የማስተማሪያ መፅሔት
የስያሜዎች ዝርዝር


የስያሜዎች ዝርዝር

የአሮናዊ የክህነት ስልጣንታናሽ የክህነት ስልጣን ይህ የክህነት ስልጣን የመጥመቅ ስልጣንን በተጨማሪ የያዘ ነው እናም በብሉይ ኪዳን ውስጥ በነበረው አሮን ስም የሚጠራ ነው።

ክህደትግለሰቦች፣ ቤተክርስቲያን፣ ወይን ሀገሮች በሙሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን መተዉ ወይም መካዱ። ክህደት የመከፋፈል፣ የመምታታት፣ እና የክህነት ስልጣን፣ ወይም በእግዚአብሔር ስም የመስራት መብት የማጣት ውጤታ አለው።

ሐዋርያኢየሱስ በምድር ላይ በሚያገለግልበት ጊዜ የቅርብ ግንኙነት እንዲኖራቸው ለመረጣቸውና በስሙ እንዲሰሩ ስልጣን ለሰጣቸው አስራ ሁለት ወንዶች የሰጠው ርዕስ። በእዚህ ዘመን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎች ሰዎችን እንደ ሐዋሪያቱ እንዲያገለግሉ ጠርቷል። እንደ ድሮው ጊዜም፣ ሐዋርያ የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ ምስክር ነው እናም ከእርሱ የመጣ ስልጣን አለው።

የኃጢያት ክፍያከእግዚአብሔር ጋር እንድንታረቅ ያስቻለን ድርጊት። ለኃጢያት መክፈል ለኃጢያት ቅጣትን መሰቃየት ነው፣ በዚህም የኃጢያት ውጤትን ንስሀ ከገቡት ኃጢያተኞች ላይ ያስነሳል። ለሰው ዘር በሙሉ ፍጹም የሆነ የኃጢያት ክፍያ ለማድረግ ችሎታ የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነበር። የኃጢያት ክፍያውም ለኃጢያታችን መሰቃየቱን፣ ደሙን ማፍሰስን፣ እና ሞቱንና ትንሳኤውን ያጠቃልላል። በኃጢያት ክፍያ ምክንያት፣ ኖረው የነበሩ ሁሉም ሰዎች ከሞት ይነሳሉ። የኃጢያት ክፍያም ለኃጢያታችን ይቅርታ የምናገኝበትን እንና ከእግዚአብሔር ለዘለአለም የምንኖርበትን መንገድ ሰጥቶናል።

ጥምቀትየኃጢያት ስርየት ለማግኘት አስፈላጊ የሆነ ስራ። በክህነት ስልጣን በኩል በመጠመቅ እና በመረጋገጥ፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት እንሆናለን። ጥምቀት በመሰመጥ ነው፣ ይህም የሚጠመቀው ሰው በውሀው ውስጥ በሙሉ ጠልቋል ማለት ነው። ጥምቀት ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል እና ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ፈቃደኛ እንደሆንን የሚያሳይ ነው።

ወንጌልበእዚህ ህይወት ሰላም እና በዘለአለም ደስታ እንዲኖረን የሚረዳን የሰማይ አባት አላም። ወንጌል የሚያተኩረው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ላይ ነው እናም በእርሱ እምነት እንዲኖረን፣ ንስሀ እንድንገባ፣ እንድንጠመቅ፣ መንፈስ ቅዱስን እንድንቀበል፣ እናም እስከመጨረሻም እንድንጸና ይጠይቀናል።

መንፈስ ቅዱስደግሞም ይህ ቅዱስ መንፈስ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ እና አፅናኝ ተብሎ ይጠራል። ስለሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ነው፣ እናም እውነትን ይገልጻልም ያስተምራልም።

የመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣንከፍተኛው ወይም ታላቁ የክህነት ስልጣን። ቅዱስ ሊቀ ካህን እና ንጉስ በነበረው፣ በብሉይ ኪዳን ውስጥ በነበረው መልከ ጼዴቅ ስም የሚጠራ ነው።

ስነ ስርዓትበክህነት ስልጣን ስር የሚከናወን ቅዱስ፣ መደባዊ ስራ። ጥምቀት የእዚህ ምሳሌ ነው።

የክህነት ስልጣንየእግዚአብሔር ስልጣን እና ሀይል። እግዚአብሔር ይህን ሀይል ለሰው በእርሱ ስም እንዲሰሩ ይሰጣል። የአሮናዊ የክህነት ስልጣን ለጆሴፍ ስሚዝ በዳግም የተመለሰው ኢየሱስን በጠመቀው በመጥምቁ ዮሀንስ ነበር። የመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን በዳግም የተመለሰው ከኢየሱስ አስራ ሁለት ሐዋሪያት ሶስቱ በነበሩት በጴጥሮስ፣ በያዕቆብና፣ በዮሀንስ ነበር።

ዳግም መመለስነገርን እንደነበረ ማድረግ፤ እንገደና መመስረት፤ እንደ አዲስ መመለስ። ከምድር እውነት እና ስልጣን ከጠፋ በኋላ፣ ወንጌል በነቢዩ ጆሴፍስሚዝ እንደገና ተመልሷል። በዳግም መመለስ ከማሻሻል የሚለየው ማሻሻል ማለት የነበረውን ድርጅት ወይም ልምምድ በመጀመሪያ ወደነበረው ሁኔታ ለመመለስ መቀየር ማለት ነው፣ ይህም ሆኖ በዳግም መመለስ ማለት እንደገና መመስረት ወይም በመጀመሪያ የነበረውን ድርጅት ወይም ልምምድ በሙሉ ማሳደስ ማለት ነው።

ትንሳኤከስጋዊ ሞት በኋላ፣ ነፍስን ፍጹም ከሆነ ከስጋ እና ከአጥንት ሰውነት ጋር በድጋሚ ማገናኘት ነው። ኢየኡስ ክርስቶስ ከሞት ለመነሳት የመጀመሪያው ነበር።

ራዕይበእግዚአብሔር እና በልጆቹ መካከል፣ በልምድም በመንፈስ ቅዱስ በኩል፣ ግንኙነት ማድረግ። ግለሰቦች የእራሳቸውን ህይወት ለመምራት ራዕይ እመቀበል ይችላሉ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር የተመረጡ ነቢያት ብቻ ናቸው ለአለም በሙሉ ራዕይን ለመቀበል የሚችሉት። ራዕይ ከተለያዩ መንገዶች ይመጣል፣ ነገር ግን በብዙ ጊዜ የሚመጣው በሀሳቦች፣ በስሜታዎች፣ እና በሚያነሳሳ ስሜታዎች ነው።