አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ሰኔ 12–18 (እ.አ.አ)። ሉቃስ 22፤ ዮሐንስ 18፦ “የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ”


“ሰኔ 12–18 (እ.አ.አ)። ሉቃስ 22፤ ዮሐንስ 18፦ ‘የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 12–18 (እ.አ.አ)። ሉቃስ 22፤ ዮሐንስ 18፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ክርስቶስ እና ደቀ መዛሙርት በጌቴሴማኒ

የጌቴሴማኒ ጫካ፣ በዴረክ ሄግስትድ

ሰኔ 12–18 (እ.አ.አ)

ሉቃስ 22ዮሐንስ 18

“የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ”

በዚህ ሳምንት ጊዜ ወስዳችሁ ሉቃስ 22 እና ዮሐንስ 18 ን አንብቡ። ስለሚያስፈልጋችሁ ነገር አሰላስሉ እናም ጸልዩ። ይህን ማድረጉ ቅዱሳት መጻህፍት እውነት መሆናቸውን መንፈስ በልባችሁ እንዲመሰክር እድል ሊሰጥ ይችላል።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥቃይ ሦስት ስጋ ለባሽ ምስክሮች ብቻ ነበሩት—እነሱም አብዛኛውን ሰአት ተኝተው አሳልፈዋል። ምንም እንኳን በዚያን ጊዜ በሕይወት ያለ ማንም ሰው ምን እየተካሄደ እንደሆነ ባያውቅም፥ በዚያ የአትክልት ስፍራ እና በኋላ በመስቀል ላይ፣ ኢየሱስ የኖረን የእያንዳንዱን ሰው ኃጢአቶችን፣ ሕመሞችን እና ሥቃዮችን በራሱ ላይ ወሰደ። ለዘላለም እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ክስተቶች ብዙውን ጊዜ ያለ ብዙ ዓለማዊ ትኩረት ያልፋሉ። እግዚአብሔር አብ ግን ያውቀዋል። የታማኝ ልጁን ልመና እንዲህ ሲል ሰማ፤ “ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ። ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታ መልአክ ታየው” (ሉቃስ 22፥42–43)። ይህንን ከራስ ወዳድነት ነጻ የሆነ እና የመገዛት ድርጊት ለመመልከት እኛ እዚያ ባንኖርም፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምስክሮች ነን። ንስሐ በገባን እና የኃጢአታችንን ይቅርታ ባገኘን ቁጥር፣ የአዳኙን የማጠናከሪያ ኃይል በተሰማን ቁጥር፣ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ውስጥ ስለተከናወነው እውነታ መመስከር እንችላለን።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሉቃስ 22፥31–34፣ 54–62ዮሐንስ 18፥17–27

መለወጥ ቀጣይ ሂደት ነው።

ጴጥሮስ ከአዳኙ ጋር ስላጋጠመው ልምዶች አስቡ—እሱ ያየውን ተአምራት እና የተማረውን ትምህርት። ታዲያ አዳኙ ለጴጥሮስ “አንተም በተመለስህጊዜ ወንድሞችህን አጽና“ ያለው ለምንድን ነው? (ሉቃስ 22፥32፤ ሰያፍ ፊደላት ተጨምረዋል)። ይህን ስታሰላስሉ፣ ሽማግሌ ዴቪድ ኤ ቤድናርን ምስክርነት በማግኘት እና በእውነት በመለወጥ መካከል ስላለው ልዩነት ያስተማረውን ማሰብ ሊረዳ ይችላል (“ወደ ጌታ መቀየር፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2012 (እ.አ.አ) 106–9ን ተመልከቱ)።

ሉቃስ 22፥31–34፣ 54–62 ውስጥ ስለ ጴጥሮስ ተሞክሮዎች ስታነቡ (በተጨማሪም ዮሐንስ 18፥17–27ን ተመልከቱ) ስለራሳችሁ መለወጥ አስቡ። እናንተ ልክ እንደ ጴጥሮስ፣ “ወደ ወኅኒም ወደ ሞትም [ከአዳኙ] ጋር ለመሄድ [ዝግጁ]” እንደሆናችሁ ሆኖ ቁርጠኝነት ተሰምቷችሁ ያውቃልን? (ሉቃስ 22፥33)። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ስሜቶች ለምን ይደበዝዛሉ? አዳኙን ለመካድ ወይም ስለ እርሱ ለመመስከር ዕለታዊ እድሎች አሉ፤ ስለ እርሱ በየቀኑ ምስክር ለመሆን ምን ታደርጋላችሁ? ከጴጥሮስ ተሞክሮ ምን ሌሎች ትምህርቶች ትማራላችሁ?

አዲስ ኪዳንን ማንበባችሁን በምትቀጥሉበት ጊዜ፣ የጴጥሮስን ቀጣይነት ለውጥ ማስረጃ ተመልከቱ። እንዲሁም “ወንድሞችህን አጽና” (ሉቃስ 22፥32የሐዋርያት ስራ 3–4ን ተመልከቱ) የሚለውን የጌታን ትእዛዝ የተቀበለባቸውን መንገዶች ልብ በሉ።

ማርቆስ 14፥27–31ን ተመልከቱ።

ሉቃስ 22፥39–46

አዳኙ በጌቴሴማኒ ስለ እኔ መከራን ተቀበለ።

ፕሬዘደንት ረስል ኤም. ኔልሰን “ስለ አዳኙ እና ስለኃጢያት ክፍያ መስዋእቱ ለመማር ጊዜ እንድንወስድ” ይጋብዘናል (“የኢየሱስ ክርስቶስን ሀይል ወደ ህይወታችን መሳብ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 40)።

የፕሬዝዳንት ኔልሰን ግብዣን ለመቀበል ምን እንደምታደርጉ አስቡ። በእነዚህ ጥቅሶች እንደተገለጸው በጌቴሴማኒ የአዳኙን ስቃይ በጸሎት በማሰላሰል እና ወደ አእምሮ የሚመጡትን ግንዛቤዎች እና ጥያቄዎችን በመጻፍ መጀመር ትችላላችሁ።

ለአዳኙ እና ለኃጢያት ክፍያው ጥልቅ ጥናት፣ ለእነዚህ ላሉት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትን ለመፈለግ ሞክሩ።

በጌቴሴማኒ ውስጥ ስለተፈጠረው ስትማሩ፣ ጌቴሴማኒ የወይራ ዛፎች የአትክልት ቦታ እንደነበረ እና ከወይራ ፍሬ ለመብራት እና ለምግብ እንዲሁም ለፈውስ የሚያገለግል ዘይት ለመጭመቅ እና ለማውጣት የሚያገለግል የወይራ መጭመቂያ ማካተቱን ማወቅ አስደሳች ሊሆን ይችላል (ሉቃስ 10፥34ን ተመልከቱ )። የወይራ ዘይት የማውጣት ሂደት አዳኙ በጌቴሴማኒ ያደረገልንን እንዴት ሊያመለክት ይችላል? ለአንዳንድ ሀሳቦች የሽማግሌ ድ. ቶድ ክርስቶፈርሰንን መልዕክት “በፍቅሬ ኑሩ” (ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 50–51)ን ተመልከቱ።

በተጭዕማሪም ማቴዎስ 26፥36–46ማርቆስ 14፥32–42ን ተመልከቱ።

ዮሐንስ 8፥28–38

የአዳኙ “[መንግሥት] ከዚህ ዓለም አይደለችም።”

የፖለቲካ መሪ እንደመሆኑ ጴንጤናዊው ጲላጦስ የዚህን ዓለም ኃይል እና መንግሥታት ያውቅ ነበር። ኢየሱስ ግን በብዙ ስለሚለይ የመንግሥት አይነት ተናገረ። ስለ አዳኙ ሕይወት ያነበባችሁትን መለስ ብላችሁ በማሰብ፣ የእሱ “[መንግሥት] ከዚህ ዓለም [እንዳልሆነች]” ምን ማስረጃ ታያላችሁ? (ዮሐንስ 18፥36)። ይህንን ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ኢየሱስ ለጲላጦስ ስለተናገረው ነገር ሌላ ምን ጎልቶ ይታያችኋል?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሉቃስ 22፥31–32ጴጥሮስ ኢየሱስ ለእሱ እና ለእምነቱ እንደ ጸለየ ሲያውቅ ምን ተሰምቶት ሊሆን ይችላል? “[እምነታቸው] እንዳይጠፋ” (ቁጥር 32) ለማን ልንጸልይ እንችላለን?

ሉቃስ 22፥39–46በጌቴሴማኒ ስለ አዳኙ ስቃይ መማር ለቤተሰባችሁ የተቀደሰ ተሞክሮ ሊሆን ይችላል። ሉቃስ 22፥39–46ን በምታጠኑበት ጊዜ አክብሮታዊ እና የአምልኮ መንፈስ ለመፍጠር ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ። የቤተሰባችሁን አንዳንድ ስለ አዳኙ የተዘመሩ ተወዳጅ መዝሙሮችን ወይም የልጆች መዝሙሮችን አብራችሁ ልትጫወቱ ወይም ልትዘምሩ ትችላላችሁ። ተዛማጅ የሆኑ የጥበብ ሥራዎችን ወይም እንደ “አዳኙ በጌቴሴማኒ ተሰቃየ” (ChurchofJesusChrist.org) ያሉ ቪድዮዎችን መመልከት ትችላላችሁ። ጥቅሶቹን በምታነቡበት ጊዜ፣ የቤተሰብ አባላት በተለይ ለእነሱ ትርጉም ያላቸውን፥ ምናልባትም የአዳኙ ፍቅር እንዲሰማቸው የሚረዱ ምንባቦች ማጋራት ይችላሉ (በተጨማሪ ማቴዎስ 26፥36–46ማርቆስ 14፥32–42ን ተመልከቱ)። እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስን እና የኃጢያት ክፍያውን ምስክርነታቸውን እንዲያካፍሉ ትጋብዟቸው ይሆናል።

ሉቃስ 22፥42የቤተሰብ አባላት “የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ” ማለትን የተማሩበትን ልምዶች ማካፈል ይችላሉ።

ሉቃስ 22፥50–51ዮሐንስ 18፥10–11ከእነዚህ ጥቅሶች ስለ ኢየሱስ ምን እንማራለን?

ክርስቶስ የአገልጋይን ጆሮ እየፈወሰ

ይህንስ ፍቀዱ፣ በዋልተር ሬን

ዮሐንስ 18፥37–38የጲላጦስን “እውነት ምንድር ነው?” (ቁጥር 38) የሚለውን ጥያቄ እንዴት እንመልሳለን? ለአንዳንድ ሃሳቦች ዮሐንስ 8፥32ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥4593፥23–28፤ እና “እውነት ምንድን ነው? በሉ፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 272ን ተመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “እኔ በመደነቅ ቆሜያለሁ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 193።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የኋለኛው ቀን ነቢያትን እና ሐዋሪያትን ቃል አጥኑ። በቅዱሳት መጻህፍት ላይ ስለምታገኟቸው መርሆዎች የኋለኛው ቀን ነቢያት እና ሐዋሪያት ምን እንዳስተማሩ አንብቡ። ለምሳሌ፣ በመጨረሻው በሊሆና፣ ስለ ጠቅላላ ጉባኤ በተለቀቀው ላይ፣ “የሃጥያት ክፍያ” የርዕስ ማውጫን መፈለግ ትችላላችሁ (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 21ን ይመልከቱ)።

ክርስቶስ በጌተሰማኒ

የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ፣ በዋልተር ሬን