አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ሰኔ 19–25 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 27፤ ማርቆስ 15፤ ሉቃስ 23፤ ዮሐንስ 19፦ “ተፈጸመ”


“ሰኔ 19–25 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 27፤ ማርቆስ 15፤ ሉቃስ 23፤ ዮሐንስ 19፦ ‘ተፈጸመ’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 19–25 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 27፤ ማርቆስ 15፤ ሉቃስ 23፤ ዮሐንስ 19፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት

እነሆ ሰውዬው፣ በአንቶኒዮ ሲሴሪ

ሰኔ 19–25 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 27ማርቆስ 15ሉቃስ 23ዮሐንስ 19

“ተፈፀመ”

ማቴዎስ 27ማርቆስ 15ሉቃስ 23፤ እና ዮሐንስ 19 የአዳኙን ምድራዊ ቆይታ የመጨረሻ ሰአታት ገለጻዎችን ይዘዋል። ስለ መስዋእትነቱ እና ስለሞቱ ስታጠኑ ለእናንተ ያለውን ፍቅር እንዲሰማችሁ ፈልጉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በእያንዳንዱ ቃል እና ድርጊት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ንፁህ ፍቅርን—ሐዋርያው ጳውሎስ ልገሳ ብሎ ለጠራው ምሳሌ ሆኗል (1 ቆሮንቶስ 13ን ተመልከቱ)። በአዳኙ የምድራዊ ሕይወት የመጨረሻ ሰዓታት በላይ ይህ ይበልጥ ግልፅ ሆኖ አያውቅም። በሐሰት ውንጀላዎች ፊት የተከበረው ዝምታው እሱ በቀላሉ “[እንደማይበሳጭ” ያሳያል (1 ቆሮንቶስ 13፥5)። ሲገርፉት፣ ሲያሾፉበት እና ሲሰቅሉት ሥቃዮቹን ይቀጥሉ ዘንድ ኃይሉን በመግታት በፈቃደኝነት ተገዛ፣ እሱ “[ታጋሽ]” እና “ሁሉን [የሚችል]” እንደሆነ አሳየ (1 ቆሮንቶስ 13፥4፣ 7)። ለእናቱ ያለው ርህራሄ እና ተወዳዳሪ በሌለው ሥቃይ ወቅት እንኳን ለሰቃዮቹ ያሳየው ምህረት—እርሱ “[የራሱን እንደማይፈልግ]” ገልጧል (1 ቆሮንቶስ 13፥5)። ኢየሱስ በምድር ላይ ባሳለፋቸው የመጨረሻዎቹ ጊዜያት በሥጋዊ አገልግሎቱ ውስጥ ያደረገውን ሁሉ እያደረገ ነበር—እኛን በማሳየት ማስተማር። በእርግጥ ልግስና “የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር” ነው (ሞሮኒ 7፥47)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማቴዎስ 27ማርቆስ 15ሉቃስ 23ዮሐንስ 19

ኢየሱስ ክርስቶስ ለመከራ ፈቃደኛ መሆኑ ለአባቱ እና ለሁላችንም ያለውን ፍቅር ያሳያል።

አዳኙ “የመላእክት ጭፍሮችን” (ማቴዎስ 26፥53) የመጥራት ኃይል ቢኖረውም፣ ፍትሃዊ ያልሆኑ መከራዎችን፣ መሳለቅን፣ እና ሊታሰብ የማይችል ሥቃይን በፈቃደኝነት መቻልን መርጧል። ይህን ለምን አደረገ? ኔፊ “በቸርነቱ እና ለሰው ልጆች ባለው ጽናት ምክንያት” (1 ኔፊ 19፥9) እንደሆነ መሰከረ።

ምስል
ክርስቶስ መስቀል ተሸክሞ

“መስቀሉንም ተሸክሞ … ጎልጎታ ወደ ተባለው ስፍራ ወጣ” (ዮሐንስ 19፥17)።

1 ኔፊ 19፥9ን በማንበብ የአዳኙን የመጨረሻ ሰዓታት ማጥናት ልትጀምሩ ትችላላችሁ። ማቴዎስ 27ማርቆስ 15ሉቃስ 23፤ እና ዮሐንስ 19 ላይ ኔፊ ኢየሱስ ይሰቃያል ያለውን የእያንዳንዱ ነገሮች ምሳሌዎችን የት ታገኛላችሁ?

  • “[እነሱ] ዋጋ እንደሌለው ነገር ይፈርዱበታል”

  • “ይገርፉታል”

  • “ይመቱታል”

  • “ይተፉበታል”

የአዳኙን “ቸርነት” እንዲሰማችሁ የሚረዱት የትኞቹ ክፍሎች ናቸው? እነዚህን ዘገባዎች ስታነቡ ሌሎች ሀሳቦች እና ስሜቶች ምን አላችሁ? እነሱን መጻፍ ወይም ለሌላ ሰው ማጋራት አስቡ።

በተጨማሪም “ኢየሱስ በጲላጦስ ፊት ተኮነነ” እና “ኢየሱስ ተገረፈ እናም ተሰቀለ” (ቪዲዮዎች) ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

ማቴዎስ 27፥27–49፣ 54ማርቆስ 15፥16–32ሉቃስ 23፥11፣ 35–39ዮሐንስ 19፥1–5

መሳለቅ እውነትን ሊለውጥ አይችልም።

ኢየሱስ በአገልግሎቱ ጊዜ ሁሉ ሲሳለቁበት ቢታገስም በመገረፉ እና በስቅለቱ ጊዜ ይበልጥ እየጠነከረ ሄደ። ነገር ግን ይህ ሹፈት እውነትን ሊለውጥ አልቻለም፤ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ኢየሱስ ስለደረሰበት ውርደት በምታነቡበት ጊዜ፣ ዛሬ በሥራዎቹ ላይ ስለሚደርሱ ተቃውሞዎች እና ሹፈቶች አስቡ። ተቃውሞዎችን ስለመቋቋም ምን ግንዛቤዎችን ታገኛላችሁ? በማቴዎስ 27፥54፣ ላይ ስላለው የመቶ አለቃ ቃል ምን ያስደንቃችኋል?

ማቴዎስ 27፥46ማርቆስ 15፥34

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻውን የተሰቃየው እኔ እንዳልሰቃይ ነው።

በመስቀል ላይ እጅግ ከሚያሳዝኑ ጊዜያት በአንዱ፥ ሁል ጊዜ በሰማይ አባቱ ይደገፍ የነበረው ኢየሱስ በድንገት እንደተተወ ተሰማው። ስለ እነዚህ ማንበብ ከእግዚአብሔር እንደራቃችሁ የተሰማችሁን ጊዜያት እንድታስቡ ሊያደርጋችሁ ይችላል። በመስቀል ላይ የአዳኙ መስዋእት ያንን ርቀት ለማሸነፍ እንዴት እንደሚያስችል ልታስቡ ትችላላችሁ። ሽማግሌው ጄፍሪ አር ሆላንድ እንደመሰከሩት፣ “ኢየሱስ ረዥም፣ ብቸኛ በሆነ መንገድ ብቻውን ስለሄደ እኛ መሄድ አይጠበቅብንም። … ከቀራንዮ አናት ላይ የታወጀው እውነት፥ እኛ ብቻችንን እንደማንተው ወይም ረዳት የሌለን እንደማንሆን ነው፤ ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ እንደዛ እንደሆነ ሆኖ ቢሰማንም” (“ከእርሱ ጋር ማንም አልነበረም፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 88)። የተቀረውን የሽማግሌ ሆላንድን መልእክት ስታነቡ አዳኙ ብቸኝነትን ለማሸነፍ እንዴት እንደሚረዳችሁ አስቡ።

ሉቃስ 23፥34

አዳኙ የይቅርታ ምሳሌያችን ነው።

ሉቃስ 23፥34፣ ላይ የአዳኙን ቃል ስታነቡ ምን ይሰማችኋል? (የ ግርጌ ማስታወሻ ፣ ላይ በጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም የቀረበውን መረዳት ተመልከቱ)። የአዳኙን ቃል በመጥቀስ፣ ፕሬዘደንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ እንዲህ ብለው አስተምረው ነበር፤ “እኛ የሚበድሉንን ሰዎች ይቅር ማለት እና ለእነሱ ክፉ ማሰብ የለብንም። አዳኙ ምሳሌውን ከመስቀል ላይ አሳየ። … የበደሉንን ሰዎች ልብ አናውቅም” (“አንድ እንሆን ዘንድ፣” ኢንዛይን፣ ግንቦት 1998 (እ.አ.አ)፣ 68)። አንድን ሰው ይቅር ለማለት ከተቸገራችሁ ይህ ጥቅስ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 27ማርቆስ 15ሉቃስ 23ዮሐንስ 19በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ስለተገለጹት ክስተቶች ቤተሰባችሁ እንዲያውቅ ለማገዝ፣ “ምዕራፍ 52፤ የኢየሱስ ክርስቶስ መከራዎች” እና “ምዕራፍ 53፤ ኢየሱስ ተሰቀለ” (በየአዲስ ኪዳን ታሪኮች፣ 133–38፣ ወይም የሚመሳሰሉ ቪድዮዎችን በChurchofJesusChrist.org) ማካፈል ትችላላችሁ። ወይም እነዚህን ክስተቶች የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን አብራችሁ ማየት ትችላላችሁ፦ “ኢየሱስ በጲላጦስ ፊት ተኮነነ” እና “ኢየሱስ ተገረፈ እናም ተሰቀለ” (ChurchofJesusChrist.org)። ልጆች ታሪኮቹን በራሳቸው ቃላት እንዲናገሩ መጋበዝ ትችላላችሁ። የቤተሰብ አባላት አዳኙ ስለኛ ስለተሰቃየው የሚሰማቸውን ሊያጋሩ ይችላሉ።

ማቴዎስ 27፥11–26ማርቆስ 15፥1–15ሉቃስ 23፥12–25; ዮሐንስ 19፥1–16ጲላጦስ ኢየሱስ ንፁህ መሆኑን እያወቀ ለምን እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው? ትክክል እንደሆነ ስለምናውቀው ነገር ስለመቆም ከጲላጦስ ተሞክሮ ምን ትምህርት እናገኛለን? ለትክክለኛው ነገር መቆምን እንዲለማመዱ የሚያስችላቸውን ትወናዎች ለቤተሰባችሁ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።

ማቴዎስ 27፥46ሉቃስ 23፥34፣ 43፣ 46ዮሐንስ 19፥26–28፣ 30ምናልባት በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ አዳኙ በመስቀል ላይ ከተናገራቸው ቃላት አንዱን ወይም ከዚያ በላይ እንዲያነቡ እያንዳንዱን የቤተሰብ አባል መመደብ ትችላላችሁ። ስለ አዳኙ እና ስለ ተልዕኮው ከእነዚህ ቃላት የተማሩትን እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው።

ማርቆስ 15፥39ስለ ኢየሱስ ስቅለት ማንበብ ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ስለመሆኑ ምስክርነታችሁን ያጠናከረው እንዴት ነው?

ዮሐንስ 19፥25–27የቤተሰብ አባላትን እንዴት መውደድ እና መደገፍ እንደምንችል ከእነዚህ ጥቅሶች ምን እንማራለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “በቀራንዮ በመስቀል ላይ፣” መዝሙር፣፣ ቁጥር 184።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የአዳኙን ህይወት ተከተሉ። “አዳኙ ያስተማረባቸውን መንገዶች—የተጠቀመባቸውን ዘዴዎች እና የተናገራቸውን ነገሮች ማጥናት ጠቃሚ ነው። ነገር ግን የጌታ ሌሎችን የማስተማርና ከፍ የማድረግ ሀይል የመጣው በሚኖርበት ህይወት ምክንያት እና ከእርሱ ማንነት ነው። በታታሪነት እንደ ክርስቶስ ለመኖር ስንጥር፣ ይበልጥ ልክ እንደርሱ ማስተማር እንችላለን” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር13)።

ምስል
ክርስቶስ በመስቀል ላይ

ክርስቶስ በመስቀል ላይ፣በካርል ሄንሪክ ብሎች

አትም