አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ግንቦት 22–28 (እ.አ.አ)። የጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፤ ማቴዎስ 24–25፤ ማርቆስ12–13፤ ሉቃስ 21፦ “የሰው ልጅ … [ይመጣል]”


“ግንቦት 22–28 (እ.አ.አ)። የጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፤ ማቴዎስ 24–25፤ ማርቆስ12–13፤ ሉቃስ 21፤ ‘የሰው ልጅ … [ይመጣል]’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 22–28 (እ.አ.አ)። የጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፤ ማቴዎስ 24–25፤ ማርቆስ12–13፤ ሉቃስ 21፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ዳግም ምፅዓት

ዳግም ምፅዓት፣ በሃሪ አንደርሰን

ግንቦት 22–28 (እ.አ.አ)

ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1ማቴዎስ 24–25ማርቆስ 12–13ሉቃስ 21

“የሰው ልጅ… [ይመጣል]”

ጆሴፍ ስሚዝ— ማቴዎስ 1ማቴዎስ 24–25ማርቆስ 12–13፤ እና ሉቃስ 21ን ስታነቡ “እነዚህ ምዕራፎች ለእኔ፣ ለቤተሰቤ እና ለጥሪዬ ምን መልዕክት አላቸው?” በማለት ልትጠይቁ ትችላላችሁ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ታላቁ የኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ፥ የአይሁድ ህዝብ መንፈሳዊ እና ባህላዊ ማእከል “ድንጋይ በድንጋይ ላይ [ሳይቀር]” ፈጽሞ ይጠፋል የሚለውን የእርሱን ትንቢት አስገራሚ ሆኖ አግኝተውት ይሆናል። ደቀመዛሙርቱ የበለጠ ለማወቅ ፈለጉ። “እነዚህ ነገሮች መች ይሆናሉ?” በማለት ጠየቁ። “የመምጣትህስ ምልክቶች ምንድናቸው?” (የጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፥2–4)። የአዳኙ መልስ በ70 ዓመተ ምህረት የተፈጸመው ትንቢት—የኢየሩሳሌም ታላቅ ጥፋት—ከእርሱ ዳግም ምጽዓት ጋር ሲነጻጸር ያነሰ እንደሚሆን ገለጠላቸው። በኢየሩሳሌም ካለው ቤተመቅደስ ይልቅ ቋሚ የሚመስሉ ነገሮችም ጊዚያዊ ይሆናሉ—ፀሃይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ሃገሮች እና ባህር። “የሰማይ ሃይላት [እንኳን] ሳይቀሩ ይንቀጠቀጣሉ” (ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ1፥33)። በመንፈስ ያወቅን ከሆንን ይህ ሁከት እምነታችንን በእውነት ቋሚ በሆነ ነገር ላይ እንድናደርግ ሊያስተምረን ይችላል። ኢየሱስ ቃል እንደገባው “ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም። … ቃሌን የሚያከማች ሁሉ አይስትም” (ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፥35፣ 37)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

የጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ ምንድን ነው?

በታላቅ ዋጋ እንቁ ላይ የሚገኘው የጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ የ ማቴዎስ 23 የመጨረሻ ቁጥር እና የ ማቴዎስ 24፣ ሙሉ ምዕራፍ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ነው። የጆሴፍ ስሚዝ በመንፈስ የተመራ ክለሳ ጠፍተው የነበሩ ውድ እውነቶችን መልሷል። ቁጥሮች 12–21 ስለ ጥንት ኢየሩሳሌም ጥፋት የሚያወራ ሲሆን፤ ቁጥሮች 21–55 ደግሞ ስለ ኋለኛው ቀን ትንቢቶችን ይይዛል።

የጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፥21–37ማርቆስ 13፥21–37ሉቃስ 21፥25–38

የአዳኙ ዳግም ምፅአት ትንቢቶች ወደፊትን በእምነት እንድጋፈጥ ይረዱኛል።

ወደ ኢየሱስ ክርስቶሰ ዳግም ምጽአት ስለሚመሩ ክስተቶች ማንበብ የሚረብሽ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ኢየሱስ ስለእነዚህ ክስተቶች ሲተነብይ ለደቀመዛሙርቱ “አትረበሹ” (የጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፥23) በማለት ተናግሮ ነበር። ስለ ጦርነቶች፣ የምድር መንቀጥቀጥ፣ ማታለያዎች እና ድርቅ ስትሰሙ “[አለመረበሽ]” እንዴት ትችላላችሁ? እነዚህን ቁጥሮች ስታነቡ ስለሚከተሉት ጥያቄዎች አስቡ። የምታገኙትን ማንኛውም አጽናኝ ምክር ምልክት አድርጉ ወይም ልብ በሉ።

በተጨማሪም በወንጌል ርዕሶች “የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ትጻት፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

የጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ1፥26–27፣ 38–55ማቴዎስ 25፥1–13ሉቃስ 21፥29–36

ለአዳኙ ዳግም ምፅዓት ሁል ጊዜም ዝግጁ መሆን አለብኝ።

እግዚአብሄር የሰው ልጅ የሚመጣበት “ቀኒቱንና ሰዓቲቱን” (ማቴዎስ 25፥13) አልገለጠም። ነገር ግን ያ ቀን “በድንገት” (ሉቃስ 21፥34) እንዲመጣብን አይፈልግም፤ ስለዚህ እንዴት መዘጋጀት እንዳለብን ምክር ሰጥቶናል።

እነዚህን ቁጥሮች ስታነቡ አዳኙ ሁል ጊዜም እንድንዘጋጅ ለማስተማር የተጠቀመውን ምሳሌዎችን እና ሌሎች ንጽጽሮችን ለዩ። ከእነርሱ ምን ትማራላችሁ? ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል?

ለአዳኙ ዳግም ምጽአት አለም እንዲዘጋጅ እንድትረዱ አዳኙ እንዴት እንደሚፈልግ ማሰብ ትችላላችሁ። አዳኙ ሲመጣ ለመቀበል ዝግጁ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ይሰማችኋል? የሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን መልዕክት “ለጌታ መመለስ መዘጋጀት” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 81–84) ይህን እንድታሰላስሉ ሊረዳችሁ ይችላል።

በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን “ወደፊትን በእምነት ተቀበሉ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ) 73–76ን ተመልከቱ።

ማቴዎስ 25፥14–30

የሰማይ አባት ስጦታዎቹን በብልሃት እንድጠቀም ይፈልጋል።

በአዳኙ ምሳሌ “መክሊት” የሚወክለው ገንዘብን ነው። ነገር ግን የመክሊቱ ምሳሌ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም በረከቶቻችንን እንዴት እየተጠቀምን እንደሆነ እንድናሰላስል ያነሳሳናል። ይህንን ምሳሌ ካነበባችሁ በኋላ የሰማይ አባት የሰጣችሁን አንዳንድ በረከቶች እና ሃላፊነቶች መዘርዘር ትችላላችሁ። በእነዚህ በረከቶች ምን እንድናደርግ ይጠብቃል? እነዚህን ስጦታዎች ይበልጥ በብልሃት እንዴት ነው መጠቀም የምትችሉት?

ማቴዎስ 25፥31–46

እኔ ሌሎችን ሳገለግል ጌታን እያገለገልኩ ነው።

ጌታ ህይወታችሁን እንዴት እንደሚዳኝ ማወቅ ከፈለጋችሁ የበጎችን እና የፍየሎችን ምሳሌ አንብቡ። የተቸገሩትን መንከባከብ የእግዚአብሄርን “መንግስት ለመውረስ” እንዴት ያዘጋጃችኋል?

ይህ ምሳሌ በማቴዎስ 25፣ ላይ ካሉ ሌሎች ምሳሌዎች ጋር እንዴት ይመሳሰላል? ሶስቱም በአንድነት የሚያመሳስላቸው ምን መልዕክት አላቸው?

በተጨማሪም ሞዛያ 2፥175፥13ን ተመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስቤተሰባችሁ ይህንን ምዕራፍ ማሰስ እንዲችል ለዳግም ምጻቱ እንዴት መዘጋጀት እንዳለብን የሚያሳዩ የአዳኙን አስተምሮቶች እንዲፈልጉ ጋብዟቸው (ለምሳሌ ቁጥሮች 22–23፣ 29–30፣ 37፣ 46–48ን ተመልከቱ)። ይህን ምክር ለመከተል ምን ማድረግ እንችላለን? ቤተሰባችሁ “ዳግም ሲመጣ” (የልጆች መዝሙር፣ 82–83) የሚለውን በመዘመር ሊደሰት እና የአዳኙ ዳግም ምጽአት ምን ሊመስል እንደሚችል የሚያስቡትን እንዲስሉ በማድረግ ሊደሰት ይችላል።

የጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፥22፣37የእግዚአብሔርን ቃል ማከማቸት ማለት ምን ማለት ነው? ይህን በግል እና እንደ ቤተሰብ ማድረግ እንዴት እንችላለን? እንዲህ ማድረጋችን እንዳንታለል የሚረዳን እንዴት ነው?

ማቴዎስ 25፥1–13 ማቴዎስ 25፥1–13ን ለማብራራት ከዚህ ዝርዝር ጋር ተያይዘው የሚመጡትን የአሥሩን ደናግልን ሥዕሎች መጠቀም ትችላላችሁ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተገለጹት በስዕሉ ላይ ምን ዝርዝሮች እናያለን?

በዘይት ጠብታዎች ቅርፅ ወረቀት ቆርጣችሁ በቤታችሁ ዙሪያ ልትደብቋቸው ትችላላችሁ። ጠብታዎቹን ከቁሶች ጋር ለምሳሌ ከቅዱሳን መጻህፍት ወይም ከቤተመቅደስ ምስል ጋር ልታያይዟቸው ትችላላችሁ። የቤተሰብ አባላት ጠብታዎቹን ሲያገኙ እንደዚህ ነገሮች ለዳግም ምጽአቱ እንዴት እንድንዘጋጅ እንደሚረዱን መወያየት ትችላላችሁ።

ማርቆስ 12፥38–44ሉቃስ 21፥1–4እነዚህ ጥቅሶች በኩራቶችን ክርስቶስ እንዴት እንደሚያይ ያስተምሩናል? ቤተሰባችሁን አስራት እንዴት እንደሚከፈል እና የጾም በኩራት እንዴት እንደሚሰጥ አስተምሩ። እነዚህ ስጦታዎች የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት እንዴት ይረዳሉ? “[ያለንን… ሁሉ” ለጌታ የምንሰጥባቸው ሌሎች መንገዶች ምንድናቸው? (ማርቆስ 12፥44)።

ምስል
አንዲት ሴት ሳንቲም ሳጥን ውስጥ እየጨመረች

የመበለቷ ሳንቲም፣ በሳንድራ ራስት

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦“ዳግም ሲመጣ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 82–83።

የግል ጥናትን ማሻሻል

አካባቢያችሁን አዘጋጁ። “እውነት የመሰማት እና የመማር ብቃታችንን ላይ አካባብያችን ትልቅ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 15)። የመንፈሱ ተፅዕኖ እየተሰማችሁ ቅዱሳን መጽሐፍትን ለማጥናት የምትችሉበትን ቦታ አግኙ። የሚያነሳሳ መዝሙር እና ስዕሎች መንፈስን ሊጋብዙ ይችላሉ።

ምስል
ሴቶች መብራት ይዘው

አምስቱ ብልሆች ነበሩ፣ በዋልተር ሬን

አትም