ቅዱሳት መጻህፍት
የግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናትዎን ማሻሻያ ሀሳቦች


“የግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናትዎን ማሻሻያ ሀሳቦች፣” ቅዱስ መጽሐፍን የማጥኒያ ሃሳቦች (2021 እ.አ.አ)

“የግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናትዎን ማሻሻያ ሀሳቦች፣” ቅዱስ መጽሐፍን የማጥኒያ ሃሳቦች

ምስል
ቅዱሳት መጻህፍትን የምታጠና ሴት

የግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል ሀሳቦች

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የሚገኘውን የእግዚአብሔር ቃል ጥናትዎን የሚያሳድጉ አንዳንድ ቀላል መንገዶች እንደ ሚከተሉት ናቸው።

ለመነሳሳት ይፀልዩ

ቅዱሳት መጻህፍት የእግዚአብሔርን ቃል ይዘዋል። ስታጠኗቸው የሰማይ አባታችሁን ለምሪቱ ጠይቁ እና እነሱን መረዳት ትችሉ ዘንድ የእርሱን መንፈስ ተቀበሉ።

ስለኢየሱስ ክርስቶስ እውነቶችን ይፈልጉ

ቅዱሳት መጻህፍት ሁሉም ነገሮች ስለ ክርስቶስ እንደሚመሰክሩ ያስተምሩናል ( 2 ኔፊ 11፥ 4ሙሴ 6፥63፣ ይመልከቱ)፣ ስለሆነም በቅዱት መጻህፍት ክስተቶች፣ ታሪኮች እና ትምህርቶች ውስጥ እርሱን እሹት። ስለ አዳኙ እና እንዴት እርሱን መከተል እንደምንችል የሚያስተምሩ ጥቅሶችን መጻፍን እና ምልክት ማድረግን አስቡ።

የሚያነሳሱ ቃላትን እና ሃረጎችን ይፈልጉ

በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ የተወሰኑ ቃላቶች እና ሀረጎች በተለይ ለእርስዎ እንደተጻፉ ሆነው ሊሰሟችሁ ይችላሉ። እነሱ ለግላችሁ ተገቢ እንደሆኑ ይሰማዎታል እናም ያነሳሱዎታል እንዲሁም ያነቃቁዎታል ። እነዚህንም በቅዱሳት መጻህፍትዎ ላይ ምልክት ማድረግ ወይም በጥናት ደብተር ውስጥ ለመፃፍ አስቡ።

የወንጌል እውነቶችን ይፈልጉ

አንዳንድ ጊዜ የወንጌል እውነቶች (ብዙውን ጊዜ ትምህርት ወይም መርሆዎች ተብለው ይጠራሉ) በቀጥታ ይገለጻሉ፣ እናም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በምሳሌ ወይም በታሪክ አማካይነት ይገለጻሉ። እራሳችሁን ጠይቁ፣ “እነዚህ ጥቅሶች ምን የወንጌል እውነቶችን ያስተምራሉ?”

መንፈስን ስሙ

ከምታነቡት ጋር የማይዛመዱ ቢመስሉም፣ ለሀሳብዎ እና ለስሜትዎ ትኩረት ስጡ። እነዚያ ግንዛቤዎች የሰማይ አባትዎ እንዲማሩ እና እንዲሰማችሁ የሚፈልጋቸው ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ።

ምስል
ቅዱሳት መጻህፍትን የምታጠና ሴት 2

ቅዱሳን መጻህፍትን ከሕይወትዎ ጋር አመሳስሉ

የምታነቧቸው ታሪኮች እና ትምህርቶች በሕይወትዎ ውስጥ እንዴት እንደሚሠሩ ልብ ይበሉ። ለምሳሌ፣ “እኔ ከማነበው ጋር የሚመሳሰሉ ምን ልምዶች አግኝቻለሁ?” ወይም “በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ያለውን የዚህን ሰው ምሳሌ መከተል የምችለው እንዴት ነው?” ብለው መጠየቅ ይችላሉ።

ጥያቄዎችን ጠይቁ

ስለ ወንጌል ጥያቄዎችን መጠየቅ ምን ማጥናት እንዳለባችሁ ሊረዳችሁ ይችላል። ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያጠኑ፣ ጥያቄዎች ወደ አዕምሮዎ ሊመጡ ይችላሉ። እነዚህ ጥያቄዎች ከምታነቡት ጋር ወይም በአጠቃላይ ከሕይወትዎ ጋር ሊዛመዱ ይችላሉ። እነዚህን ጥያቄዎች አሰላስሉ እና ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት ስትቀጥሉ መልሶቹን ፈልጉ። ከጥናትዎ በኋላ እግዚአብሔር የበለጠ ምን መማር እንዳለቦት ስለሚፈልገው ነገር ይጠይቁ እና ምላሾቹን በሚመጡት ሰዓታት እና ቀናት ውስጥ ይጠብቁ።

የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት መርጃን ይጠቀሙ

በምታነቡት አንቀጾች ላይ ግንዛቤ ለማግኘት የግርጌ ማስታዎሻዎቹን፣ የአርዕስት መምሪያን፣ የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ-ቃላትን፣ እና የቅዱሳን መጻህፍት መመሪያ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org)፣ እንዲሁም ሌሎች የጥናት እርዳታዎችን ይጠቀሙ።

የቅዱሳን መጻህፍትን አገባብ ከግምት ውስጥ ያስገቡ

የቅዱስ ጽሑፍን አገባብ ማለትም ፅሁፉ የተከናወነበትን ሁኔታ እንዲሁም ጊዜ እና ቦታ ከግምት ውስጥ ካስገቡ ትርጉም ያላቸውን ግንዛቤዎችን ማግኘት ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ነብይ ያነጋግራቸውን ሰዎች ያለፈ ታሪክ እና እምነቶች ማወቁ የመልዕክቶቹን ዓላማ በተሻለ ለመረዳት ይረዳዎታል።

ምስል
ቅዱሳን መጽሐፍትን የሚያጠና ወንድ

ሀሳብዎን እና ስሜትዎን መዝግቡ

በሚያጠኑበት ጊዜ የሚመጡትን ግንዛቤዎች ለመመዝገብ ብዙ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ፣ ትርጉም ያለው ቃል ወይም ሐረግን ምልክት ማድረግ እና ሀሳብዎን በቅዱሳት መጻህፍትዎ ውስጥ እንደ ማስታወሻ መጻፍ ይችላሉ። እንዲሁም የሚቀበሉትን ግንዛቤዎች፣ ስሜቶች፣ እና ሃሳቦች ማስታወሻ ደብተርዎ ላይ መያዝ ይችላሉ። ወይም ጥናትዎን ከመጀመሮ በፊት የጠየቁትን ጥያቄ የተመሩትን ምላሾች በማስከተል ሊዘግቡ ይችላሉ።

የኋለኛው ቀን ነቢያትን እና ሐዋርያትን ቃል ያጥኑ

በቅዱሳት መጻህፍት ላይ ስለምታገኟቸው መርሆዎች የኋለኛው ቀን ነቢያት እና ሐዋሪያት ምን እንዳስተማሩ አንብቡ። ምላሻቸው በ “አጠቃላይ ጉባኤ፣” “መፅሔቶች፣” ውስጥ እና ሌሎች የወንጌል መዝገበ መጽሐፍት ስብስቦች ውስጥ ይገኛሉ።

ታሪኮቹን አንብቡ

የቅዱሳት መጻሕፍት ታሪኮችን ያንብቡ፣ አውዳቸውን (ጊዜውን፣ ቦታውን፣ ተናጋሪውን እና ታዳሚውን) ለመረዳት ይሹ። በምስል የተገለፀው የቅዱስ መጽሐፍ ታሪኮች ለዚህ ትልቅ ግብዓት ናቸው በተለይ ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ብዙም ትውውቅ ለሌላቸው ልጆች እና አባሎች።

ግንዛቤዎችን ያጋሩ

ከግል ጥናትዎ ያገኙትን ግንዛቤዎች መወያየት ሌሎች ሰዎችን ለማስተማር ጥሩ የሆነ መንገድ ነው፣ እንዲሁም ያነበቧቸውን በተመለከተ ያሎትን ግንዛቤ ለማጠናከር ይረዳል።

በተማሩት ይኑሩ

የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ሊያነሳሳን እና አኗኗራችንን ለመቀየር ሊመራን ይችላል። በሚያነቡበት ጊዜ መንፈስ እንዲያደርጉ የሚገፋፋዎትን ያድምጡ፣ ከዚያም በእነዚያ ማነሳሻዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ይወስኑ።

አትም