የማስተማሪያ መፅሔት
የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዳግም መመለስ


እግዚአብሔር አፍቃሪ የሰማይ አባታችሁ ነው።

እግዚአብሔር የሰማይ አባታችሁ ነው። እንደግለሰብ ያውቃችኋል እና ሊገባችሁ ከምትችሉት በላይ ያፈቅራችኋል። በእዚህ ህይወት እና በዘለአለም ውስጥ ደስተኛ እንድትሆኑ ይፈልጋችኋል።

ይህን አላማ ለማሟላት፣ የሰማይ አባት የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል* የሚባለውን አላማ ሰጠን። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔ ልጅ ነው፤ የእርሱ ህይወት እና ትምህርቶች በእዚህ ህይወት ወደ ሰላም እና በዘለአለም ውስጥ ወደ ደስታ ይመራሉ።

ወንጌል ቤተሰቦችን እና ግለሰቦችን ይባርካል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሚቀበሉትን እና የሚኖሩበትን በሙሉ ይባርካል። ወንጌሉን በቤተሰብ ውስጥ ማስተማር እና መጠቀም ከቦታዎች ሁሉ በጣም ጥሩ ከሆኑት አንዱ ነው። እግዚአብሔር ቤተሰቦችን የመሰረተው ለጆቹ ደስታን ለማምጣት፣ ትክክለኛ መሰረታዊ መመሪያዎችን በምንፈቀርበት እንድንማር ለመፍቀድ፣ እና ከሞትን በኋላ ወደ እርሱ ለመመለስ ለማዘጋጀት ነው። የቤተሰብ ግንኙነት አንዳንዴ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ የሰማይ አባት የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርቶች ለመከተል ስንጥር ይባርከናል። እነዚህ ትምህርቶች ቤተሰቦቻችንን ለምጠናከር ይረዱናል።

የሰማይ አባት ወንጌሉን ይገልጻል።

እንደ አላማው ክፍል፣ እግዚአብሔር እንደ አዳም፣ ኖኅ፣ አብርሐም፣ እና ሙሴ አይነት ነቢያትን ይመርጣል። ነቢያት

  • ስለእግዚአብሔር ያስተምራሉ እናም የልጁ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ ምስክሮች ናቸው።

  • ራዕይን ወይም ከጌታ መመሪያን ይቀበላሉ።

  • ወንጌልን ለአለም ያስተምራሉ እናም የእግዚአብሔርን ቃል ይተረጉማሉ።

ነቢያት የክህነት ስልጣንን ወይም ለልጆቹ በእግዚአብሔር ስም ለመናገር እና ለመስራት ስልጣን ተቀብለዋል። ነቢያትን የሚከተሉ ሰዎች እግዚአብሔር ቃል የገባቸውን በረከቶች ይቀበላሉ። ወንጌሉን እና የእግዚአብሔን ነቢያት የሚያስወግዱ እነዚያን በረከቶች ያጣሉ እናም ከእግዚአብሔርም እራሳቸውን ያርቃሉ። ነቢያትን የሚያስወግዱ እና እግዚአብሔርን ለመከተል የወሰኑበትን የሚተዉት ክህደትበሚባለው ሁኔታ ውስጥ ናቸው።

ምንም እንኳን ብዙዎቹ ልጆቹ እርሱን እና ነቢያቱን ደጋግመው ቢያስወግዱም፣ የሰማይ አባት ልጆቹን ማፍቀር ቀጥሏል። አሁን ደስተኛ እንድንሆን እና ከሞትን በኋላ ወደ እርሱ እንድንመለስ ዘንድ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ሁሉ ሊሰጠን ይፈልጋል። ቅዱሳት መጻህፍት ምንም እንኳን ሁልጊዜም የማናዳምጥ ብንሆንም፣ እግዚአብሔር ወደ ልጆቹ በተደጋጋሚ የሚቀርብበትን ንድፍ ገልጸዋል።

  • እግዚአብሔር ነቢይን ይመርጣል።

  • ነቢያት ወንጌልን ያስተምራል እናም ህዝብን ይመራል።

  • እግዚአብሔር ህዝብን ይባርካል።

  • ህዝብም ቀስ በቀስ የነቢይን ትምህርቶች ችላ ይላሉ ወይም ታዛዥ አይሆኑባቸውም። በመጨረሻም ነቢዩን እና የሚያስተምረውን ያስወግዳሉ እናም ወደ ክህደት ይገባሉ።

  • በክህደት ምክንያት፣ ህዝቦች የወንጌልን እውቀት ያጣሉ። የክህነት ስልጣን ከመካከላቸው ይወሰዳል።

  • ጊዜው ትክክል ሲሆን እና ህዝቡም እርሱን ለመከተል ሲዘጋጁ፣ እግዚአብሔር ሌላ ነቢይ ይመርጣል፣ የክህነት ስልጣንን እና ቤተክርስቲያኗን በዳግም ይመልሳል፣ እና ነቢዩ ወንጌልን እንዲያስተምሩ መመሪያ ይሰጣል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን መሰረተ

ከፍጥረት ጊዜ ጀምሮ፣ የእግዚአብሔር ልጆች የአዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓትን እየጠበቁ ናቸው። ቃል እንደገባውም፣ የሰማይ አባት ልጁን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ወደ ምድር ከ2 ሺህ አመት በፊት ላከ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም፣ ኃጢያት የለሽ ህይወት ኖረ። ቤተክርስቲያኑን መሰረተ፣ ወንጌሉን አስተማረ፣ እናም ብዙ ታዕምራቶችን ፈጸመ። ጴጥሮስን፣ ያዕቆብን፣ እና ዮሀንስን የሚጨምሩ አስራ ሁለት ወንዶችም ሐዋሪያቱ እንዲሆኑ መረጠ። በእርሱ ስም እንዲያስተምሩ እና ቅዱስ እንደ ጥምቀት አይነት ስነ ስርዓቶችን እንዲፈፅሙ አስተማራቸው እናም የክህነት ስልጣን ሰጣቸው።

ኢየሱስ ቤተክርስቲያኑን ሲመሰርት፣ ከሰማይ አባት መመሪያዎችን ተቀበለ። ከእዚያም እርሱም ደቀ መዛሙርቱን መመሪያ ሰጠ። ቤተክርስቲያኑን የሚገነባበት አለት ከእግዚአብሔር የመጣ ራዕይ እንደነበረ ኢየሱስ ተከታዮቹን አስተማረ።

ወደ ህይወቱ መጨረሻ አካባቢ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ለኖሩት እና ወደፊት ለሚኖሩት ሰዎች ኃጢያት በሙሉ ተሰቃየ እናም ሞተ። ይህም መስዋዕት የኃጢያት ክፍያ ይባላል።በስቃዩ፣ በሞቱ፣ እና በትንሳኤው፣ አዳኝ ምህረት እንዲሰጠን እንድንችል አደረገ። በእርሱ እምነት ያላቸው፣ ንስሀ የሚገቡ፣ እና ትእዛዛቱን የሚያከብሩ ለኃጢያት ስርየት ያገኛሉ እናም በሰላምና በደስታ ይሞላሉ።

ከትንሳኤው በኋላ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋሪያቱን በራዕይ መራ። መፅሐፍ ቅዱስ ቤተክርስቲያኑን በመምራት የቀጠለበትን ብዙ መንገዶች መዝግቧል (ስራ 10; ራዕይ 1:1 ተመልከቱ)። እንደዚህም ነው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በሰዎች ሳይሆን በእግዚአብሔር የተመራችው።

ታላቁ ክህደት

ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በኋላ፣ ክፉ ሰዎች ብዙዎቹን የቤተክርስቲያን አባላታዳደዱ እናም ገደሉ። ሌሎች የቤተክርስቲያን አባላት በኢየሱስ ክርስቶስ እና በሐዋሪያቱ ከተማሩት መሰረታዊ መመሪያዎች ፈቀቅ ብለው ሄዱ። ሐዋሪያት ተገደሉ፣ እናም ቤተክርስቲያኑን የመምራትና ለእርሷም ራዕይ ለመቀበል ከሚያስችሉት ቁልፎች በተጨማሪ የክህነት ስልጣን ከምድር ተወሰደ። ቤተክርስቲያኗ በክህነት ስልጣን ስላልተመራች፣ በቤተክርስቲኢያኑ ትምህርቶች ውስጥ ስህተቶች ገቡ። ጥሩ ሰዎች እና ብዙ እውነቶች ቀርተው ነበር፣ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ተመስርቶ የነበረው ወንጌል ጠፋ። ይህም ጊዜ ታላቁ ክህደት ይባላል።

ይህም ክህደት የሚያስተምሩት የማይስማማ ብዙ ቤተክርስቲያናት የመመስረት ውጤታ ነበረው። በዚህ ጊዜም፣ ብሱ ሰዎች እውነትን ፈለጉ፣ ነገር ግን ይህን ለማግኘት አልቻሉም ነበር። ብዙ ሰዎች በእግዚአብሔር እና በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ እና እውነትን ለመረዳት እና ለማስተማር ይጥሩ ነበር፣ ነገር ግን ሙሉ ወንጌል ወይም የክህነት ስልጣን አልነበራቸውም። በዚህም ምክንያት፣ ከተቀየሩት ከክርስቶስ ወንጌል በተጨማሪ ሰዎች የወደፊት ትውልዶች አሳልፈው በሰጧቸው ተጽዕኖ ሲኖርባቸው፣ እያንዳንዱ ትውልድ የክህደት ሁኔታን ወረሱ።

እንደ ማርቲን ሉተር እና ጆን ካልቭን አይነት የተነሳሱ ሰዎች ስነስርዓቶች እና ትምህርቶች እንደተቀየሩና እንደጠፉ አውቀው ነበር። አባላት የነበሩባቸውን ቤተክርስቲያኖች ለማሻሻል ጣሩ። ያለ ክህነት ስልጣን ግን የክርስቶስ ወንጌል በመጀመሪያ ወደነበረበት እንደገና ለመመለስ አልተቻለም። በዳግም መመለስ አስፈላጊ ነበር።

እግዚአብሔር ክህደት እንደሚኖር አውቆ ነበር። በብሉይ ኪዳን ነቢይ በኩል እንዲህ አለ፥

“እነሆ፥ በምድር ላይ ራብን የምሰድድበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማት እንጂ እንጀራን ከመራብና ውኃን ከመጠማት አይደለም።

“ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ለመሻት ይርዋርዋጣሉ፥ አያገኙትምም።”

የወንጌል ዳግም መመልስ

በ1820 (እ.አ.አ)፣ በታሪክ እንዳደረገው፣ የሰማይ አባት ወንጌልን እና የክህነት ስልጣንን በምድር በዳግም ለመመለስ ነቢይ መረጠ። የእዚያም ነቢይ ስም ጆሴፍ ስሚዝ ነበር። በወጣትነቱ፣ ጆሴፍ በአካባቢው ባሉ ብዙ ቤተክርስቲያኖች መካከል ባለው ልዩነት ተምታትቶ እና የትኛው ቤተክርስቲያን እውነት እንደሆነ ለማወቅ ፈልጎ ነበር። ጥበብ እንደሌልው በማወቅ፣ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል” የሚለውን ምክር ተከተለ (ያዕቆብ 1:5)።

ጆሴፍ ስሚዝ እግዚአብሔርን ምን ማድረግ እንደሚገባው ለመጠየቅ ወሰነ። ጆሴፍ እውነትን ለማወቅ ሲጸልይ፣ የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጡ። ኢየሱስ ጆሴፍ “ሁሉም ስህተተኞች” ስለሆኑ እና ““በአፉ ወደ እኔ ለይቀርባሉ፣ ሐልባቸው ግን ከእኔ የራቀ ነው፣ የሰው መትእዛዛት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ፣ ሠየአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል” በማለት ከማንኛቸውም ቤተክርስቲያናት አባል እንዳይሆን ነገረው(ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1:19)።

እግዚአብሔር በአዳም፣ በኖኅ፣ በሙሴ፣ እና በሌሎች ነቢያት እንዳደረገው፣ በእርሱ በሙል የወንጌል ሟት በዳግም የሚመለስበት ነቢይ እንዲሆን ጆሴፍ ስሚዝን ጠራው።

የክህነት ስልጣን ዳግም መመለስ

በ1829 (እ.አ.አ)፣ ጆሴፍ ስሚዝ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋሪያቱ የሰጠው የክህነት ስልጣንን ተቀበለ። ኢየሱስን የጠመቀው መጥምቁ ዮሀንስ ወደ ጆሴፍ ስሚዝ መጣ እናም እርሱንም በአሮናዊ የክህነት ስልጣን ወይም በታናሹ የክህነት ስልጣን ሾመው። ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ እና ዮሀንስ (የኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ሐዋሪያት) በኋላም ወደ ጆሴፍ ስሚዝ መጡ እናም እርሱን በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን፣ ወይም በታላቁ የክህነት ስልጣን ሾሙት።

የክህነት ስልጣንን ከተቀበለ በኋላ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደገና በምድር ላይ እንዲመሰርት መመሪያ ተሰጠው። በእርሱም በኩል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና አስራ ሁለት ሐዋሪያትን ጠራ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሳኤ በኋላ ሐዋሪያቱን በራዕይ እንደመራ፣ ዛሬ ቤተክርስቲያኑን በህያው ነቢያት እና ሐዋሪያት በመምራት ቀጥሏል። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዘደንት ዛሬ የተመረጠ የእግዚአብሔር ነቢይ ነው። እርሱ፣ አማካሪዎቹ፣ እና አስራ ሁለቱ ሐዋሪያት የድሮ ጊዜ ነቢያት እና ሐዋሪያት በሙሉ የነበራቸው የክህነት ስልጣን አላቸው። እነዚህ ሰዎች ነቢያት፣ ባለራዕይ፣ እና ገላጮች ናቸው።

መፅሐፈ ሞርሞን

እንደ ወንጌል ዳግም መመለስ ክፍል፣ እግዚአብሔር መፅሐፈ ሞርሞን፥ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነትን አመጣ። በእግዚአብሔር ሀይል፣ ጆሴፍ ስሚዝ በወርቅ ሰሌዳዎች ላይ ከተጻፈውን የጥንት መዝገብ ይህን መፅሐፍ ተረጎመ። መፅሐፈ ሞርሞን “እግዚአብሔር በጥንት በአሜሪካ ከኖሩት ህዝቦች ጋር ያደረጋቸው ነገሮች መዝገብ ነው፣ እናም ዘለዓለማዊ የሆነውን የወንጌል ሙላት የያዘ ነው” (የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ)።

መፅሐፈ ሞርሞን የኢየሱስ ክርስቶስ ሀይለኛ ምስክር ነው። በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት በተጨማሪ፣ የእርሱን ትምህርቶች እንዲገባን ይረዳናል።

መፅሐፈ ሞርሞን ወንጌሉ በጆሴፍ ስሚዝ በዳግም እንደተመለሰ የሚያሳምን መረጃ ነው። መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ለእራሳችሁ ለማወቅ ትችላላችሁ። ይህን እውቀት ለማግኘት፣ ይህን ማንበብ፣ መልዕክቱን ማሰላሰል፣ እና ይህም እውነት እንደሆነ ለማወቅ ፍላጎት እንዲኖራችሁ ያስፈልጋችኋል። ይህ ቃሉ እንደሆነ ለማረጋገጥ የሰማይ አባትን መጠየቅ አለባችሁ። ይህን ስታደርጉ፣ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ይህ እውነት እንደሆነ ይገልፅላችኋል።

መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ስታውቁ፣ በመንፈስ ቅዱስ ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደሆነ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በእርሱ በኩል በዳግም እንደተመለሰ፣ እናም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በነብይ እና ሐዋሪያት ዛሬም እንደምትመራ ለማወቅ ትችላላችሁ።

እንዴት ለማወቅ እችላለሁ?

ይህ መልእክት እውነት እንደሆነ ለማወቅ ትችላላችሁ። የሰማይ አባታችሁን በጸሎት ከጠየቃችሁ፣ መልስ ከእርሱ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ለመቀበል ትችላላችሁ። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር መንፈስ ተብሎ ይጠራል፣ እናም ሀላፊነቱም ስለእውነት ምስክር ለመሆን፣ ወይም ለመመስከር፣ ነው።

ይህ እውቀት ታዕምራታዊ እና ህይወት የሚቀይር ለመሆን ይችላል፣ ነገር ግን የሚመጣው በእግዚአብሔር ሀይል አስደናቂ እይታ ሳይሆን፣ እንደ ጸጥተኛ ማረጋገጫ ነው። መንፈስ ቅዱስ እውነትን የሚያረጋገጠው በስሜታ፣ በሀሳቦች፣ እና በማነሳሻዎች ነው። በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደምንማረው፣ “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው” (ገላትያ 5:22–23)። በጆሴፍ ስሚዝ በኩል በዳግም የተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እውነት እንደሆነ ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጡት እነዚህ ስሜታዎች የግል ራዕዮች ናቸው። ከእዚያም ከተቀበላችሁት እውቀት ጋር በስምምነት ለመኖር መምረጥ ያስፈልጋችኋል።

  • በቀይ ቀለም ያሉት ቃላት በገጾች 18 እና 19 ውስጥ ተገልጸዋል።