አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 17–23 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 18፤ ሉቃስ 10፦ “የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?”


“ሚያዝያ 17-23 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 18፤ ሉቃስ 10፦ ‘የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) (2022 (እ.አ.አ))

“ሚያዝያ 17-23 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 18፤ ሉቃስ 10፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ደጉ ሳምራዊ

ደጉ ሳምራዊ፣ በዳን በር

ሚያዝያ 17-23 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 18ሉቃስ 10

“የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?”

በጸሎት መንፈስ ማቴዎስ 18 እና ሉዋስ 10ን ስታነቡ እና ስታሰላስሉ ዝግ ላለው የመንፈስ ቅዱስ ማነሳሳት ትኩረት ስጡ። እነዚህ አስተምሮቶች እና ታሪኮች ለእናንተ እንዴት እንደሚሰሩ ይነግራችኋል። የምትቀበሉትን ስሜቶች መዝግቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ጌታን አንድ ጥያቄ ስትጠይቁ ያልጠበቃችሁትን መልስ ልታገኙ ትችላላሁ። ባልንጀራዬ ማነው? የእናንተ እርዳታ እና ፍቅር የሚያስፈልገው ሁሉ። በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው? ህጻን የበደለንን ሰባት ጊዜ ይቅር ማለት በቂ ነውን? አይደለም፥ ሰባ ጊዜ ሰባት ጊዜ ይቅር ማለት አለብን። (ሉቃስ 10፥29–37ማቴዎስ 18፥4፣ 21–22ን ተመልከቱ)። ከጌታ ያልተጠበቁ መልሶች የምናስብበትን፣ የሚሰማንን እና ድርጊታችንን እንድንቀይር ይጋብዙናል። ከጌታ በእውነት መማር ስለምትፈልጉ የእርሱን ፈቃድ የምትሹ ከሆነ ከእርሱ ጋር ወደ ዘላለማዊ ህይወት የሚመራውን አኗኗር ያስተምራችኋል።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማቴዎስ 18፥21–35

ከጌታ ይቅርታን ለመቀበል ሌሎችን ይቅር ማለት አለብኝ።

ጴጥሮስ ሰባት ጊዜ ይቅር ማለት እንዳለበት ያነሳው ሃሳብ በቸርነት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ኢየሱስ ከፍ ያለን ህግ አስተማረ። “እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም” (ቁጥር 22) የሚለው ምላሽ ስለ ቁጥሮች ሳይሆን እንደ ክርስቶስ አይነት የይቅርባይነት ባህርይ እንድናዳብር ለማስተማር ነው። ምህረት የሌለው ባርያን ምሳሌ ስታነቡ የእግዚአብሔር ምህረት እና ርህራሄ የተሰማችሁ ጊዜን አሰላስሉ። ከእናንተ ምህረት ወይም ርህራሄ ሊሰማው የሚገባ ሰው አለ?

ሽማግሌ ዴቪድ ኢ. ሶረንሰን ይህን ጠቃሚ ማስጠንቀቅያ ሰጥቷል፤ “የጎዳንን ባልንጀራን ይቅር ማለት ቢገባንም ይህ ጉዳት እንዳይደገም ለመከላከል ገንቢ በሆነ መልኩ መስራት አለብን። … ይቅርታ ክፉን እንድንቀበል ወይም እንድንችል አይጠይቅም። … ነገር ግን ሃጥያትን ስንዋጋ ጥላቻ ወይም ንዴት ሃሳባችንን እና ተግባራችንን እንዲቆጣጠር መፍቀድ የለብንም (“ይቅርታ ምሬትን ወደ ፍቅር ይቀይራል፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2003 (እ.አ.አ)፣ 12)።

ሉቃስ 10፥1-20

ሰባዎቹ እነማን ናቸው?

በብሉይ ኪዳን ጊዜ የነበረውን ምስረታ በመከተል (ዘጸአት 24፥1ዘሁልቁ 11፥16ን ተመልከቱ) ኢየሱስ ክርስቶስ ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት በተጨማሪ ስለእርሱ እንዲመሰክሩ፣ ወንጌልን እንዲሰብኩ፣ እና በእርሱ ስራ እንዲረዱት “ሰባዎቹን.[ጠራቸው]”። ይህ በተመለሰው ቤተክርስትያኑ ይቀጥላል። ሰባዎቹ የተጠሩት ለአለም ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ተልዕኳቸው ላይ አስራ ሁለቱን እንዲያግዟቸው ነው።

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥25-26፣ 33-34፣ 97ን ተመልከቱ።

ሉቃስ 10፥25–37

ዘላለማዊ ህይወት ለማግኘት እግዚአብሔር ን እና ባልንጀራዬን እንደራሴ መውደድ አለብኝ።

“የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?” እና “ባልንጀራዬስ ማን ነው?” ለሚሉ ሁለት ጥያቄዎች የደጉ ሳምራዊ ምሳሌ የኢየሱስ መልስ እንደሆነ ማስታወስ ጠቃሚ ነው። (ሉቃስ 10፥25፣ 29)። ይህንን ምዕራፍ በምታነቡበት ጊዜ እነዚህን ጥያቄዎች በአዕምሯችሁ ያዙ። ምን መልሶችን ታገኛላችሁ?

በኢየሱስ ዘመን፥ በአይሁዶች እና በሳምራውያን መካከል የነበረው ጥላቻ ለምዕተ አመታት የዘለቀ ነበር። ሳምራውያን ከአህዛብ ጋር የተጋቡ በሰማርያ ይኖሩ የነበሩ የአይሁድ ተወላጆች ነበሩ። ሳምራውያን ከአህዛብ ጋር በነበራቸው ግንኙነት ምክንያት ራሳቸውን የበከሉ እና ከሃዲ እንደሆኑ አድርገው አይሁዳውያን ያስባሉ። በሰማርያ አቋርጦ ላለማለፍ አይሁዳውያን ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ከመንገድ ወተው ይጓዙ ነበር። (በተጨማሪም ሉቃስ 9፥52–5417፥11–18ዮሐንስ 4፥98፥48ን ትተመልከቱ።)

አዳኙ በአይሁዶች የተጠላን ሳምራዊን የርህራሄ እና ባልንጀራን የመውደድ ምሳሌ አድርጎ የመረጠው ለምን ይመስላችኋል? ይህ ምሳሌ ምን እንድታደርጉ ያነሳሳችኋል?

በተጨማሪም ሞዛያ 2፥17፤ “የደጉ ሳምራዊ ምሳሌ” እና “ደጉ ሳምራዊ” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

5:11

ሉቃስ 10፥38–42

ወደ ዘላለማዊ ህይወት የሚመሩ ምርጫዎችን በየቀኑ በመምረጥ “መልካም ዕድልን” እንመርጣለን።

ሉቃስ 10፥38–42፣ ላይ ኢየሱስ ማርታ ጊዜዋን ስለምታሳልፍበት መንገድ በተለየ መልኩ እንድታስብ በትህትና ጋበዛት። እነዚህ ጥቅሶች ከጠቀሰች በኋላ እህት ካሮል ኤፍ. ማኮንኪ፤ “ቅዱስ መሆን ከፈለግን፥ በእስራኤል ቅዱስ እግር ስር መቀመጥ እና ለቅድስና ጊዜ መስጠትን መማር አለብን። ስልካችንን፣ ማብቅያ የሌለውን የስራ ዝርዝራችንን እና አለማዊ ጭንቀታችንን እንተዋለን? ጸሎት፣ ጥናት እና የእግዚአብሔር ን ቃል ማክበር የእርሱን የሚያነጻ እና የሚፈውስ ፍቅር ወደ ነፍሳችን ይጋብዛል። በእርሱ የተቀደሰ እና የሚያነጻ መንፈስ ለመሞላት ቅዱስ ለመሆን ጊዜን እንውሰድ (“የቅድስና ውበት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ) 11)። ጊዜያችሁን መልካም ነገር እያደረጋችሁም ቢሆን—እንዴት እያሳለፋችሁ እንደሆነ መፈተሽ ሊኖርባችሁ ይችላል። የናንተን ትኩረት የሚሻ ይበልጥ “[የሚያስፈልግ] (ቁጥር 42) ነገር አለ?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 18፥1-11ኢየሱስ እንደ ህጻናት እንድንሆን የሚፈልገው ለምንድነው? ይበልጥ እንደ ክርስቶስ እንድንሆን እንድናድግ የሚረዱን የህጻናት ባህሪዎች ምንድናቸው? (ሞዛያ 3፥19ን ተመልከቱ)።

ኢየሱስ ከህጻናት ጋር

ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ እንደ ህጻናት እንዲሆኑ ይፈልጋል።

ማቴዎስ 18፥15ማቴዎስ 18፥15 ላይ ያለውን ምክር በቤተሰብ ግንኙነቶቻችን ላይ እንዴት መተግበር እንችላለን? ይህን ማድረግ ቤተሰባችንን እንዴት ይባርካል?

ማቴዎስ 18፥21-35እነዚህ ምሳሌዎች ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ያስተምሩናል? ሌሎችን መንከባከብ እንዳለብን እንዴት ያሳተምረናል?

ሉቃስ 10፥25–37የቤተሰብ አባላት የትወና ልብስ በመልበስ እና ይህን ምሳሌ በመተወን ሊዝናና ይችላል። አንዳንዴ በዚህ ምሳሌ ላይ እንዳሉ ሰዎች የምንሆነው እንዴት ነው? አዳኙ እንደ ደጉ ሳምራዊ የሆነው እንዴት ነው? እንደ ደጉ ሳምራዊ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

በዚህ ምሳሌ ላይ ያሉ እውነቶችን የሚደግፉ ዝማሬዎችን ወይም የህጻናት መዝሙሮችን ለመዘመር ማሰብ ትችላላችሁ። አንድ ምሳሌ “ጌታ፣ እከተልሃለሁ” (መዝሙር፣ ቁጥር 220) ነው፣ ነገር ግን ሌሎች ብዙ አሉ። የቤተሰብ አባላት መዝሙር መፈለግ እና እንዴት ከምሳሌው ጋር እንደሚገናኝ ማስረዳት ይችላሉ።

ሉቃስ 10፥38–42መንፈሳዊ ነገሮችን በቤተሰባችሁ መርሃ ግብር ላይ ማካተት ከባድ ነው? የማርታ እና የማርያም ታሪክ የቤተሰብ ስብሰባ ወይም ይህን በተሻለ መልኩ ለማድረግ የቤተሰብ ምሽት ሊያነሳሳ ይችላል። እንደ ቤተሰብ “መልካም እድልን” የመምረጫ መንገዶች ዝርዝር ማውጣት ትችላላችሁ (ሉቃስ 10፥42)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “ኢየሱስ ሁሉንም ውደዱ ብሏል፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 61።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ፍቅር የተሞላበት አካባቢን አሳድጉ። የቤተሰብ አባላት እርስ በርስ ያላቸው ስሜትና አንዳቸው ሌላኛውን የሚመለከቱበት መንገድ በቤት ውስጥ ያለውን መንፈስ ይወስነዋል። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ተወዳጅ፣ ክብር ያለበት ቤት እንዲፈጠር የበኩሉን አስተዋጽዎ እንዲያበረክትና ሁሉም ልምዱን እንዲያካፍል፣ ጥያቄን እንዲያነሳና ምስክርነትን መስጠት የሚያስችል እንዲሆን የበኩላቸውን እንዲያረጉ እርዷቸው። (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 15ን ይመልከቱ።)

ክርስቶስ ከማርያም እና ከማርታ ጋር

ክርስቶስ በማርያም እና ማርታ ቤት፣ በዋልተር ሬን