“ሚያዝያ 10–16 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 15–17፤ ማርቆስ 7–9፦ ‘አንተ ክርስቶስ ነህ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]
“ሚያዝያ 10–16 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 15–17፤ ማርቆስ 7–9፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 10–16 (እ.አ.አ)
ማቴዎስ 15–17፤ ማርቆስ 7–9
“አንተ ክርስቶስ ነህ”
ቅዱሳን መጻህፍትን ማንበብ መንፈስ ቅዱስን ወደ ህይወታችሁ ይጋብዛል። ከመንፈስ ቅዱስ አስፈላጊ ተልዕኮዎች አንዱ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መመስከር ነው። በዚህ ሳምንት ቅዱሳን መጻህፍትን ስታነቡ፣ የአዳኙን ምስክርነት ለሚያጠነክሩ መንፈሳዊ ስሜቶች ትኩረት ስጡ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን ከኢየሱስ “ከሰማይ ምልክት [መፈለጋቸው]” እንግዳ ነገር አይደለም? በደንብ የሚታወቁ የእርሱ ተአምራት በቂ አልነበሩም? የእርሱ በሃይል የተሞላ አስተምሮት ወይም ጥንታዊ ትንቢቶችን የፈጸመበት ብዙ መንገዶችስ? የእነሱ ፍላጎት የተነሳሳው በምልክቶች ማነስ ሳይሆን “ምልክት [ለመለየት]” እና ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው። (የማቴዎስ ወንጌል 16፥1–4ን ተመልከቱ።)
ጴጥሮስ ልክ እንደ ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን የአዳኙን ተአምራት ተመልክቷል፤ አስተምሮቶቹንም አድምጧል። ነገር ግን የጴጥሮስ ቁርጥ ያለ ምስክርነት፣ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ከአካላዊ ስሜት—ከእርሱ “ስጋና ደም” የመጣ አልነበረም። የሱ ምስክርነት የተገለጠው “[በሰማያት ባለው አባታችን]” አማካኝነት ነው። መገለጥ ቀድሞም አሁንም አዳኙ ቤተክርስትያኑን የገነባበት አለት ነበር—መገለጥ ለአገልጋዮቹ ከሰማይ። ይህ ደቀ መዛሙርትነታችንን የምንገነባበት አለት ነው—ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ እና አገልጋዮቹ “የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻዎች “ እንደያዙ መገለጥ። በእዚህ መሰረት ላይ ስንገነባ “የገሃነም ደጆች [አይችሉንም]” (ማቴዎስ 16፥15–19)።
ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት የሚመጣው በመገለጥ አማካኝነት ነው።
ዛሬ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” በማለት ህዝቡን ቢጠይቅ ምን ሊሉ ይችላሉ? “እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” ብሎ ኢየሱስ ቢጠይቃችሁ እንዴት ትመልሳላችሁ? (ማቴዎስ 16 ፥13–15ን ተመልከቱ።)
የአዳኙን ምስክርነታችሁን እና እንዴት እንደተቀበላችሁ አሰላስሉ። ከ ማቴዎስ 16፥15–17 ላይ ሊያጠነክረው የሚችል ምን ተማራችሁ? ስለ ምስክርነት እና የግል መገለጥ መማር ከፈለጋችሁ እነዚህን ጥቅሶች አስሡ፤ ዮሐንስ 15፥:26፤ 2 ኔፊ 31፥17–18፤ አልማ 5፥45–48፤ እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፥2–3።
በተጨማሪም “ፕሬዝዳንት ኔልሰን፤ እርሱን ስሙት—የግል መገለጥ” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።
ማቴዎስ 16፥13–19፤ 17፥1–9፤ ማርቆስ 9፥2–9
“የመንግሥተ [ሰማያት] መክፈቻዎች” ዛሬ በምድር ላይ ናቸው።
አዳኙ ለጴጥሮስ ለመስጠት ቃል የገባው “የመንግሥተ [ሰማያት] መክፈቻዎች” የክህነት ቁልፎች ናቸው (ማቴዎስ 16፥19)። የክህነት ቁልፎች ምንድናቸው? ለምን ያስፈልጉናል? እነዚህን ጥያቄዎች በሚከተሉት ምዕራፎች የአዳኙን ቃልኪዳን ስታነቡ አሰላስሉ፤ ማቴዎስ 16፥13–19 እናም መፈጸማቸውን በማቴዎስ 17፥1–9፤ ማርቆስ 9፥2–9 (በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማርቆስ 9፥3 [በማርቆስ 9፥4, የግርጌ ማስታወሻ ሃ ] ተመልከቱ)።
ስለ ክህነት ቁልፎች ለመማር ሌሎች ምንጮችን የሚከተሉትን ያካትታሉ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 65፥2፤ 107፥18–20፤ 110፥11–16፤ 128፥9–11፤ “የክህነት ቁልፎች” በለቅዱሳን መጻህፍት መመርያ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org)፤ እና ሽማግሌ ጋሪ ኢ. ስቲቨንሰን መልዕክት “የክህነት ቁልፎች እና ስልጣን የት ነው ያለው?፣” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ) 29–32)። እነዚህን ምንጮች ስታጠኑ ስለ ክህነት ቁልፍ የምትማሩትን እና ስለሚመጡ በረከቶች ዝርዝር ማውጣት ትችላላችሁ። የክህነት አገልግሎትን ለመምራት ቁልፍ ጥሩ ምልክት የሆነው ለምን ይመስላችኋል?
በተጨማሪም ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “የመልከጸዴቅ ክህነት እና ቁልፎቹ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 69–72፤ የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበቃላት “የለውጥ ተራራ”ን ተመልከቱ።
ትልቅ እምነትን ስፈልግ ባለኝ እምነት መጀመር እችላለሁ።
በማቴዎስ 17 እና ማርቆስ 9 ላይ የተገለጸው አባት ኢየሱስ ልጁን ይፈውስ እንደሆን እርግጠኛ ላለመሆን ምክንያቶች ነበሩት። የእየሱስ ደቀመዛሙርት እንዲፈውሱት ቢጠይቃቸውም አልቻሉም። ነገር ግን አዳኙን ለተአምር ሲጠይቅ እምነትን ለመግለጽ መረጠ። “አምናለሁ” አለ። ከዚያም እምነቱ ፍጹም እንዳልሆነ ለማሳወቅ “አለማመኔን እርዳው” በማለት አከለ።
ስለዚህ ተአምር ስታነቡ መንፈስ ምን ያስተምራችኋል? የሰማይ አባት እምነታችሁ እንዲጨምር እንዴት ረድቷችኋል? ባላችሁ እምነት ላይ ለመገንባት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? ምናልባትም የቅዱሳን መጻህፍት፣ የጉባኤ መልዕክቶችን ወይም እምነታችሁን ያጠነከሩ አጋጣሚዎችን ዝርዝር ማዘጋጀት ትችላላችሁ።
በተጨማሪም ጄፍሪ አር. ሆላንድ፣ “አምናለሁ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2013 (እ.አ.አ)፣ 93–95ን ተመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ማቴዎስ 15፥7–9፤ ማርቆስ 7፥6–7።እግዚአብሔር ን በከንፈር ወይም በቃላት በማክበር እና በልባችን ማክበር መሃል ምን ልዩነት አለ?
-
ማቴዎስ 15፥17–20፤ ማርቆስ 7፥18–23።ወደ አፋችን ለሚገባ ነገር የምንጠነቀቀው ለምንድነው? በዚህ ጥቅስ ላይ ኢየሱስ ባስተማረው መሰረት ከአፋችን—እና ከልባችን ስለሚወጣ ነገር ይበልጥ መጠንቀቅ ያለብን ለምንድነው? ልባችንን ንጹህ አድርገን መጠበቅ እንዴት እንችላለን?
-
ማቴዎስ 16፥15–17።እግዚአብሔር “ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ” (ቁጥር 16) እንደሆነ የሚገልጥልን እንዴት ነው? ይህም መገለጥ ከእርሱ ለመቀበል ራሳችንን እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን?
-
ማቴዎስ 16፥13–19፤ 17፤1–9።ልጆችን ስለ ክህነት ቁልፎች ለማስተማር ሽማግሌ ጋሪ ኢ. ስቴቨንሰን መኪናው የተቆለፈበትን ታሪክ መንገር ትችላላችሁ (“ቁልፎቹ የት ናቸው?” የሚለውን ቪድዮ በChurchofJesusChrist.org፣ ላይ ተመልከቱ)። ልጆች ቁልፍ በመጠቀም ቤት፣ መኪና እና ሌሎች ቁልፎችን እንዲከፍቱ ማድረግ ትችላላችሁ። የቤተክርስትያኑን ፕሬዝዳንት ፎቶ ማሳየት እና እንደ ጴጥሮስ ሁሉንም የክህነት ቁልፎች እንደያዘ መመስከር ትችላላችሁ።
2:51 -
ማቴዎስ 17፥20።በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ነቢያት ተራሮችን አንቀሳቅሰዋል (ያዕቆብ 4፥6፤ ሙሴ 7፥13ን ተመልከቱ)። ብዙ ጊዜ ይህ እኛ የምንፈልገው ተአምር አይደለም። ፕሬዝዳንት ኤም. ረስል ባላርድ፤ “እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ያህል ትንሽ እምነት ቢኖረን ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር ስናገለግል የቤተሰብ አባልት፣ የቤተክርስትያን አባላት እና የቤተክርስትያኑ አባል ያልሆኑትን ጨምሮ፥ ጌታ ከፊታችን ባለው ስራ የተስፋ መቁረጥን እና የጥርጣሬን ተራሮች እንድናስወግድ ሊረዳን ይችላል” በማለት አስተምሯል፤ (“ውድ ስጦታዎች ከእግዚአብሔር ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ) 10)። በህይወታችን መነሳት ያለባቸው አንዳንድ ተራሮች ምንድናቸው? እነዚህን ተራሮች ለማንቀሳቀስ እንዲረዳን በእግዚአብሔር ሃይል ላይ እምነት እንዴት ማሳየት እንችላለን።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።
በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “በክርስቶስ አምናለሁ፤” መዝሙሮች፣ ቁጥር 134።