አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ግንቦት 29–ሰኔ 4 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 26፤ ማርቆስ 14፤ ዮሐንስ 13፦ “[ለመታሰቢያ]”


“ግንቦት 29–ሰኔ 4 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 26፤ ማርቆስ 14፤ ዮሐንስ 13፤ ‘[ለመታሰቢያ]’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ግንቦት 29–ሰኔ 4 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 26፤ ማርቆስ 14፤ ዮሐንስ 13፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

የመቸረሻው እራት

እኔን በማሰብ፣ በዋልተር ሬን

ግንቦት 29–ሰኔ 4 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 26ማርቆስ 14ዮሐንስ 13

“[ለመታሰብያ]”

ማቴዎስ 26ማርቆስ 14፤ እና ዮሐንስ 13፣ ላይ የተጠቀሱ ትዕይንቶችን ስታነቡ ለሚያሳድርባችሁ ማንኛውም ስሜት ትኩረት ስጡ፣ በተለይም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት እና መሰጠታችሁን ጥልቅ የሚያደርጉ ስሜቶች።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ኢየሱስ ከመሞቱ አንድ ቀን በፊት ደቀመዛሙርቱ እርሱን የሚያስታውሱበትን አንድ ነገር ሰጣቸው። “እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ … ደሜ ይህ ነው” አላቸው (ማቴዎስ 26፥26–28)።

ይህ የሆነው አብዛኛዎቻችን ልናየው በማንችለው ቦታ እና ጥቂቶቻችን ብቻ በምንረዳው ቋንቋ ከ2,000 አመታት በፊት ነው። ነገር ግን አሁን በየእሁዱ በመሰብሰቢያ ቦታዎቻችን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲተገብሩ የተፈቀደላቸው ክህነት መሪዎች በአንድ ወቅት እርሱ ያደረገውን ያደርጋሉ። እነሱ ዳቦ እና ውሃ በመውሰድ ይባርኩታል፥ ለእያንዳንዳችን፣ ለእርሱ ደቀመዛሙርት ይሰጡናል። ቀላል ተግባር ነው—ዳቦ እንደመብላት እና ውሃ እንደመጠጣት ያለ ቀላል፣ ይበልጥ መሰረታዊ ነገር ሊኖር ይችላል? ነገር ግን ያ ዳቦ እና ውሃ ለኛ የተቀደሱ ነገሮች ናቸው ምክንያቱም እርሱን እንድናስታውሰው ስለሚረዱን ነው። እነሱ “እኔ ፈጽሞ አልረሳውም” የምንልበት መንገድ ናቸው “ስለ አስተምሮቶቹ እና ስለ ህይወቱ ያነበብኩትን አልረሳም” ብቻ አይደለም። ይልቁንም “ለእኔ ያደረገውን በፍጹም አልረሳም” እያልን ነው። “ለእርዳታ ስጮህ እንዴት እንዳዳነኝ በፍጹም አልረሳም” እናም “የገባነውን ቃል ኪዳን—ለእኔ ያለውን ቁርጠኝነት እና ለእሱ ያለኝን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አልረሳውም”

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማቴዎስ 26፥6–13ማርቆስ 14፥3–9

“ሥጋዬን [ለመቀባት መጣች]”።

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተገለጸችው ሴት በትሕትና የአምልኮ ድርጊት ኢየሱስ ማን እንደ ሆነ እና ምን ሊያደርግ እንደሆነ እንዳወቀች አሳይታለች (ማቴዎስ 26፥12ን ይመልከቱ)። ድርጊቶቿ ለአዳኙ በጣም ትርጉም ያለው የሆነው ለምን ይመስላችኋል? (ቁጥር 13ን ተመልከቱ) ስለ ሴቲቱ እና ስለ እምነቷ የሚያስደንቃችሁ ምንድን ነው? የእሷን ምሳሌ እንዴት መከተል እንደምትችሉ አሰላስሉ።

በተጨማሪም ዮሐንስ 12፥1–8ን ተመልከቱ።

ማቴዎስ 26፥20–22ማርቆስ 14፥17–19

“ጌታ ሆይ፥ እኔ እሆንን?”

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጌታን ከጠየቁት ጥያቄ ስለ ደቀመዛሙርቱ ምን ትማራላችሁ? ለምን የጠየቁ ይመስላችኋል? ጌታን “እኔ እሆንን?” ብላችሁ እንዴት እንደምትጠይቁ አስቡ።

በተጨማሪም ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “ጌታ ሆይ፥ እኔ እሆንን?፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2014 (እ.አ.አ)፣ 56–59ን ተመልከቱ።

ማቴዎስ 26፥26–29ማርቆስ 14፥22–25

ቅዱስ ቁርባን አዳኙን ማስታወሻ እድል ነው።

አዳኙ ቅዱስ ቁርባንን ለደቀ መዛሙርቱ ባስተዋወቀ ጊዜ፣ ምን ሀሳቦች እና ስሜቶች ይኖሯቸዋል ብላቹ ታስባላችሁ? በማቴዎስ 26፥26–29 እና ማርቆስ 14፥22–25፣ ላይ ስላጋጠሟቸው ልምዶች ስታነቡ ይህን አስቡ። ኢየሱስ እርሱን እንድናስታውስ ይህን መንገድ የመረጠው ለምን ይመስላችኋል? በቅዱስ ቁርባን ወቅት ያገጠማችሁን ማሰላሰል ትችላላችሁ። ልምዳችሁን ይበልጥ የተቀደሰ እና ትርጉም ያለው እንዲሆን ማድረግ ያለባችሁ ነገር አለ?

እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ እና ካሰላሰላችሁ በኋላ፣ ስለ አዳኙ ለማስታወስ የተነሳሳችሁትን አንዳንድ ነገሮች ልትጽፉ ትችላላችሁ። በቀጣይ ጊዜ ቅዱስ ቁርባን ስትቀበሉ እነዚህን ነገሮች ደግማችሁ ማየት ትችላላችሁ። በሌሎች ጊዜያትም “ሁልጊዜ እርሱን [ለማስታወስ]” ልታጠኗቸው ትችላላችሁ (ሞሮኒ 4፥3)።

በተጨማሪም ሉቃስ 22፥7–393 ኔፊ 18፥1–13ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥76–79፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “ቅዱስ ቁርባን፣” topics.ChurchofJesusChrist.org፤ “ሁል ጊዜ እርሱን እንዲያስታውሱት” (ቪድዮ) ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

ዮሐንስ 13፥1፟–17

አዳኙ በትህትና ሌሎችን የማገልገል ምሳሌያችን ነው።

በኢየሱስ ዘመን የሌላ ሰውን እግር ማጠብ የአገልጋዮች ተግባር እንጂ የመሪዎች አልነበረም። ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ መምራት እና ማገልገል ምን ማለት እንደሆነ በተለየ መንገድ እንዲያስቡ ፈለገ። በዮሐንስ 13፥1–17፣ ላይ ካለው ከአዳኙ ቃላት እና ተግባር ምን መልዕቶችን ታገኛላችሁ? በእናንተ ባህል የሌሎችን እግር ማጠብ የተለመደ የማገልገል መንገድ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን የአዳኙን የትህትና አገልግሎት ምሳሌ ለመከተል ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ።

በዚህ ከሐዋርያቱ ጋር በነበረው ቅዱስ ጊዜ ኢየሱስ ያወቃቸውን እና የተሰማውን ነገሮች ማስተዋልም አስደሳች ሊሆን ይችላል (ቁጥር 1 እና 3ን ተመልከቱ)። እነዚህ መረዳቶች ስለ አዳኙ እንድትረዱ ምን ይረዷችኋል?

በተጨማሪም ሉቃስ 22፥24–27

ዮሐንስ 13፥34–35

ለሌሎች ያለኝ ፍቅር እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ስለመሆኔ ማሳያ ምልክት ነው።

አስቀድሞ “ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ” የሚል ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር (ማቴዎስ 22፥39)። አሁን ግን “አዲስ ትእዛዝ” ሰጠ። ኢየሱስ እኛን እንደወደደን ሌሎችን መውደድ ምን ማለት ይመስላችኋል? (ዮሐንስ 13፥34ን ተመልከቱ)።

እናንተ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደሆናችሁ ሌሎች ሰዎች እንዴት ማወቅ እንደሚችሉም አሰላስሉ። ፍቅር እንደ ክርስቲያን መገለጫችሁ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ ትችላላችሁ?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 26፥26–29ማርቆስ 14፥22–25በየሳምንቱ በቅዱስ ቁርባን ወቅት የቤተሰባችሁ ተሞክሮ ምን ይመስላል? ስለ መጀመሪያው ቅዱስ ቁርባን ማንበብ ስለ ቅዱስ ቁርባን አስፈላጊነት እና ተሞክሯችሁን ማሻሻያ መንገዶች ላይ ውይይት ሊያነሳሳ ይችላል። ቅዱስ ቁርባንን ማሳለፍ (የወንጌል ጥበብ መጽሃፍ፣ ቁጥር 108) የሚለውን ስእል ለማሳየት እና ከቅዱስ ቁርባን በፊት፣ በስነስርዓቱ ወቅት እና በኋላ ምን ማድረግ እንደምትችሉ ሀሳቦችን ለማጋራት አስቡ።

አንዲት ሴት ቅዱስ ቁርባን እየተካፈለች

ቅዱስ ቁርባን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናስታውስ ይረዳናል።

ማቴዎስ 26፥30ኢየሱስ እና ሐዋርያቱ እንዳደረጉት መዝሙርን መዘመርን አስቡ—ምናልባትም የቅዱስ ቁርባን መዝሙር። በዚያን ጊዜ መዝሙር መዘመር ለኢየሱስ እና ለሐዋርያቱ እንዴት በረከት ሊሆን ይችላል? መዝሙሮች ለእኛ በረከት እንዴት ይሆናሉ?

ዮሐንስ 13፥1–17እነዚህን ጥቅሶች በምታነቡበት ጊዜ በዚህ ረቂቅ መጨረሻ ላይ ሥዕሉን ለቤተሰባችሁ ማሳየት ትፈልጉ ይሆናል። አዳኙ በድርጊቱ ምን እውነቶች አስተምሯል? እነዚህን እውነቶች ለመረዳት በሥዕሉ ውስጥ ምን ዝርዝሮች ይረዱናል? ምናልባት የቤተሰብ አባላት በእነዚህ እውነቶች መኖር ደስታን እንዴት እንዳመጣላቸው ሊያጋሩ ይችላሉ (ዮሐንስ 13፥17ን ይመልከቱ)።

ዮሐንስ 13፥34–35እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ሌሎች ሰዎች እንዴት እንደሚያውቁ አብራችሁ ልትወያዩ ትችላላችሁ። አዳኙ ተከታዮቹ እንዴት እንዲታወቁ ይፈልጋል? ለሌሎች ሰዎች ያላቸው ፍቅር የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት እንደሆኑ ስለሚያሳዩ ሰዎች የቤተሰብ አባላት እንዲናገሩ መጠየቅ ትችላላችሁ። እንዲሁም እንደ ቤተሰብ የበለጠ ፍቅርን ማሳየት በምትችሉበት መንገዶች ላይ ልትወያዩ ትችላላችሁ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “አብሩ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 136።

የግል ጥናትን ማሻሻል

አሰላስሉ። ቅዱሳት መጻህፍትን እንደ ሌሎች የንባብ ጽሑፎች እንዲሁ በግዴለሽነት ካነበብን ሊያመልጡን የሚችሉ መንፈሳዊ ትርጉሞች አሏቸው። አንድን ምዕራፍ ለመጨረስ አትቸኩሉ። ስለምታነቡት ነገር በጥልቀት ለማሰብ ጊዜ ውሰዱ።

ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር እያጠበ

በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ፣ በጄ. ከርክ ሪቻርድስ