወሰደ]”፣ (ቪዲዮ)፣ChurchofJesusChrist.org

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

የኢየሱስን ልደት ለማክበር “ምሥክርነቴን መሥጠት” እችላለሁ።

  • ህያው ክርስቶስን” ለልጆቻችሁ እንዴት እንደምታስተዋውቁ አስቡ። ምናልባት በርዕሱ ውስጥ ወዳለው ክርስቶስ ወደሚለው ስም እና ወደቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ፊርማዎች እንዲጠቁሙ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ይህ ለዓለም ሊያካፍሉት የፈለጉት ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸው ምስክርነት መሆኑን ልታስረዱ ትችላላችሁ።

  • ለእያንዳንዱ ልጅ “ከህያው ክርስቶስ” ውስጥ አንድ ሃረግ ልትሠጡ እና የዚያን ሀረግ ምሥል እንዲፈልጉ ወይም እንዲስሉ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ከዚያም እነዚያን ሃረጎች “በህያው ክርስቶስ” እንዲፈልጉ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። እነዚያን ስዕሎች እና ሐረጎች እንደ መፅሀፍ ልታቀናብሯቸውም ትችላላችሁ።

  • የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነታችሁን እንዴት እንዳገኛችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ። ምናልባት የአዳኙን ምሥል ልትቀባበሉ እና ስለእርሱ የምታዉቁትን ነገር (“በህያው ክርስቶስ” ውስጥ የተሠጡትን ጨምሮ) ተራ በተራ ልታካፍሉ ትችላላችሁ።

ምስል
የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ

“[እርሱ] መልካም እያደረገ ዞረ።”

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ የ“ህያው ክርስቶስን” ሁለተኛ አንቀፅ ስታነቡ፣ ኢየሱስ ስላደረጋቸው አንዳንድ ነገሮች ከእነርሱ ጋር ተነጋገሩ። ህይወቱን የሚያሳዩ ምስሎችን (የዚህን ሣምንት የአክቲቪቲ ገፅ እና የወንጌል ስዕሎች መፅሐፍን) መመልከትም ትችላላችሁ። በሥዕሎቹ ውስጥ ኢየሱስ ምን እያደረገ እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዟቸው፡፡ እርሱ እንዳደረገው ሌሎችን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው? በወንጌል ቤተመጻህፍት ውስጥ ያሉት Light the World [አለምን አብሩ]” የተሠኙ ቪዲዮዎች ሃሳቦችን ሊሠጧችሁ ይችላሉ።

“እርሱ የአለም ብርሀን፣ ህይወት እና ተስፋ ነው።”

  • ልጆቻችሁ እንደ “O Little Town of Bethlehem [ትንሿ የቤተልሔም ከተማ]” (መዝሙር፣ ቁ. 208) ያሉ ስለብርሃን፣ ስለህይወት እና የአዳኙ መወለድ ወደ አለም ስላመጣው ተስፋ የሚናገሩ የገና መዝሙሮችን እንዲፈልጉ እርዷቸው። መዝሙሮቹን አብራችሁ ዘምሩ፣ እንዲሁም ልጆቻችሁ፣ ኢየሱስ ብርሃንን፣ ህይወትን እና ተስፋን ወደ ህይወታቸው እንዴት እንዳመጣ እንዲያካፍሉ አድርጉ።

“ወደር የለሽ ለሆነ መለኮታዊ ልጁ ስጦታ እግዚአብሔር ይመስገን።”

  • በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ምን ስጦታዎች ተቀበልን? ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ እነዚህን ሥጦታዎች በ “ህያው ክርስቶስ” ወይም እንደ “He Sent His Son [ልጁን ላከ]” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 34–35) ባሉ መዝሙሮች ውስጥ ልትፈልጉ ትችላላችሁ። ከዚያም እነዚያን ስጦታዎች የሚወክሉ ነገሮችን እንደስጦታ ዕቃ ሊጠቀልሉ ይችላሉ። ልጆቻችሁ አዳኙን እና ለእኛ የሰጠንን ሥጦታዎች እንዲያስታውሱ ለመርዳት ሥጦታዎቹን በገና ቀን እንዲከፍቱ ሀሳብ ልታቀርቡላቸው ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

አትም