2022 (እ.አ.አ)
የቤተመቅደስ ስርዓቶች በረከት በሕይወታችን ውስጥ—አሁን እና ለዘላለም
ጥቅምት 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ ሰባዎች አመራር መልዕክት

የቤተመቅደስ ስርዓቶች በረከት በሕይወታችን ውስጥ—አሁን እና ለዘላለም

“በቅድመ አያቴ የተመዘገበው አስደናቂ ተሞክሮ ቅድመ አያቶቻችንን በቤተመቅደስ ስርዓቶች ስንረዳ ደስታቸው ታላቅ እንደሚሆን እንድናውቅ ይረዳናል።”

ከ40 ዓመታት በላይ ታላቅ አያቴ ጄ. ሃተን ካርፔንተር ለማንታይ ቤተመቅደስ እንደ መዝገብ ያዥ አገለገለ። በእያንዳንዱ ቀን በማንታይ ዩታ ካለው ቤቱ ወደ ማንታይ ቤተመቅደስ ግዴታውን እና ሃላፊነቱን ለመፈፀም ይሄድ ነበር። እንደ ቤተመቅደስ መዝገብ ያዥነቱ በቤተመቅደስ ውስጥ የተከናወኑ ቅዱስ መንፈሳዊ ልምዶችን ይገነዘብ ነበር።

ካካፈላቸው ልምዶች አንዱ አንድ ፓትርያርክ የተለያዩ ጥምቀቶችን በቤተመቅደስ ውስጥ ሲካሄዱ ማየቱን ያካትታል።

ፓትርያርኩ “ጥምቀትን እየፈፀሙላቸው ያሉትን ነፍሳት በመጠመቂያው ውስጥ” እንዳየ ይናገራል። እዛ ነፍሳቱ ተራቸውን በመጠበቅ ቆሙ፣ እና መዝገብ ያዡ የሚጠመቀውን ሰው ስም ሲጠራ፣ ስሙ በተጠራው ነፍስ ፊት ላይ ደስ የሚል ፈገግታ ሲመጣ እናም የተሰበሰቡትን ነፍሳት ትቶ ወደ መዝገብ ያዡ ጎን ሲቆም ፓትርያርኩ አስተዋሉ። እዛ በመቆም የግሉን ጥምቀት ይመለከታል፤ ከዛ በደስታ ስሜት የሚቀጥለው ሰው ተመሳሳይ እድልን እንዲያገኝ ቦታውን ለቆ ይሄዳል”።1

ጊዜ እየሄደ ሲመጣ፣ የተወሰኑት ነፍሳት ያዘኑ እንደሚመስሉ ፓትርያርኩ አስተዋሉ። ሰዎቹ በቤተመቅደስ ውስጥ ጥምቀትን ለዛ ቀን እንደጨረሱ ፓትርያርኩ ተገነዘቡ። ደስተኛ ያልሆኑት ነፍሳት ጥምቀታቸው በዛ ቀን ያልተፈፀመው ነበሩ።

ታላቅ ቅድመ አያቴ እያንዳንዱ ነፍስ ቅዱስ ስርዓቶችን ስለመቀበል ጥቅም ጠንካራ ምስክርነት ነበረው። እነዚህ ስርዓቶች በዚህኛው የመጋረጃው በኩል ላሉ እና በእዛኛው የመጋረጃ በኩል ላሉ በእግዚአብሔር ፊት ሃላፊነት ላለባቸው ሰዎች አስፈላጊ ናቸው። ስርዓቶቹ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ለመኖር በሚሄዱበት መንገድ ላይ ወደ ፊት እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል።2

ጊዜ እየሄደ ሲመጣ፣ የተወሰኑት ነፍሳት ያዘኑ እንደሚመስሉ ፓትርያርኩ አስተዋሉ። ሰዎቹ በቤተመቅደስ ውስጥ ጥምቀትን ለዛ ቀን እንደጨረሱ ፓትርያርኩ ተገነዘቡ። ደስተኛ ያልሆኑት ነፍሳት ጥምቀታቸው በዛ ቀን ያልተፈፀመው ነበሩ።

ታላቅ ቅድመ አያቴ እያንዳንዱ ነፍስ ቅዱስ ስርዓቶችን ስለመቀበል ጥቅም ጠንካራ ምስክርነት ነበረው። እነዚህ ስርዓቶች በዚህኛው የመጋረጃው በኩል ላሉ እና በእዛኛው የመጋረጃ በኩል ላሉ በእግዚአብሔር ፊት ሃላፊነት ላለባቸው ሰዎች አስፈላጊ ናቸው። ስርዓቶቹ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ለመኖር በሚሄዱበት መንገድ ላይ ወደ ፊት እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል።

ቅዱሳት መጻህፍት እንዲህ ያረጋግጣሉ፣ “ስለዚህ በዚህም ስርዓት ውስጥ የአምላክ አይነት ሀይል ይታያል። ካለዚህም ስርዓት እናም ካለክህነት ስልጣን የአምላክነት ሀይል ለሰዎች በስጋ አይታይም። ካለዚህ ማንም ሰው የእግዚአብሔርን ፊት እንዲሁም አብን ለመመልከት እና ለመኖር አይችልም።”3

እነዚህን ሥርዓቶች መቀበል የሰው መስፈርት አይደለም—የእግዚአብሔር መስፈርት ነው። ስርዓቶችን መቀበል ጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከተቀበልናቸው በኋላ ለእነዚህ ቅዱስ ስርዓቶች ለገባናቸው ቃል-ኪዳኖች እውነተኛ እና ታማኝ መሆን አስፈላጊ ነው።

ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ ውስጥ የሆኑት ሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራስባንድ ይህን ማበረታቻ አቅርበዋል፦ “የእርሱ መንፈስ በሙላት ከእናንተ ጋር እንዲሆን ‘ለጌታ ብቁ’ ለመሆን ሂደቱን አሁን ጀምሩ እናም የእርሱ መስፈርቶች ‘የህሊና ሰላምን’ ያመጣላችኋል። እዚህ ነገር ላይ ላተኩር፣ ቤተመቅደስ አቅራቢያችሁ ይኑርም አይኑር በቃል-ኪዳን መንገዱ ላይ ለመሆን ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ሊኖራችሁ ይገባል።”4

እነዚህን ሥርዓቶች መቀበል የሰው መስፈርት አይደለም—የእግዚአብሔር መስፈርት ነው። ስርዓቶችን መቀበል ጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከተቀበልናቸው በኋላ ለእነዚህ ቅዱስ ስርዓቶች ለገባናቸው ቃል-ኪዳኖች እውነተኛ እና ታማኝ መሆን አስፈላጊ ነው።

በብቁነት ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ መያዝ ለእግዚአብሔር አብ እና ለልጁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁ ምስክርነት ጠንካራ ነው ማለት ነው። ስለተመለሰው ቤተክርስቲያኑ ማለትም ስለ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዛሬ ምስክርነት አላችሁ ማለት ነው። ህያው ነብያቶችን እና ሐዋርያቶችን እናም የአካባቢ መሪዎቻችሁን ታግዛላችሁ እንዲሁም ትደግፋላችሁ ማለት ነው። እናም ቅዱስ ትዕዛዛትን እየጠበቃችሁ ነው እንዲሁም ለገባችኋቸው ቃል-ኪዳኖች ታማኝ ናችሁ ማለት ነው። ፍፁም ናችሁ ማለት አይደለም፣ ነገር ግን በቃል-ኪዳኑ መንገድ ላይ ናችሁ እናም የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርቶች በሕይወታችሁ ውስጥ ለመተግበር እየሞከራችሁ ነው ማለት ነው።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ እግዚአብሔር ወደ እርሱ መገኛ እንድንመለስ የሚረዱንን ቅዱስ ቃል-ኪዳኖችን ለመግባት እና ለመጠበቅ ለመርዳት ቤተክርስቲያኑን ከክህነት ስልጣኑ ጋር ሰጥቷል። እውነተኛ እና ታማኝ ከሆንን ቅዱስ ቤተመቅደሶች ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመሩንን ስርዓቶች እንድንቀበል ቦታን ይሰጣሉ። እነዚህ ተመሳሳይ ቤተመቅደሶች በሞት ለተለዩን የዘር ግንዶቻችን በተመሳሳይ ሥነ-ስርዓቶች ጥቅም እንዲያገኙ እድል ይሰጣሉ። ልንረዳቸው ይገባል። የእነሱ ደህንነት ለእኛ ደህንነት አስፈላጊ እና ጠቃሚ ነው። ጳውሎስ አባቶችን አስመልክቶ እንደተናገረው—“ያለ እኛ ፍፁማን ሊሆኑ አይችሉም—ወይም እኛ ያለሙታኖቻችን ፍፁም ልንሆን አንችልም።”5

ታላቅ ቅድመ አያቴ እንደመሰከረው፣ የዘር ግንዳችንን በእነዚህ ስርዓቶች ስንረዳቸው፣ ደስታቸው ታላቅ ይሆናል። ስንረዳቸው ወደ ፍፁምነት በምናደርገው መንገድ ውስጥ እኛም እንረዳለን።

ፕሬዝዳንት ኔልሰን፣ በሚያዚያ 2021 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ ይህንን ማሳሰቢያ አክለዋል፦

“ቤተመቅደሶች የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በሙሉነት መመለስ ላይ አስፈላጊ ክፍል ናቸው። የቤተመቅደስ ስርዓቶች ሕይወታችንን በሌላ መንገድ በማይገኝ ኃይል እና ጥንካሬ ይሞላሉ። ለእነዛ በረከቶች እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን።”6

ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለመያዝ እያንዳንዳችን በብቁነት እንኑር። ሁሌም ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን ለመያዝ እንሻ። ግላዊ ሁኔታዎች እስከፈቀዱልን ድረስ ቤተመቅደስን በብዛት እንሳተፍ። ይህን ስናደርግ፣ ሕይወታችን በሌላ መንገድ በማይገኝ በበለጠ ኃይል እና ጥንካሬ እንደሚሞላ ያለኝን ምስክርነት በፕሬዚዳንት ኔልሰን ምስክርነት ላይ አክላለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማቲው ኤል. ካርፔንተር እንደ አጠቃላይ የሰባዎች ባለስልጣን የተጠሩት በመጋቢት 2018 (እ.አ.አ) ነበር። ከሚሼል (ሼሊ) ኬይ ብራውን ጋር ትዳር መስርተዋል፤ የአምስት ልጆች ወላጆች ናቸው።

ማስታወሻዎች

  1. ከጆሴፍ ሂነርማን፣ Temple Manifestations [ማንታይ ዩታ፦ Mountain Valley Publishers፣ 1974 (እ.አ.አ)]፣ ገፅ 101–2 የተወሰደ፤ እንዲሁም The Utah Genealogical and Historical Magazine 11 [ነሐሴ 1920 እ.አ.አ]፦ 119 ይመልከቱ።

  2. ጆሴፍ ሄነርማን፣ Temple Manifestations፣ 102።

  3. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 84፥20–22።

  4. ሮናልድ ኤ. ራስባንድ፣ “Recommended to the Lord”፣ ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ) ይመልከቱ።

  5. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 128:15።

  6. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “COVID-19 and Temples”፣ ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 እ.አ.አ።