“ሚያዝያ 3–9 (እ.አ.አ)። ትንሳኤ፤ ‘መቃብር ሆይ፣ ድል መንሳትህ የት አለ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) 2022 (እ.አ.አ)
“ሚያዝያ 3–9 (እ.አ.አ)። ትንሳኤ፤ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 3–9 (እ.አ.አ)
ትንሳኤ
“መቃብር ሆይ፣ ድል መንሣትህ የት አለ?”
በዚህ ረቂቅ ላይ ስለ አዳኙ ትንሳኤ ምስክርነቶችን ስታነቡ ከመንፈስ ቅዱስ ለሚመጡ ስሜቶች ትኩረት ስጡ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
በአዳኙ ህይወት የመጨረሻ ሳምንት ላይ በእርሱ ዙርያ ያሉ ብዙ አይሁዶች በፋሲካ በአል ላይ ይሳተፉ ነበር። የእስራኤልን ቤት ከግብጽ ባርነት ነጻ መውጣት ለማስታወስ በአንድነት በመሰብሰብ ምግብ ያዘጋጃሉ፣ ሙዚቃ ይጫወታሉ። በጠቦት ደም በራቸው ላይ ምልክት ያደረጉ ቅድመ አያቶቻቸውን ቤት አጥፊው መልአክ ያለፈበትን ታሪክ ቤተሰቦች ይሰማሉ። በአንጻራዊው በነጻ መውጣት ምልክቶች በተሞላው በዓል ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር በግ በስቃዩ፣ በሞቱ እና በትንሳኤው ከሃጢያት እና ሞት ነጻ ሊያወጣቸው እንደነበር የሚያውቁት ጥቂት ሰዎች ነበሩ። ቢሆንም ኢየሱስን፥ ቃል የተገባለትን መሲህ፥ የዘላለም አዳኛቸውን ያወቁት ነበሩ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት “ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም…፤ በሦስተኛው ቀን ተነሣ” (1 ቆሮንቶስ 15፥3–4) በማለት ለአለም ሁሉ መሰከሩ።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሃጢያት እና ሞት ያድነኛል፣ በድካሜ ያበረታኛል፤ በፈተናዎቼ ያጽናናኛል።
በዚህ ሳምንት በአዳኙ የሃጢያት ክፍያ በረከቶች ላይ ማተኮርያ አንዱ መንገድ ስለ አዳኙ ህይወት የመጨረሻ ሳምንት በየቀኑ በማንበብ ጊዜ በማሳለፍ ነው። የአዳኙ ፍቅር እንዲሰማችሁ በእነዚህ ቁጥሮች ላይ የሚረዳችሁን ምን ታገኛላችሁ? እነዚህ ምዕራፎች እርሱ ከሃጢያት፣ ከሞት፣ ከፈተና እና ከድካም እንዴት እንደሚያድናችሁ የሚያስተምራችሁን አሰላስሉ። በማዳን ሃይሉ ላይ እምነታችሁን እንዴት እየተለማመዳችሁ ነው?
-
እሁድ፦ በድል ወደ ኢየሩሳሌም መግባት (ማቴዎስ 21፥6–11)
-
ሰኞ፦ ቤተመቅደስን ማንጻት (ማቴዎስ 21፥12–16)
-
ማክሰኞ፦ በኢየሩሳሌም ማስተማር (ማቴዎስ 21–23)
-
እሮብ፦ ማስተማሩን ቀጠለ (ማቴዎስ 24–25)
-
ሐሙስ፦ ፋሲካ እና በጌቴሴማኒ የክርስቶስ ስቃይ (ማቴዎስ 26)
-
አርብ፦ ለፍርድ መቅረብ፣ ስቅለት እና ቀብር (ማቴዎስ 27፥1–61)
-
ቅዳሜ፦ የክርስቶስ ስጋ በመቃብር ላይ አኖሩ (ማቴዎስ 27፥62–66)፤ በመንፈስ አለም አገለገለ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138)
-
እሁድ፦ የኢየሱስ ክርስቶስ እርገት እና ለደቀመዛሙርቱ መገለጥ (ማቴዎስ 28፥1–10)
በተጨማሪም Easter.ComeuntoChrist.orgን ተመልከቱ።
ማቴዎስ 28፥1–10፤ ሉቃስ 24፥13–35፤ ዮሐንስ 20፥19–29፤ 1 ቆሮንቶስ 15፥1–8፣ 55
ብዙ የአይን እማኞች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ መስክረዋል።
ክርስቶስ ላይ ሲያሾፉ፣ ሲበድሉት እና ሲሰቅሉት ደቀመዝቅሙርቱ ሲመለከቱት ምን ተሰምቷቸው ሊሆን እንደሚችል ገምቱ። ሃይሉን ተመልክተዋል፣ የአስተምሮቱን እውነተኛነት ተሰምቷቸዋል እና የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነም እምነት ነበራቸው። ሞቱን መመልከት ደቀመዛሙርቱ ከባድ ሃዘን እና ግራ መጋባት እንዲሰማቸው አድርጎ ይሆናል። ነገር ግን ብዙም ሳይርቅ የእርሱን ትንሳኤ ታላቅ ተአምር ምስክር ሆኑ።
ትንሳኤ ያደረገውን አዳኝ ከተመለከቱ ሰዎች ጽሁፍ ምን ትማራላችሁ? በማቴዎስ 28፥1–10፣ ሉቃስ 24፥13–35፤ ዮሐንስ 20፥19–29፤ እና 1 ቆሮንቶስ 15፥1–8፣ 55፣ ላይ የእያንዳንዱን ሰው ገጠመኝ ምልክት አድርጉ ወይም ልብ በሉ። (ትንሳኤ ያደረገው ክርስቶስ ሌሎች ምስክሮች በ3 ኔፊ 11፤ ሞርሞን 1፥15፤ ኤተር 12፥38–39፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥19–24፤ 110፥1–10፤ እና የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥15–17፣ ላይ ይገኛሉ።) ስለ እነዚህ ምስክሮች የሚያስደንቃችሁ ምስክርነት ምንድነው? ከትንሳኤው በኋላ ሌሎችም ከሞት ተነስተው ለብዙዎች ታይተው ነበር (ማቴዎስ 27፥52–53፤ 3 ኔፊ 23፥9ን ተመልከቱ)። በአዳኙ ላይ ያላችሁ እምነት እና የትንሳኤ ቃልኪዳን በአኗኗራችሁ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?
በተጨማሪም “ኢየሱስ ትንሳኤ አድርጓል” “የተነሳው ጌታ ለሐዋርያት ታየ” “ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org፣ ላይ ተመልከቱ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋ እና ደስታን ይሰጠኛል።
በ1 ጴጥሮስ 1፥3–11 ላይ ያሉ የትኞቹ ቃላት ወይም ሃረጎች በኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋ ይሰጧችኋል? ይህ ተስፋ መች ተሰምቷችሁ ያውቃል?
ሽማግሌ ጋሬት ደብሊው. ጎንግ ትንሳኤ “እግሮቻቸውን ላጡ፣ ማየት፣ መስማት ወይም መራመድ ለተሳናቸው፣ ለከባድ በሽታ፣ ለአእምሮ ህመም ወይም ሌላ አቅማቸው ለተዳከሙ ሰዎች ተስፋ ይሰጣል። ያገኘናል። ሙሉም ያደርገናል። … [ደግሞም] ‘እግዚአብሔር እራሱ ለአለም ሃጢያቶች የሃጢያት ክፍያ [ይከፍላል]’ [አልማ 42፥15]፣… በምህረት እርሱ በድካማችን ይረዳናል።… ንስሀ እንገባለን እናም የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። በዘላለም ‘ፍቅር ክንዶች [ይከበናል]’ [2 ኔፊ 1፥15]” በማለት መስክሯል (“ሆሳና እና ሃሌሉያ—ህያው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ፤ የዳግም መመለስ እና ትንሳኤ ማዕከል፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ) 54)።
በተጨማሪም አልማ 27፥28፤ 36፥1–24፤ 3 ኔፊ 9፥11–17፤ ሞሮኒ 7፥40–41ን ተመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ComeuntoChrist.org።Easter.ComeuntoChrist.org በአዳኙ ህይወት የመጨረሻ ሳምንት በእያንዳንዱ ቀን የተከናወኑ ክስተቶችን የጊዜ ሰሌዳ እና ማብራርያ ይዟል። በሳምንቱ እያንዳንዱ ቀን ቤተሰባችሁ አዳኙ በዚያች ቀን ምን እንዳደረገ ለማወቅ እነዚህን ማብራርያዎች መከለስ ይችላል ወይም ስለ እሱ የመጨረሻ ሳምንት እንደ ቤተሰብ ማንበብ ትችላላችሁ (የሚመከር ዝርዝር በ“ለግል የቅዱስ መጽሃፍ ጥናት ሃሳቦች” ላይ ከላይ ተመልከቱ)።
-
መዝሙር እና የልጆች መዝሙር መጽሐፍ።በዚህ ሳምንት ስለ አዳኙ የሃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ መዝሙር፥ በአንድነት ልትዘምሩ ትችላላችሁ፤ ለእናንተ ያልተለመዱ የሆኑትን ጨምሮ። (የመዝሙሮች ወይም የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ የርዕስ ማውጫ በእነዚህ ርዕሶች ተመልከቱ፤ “የሃጥያት ክፍያ”፣ “ትንሳኤ” ወይም “ከሞት መነሳት።”) የቤተሰብ አባላት መዝሙሮቹን እንዲለምዱ ከቃላቱ ጋር የሚሄዱ ስዕሎችን ማሳየት ትችላላችሁ።
-
“ኢየሱስ ክርስቶስ” ስብስብ በወንጌል ላይብረሪ።“ኢየሱስ ክርስቶስ” የሚል ርዕስ ያለው የወንጌል ላይብረሪ ስብስብ በዚህ ትንሳኤ የአዳኙን ከሞት መነሳት ለማክበር ቪድዮዎችን፣ የጥበብ ስራዎችን እና ሙዚቃዎችን ይዟል።
-
“ህያው ክርስቶስ፥ የሐዋሪያት ምስክርነት”እንደ ቤተሰብ “ህያው ክርስቶስ፥ የሐዋሪያት ምስክርነት” (ChurchofJesusChrist.org)ን አንብቡ። ከዚህ ምስክርነት እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የትንሳኤ መልዕክት እንዲመርጡ እና እንዲያካፍሉ ጋብዟቸው። ለምሳሌ፣ በማህበራዊ ሚድያ፣ በፊት ለፊት በራችሁ ወይም በቤታችሁ እንዲታይ የሚለጠፍ ስዕል ማዘጋጀት ትችላላችሁ።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፦ “ኢየሱስ ተነስቷል፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣70።