ቅዱሳት መጻህፍት
የቤተሰባችሁን የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ማሻሻያ ሀሳቦች


“የቤተሰባችሁን የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ማሻሻያ ሀሳቦች፣” ቅዱስ መጽሐፍን የማጥኒያ ሃሳቦች (2021 እ.አ.አ)

“የቤተሰባችሁን የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ማሻሻያ ሀሳቦች፣” ቅዱስ መጽሐፍን የማጥኒያ ሃሳቦች

ምስል
ቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነቡ

የቤተሰባችሁን የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ማሻሻያ ሀሳቦች

መደበኛ የቤተሰብ የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ቤተሰባችሁ ወንጌልን እንዲማሩ ለመርዳት ሀይለኛ መንገድ ነው። እንደቤተሰብ የሚያነቡት ነገር ብዛት እና የሚያነቡበት ጊዜ ርዝመት ያላሰለሰ ጥረት የማድረጋችሁን ያህል አስፈላጊ አይደሉም። የቅዱሳን መጻህፍት ጥናትን የቤተሰባችሁ ህይወት አስፈላጊ ክፍል ስታደርጉት፣ የቤተሰባችሁ አባሎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲቀርቡ እና በእርሱ ቃል መሠረት ምስክርነታቸውን እንዲገነቡ ትረዷቸዋላችሁ።

የሚቀጥሉትን ጥያቄዎች አስቡባቸው፦

  • የቤተሰብ አባላትን በራሳቸው ቅዱሳን መጻህፍትን እንዲያጠኑ እንዴት ማበረታታት ይችላሉ?

  • የቤተሰብ አባላት የሚማሩትን እንዲያጋሩ ለማበረታታት ምን ማድረግ ይችላሉ?

  • በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ የሚማሩትን መሰረታዊ መርሆዎች በእለት ተለት ትምህርቶች ጊዜ እንዴት ማጉላት ይችላሉ?

ቤት ለወንጌል መማር እና ማስተማር አመቺ ስፍራ መሆኑን አስታውሱ። በቤተክርስቲያን ክፍል ውስጥ በማይቻል መንገድ ወንጌልን በቤታችሁ ውስጥ መማር እና ማስተማር ይችላሉ። ቤተሰባችሁ ከቅዱሳን መጻህፍት እንዲማሩ ለመርዳት መንገዶችን መፍጠርን አስቡ። የቤተሰባችሁን የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ለማጉላት የሚከተሉትን ሀሳቦች ይመልከቱ።

ሙዚቃን ይጠቀሙ

በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ የተማራችሁትን መሰረታዊ መርሆዎች የሚያጠናክሩ መዝሙሮች ይዘምሩ።

ምስል
እንድ ሰው እና አንዲት ሴት ቅዱሳን መጽሐፍትን እያጠኑ

ትርጉም ያላቸው የቅዱሳን መጻህፍት ጥቅሶችን ያጋሩ።

የቤተሰብ አባላት በግል ጥናታቸው ያገኟቸውን ለእነሱ ትርጉም የሰጧቸውን የቅዱሳን መጻህፍት ምንባቦች እንዲያካፍሉ ጊዜ ይስጧቸው።

የራስዎን ቃላት ይጠቀሙ

ከምታጠኗቸው ቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ምን እንደተማሩ በገዛ ቃላቸው እዲያብራሩ የቤተሰብ አባሎቻችሁን ይጋብዟቸው።

ቅዱሳን መጻህፍት በሕይወታችሁ እንዲሰሩ ያድርጉ

የቅዱሳን መጻህፍትን ምንባብ ካነበባችሁ በኋላ የቤተሰብ አባላት መልዕክቱ በህይወታቸው እንዴት ሊሰራ እንደሚችል እንዲያካፍሉ ይጠይቋቸው።

ጥያቄ ይጠይቁ

የቤተሰብ አባላት የወንጌል ጥያቄ እንዲጠይቁ ይጋብዙ፣ እናም ከዚያ ለጥያቄው መልስ ሊያግዙ የሚችሉ ጥቅሶችን በመፈለግ ጊዜአችሁን ያሳልፉ።

የቅዱሳን መጻህፍት ጥቅስን ያሳዩ

ያገኙትን ትርጉም ያለው ጥቅስ ይምረጡ፣ እና የቤተሰብ አባላት ብዙውን ጊዜ በሚያዩበት ቦታ ላይ ያስቀምጡት። የቤተሰብ አባላት አንድ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅስ በመምረጥ በየተራ እንዲያሳዩ ጋብዙ።

የቅዱሳን ፅሁፎች ዝርዝር ያዘጋጁ

በሚመጣው ሳምንት እንደ ቤተሰብ በጥልቀት ለመወያየት የምትፈልጓቸውን የተለያዩ ጥቅሶች ይምረጡ።

ቅዱሳን ፅሁፎችን በቃልዎ ያጥኑ

ለቤተሰብዎ ትርጉም ያለው የቅዱስ ፅሁፍ ምንባብ ይምረጡ፣ እና የቤተሰብ አባላቱ በየዕለቱ በመድገም ወይም የማስታወሻ ጨዋታ በመጫወት በአዕምሮአቸው በመያዝ እንዲያስታውሱ ይጋብዙአቸው።

የምሳሌያዊ ነገረ ትምህርቶችን ያጋሩ

እንደ ቤተሰብ ከምታነቧቸው ምዕራፎች እና ጥቅሶች ጋር የሚዛመዱ ነገሮችን ፈልጉ። እያንዳንዱ ነገር በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ካሉት ትምህርቶች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እንዲናገሩ የቤተሰብ አባላትን ጋብዙ።

ምስል
አንዲት ሴት ልጅን እያስተማረች

ርዕስ ይምረጡ

ቤተሰቡ አብሮ የሚያጠናውን ርዕስ የቤተሰብ አባላት ተራ በተራ እንዲመርጡ ያድርጉ። በቅዱሳን መጻህፍት ምንባብ ውስጥ ስለርዕሶች መረዳጃ ለማግኘት፣ የርዕስ መመሪያን፣ የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገብ ቃላትን፣ ወይም የቅዱሳን መጻህፍት መመሪያን (scriptures.ChurchofJesusChrist.org) ይጠቀሙ።

ስዕል ይሳሉ

እንደቤተሰብ ጥቂት ጥቅሶችን አንድ ላይ ያንብቡ፣ ከዚያ የቤተሰብ አባላቶች ካነበቡት ነገር ጋር የሚዛመድ አንድ ነገር እንዲስሉ ጊዜ ይስጧቸው። አንዳችሁ በሌላውን ስዕሎች ላይ ለመወያየት ጊዜ ይመድቡ።

ታሪኩን ይተውኑ

አንድ ታሪክ ካነበባችሁ በኋላ የቤተሰብ አባላት እንዲተውኑት ይጋብዙ። ከዚያ በኋላ፣ ታሪኩ በግል እና በቤተሰባችሁ ውስጥ ከሚገኙ ነገሮች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ይነጋገሩ።

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዲህ አስተማረ፦ “እያንዳንዱ የቤተሰብ ጸሎት፣ እያንዳንዱ የቤተሰብ የቅዱስ መጽሃፍ ጥናት፣ እና እያንዳነዱ የቤተሰብ ምሽት በነፍሳችን ምስል ላይ ቀለም ቅብ ነው። ሌላ ክስተት ምንም ቢሆን አስደናቂ እና ትውስታ አይሆንም። ቢጫ እና ወርቃማ እና ቡኒ ቅብ እርስ በእርሳቸው እንደሚደጋገፉ እና አስደናቂ ምስል እንደሚፈጥሩ፣ የእኛም ትንንሽ የሚመስሉ ተከታታይ ድርጊቶች ወደ ወሳኝ መንፈሳዊ ውጤቶች ይመራሉ”(“More Diligent and Concerned at Home፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2009 እ.አ.አ፣ 19–20).

አትም