ቅዱሳት መጻህፍት
ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት ለምን ያስፈልጋል?


“ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥነናተ ለምን ያስፈልጋል?” ቅዱስ ጽሁፍን የማጥኛ ሃሳቦች (2021 አ.አ.አ)

“ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት ለምን ያስፈልጋል?” ቅዱስ ጽሁፍን የማጥኛ ሃሳቦች

ምስል
ክርስቶስ በኔፊያውያን መካከል ቅዱስ ቁርባንን አካፈለ፣ በአንድሪው ቦስሊ

ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት ለምን ያስፈልጋል?

ቅዱሳት መጻሕፍትን በትጋት ስናጠና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመቅረብ እና የእርሱን ወንጌል እና የሃጢያት ክፍያ የበለጠ ለመረዳት ያግዛል። ነብዩ ኔፊ በዚህ መንገድ አበረታታን።

“ስለሆነም በክርስቶስ ባላችሁ ጠንካራ እምነት መቀጠል አለባችሁ፣ የተስፋ ብርሃን፣ እናም የእግዚአብሔርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር ይኖራችኋል። ስለሆነም አብም፣ የክርስቶስን ቃል በመመገብ፣ እናም እስከመጨረሻው በመፅናት የምትቀጥሉ ከሆነ፣ እነሆ አብ እንዲህ ይላል፦ የዘለዓለም ህይወት ይኖራችኋል” (2 ኔፊ 31፥20)።

ምስል
ቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነብ

የቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርቶች ወደ ሰማይ አባታችን ለመመለስ ይረዱናል። የኋለኛ ቀን ነብያቶቻችን እንደ ግለሰቦች እና ተገቢ ሲሆን ደግሞ እንደ ቤተሰቦች በተደጋጋሚ እንድናጠናቸው ጠይቀዋል። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ካሉ ልምዶች እንድንማር እና የቅዱስ መጽሐፍ መዝገቦችን እና ትምህርቶችን ኔፊ በ 1 ኔፊ 19፥23ውስጥ እንደመከረው በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ እንድናደርግ ጋብዘውናል። የጥንት እና ዘመናዊ ነብያት ቅዱሳት መጻሕፍትን እንድናጠና እና “የክርስቶን ቃላት እንድንመገብ” ጋብዘውናል (2 ኔፊ 32፥3)።

ምስል
አንድ ሰው ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነብ

ፕሬዝደንት ረስልኤም. ኔልሰን ስለ ቅዱት መጻሕፍትን “መመገብ” ይህን ጠቃሚ እውነታ አስተማሩ፦

“መብላት ማለት ከመቅመስ የበለጠ ማለት ነው። መብላት ማለት በደንብ ማጣጣም ማለት ነው። በአስደሳች ግኝት እና በታማኝነት ታዛዥነት መንፈስ በማጥናት ቅዱሳት መጻህፍትን እናጣጥማለን። የክርስቶስን ቃላት ስንጠግብ እነሱ ‘በስጋዊ የልብ ጠረጴዛዎች’ ውስጥ ተካትተዋል። [2 ቆሮንጦስ 3፥3]። እነሱ የእኛ የተፈጥሮ አካል ይሆናሉ” [“Living by Scriptural Guidance [በቅዱስ ጽሑፋዊ መመሪያ መኖር]፣” ኢንሳይን ህዳር 2000(እ.አ.አ.)፣ 17]።

በግል እና በቤተሰብ የቅዱስ መጽሐፍ ጥናት ላይ በተደጋጋሚ ስንሳተፍ እኛ እና ቤተሰቦቻችን መመራት፣ መጠበቅ እና ከብዙ የቀናችን ተግዳሮቶች መከለል ይችላሉ።

አትም