አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ግንቦት 15–21 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 21–23፤ ማርቆስ 11፤ ሉቃስ 19–20፤ ዮሐንስ 12፦ “ እነሆ፥ ንጉሥሽ … ይመጣል”


“ግንቦት 15–l21 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 21–23፤ ማርቆስ 11፤ ሉቃስ 19–20፤ ዮሐንስ 12፦ ‘እነሆ፥ ንጉሥሽ … ይመጣል’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፣ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) (2022 (እ.አ.አ))

“ግንቦት 15–l21 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 21–23፤ ማርቆስ 11፤ ሉቃስ 19–20፤ ዮሐንስ 12፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ሲቀርብ አንድ ሰው ዛፍ ላይ ሆኖ

ዘኬዎስ በሾላ ዛፍ ላይ፣ በጄምስ ቲሦት

ግንቦት 15–21 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 21–23ማርቆስ 11ሉቃስ 19–20ዮሐንስ 12

“እነሆ፥ ንጉሥሽ … ይመጣል”

በዝርዝሩ ውስጥ ሃሳቦቹን ከማንበባችሁ በፊት ማቴዎስ 21–23ማርቆስ 11ሉቃስ 19–20፤ እና ዮሐንስ 12ን አንብቡ። ያደረባችሁን ስሜት ለቤተሰቦቻችሁ ወይም በቤተክርስትያን ክፍሎቻችሁ ለማካፈል መዝግቡ።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

አዳኙ ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ከተጓዘ በኋላ ተራበ፤ እናም በሩቅ ያለች የበለስ ዛፍ የምግብ ምንጭ ትመስል ነበር። ነገር ግን ዛፏን ሲጠጋ ፍሬ እንደሌላት ተመለከት (ማቴዎስ 21፥17–20ማርቆስ 11፥12–14፣ 20ን ተመልከቱ)። በአንድ መንገድ፣ የበለሱ ዛፍ በኢየሩሳሌም ውስጥ እንዳሉ ግብዝ የሃይማኖት መሪዎች ነበረች፤ ባዶ ትምህርታቸው እና ውጫዊ የቅድስና ማሳያዎቻቸው የመንፈሳዊ ምግብ የማይሰጡ ነበሩ። ፈሪሳውያን እና ጻህፍት ብዙ ትዕዛዞችን የሚጠብቁ ሆነው ይታያሉ ነገር ግን ሁለቱን ታላላቅ ትዕዛዞችን፥ እግዚአብሄርን እና ባልንጀራን እንደራስህ ውደድ የሚለውን አላከበሩም (ማቴዎስ 22፥34–4023፥23ን ተመልከቱ)።

በአንጻሩ፣ ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ትምህርቶች ውስጥ ጥሩ ፍሬን መቀበል ጀመሩ። ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ በስተመጨረሻም በጥንት ትንቢት “ንጉሥሽ… ይመጣል” (ዘካርያስ 9፥9) እንደተባለው በደስታ መንገዱን ለማስተካከል ከዛፎች በተቆረጡ ቅርንጫፎች ተቀበሉት። በዚህ ሳምንት ስታነቡ ስለ አዳኙ ትምህርት እና በህይወታችሁ የሃጢያት ክፍያው መስዋዕት ፍሬዎች እናም “ፍሬ [ማፍራት]” (ዮሐስን 12፥24) እንዴት እንደምትችሉ አስቡ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሉቃስ 19፥1–10

ጌታ የሚፈርደው በውጫዊ መልክ ሳይሆን በልብ ምኞት ነው።

በኢየሱስ ዘመን፥ ብዙ ሰዎች ቀራጮች ወይም ግብር ሰብሳቢዎች የማይታመኑ እና ከሰው የሚሰርቁ ይመስሏቸው ነበር። ስለዚህ ዘኬዎስ የቀራጮች አለቃ እንዲሁም ባለ ጠጋም ስለነበረ ብዙ የሚጠረጠር ሰው ሊሆን ይችል ይሆናል። ነገር ግን ኢየሱስ የዘኬዎስን ልብ ተመለከተ። ሉቃስ 19፥1–10 ስለ ዘኬዎስ ልብ ምን ይገልጣል? በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ዘኬዎስ ለአዳኙ መሰጠቱን ለማሳየት ያደረገውን ነገር ማስተዋል ትችላላችሁ። የልባችሁ ፍላጎት ምንድነው? ዘኬዎስ እንዳደረገው አዳኙን ለማግኘት ምን እያደረጋችሁ ነው?

በተጨማሪም ትምህርተ እና ቃል ኪዳኖች 137፥9ን ተመልከቱ።

ማቴዎስ 23ሉቃስ 20፥45–47

ኢየሱስ ግብዝነትን ያወግዛል።

አዳኙ ከጻፍት እና ፈሪሳውያን ጋር የነበረው ቆይታ ከዘኬዎስ ጋር ከነበረው ጊዜ ይለያል። ፕሬዝዳንት ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዳብራሩት “[ኢየሱስ] እንደ ጻህፍቶች፣ ፈሪሳዊያን እና ሰዶቃውያን ባሉ ግብዞች ላይ በጽድቅ ቁጣ ተነስቶ ነበር። እነርሱም የአለምን ሙገሳ፣ ተፅእኖ፣ እና ሀብት ለማግኘት ፃዲቅ መስሎ ለመታየት የሚሞክሩ፣ ሰዎችን ከመባረክ ይልቅ ሲጨቁኑ የቆዩ ነበሩ” (“ቀና በመሆን ላይ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ) 81)።

ማቴዎስ 23፣ ላይ አዳኙ ግብዝነትን ለማብራራት የተለያዩ ዘይቤአዊ አነጋገሮችን ተጠቅሟል። እነዚህን ዘይቤአዊ አነጋገሮችን ስለ ግብዝነት የሚያስተምሩትን በማስተዋል ምልክት ለማድረግ ወይም ለመዘርዘር አስቡ። ወንጌልን ለመኖር ስንሞክር ሁላችንም የምንጋፈጠው በግብዝነት እና በሰው ድክመቶች መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? በአዳኙ አስተምሮት ምክንያት ምን የተለየ ነገር ማድረግ እንዳለባችሁ ይሰማችኋል?

በተጨማሪም በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበቃላት “ግብዝ”ን ተመልከቱ።

ማቴዎስ 21፥1–11ማርቆስ 11፥1–11ሉቃስ 19፥29–44ዮሐንስ 12፥1–8፣ 12–16

ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሴ ነው።

ኢየሱስ የኃጢያት ክፍያውን ከመፈጸሙ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርስ፣ እሱን እንደ ንጉሣቸው ያወቁት እርሱን በመቀባት፣ ልብስንና የዘንባባ ቅርንጫፎችን በመንገዱ ላይ በማድረግ ውዳሴ በመጮህ መሰጠታቸውን አሳይተዋል። የሚከተሉት ምንጮች በአዳኙ የመጨረሻ ሳምንት ላይ የጀመሩትን ክስተቶች መረዳታችሁን እንዴት ጥልቅ እንደሚያደርጉ አስቡ።

አዳኙን ማክበር እና እንደ ጌታ እና ንጉስ መቀበል እንዴት ትችላላችሁ?

በተጨማሪም ጋሬት ደብሊው. ጎንግ፣ “ሆሳዕና እና ሃሌሉያ—ህያው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ፤ የዳግም መመለስ እና የትንሳኤ ማዕከል፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 52–55፤ “የጌታ የድል አገባብ ወደ ኢየሩሳሌም” (ቪድዮ)ን ተመልከቱ ChurchofJesusChrist.org

ማቴዎስ 22፥34–40

ሁለቱ ታላላቅ ትዕዛዛት እግዚአብሄርን እና ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ስትጥሩ ከአቅም በላይ ሆኖ ከተሰማችሁ፣ በማቴዎስ 22 ውስጥ አዳኙ ለጠበቃው የተናገረው ቃል ደቀ መዝሙርነታችሁን እንድታቀሉ እና እንድታተኩሩ ይረዳችኋል። ይህን ማድረጊያ አንዱ መንገድ ይህ ነው፤ የጌታን ትዕዛዛት ዝርዝር አውጡ። በዝርዝራችሁ ላይ ያለው እያንዳንዱ ንጥል ከሁለቱ ታላላቅ ትዕዛዞች ጋር እንዴት ይገናኛል? በሁለቱ ታላላቅ ትዕዛዞች ላይ ማተኮር ሌሎችን እንድትጠብቁ እንዴት ይረዳችኋል?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 21፥12–14ማቴዎስ 21፥12–14 ላይ ያሉ የኢየሱስ ቃላት እና ተግባሮች ስለ ቤተመቅደስ እንዴት እንደሚሰማው ያሳያል? ስለ ቤተመቅደስ የሚሰማንን እንዴት ማሳየት እንችላለን? ቤታችንን እንደ ቤተመቅደስ ለማድረግ ከህይወታችን ምን “[ማውጣት]” (ቁጥር 12) እንችላለን? ስለ ቤተመቅደስ መዝሙር ለመዘመር አስቡ፣ ለምሳሌ “ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ” (የልጆች መዝሙር፣ 95)።

ማቴዎስ 21፥28–32ሁለት ልጆች ከነበሩት ሰው ምሳሌ ቤተሰባችሁን የሚረዳ ትምህርት ምንድነው? ለምሳሌ፣ ከልብ ስለመታዘዝ እና ንስሃ አስፈላጊነት ለመወያየት ታሪኩን መጠቀም ትችላላችሁ። ምናልባት ቤተሰባችሁ ስለ ምሳሌው የድራማ ጽሁፍ መጻፍ እና እየተቀያየሩ የተለያዩ ክፍሎችን መተወን ይችላሉ።

ማቴዎስ 22፥15–22ሉቃስ 20፥21–26ልጆች የማስመሰል ሳንቲም የኢየሱስን “[መልክ ጽሕፈት]” በላያቸው ላይ አድርገው በመስራት ሊደሰቱ ይችላሉ። በሳንቲሞቹ ጀርባ ላይ መስጠት ያለብንን “የእግዚአብሔርን” (ማቴዎስ 22፥21) አንዳንድ ነገሮች መጻፍ ይችላሉ። በእኛ ላይ የአዳኙ “[መልክ ጽሕፈት] (ማቴዎስ 22፥20) መኖር ምን ማለት እንደሆነ መነጋገር ትችላላችሁ (በተጨማሪም ሞዛያ 5፥8አልማ 5፥14ን ተመልከቱ)።

ዮሀንስ 12፥1–8ማርያም ለአዳኙ ያላትን ፍቅር እንዴት አሳየች? ለእርሱ ያለንን ፍቅር የምናሳየው እንዴት ነው?

አንዲት ሴት በጠጕርዋ የኢየሱስን እግር እያበሰች

የኢየሱስን እግር ማጠብ፣ በብራይን ኮል

ዮሀንስ 12፥42–43በኢየሱስ ላይ ያለንን እምነት እንዳንገልጽ ወይም እንዳንጠብቅ አንዳንድ ጊዜ ተስፋ የሚያስቆርጡን ማህበራዊ ሁኔታዎች ምንድናቸው? ለማህበራዊ ግፊት እጅ የማይሰጡ ሰዎች ምሳሌ፣ ዳንናኤል1፥3–2036ዮሐንስ 7፥45–539፥1–38፤ እና ሞዛያ 17፥1–4ን ተመልከቱ። ሰዎች ሃይማኖታዊ እምነታቸውን ሲያሳዩ ወይም ሲከላከሉ ክብርን እንዴት ማሳየት እንችላለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “ተደሰቱ፣ ጌታ ንጉስ ነው!፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 66።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የቤተሰብ አባላትን ለማሳተፍ ጥበብን ተጠቀሙ።የወንጌል ጥበብ መጽሃፍ እና የወንጌል ሚድያ ላይብረሩChurchofJesusChrist.org ላይ ቤተሰባችሁ ጭብጦችን እና ክስተቶችን በምዕናብ መሳል እንዲችል ብዙ ምስሎችን እና ቪድዮዎችን ይዘዋል” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 22)።

የክርስቶስ የድል አገባብ

የድል አገባብ፣ በዋልተር ሬን