አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 24–30 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 7–10፦ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ”


“ሚያዝያ 24–30 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 7–10፤ ‘መልካም እረኛ እኔ ነኝ’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ሚያዝያ 24–30 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 7–10፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ መሬት ላይ ከወደቀች ሴት ጋር

እኔም አልፈርድብሽም፣ በኮሌቫ ቲሞቲ

ሚያዝያ 24–30 (እ.አ.አ)

ዮሐንስ 7–10

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ”

ዮሐንስ 7–10ን ስታነቡ በእነዚህ ምዕራፎች ላይ ስላሉ ትምህርታዊ መርሆዎች ከመንፈስ ቅዱስ መነሳሳትን ልትቀበሉ ትችላላችሁ። እነዚህን ስሜቶች መመዝገብ ለመተግበር እቅድ እንድታወጡ ሊረዳችሁ ይችላል።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ምንም እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው “ሰላም [እና] ለሰውም በጎ ፈቃድ” (ሉቃስ 2፥14) ለማምጣት ቢሆንም “ከእርሱ የተነሣ በሕዝቡ መካከል መለያየት ሆነ” (ዮሐንስ 7፥43)። ተመሳሳይ ትዕይንቶችን የተመለከቱ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ማንነት እጅግ የተለየ አመለካከት ነበራቸው። አንዳንዶቹ “ደግ ሰው ነው” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “ሕዝቡን ግን ያስታል ይሉ ነበር “(ዮሐንስ 7፥12)። በሰንበት አይነ ስውርን ሲፈውስ አንዳንዶች “ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና ከእግዚአብሔር አይደለም” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “ኃጢአትኛ ሰው እንደነዚህ ያሉ ምልክቶች ሊያደርግ እንዴት ይችላል?” በማለት ጠየቁ። (ዮሐንስ 9፥16)። በዚህ ሁሉ ግራ መጋባት ውስጥ እውነትን የፈለጉ በቃላቶቹ ውስጥ ሃይልን አገኙ፤ ምክንያቱም “እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም” (ዮሐንስ 7፥46)። አይሁዶች እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ “[ገልጦ እንዲነግራቸው]” ሲጠይቁት፥ “በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል” በማለት እውነትን ከስህተት መለየት እንድንችል የሚረዳ መርህ ገለጠ (ዮሐንስ 10፥24፣ 27)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ዮሐንስ 7፥14–17

ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማራቸውን እውነቶች ስኖር እውነት ስለመሆናቸው አውቃለሁ።

ክርስቶስ ቢያንስ እነሱ በለመዱት መንገድ—ያልተማረ ሆኖ ሳለ ብዙ ማወቁ አይሁዶችን ያስደንቃቸው ነበር (ቁጥር 15ን ተመልከቱ)። ኢየሱስ የትምህርት ደረጃ ወይም የኋል ታሪክ ምንም ቢሆን ለሁሉ የሚገኝ እውነትን ማወቅያ የተለየ መንገድ በመልሱ አስተማረ። በዮሐንስ 7፥14–17፣ መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው ትምህርት እውነት መሆኑን እንዴት ማወቅ ትችላላችሁ? ይህ ሂደት የወንጌል ምስክርነታችሁን እንድታሳድጉ እንዴት ረዳችሁ?

ዮሀንስ 8፥2–11

የአዳኙ ምህረት ለሁሉም የሚገኝ ነው።

አዳኙ በምንዝር ከተያዘች ሴት ጋር ስለነበው ጊዜ ሽማግሌ ዴል ጂ. ረንላንድ፤ “በእውነት አዳኙ ዝሙትን አልፈቀደም። ነገር ግን ሴቲቱን ችላ አላለም። ህይወቷን እንድታስተካክል አበረታታት። በእርሱ ርህራሄ እና ምህረት የተነሳ ለለውጥ ተነሳሳች። የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ‘ሴቲቱም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ እግዚአብሔር ን አከበረች፣ በስሙም አመነች’ በማለት ስለ ደቀ መዝሙርነቷ ያረጋግጣል’ [ ዮሐንስ 8፥11፣ የግርጌ ማስታወሻ ]፤ (“የእኛ መልካም እረኛ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ) 30ን ተመልከቱ)።

እንደ ሴቲቱ ከአዳኙ ፍርድ ሳይሆን ምህረትን እንደተቀበላችሁ ሆኖ የተሰማችሁ መቼ ነው? እናንተ ያለ ሃጢያት ሳትሆኑ እንደ ጻህፎች እና ፈሪሳውያን ሌሎችን የከሰሳችሁት ወይም የፈረዳችሁት መቼ ነበር? (ዮሐንስ 8፥7ን ተመልከቱ)። አዳኙ ከጻህፎች፣ ፈሪሳውያን እና በምንዝር ከተያዘችው ሴት ጋር ቆይታ ካደረገበት መንገድ ሌላ ምን ልትማሩ ትችላላሁ? እነዚህን ቁጥሮች ስታነቡ ስለ አዳኙ ይቅር ባይነት ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም “ሂጂ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

ዮሀንስ 9

እምነት ካለን እግዚአብሔር በድካሞቻችን ላይ ራሱን ሊያሳየን ይችላል።

ዮሐንስ 9፥1–3 ስለ ህይወት ፈተና እና መከራ ምን ያስተምራችኋል? ዮሐንስ 9ን ስታነቡ አይነ ስውር ሆኖ በተወለደው ሰው ህይወት ውስጥ “የእግዚአብሔር ሥራ [እንዴት እንደተገለጠ]” አሰላስሉ። በመከራችሁ ጨምሮ በእናንተ ህይወት እንዴት ተገልጠዋል?

ዮሀንስ 10፥1–30

ኢየሱስ ክርስቶስ መልካሙ እረኛ ነው።

ምንም እንኳን በግ እና እረኝነት የለመዳችሁት ነገር ባይሆንም አዳኙ በዮሐንስ 10፣ ላይ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ” ብሎ የሚናገርበትን ማንበብ ስለ እርሱ አስፈላጊ እውነቶችን ሊያስተምረን ይችላል። እነዚህን እውነቶች ለማግኘት መልካም እረኛ ምን አይነት እንደሆነ የሚገልጹ ሃረጎችን በመፈለግ እንዴት ከአዳኙ ጋር እንደሚሄዱ አስቡ። ከታች አንዳንድ ምሳሌዎች ይገኛሉ፦

  • ቁጥር 3፦ “የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።”

  • ቁጥር 11፦ እርሱ “ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”

  • ቁጥር 16፦ “አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።”

ይህም ምዕራፍ ይበልጥ እንድታሰላስሉ አንዳንድ ተጨማሪ ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፤ ኢየሱስ እንደ በር የሚሆነው እንዴት ነው? (ቁጥር 7–9ን ተመልከቱ)። “ሕይወት [እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁ]” ያደረገው እንዴት ነው? (ቁጥር 10)። በግል እንደሚያውቃችሁ የተሰማችሁ መች ነው? (ቁጥር 14ን ተመልከቱ)። የመልካሙን እረኛ ድምጽ እንዴት መለየት ትችላላችሁ? (ቁጥር 27ን ተመልከቱ)።

በተጨማሪም መዝሙር 23ህዝቅኤል 34አልማ 5፥37–393 ኔፊ 15፥21–16፥5፤ ጋሬት ደብሊው. ጎንግ፣ “መልካም እረኛ፣ የእግዚአብሔር በግ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ) 97–101ን ተመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ዮሀንስ 7፥24ዮሐንስ 7፥24፣ ላይ ያለውን የኢየሱስ አስተምሮት ቤተሰባችሁ እንዲረዳ ለማገዝ ከውጭ ሲታይ እና ከውስጥ የተለያየ የሆነን ነገር ማሳየት ትችላላችሁ። ወይም የቤተሰብ አባላት በውጫዊ መልክ መፍረድ እንደሌለባቸው ያስተማራቸውን ልምድ ማካፈል ይችላሉ። በተጨማሪም የእያንዳንዱን የቤተሰብ አባል በአይን የማይታዩ ባህርያት መዘርዘር ትችላላችሁ (በተጨማሪ 1 ሳሙኤል 16፥7፤ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “ሌሎች መሆን የሚችሉትን ተመልከቱ፣ ” ሊያሆና፣ ህዳር፣ 2012 (እ.አ.አ) 68–71 ን ተመልከቱ)።

ዮሐንስ 8፥31–36“የዲያቢሎስ አገልጋይ” መሆን ማለት ምን ማለት ነው? (በተጨማሪም ሞሮኒ 7፥11ን ተመልከቱ)። ኢየሱስ ያስተማረው የትኛው እውነት ነው ነጻ ሊያደርገን የሚችለው?

ኢየሱስ አይነ ስውርን ሲፈውስ

ኢየሱስ አይነስውርን ሲፈወስ፣ በካርል ሄንሪክ ብሎች

ዮሐንስ 9ዮሐንስ 9፣ ላይ ኢየሱስ አይነ ስውሩን የፈወሰበትን ምዕራፍ ቤተሰባችሁ በምዕናብ እንዲያይ እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ? በአንድነት ታሪኩን ልትተውኑት ወይም “ኢየሱስ አይነስውር ሆኖ የተወለደን ፈወሰ” የሚለውን ቪድዮ ማየት ትችላላችሁ (ChurchofJesusChrist.org)። ቤተሰባችሁ በዮሐንስ 9፣ ላይ ያሉትን ተመሳሳይ ቁጥሮችን እንዲያነብ ቪድዮውን አልፎ አልፎ አቁሙ። ከምዕራፉ የሚማሩትን፥ ለምሳሌ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መቀየር ምን ማለት እንደሆነ፥ እንዲያስተውሉ ጋብዟቸው።

ዮሐንስ 10፥1–18፣ 27–29ቤተሰባችሁን በመልካሙ እረኛ ምሳሌ ትምህርት ላይ እንዲሳተፉ እያንዳንዳቸው ከሚከተሉት አንዱን እንዲስሉ ጠይቁ፤ ሌባ፣ በር፣ እረኛ፣ ሰራተኛ (ተቀጥሮ የሚሰራ)፣ ተኩላ እና በግ። ዮሐንስ 10፥1–18፣ 27–29ን እንዲያነቡ ጋብዟቸው እናም እንደ ቤተሰብ ስለ ሳሉት ስዕል አዳኙ ምን እንዳስተማረ ተወያዩ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፣” መዝሙር፣፣ ቁጥር 108።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የሚያነሳሱ ቃላትን እና ሃረጎችን ፈልጉ። እያነበባችሁ እያላችሁ መንፈስ ለእናንተ ብቻ የተጻፉ የሚመስሉ አንዳንድ ቃላትን እና ሃረጎችን እናንተ ሊያነሳሳ እና ሊያነቃቃ ወደ ትኩረታችሁ ሊያመጣ ይችላል። በዮሐንስ 7–10፣ ላይ እናንተን የሚያነሳሱ የትኞቹንም ቃላት ወይም ሃረጎች ለመጻፍ አስቡ።

ኢየሱስ ከጠቦት ጋር

የጠፋ አይደለም፣ በግሬግ ኬ. ኦልሰን።