“ሰኔ 5–11 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 14–17፦ ‘በፍቅሬ ኑሩ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]
“ሰኔ 5–11 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 14–17፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ሰኔ 5–11 (እ.አ.አ)
ዮሐንስ 14–17
“በፍቅሬ ኑሩ”
በ ዮሐንስ 14–17፣ ላይ የአዳኙን አስተምሮቶች ስታነቡ መንፈስ ቅዱስ ለናንተ የሆነውን መልዕት እንድትለዩ ይረዳችኋል። የሚቀበሉትን ስሜቶች ይመዝግቡ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ዛሬ እኛ “የመጨረሻው እራት” ብለን እንጠራዋለን፣ ነገር ግን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ለዓመታዊው የፋሲካ በዓል በተሰበሰቡ ጊዜ ይህ ከመሞቱ በፊት ከመምህራቸው ጋር የመጨረሻ ምግባቸው መሆኑን ሙሉ በሙሉ ተገንዝበው እንደሆነ አናውቅም። ነገር ግን ኢየሱስ “[ሰዓቱ] እንደ ደረሰ አውቆ” ነበር (ዮሐንስ 13፥1)። ብዙም ሳይቆይ የጌቴሴማኒን ስቃይ፣ የቅርብ ጓደኞቹን ክህደት እና ማስተባበያ በመስቀል ላይም አሰቃቂ ሞት ይገጥመዋል። ይህ ሁሉ በፊቱ እየቀረበ ቢሆንም የኢየሱስ ትኩረት በራሱ ላይ ሳይሆን በደቀ መዛሙርቱ ላይ ነበር። በሚቀጥሉት ቀናት እና ዓመታት ውስጥ ምን ማወቅ አለባቸው? በ ዮሐንስ 14–17 ላይ የኢየሱስ በርህራሄ የተሞሉ ትምህርቶች በዚያን ጊዜ እና አሁን ስለ ደቀ መዛሙርቱ ምን እንደሚሰማው ያሳያሉ። በአንድ በኩል ካካፈላቸው ብዙ የሚያጽናኑ እውነቶች መካከል አንዱ ፈጽሞ እንደማይለየን ማረጋገጡ ነው። “ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ” በማለት ቃል ገባ (ዮሐንስ 15፥10)።
ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝን ፍቅር አሳያለሁ።
ዮሐንስ 14–15ን ስታነቡ ፍቅር፣ የሚለውን ቃል ምልክት አድርጉ ወይም ልብ በሉ። ምናልባት በዚህ ምዕራፍ ትዕዛዛት የሚለውን ቃል በተደጋጋሚ ፍቅር ከሚለው ቃል ጋር ተያይዞ እንደተጠቀሰ ልብ ትሉ ይሆናል። ከአዳኙ ትምህርቶች በፍቅር እና በትእዛዛት መካከል ስላለው ግንኙነት ምን ትማራላችሁ? በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ከ ፍቅር ጋር የተቆራኙ ሌሎች ቃላቶች እና ሀረጎች ምንድናቸው?
የአዳኙ ፍቅር እናንተን እንዴት እንደነካችሁ አስቡ።
በተጨማሪም ዮሐንስ 13፥34–35፤ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን፣ “በፍቅሬ ኑሩ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 48–51ን ተመልከቱ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር የመሆን ዓላማዬን እንድፈጽም መንፈስ ቅዱስ ይረዳኛል።
ደቀ መዛሙርቱ ከአዳኙ ጋር የነበራቸው ጊዜ ከሞላ ጎደል ማለቁን መስማታቸው ልብን የሚሰብር መሆን አለበት። በተጨማሪም እነሱ ያለ እሱ እንዴት እንደሚስማሙ ተጨንቀው ይሆናል። ዮሐንስ 14–16ን በምታነቡበት ጊዜ፣ ለማፅናናት አዳኙ የተናገረውን ፈልጉ። በተለይ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማራቸውን አስተውሉ። በሚከተሉት ጥቅሶች ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ከአዳኙ ቃላት ምን ትማራላችሁ?
ደቀ መዛሙርቱ ይህን አይነት የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ለምን አስፈለጋቸው? መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ሚናዎች ለእናንተ እንዴት ፈጸመ? የእሱ ተፅእኖ በሕይወታችሁ ውስጥ ጠንካራ እንዲሆን እናንተ ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ።
በተጨማሪም 3 ኔፊ 19፥9፤ 27፥20፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥12–14፤ ሙሴ 6፥61፤ ሚሼል ዲ. ክሬግ፣ “መንፈሳዊ ብቃት፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ) 19–21ን ተመልከቱ።
በክርስቶስ ስኖር መልካም ፍሬ አፈራለሁ።
“[በክርስቶስ መኖር]” ምን ማለት ይመስላችኋል? (ዮሐንስ 15፥4)። ኢየሱስ ክርስቶስን ከሚወክለው ከወይኑ ጋር እንደተጣበቃችሁ የሚያሳይ “[ፍሬያችሁ]” ምንድነው?
ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ይማልዳል።
በ ዮሐንስ 17 ላይ የተመዘገቡት የኢየሱስ ቃላት የምልጃ ጸሎት በመባል ይታወቃሉ። በዚህ ጸሎት ውስጥ ለሃዋርያቱ እና “ከቃላቸው የተነሣ [በእርሱ] ስለሚያምኑ” (ዮሐንስ 17፥20) ጭምር ጸልዩአል። ያም ማለት እርሱ ስለ እናንተ ይጸልይ ነበር ማለት ነው። ኢየሱስ ለእርናንተ እና ለሌሎች አማኞች ሁሉ ከአባቱ ምን ጠየቀ? ያ እርሱ ስለ እናንተ ስላለው ስሜት ምን ያስተምራችኋል?
ይህ ጸሎት ጥልቅ፣ ዘላለማዊ እውነትንም ያስተምራል። ምን እውነቶች ታገኛላችሁ? ይህንን ምዕራፍ በምታነቡበት ጊዜ፣ ስለሚከተሉት ስለምትማሩት ነገር መመዝገብ አስቡ፦
-
ጸሎት
-
የአዳኙ ግንኙነት ከአባቱ ጋር
-
የአዳኙ ግንኙነት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር
-
ደቀ መዛሙርት ከዓለም እንዴት መለየት እንዳለባቸው
-
ለእናንተ ጎልተው የሚታዩ ሌሎች እውነቶች
የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አንድ ናቸው።
በ ዮሐንስ 17፣ ጸሎቱ ላይ፣ ኢየሱስ ከአብ ጋር ያለውን አንድነት አፅንዖት ሰጥቷል። አብ እና ወልድ በየትኛው መንገዶች “አንድ” ናቸው? (ዮሐንስ 17፥11፣ 21–23)። አዳኙ እርሱ እና አባቱ አንድ እንደሆኑ ደቀ መዛሙርቱም በተመሳሳይ መልኩ አንድ “እንዲሆኑ” እንደጸለየ ልብ በሉ (ዮሐንስ 17፥22)። ይህ ለእናንተ ምን ማለት ነው? ስለ ግንኙነታችሁ አስቡ ለምሳሌ—ከባለቤታችሁ ወይም ከሌሎች የቤተሰብ አባላት፣ ከቅርንጭፍ አባላት፣ እና ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር። ኢየሱስ ከአብ ጋር ወዳለው አይነት አንድነት እንዴት ልትሰሩ ትችላላችሁ?
በተጨማሪም ኩዊንተን ኤል. ኩክ፣ “በጽድቅ እና በአንድነት የተሳሰሩ ልቦች፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ) 18–22፤ ሼረን ዩባንክ፣ “በስሜት ህብረት ከእግዚአብሔር ጋር ኃይልን እናገኛለን፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ) 55–57ን ተመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ዮሐንስ 14፥5–6።የቤተሰብ አባላት ተራ በተራ በመንገድ ላይ ሆነው ቤተሰባችሁን በመምራት ሊደሰቱ ይችላሉ። ኢየሱስ “መንገድ” የሆነው እንዴት ነው? እርሱ ወዴት ይመራናል?
-
ዮሐንስ 14፥ 26–27።የኢየሱስ ሰላም “ዓለም [ከሚሰጠው]” ዓይነት የሚለየው እንዴት ነው? የቤተሰብ አባላት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሰላምን እና መፅናናትን ያገኙበትን መንገዶች ማጋራት ይችላሉ።
-
ዮሐንስ 15፥1–8።ውጭ ከወይን፣ ከዛፍ ወይም ከሌላ ተክል አጠገብ እነዚህን ጥቅሶች ማንበብ አስደሳች ሊሆን ይችላል። ቅርንጫፍ ከተክሉ ሲወገድ ምን ይሆናል? እኛ እንደ ቅርንጫፎች እንዴት እንደሆንን እና በአዳኙ “መኖር” እና “ፍሬ [ማፍራት]” ምን ማለት እንደሆነ ማውራት ትችላላችሁ።
-
ዮሐንስ 15፥17–27፤ 16፥1–7።ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ስለ መከራ ያስጠነቀቃቸው ለምን ይመስላችኋል? ዛሬ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መከራ እንዴት ይገጥማቸዋል? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የአዳኙ ምክር መከራ ሲያጋጥመን እንዴት ሊረዳን ይችላል?
-
ዮሐንስ 16፥33።ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ያሸነፈው እንዴት ነው? የእርሱ የኃጢያት ክፍያ ሰላምን እና ብርታትን እንዴት አመጣልን? (በተጨማሪም ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 68፥6ን ተመልከቱ)።
-
ዮሐንስ 17፥21–23።ቤተሰባችሁ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እና የሰማይ አባት እንዴት ይበልጥ አንድ መሆን እንደሚችሉ እንዲማሩ ምን ይረዳቸዋል? ምናልባት ስለ አንድ ተወዳጅ የስፖርት ቡድን እና እንዴት ወደ አንድ የጋራ ግብ አብረው እንደሚሠሩ ማውራት ትችሉ ይሆናል። ወይም መዘምራን ወይም ኦርኬስትራ በማዳመጥ ሙዚቀኞች እንዴት ውብ ሙዚቃን እንደሚፈጥሩ መወያየት ትችላላችሁ።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።
በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “መንፈስ ቅዱስ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 105።