ቅዱሳት መጻህፍት
የGospel Library app [የወንጌል ላይብረሪ መተግበሪያ] የመጠቀሚያ ሃሳቦች


“የGospel Library app [የወንጌል ላይብረሪ መተግበሪያ] የመጠቀሚያ ሃሳቦች፣” ቅዱስ መጽሐፍን የማጥኛ ሃሳቦች (2021 እ.አ.አ)

“የGospel Library app [የወንጌል ላይብረሪ መተግበሪያ] የመጠቀሚያ ሃሳቦች፣” ቅዱስ መጽሐፍን የማጥኛ ሃሳቦች

ምስል
ሴት እና ህጻን ታብሌትን ሲመለከቱ

የGospel Library app [የወንጌል ላይብረሪ መተግበሪያ] የመጠቀሚያ ሃሳቦች

አድምጡ

ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማጥናት አንዱ የተሻለ መንገድ ቅጂዎችን ማዳመጥ ነው። ይህን በቤትዎ ውስጥ ወይም በየትኛውም ቦታ ማድረግ ይችላሉ። በተለያየ ፍጥነት እና በተለያየ ቋንቋዎች ማዳመጥም ይችላሉ።

በርዕሶች ያጥኑ

የፍለጋ ሳጥኑን በመጠቀም እና ተገቢ የሆኑ የፍለጋ ውጤቶችን በመከለስ ስለአንድ ርዕስ ቅዱስ ጽሁፍን ማግኘት ይችላሉ። ለሆነ ርዕስ ቁልፍ የሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚሰጡ የወንጌል ርዕሶችን ዕትምን መጠቀምም ይችላሉ።

በርዕስ ያስተካክሉ

“መለያዎችን” እና “ማስታወሻዎችን” በመጠቀም ይዘቶችን በርዕሶች ማስተካከል ይችላሉ። እነዚህ ርዕሶች ንግግር ወይም ትምህርት ሲያዘጋጁ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።

ማጉላት

አንድን ምንባብ ከዚያም ቅጥን በመምረጥ ቅዱሳት መጻሕፍቶቻችሁን ማጉላት ወይም ምልክት ማድረግ ይችላሉ። ቅጡ የለተያዩ ቀለሞች ውህድ እና ማስመር ወይም ማድመቅ ሊሆን ይችላል።

የገጽ አገናኞችን ይፍጠሩ

በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶች እና በሌሎች ይዘቶች መካከል የገጽ አገናኞችን መፍጠር ይችላሉ። ይህ የፈጠሩትን ትስስሮች እንዲያስታውሱ እና በፍጥነት እንዲያገኙ ሊረዳ ይችላል።

ትርጉሞችን ይመልከቱ

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የአንድን ቃል ትርጉም በመምረጥ እና “ትርጉም” የሚለውን በመጫን በቀላሉ መመልከት ይችላሉ።

የገጽ ማስታወሻዎችን እና ማሳያዎችን ይጠቀሙ

የተወሰኑ ቦታዎችን እና ማሳያዎችን ለመከታተል የገጽ ማስታወሻዎችን በመጠቀም ወደ ተመረጠ ይዘት በፍጥነት መመለስ ይችላሉ። የገጽ ማስታወሻዎችን መጠቀም የተለያዩ ምዕራፎችን እና ሌላ ይዘትን በተመሳሳይ ሰዓት ለመክፈት ሊፈቅድ ይችላል።

የጊዜ ሰሌዳን ያዘጋጁ

የቅዱሳት መጻሕፍትን ጥናትዎን እድገት ለመጠበቅ እንዲረዳ የጥናት ዕቅድን መፍጠር ይችላሉ። የጥናት ግባችሁን ለማሳካት እንዲረዳዎት ማስታወሻዎችን ማድረግ ይችላሉ። የጊዜ ሰሌዳ የ ኑ፣ ተከተሉኝ ን የጊዜ ሰሌዳ ለመከተል ወይም በግል መጽሐፈ ሞርሞንን ለማንበብ ሊረዳ ይችላል።

አትም