አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ግንቦት 1–7 (እ.አ.አ)። ሉቃስ 12–17፤ ዮሐንስ 11፦ “የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ”


“ግንቦት 1–7 (እ.አ.አ)። ሉቃስ 12–17፤ ዮሐንስ 11፦ ‘የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) (2022 (እ.አ.አ))

“ግንቦት 1–7 (እ.አ.አ)። ሉቃስ 12–17፤ ዮሐንስ 11፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
አንድ ሰው ልጁን እያቀፈ

አባካኙ ልጅ፣ በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

ግንቦት 1–7 (እ.አ.አ)

ሉቃስ 12–17ዮሐንስ 11

“የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ”

ሉቃስ 12–17 እና ዮሐንስ 11ን ስታነቡ የሰማይ አባት ምን እንድታውቁ እና እንድታደርጉ እንደሚፈልግ በጸሎት ፈልጉ። የእነዚህ ምዕራፎች ጥናት ለናንተ ለተባሉ መልዕክቶች ልባችሁን ሊከፍቱ ይችላሉ።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

በብዙ ሁኔታዎች ከ 100 ውስጥ 99 አስደናቂ ተብሎ ይታሰባል—ነገር ግን እነዚህ ቁጥሮች የተወደዱ የእግዚአብሔር ልጆችን ሲወክሉ አይደለም (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10ን ተመልከቱ)። እንደዛ ከሆነ አዳኙ በጠፋው በግ ምሳሌ እንዳስተማረው አንድ ነፍስም ቢሆን “የጠፋው [እስኪገኝ ድረስ]” (ሉቃስ 15፥4) ጥብቅ ፍለጋ ሊደረግለት ይገባል። የዝያኔ መደሰት እንችላለን ምክንያቱም “ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጥኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ሃጢአተኛ በሰማይ ደስታ [ስለሚሆን]” (ሉቃስ 15፥7) ነው። ይህ ፍትሃዊ ካልመሰላችሁ በእውነት “ንስሃ [የማያስፈልጋቸው]” እንደሌሉ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ሁላችንም የሚያድነን ያስፈልገናል። በእያንዳንዱ የሚድን ነፍስ እየተደሰትን ሁላችንም በማዳን ስራ ላይ መሳተፍ እንችላለን (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥15–16ን ተመልከቱ)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሉቃስ 1214–16

በዘላለማዊ ነገሮች ላይ ልቤን ሳሳርፍ እባረካለሁ።

ትልቅ ጎተራ ገንብቶ በላቡ ፍሬ የሞላን፣ ጠንክሮ የሚሰራን እና ስኬታማ የሆነን ሰው እግዚአብሔር “አንተ ሰነፍ” ለምን ይለዋል? (ሉቃስ 12፥16–21ን ተመልከቱ)። በሉቃስ ላይ በእነዚህ ምዕራፎች አዳኙ እይታችንን ከአለማዊ ወደ ዘላለማዊ ከፍ እንድናደርግ የሚረዱ ብዙ ምሳሌዎችን አስተምሯል። አንዳንዶቹ ምሳሌዎች እዚህ ተዘርዝረዋል። የእያንዳንዱን መልዕክት እንዴት ታጠቃልላላችሁ? ጌታ ምን እየነገራችሁ ያለ ይመስላችኋል?

በተጨማሪም ማቴዎስ 6፥19–342 ኔፊ 9፥30ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥10ን ተመልከቱ።

ሉቃስ 15

የጠፉ ሲገኙ የሰማይ አባት ደስ ይለዋል።

ሉቃስ 15፣ ላይ ያሉ ምሳሌዎችን ስታነቡ ሃጢያት ስለሰሩት ወይም “ስለጠፉት” የሰማይ አባት ምን እንደሚሰማው ትማራላችሁ? መንፈሳዊ መሪ—ወይም ማናችንም ብንሆን—ስለእነሱ ሊሰማን የሚገባን እንዴት ነው? እነዚህን ጥያቄዎች ፈሪሳውያን እና ጻህፎች እንዴት ሊመልሱት እንደሚችሉ አስቡ (ሉቃስ 15፥1–2ን ተመልከቱ)። የኢየሱስ ምላሾች በሉቃስ 15፣ ላይ ባሉ ሶስት ምሳሌዎች ሊገኙ ይችላሉ። ስታነቡ ኢየሱስ ጻህፎች እና ፈሪሳውያንን እያስተማረ ያለውን ነገር አስቡ።

በተጨማሪም በምሳሌዎች መካከል ስላለው አንድነት እና ልዩነት ዝርዝር ማውጣት ትችላላችሁ። ለምሳሌ፥ በያንዳንዱ ምሳሌ ምን እንደጠፋ፣ ለምን እንደጠፋ እና እንዴት እንደተገኘ፣ እናም ሲገኝ ደግሞ የሰው ምላሽ ምን እንደነበር መለየት ትችላላችሁ። ለጠፉ—የጠፉ መስሎ ለማይሰማቸው ጨምሮ ኢየሱስ ምን መልዕክት አለው? የጠፉት ለሚፈልጉ ሰዎች እርሱ ምን መልዕክት አለው?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 18፥10–16፤ ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “ሌላኛው አባካኝ፣” ኢንዛይን፣ ግንቦት 2002 (እ.አ.አ)፣ 62–64ን ተመልከቱ።

ምስል
አንዲት ሴት ሳንቲም እየፈለገች

የጠፋው የብር ቁራጭ፣ በጄምስ ቲሶት

ሉቃስ 16፥1–12

በአመጸኛው መጋቢ ምሳሌ ክርስቶስ ምን እያስተማረ ነበር?

ሽማግሌ ጄምስ ኢ.ታልማጅ ከምሳሌው ልንማር የምችለውን አንደ ትምህርት አብራርቷል፤ “ትጉህ ሁኑ፤ ምክንያቱም ምድራዊ ሃብታችሁን የምትጠቀሙበት ቀን በቅርቡ ያልፋል። ከማይታመኑ እንዲሁም ከክፉዎችም እንኳን ትምህርት ውሰዱ፤ ለሚያስቧት ወደፊት ለማዘጋጀት እጅግ አርቀው የሚያስቡ ከሆነ እናንተ ለዘላለማዊ ወደፊት የምታስቡ ምን ያህል አብልጣችሁ ማዘጋጀት ይኖርባችኋል! “ከአመጻ ገንዘብ” አጠቃቀም ጥበብን እና አርቆ ማሰብን ካልተማራችሁ፣ ይበልጥ ዘላቂ በሆነ ሃብት እንዴት ልትታመኑ ትችላላችሁ? (ኢየሱስ ክርስቶስ [1916 (እ.አ.አ)]፣ 464)። ከዚህ ምሳሌ ሌላ ምን ተማራችሁ?

ሉቃስ 17፥11–19

ለበረከቶቼ አመስጋኝ መሆን ወደ እግዚአብሔር ያቀርበኛል።

ከአስሩ ለምጻሞች መካከል አንዱ ብትሆኑ አዳኙን ለማመስገን የምትመለሱ ይመስላችኋል? አመስጋኙ ለምጻም በማመስገኑ ምክንያት ተጨማሪ በረከት ያገኘው ምንድነው?

በተጨማሪም “ተነሣና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል” (ቁጥር 19) የሚሉትን የአዳኙን ቃላት አሰላስሉ። በእናንተ አመለካከት አመስጋኝነት እና እምነት እንዴት ይገናኛሉ? ሁለቱም እንድን ዘንድ እንዴት ይረዱናል? “ፕሬዝዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን የምስጋና የፈውስ ሃይል”(ChurchofJesusChrist.org) የሚለው ቪድዮ እነዚህን ጥያቄዎች እንድታሰላስሉ ይረዳሉ።

በተጨማሪም ዴል ጂ. ረንላንድ፤ “የእግዚአብሔርን መልካምነት እና ታላቅነት አስቡ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ) 41–44 ን ተመልከቱ።

ዮሐንስ 11፥1–46

ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ እና ህይወት ነው።

አልዓዛርን ከሞት ያስነሳበት ተአምር ኢየሱስ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ እና ቃል የተገባለት መሲህ እንደሆነ ሃይለኛ እና የማይካድ ምስክርነት ነበር። በዮሐንስ 11፥1–46 ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ “ትንሣኤና ሕይወት” ስለመሆኑ እምነታችሁን የሚያጠነክሩ የትኞቹ ቃላት፣ ሃረጎች ወይም ዝርዝሮች ናቸው? ኢየሱስ “ትንሣኤና ሕይወት” ነው የሚለው ለናንተ ምን ማለት ነው?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሉቃስ 15፥1–10የቤተሰባችሁ አባላት አንድ ነገር ማጣት—ወይም መጥፋት እንዴት እንደሚሰማ ይረዳሉ? ስለ ገጠመኛቸው ማውራት ስለጠፋው በግ እና ጠፍቶ ስለነበርው ድሪም ምሳሌ ውይይት ሊጀምር ይችላል። ወይም አንድ ሰው ሲደበቅ ሌሎች የቤተሰብ አባላት እንዲያገኘው የማድረግ ጭዋታ ልትጫወቱ ትችላላችሁ። ይህ ጨዋታ እነዚህን ምሳሌዎች እንድንረዳ እንዴት ይረዱናል?

ሉቃስ 15፥11–32የምንወዳቸው ሰዎች ሲጠፉ በዚህ ታሪክ ላይ እንዳለው አባት እንዴት መሆን እንችላለን? ከታላቁ ልጅ ልምድ ይበልጥ እንደ ክርስቶስ እንድንሆን የሚረዳንን ምን እንማራለን? በዚህ ምሳሌ ላይ ያለው አባት እንደ ሰማይ አባታችን የሆነው በምን አይነት መንገድ ነው?

ሉቃስ 17፥11–19የቤተሰብ አባላት አስሩ ለምጻሞች ታሪክ እንዲተገብር ለመርዳት በድብቅ አንዱ ለሌላው የምስጋና ማስታወሻዎችን እንዲተው ጋብዟቸው። በአንድነት “በረከታችሁን ቁጠሩ” (መዝሙር፣ ቁጥር 241) የሚለውን መዘመር እናም ቤተሰባችሁ የተቀበለውን በረከት መቁጠር እችላላችሁ።

ዮሐንስ 11፥1–46የቤተሰብ አባላት “አልዓዛር ከሞት ተነሳ” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪድዮ መመልከት እና የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነታቸውን ማካፈል ይችላሉ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ይመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “ለእረኛው ልብ ውድ ናቸው፣” መዝሙር፣ ቁጥር 221።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የወንጌል መርሆችን ለማስተማር ታሪኮችንን እና ምሳሌዎችን ተጠቀሙ። አዳኙ ብዙውን ጊዜ የወንጌል መርሆዎች ታሪኮችን እና ምሳሌዎችን በመጠቀም አስተምሯል። የወንጌልን መመሪያ ለቤተሰባችሁ ህያው ሊያደርጉ የሚችሉ ምሳሌዎችን እና ታሪኮችን ከራሳችሁ ህይወት አስቡ (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]22ን ተመልከቱ)።

ምስል
በኢየሱስ ፊት በምስጋና የተንበረከከ ሰው

ዘጠኙ የት አሉ፣ በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

አትም