ቅዱሳት መጻህፍት
ኤተር ፭


ምዕራፍ ፭

ሦስቱ ምስክሮች እናም ስራው እራሱ የመፅሐፈ ሞርሞንን እውነተኛነት ለመመስከር ይቆማሉ።

እናም እንግዲህ እኔ ሞሮኒ ባስታወስኩኝ መጠን የታዘዝኳቸውን ቃላት ፅፌአለሁ፤ እናም ያተምኳቸውን ነገሮች ነገርኳችሁ፤ ስለዚህ ትተረጉሟቸው ዘንድም አትንኳቸው፤ ከጊዜ ወደ ጊዜም በእግዚአብሔር ጥበብ ካልሆነ በቀርም ተከልክለዋልና።

እናም እነሆ፣ ይህንን ሥራ ለማምጣት ለሚረዱአችሁ ሰሌዳዎቹን ታሳዩአቸው ዘንድ ዕድሉም ይኖራችኋል፤

እናም በእግዚአብሔር ኃይልም ለሦስቱ የሚታዩ ይሆናሉ፤ ስለዚህ እነዚህ ነገሮች እውነት መሆናቸውን በእርግጥ ያውቃሉ

እናም በሦስት ሰዎች አንደበት፣ እናም በሦስቱ ምስክርነት እናም የእግዚአብሔር ኃይል በሚታይበት በዚህ ሥራ፣ እናም ደግሞ በአብ እናም በወልድ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ በሚመሰከርበት ቃል እነዚህ ነገሮች ይፀናሉ፤ እናም በመጨረሻው ቀንም ይህ ሁሉ በዓለም ላይ ለምስክርነት ይቆማል።

እናም እነርሱ ንሰሃ ቢገቡ፣ እናም በኢየሱስ ስም ወደ አብ ቢመለሱ፤ በእግዚአብሔር መንግስትም ተቀባይነትን ያገኛሉ።

እናም እንግዲህ፣ በእነዚህ ነገሮች ላይ ስልጣን ከሌለኝ እናንተ ፍረዱብኝ፤ ምክንያቱም እኔን ስትመለከቱኝ ስልጣን እንዳለኝ ታውቃላችሁና፣ እናም በመጨረሻው ቀን በእግዚአብሔር ፊት እንቆማለን። አሜን።