“ግንቦት 8–14 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 19–20፤ ማርቆስ 10፤ ሉቃስ 18፦ ‘ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022(እ.አ.አ)]
“ግንቦት 8–14 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 19–20፤ ማርቆስ 10፤ ሉቃስ 18፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ግንቦት 8–14 (እ.አ.አ)
ማቴዎስ 19–20፤ ማርዎስ 10፤ ሉቃስ 18
“ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?”
ማቴዎስ 19–20፤ ማርቆስ 10፤ እና ሉቃስ 18ን አንብቡ እናም ለሚያሳድርባችሁ ስሜት ትኩረት በመስጠት አሰላስሉ። እነዚህን ስሜቶች መዝግቡ፤ እንዴት መተግበር እንዳለባችሁም ወስኑ።
ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ
አዳኙን ጥያቄ ለመጠየቅ እድሉ ቢኖራችሁ ምን ልትጠይቁት ትችላላችሁ? አንድ ባለጠጋ ወጣት አዳኙን ለመጀመርያ ጊዜ ሲያገኘው “የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ?” በማለት ጠየቀው። (ማቴዎስ 19፥16)። የአዳኙ መልስ ወጣቱ ለሰራው መልካም ነገሮች አድናቆት እና በፍቅር ይበልጥ እንዲሰራ ማበረታቻ የያዘ ነበር። ስለ ዘላለም ህይወት ስናሰላስል ይበልጥ ማድረግ የሚገባን ነገር ይኖር ይሆን ብለን ልናስብ እንችላለን። በራሳችን መንገድ “ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?” (ማቴዎስ 19፥20) ብለን ስንጠይቅ፥ ጌታ ለባለጠጋው ወጣት እንደመለሰው አይነት ግላዊ ምላሽ ሊሰጠን ይችላል። ጌታ የሚጠይቀን ምንም ቢሆን የእርሱን መልስ መተግበር ከእኛ ጽድቅ ይልቅ እርሱን እንድናምን (ሉቃስ 18፥9–14ን ተመልከቱ) እና “የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን [መቀበልን]” (ሉቃስ18፥17፤ ይጠይቃል በተጨማሪም 3 ኔፊ 9:22ን ተመልከቱ)።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
በወንድ እና በሴት መካከል የሚደረግ ጋብቻ በእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።
የዚህ የአዳኙ እና የፈሪሳውያን ምልልስ አዳኙ ስለጋብቻ ብቻ በማተኮር ካስተማራቸው ጥቂት ግዚያቶች መካከል አንዱ ነው። ማቴዎስ 19፥3–9 እና ማርቆስ 10፥2–12ን ካነበባችሁ በኋላ የአዳኙ የጋብቻ እይታን የሚያጠቃልሉ ንግግሮችን ዝርዝር አዘጋጁ። በ“ጋብቻ” (የወንጌል ርዕሶች topics.ChurchofJesusChrist.org) ላይ የሚገኙ አንዳንድ ምንጮችን በማጥናት ተጨማሪ ቃላትን ወደ ዝርዝራችሁ ጨምሩ። የአብ የድህነት እቅድ እውቀታችሁ ስለ ጋብቻ ያላችሁን አመለካከት እና ስሜት እንዴት ይቀይራል?
ኢየሱስ ፍቺ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ወይም የፈቱ ሰዎች ደግመው ማግባት እንደሌለባቸው ነው ያስተማረው?
ስለ ፍቺ ፕሬዝዳንት ዳለን ኤች. ኦክስ ባደረገው ንግግር የሰማይ አባት የጋብቻ ግንኙነቶች ዘላለማዊ እንዲሆኑ እንደሚያስብ አስተምሯል። ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ ፍቺ አስፈላጊ እንደሆነም እግዚአብሔር ይረዳል። ፕሬዝዳንት ኦክስ ጌታ “የፈታ ሰው በከፍተኛው ህግ ላይ የተጠቀሰው ስርዓት መጣስ ሳይኖርበት ዳግም እንዲያገባ እንደሚፈቅድ። የተፋታ አባል ከባድ መተላለፍን ካልፈጸመ፣ እሱ ወይም እሷ በሌሎች አባላት ላይ በሚተገበሩ ተመሳሳይ የብቃት ደረጃዎች መሠረት ለቤተመቅደስ ብቁነት መግቢያ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ” በማለት አብራርቷ (“ፍቺ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2007 (እ.አ.አ)፣ 70)።
ማቴዎስ 19፥16–22፤ ማርቆስ 10፥17–22፤ ሉቃስ 18፥18–23
ጌታን ከጠየቅኩት ዘላለማዊ ህይወትን ለመውረስ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ያስተምረኛል።
የባለጠጋው ወጣት ታሪክ ታማኝ፣ የዕድሜ ልክ ደቀ መዝሙር እንኳን ለአፍታ ቆም እንዲል ሊያደርግ ይችላል። ማርቆስ 10፥17–22ን ስታነቡ ስለ ወጣቱ ታማኝነት እና ቅንነት ምን ማስረጃ ታገኛላችሁ? ጌታ ስለዚህ ወጣት የተሰማው ምንድነው?
ይህ ታሪክ “ደግሞስ የሚግድለኝ ምንድር ነው?” ብላችሁ እንድትጠይቁ ሊያደርጋችሁ ይችላል። (ማቴዎስ 19፥20)። የጎደለንን እንድናሟላ ጌታ የሚረዳን እንዴት ነው? (ኤተር 12፥27ን ተመልከቱ)። ለመሻሻል ስንፈልግ እራሳችንን ለማዘጋጀት የእርሱን እርማት እና እርዳታ ለመቀበል ምን ማድረግ እንችላለን?
በተጨማሪም ላሪ አር. ላውረንስ፣ “ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?፣” ሊያሆና፣ ህዳር፣ 2015 (እ.አ.አ)፣ 33–35፤ ኤስ. ማርክ ፓልመር “ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደው፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 114–16ን ተመልከቱ።
ወንጌልን በሚቀበሉበት ጊዜ ሁሉ ሁሉም ሰው የዘላለም ሕይወት በረከትን ሊቀበል ይችላል።
በወይኑ አትክልት ውስጥ ካሉ የየትኞቹ የጉልበት ሠራተኞች ተሞክሮ ከእናንተ ጋር ይዛመዳል? በዚህ ዘገባ ውስጥ ለራሳችሁ ምን ትምህርት አገኛችሁ? የሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ መልዕክት “የወይን አትክልት ሰራተኞች” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2012 (እ.አ.አ) 31–33) ይህም ምሳሌ ለመተግበር አዲስ መንገድ ሊያሳያችሁ ይችላል። መንፈስ ምን ተጨማሪ ተነሳሽነት ይሰጣችኋል?
ከራሴ ጽድቅ ይልቅ በእግዚአብሔር ምህረት መተማመን አለብኝ።
በዚህ ምሳሌ ላይ ባሉ ሁለት ጸሎቶች መካከል ያለውን ልዩነት እንዴት ታጠቃልላላችሁ? በዚህ ታሪክ ላይ እንዳለው ቀራጭ ይበልጥ ለመሆን እና እንደ ፈሪሳዊው ላለመሆን ምን ማድረግ እንዳለባችሁ የሚሰማችሁን አሰላስሉ።
በተጨማሪም ፍልጵሲዪስ 4፥11–13፣ አልማ 31፥12–23፤ 32፥12–16ን ተመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ማርቆስ 10፥13–16፤ ሉቃስ 18፥15–17።የቤተሰብ አባላት በዚህ ታሪክ ላይ ያሉ ቁጥሮችን ማሰላሰል እንዲችሉ በአንድነት በሃሳብ የሚገናኙ እንደ “ያን ጣፋጭ ታሪክ ሳነብ አስባለሁ” (የልጆች መዝሙር፣ 56) ያሉ መዝሙሮችን መዘመር ትችላላችሁ። ኢየሱስ ከባረካቸው ልጆች መሃከል መሆን ምን ሊመስል ይችላል? “የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን [መቀበል]” ምን ማለት ሊሆን ይችላል? (ማርቆስ 10፥15)።
-
ማርቆስ 10፥23–27።ሃብት ያለው በመሆን እና በሃብት በመተማመን መሃል ያለው ልዩነት ምንድነው? (ማርቆስ 10፥23–24ን ይመልከቱ)። ቁጥር 27ን ስታነቡ የጆሴፍ ስሚዝን ትርጉም ልትጠቁሙ ትችላላችሁ “ በሃብት ለሚተማመኑ ሰዎች አይቻልም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር በሚያምኑ እና ሁሉን ስለ እኔ ለሚተው የማይቻል አይደለም፤ ምክንያቱም ለእንደነዚህ አይነቶች እነዚህ ሁሉም ነገሮች የሚቻሉ ናቸው” (ጆሴድ ስሚዝ ትርጉም፣ ማርቆስ 10፥26 [በማርቆስ 10፥27፣ የግርጌ ማስታወሻ ሃ ])። እንደ ቤተሰብ ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ እግዛብሄርን እንደምናምን እንዴት እያሳየን ነው?
-
ማቴዎስ 20፥1–16።በማቴዎስ 20፥1–16 ላይ ያለውን መርህ ለማስረዳት ቀለል ያለ አጭር ወድድር ማዘጋጀት ትችላላችሁ። ውድድሩን ከጨረሳችሁ በኋላ ሁሉንም ተመሳሳይ ሽልማት ሸልሙ፤ መጨረሻ ከወጣው ሰው በመጀመር አንደኛ እስከወጣው ድረስ። በሰማይ አባት እቅድ የዘላልም ህይወት በረከቶችን ማን እንደሚቀበል ምን ያስተምረናል?
-
ማቴዎስ 20፥25–28፤ ማርቆስ 10፥42–45።“ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን” የሚለው ሃረግ ምን ማለት ነው? (ማቴዎስ 20፥27)። ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን መርህ በምሳሌ ያሳየው እንዴት ነው? በቤተሰባችን፣ በቅርንጫፎቻችን እና በሰፈራችን የእርሱን ምሳሌ እንዴት መከተል እንችላለን?
-
ሉቃስ 18፥1–14።በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ካሉ ምሳሌዎች ስለ ጸሎት ምን እንማራለን?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።
በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “ውድ ልጆች፣ እግዚአብሔር ቅርባችሁ ነው፣” መዝሙሮች፣፣ ቁጥር 96።