2022 (እ.አ.አ)
አለምአቀፍ ፖዝዌይ = ትምህርት ለተሻለ ስራ
ጥቅምት 2022 (እ.አ.አ)


አለምአቀፍ ፖዝዌይ = ትምህርት ለተሻለ ስራ

ለብዙ አፍሪካውያን ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው የመስመር ላይ ሶስተኛ ደረጃ ትምህርት ለተሻለ ወደፊት መንገድ እየቀደደ ነው።

የአካባቢ ዜናዎች

ቢዋይዩ አለም አቀፍ ፓዝዌይ ለአፍሪካ ሀገራት የተተዋወቀው ከጥቂት አመታት በፊት ነበር እናም በአሁጉሩ ላይ የብዙዎችን ህይወት እየቀየረ ነው። አባል እና አባል ያልሆኑን በተመሳሳይ ወደ 2000 የሚቃረቡ ተማሪዎችን አገልግሏል። ከሚስዮን የተመለሱ ሚስዮናዊያን ለቢዋይዩ ፓዝዌይ ቅድመ ፍቃድ ይሰጣቸዋል እና ሲመዘገቡ የ25% ቅናሽ ይሰጣቸዋል። ሁሉም ተማሪዎችም የትምህርት ክፍያቸውን በ50% ሊቀንስ ለሚችለው የሄበር ጄ. ግራንት ስኮላርሺፕ ብቁ ናቸው። በተጨማሪም እንግሊዘኛ ተናጋሪ ያልሆኑ ተማሪዎች በኢንግሊሽ ኮኔክት (EnglishConnect) እንግሊዘኛ የመማር እድል አላቸው እና ከዛም ፓዝዌይኮኔክት ውስጥ ይመዘገባሉ። የመጀመሪያ ድግሪያቸውን እየሰሩ ብዙ ተማሪዎች ስራ እንደተቀጠሩ፣ እድገት እንዳገኙ፣ ወይም የነበራቸውን ቢዝነስ እንዳስፋፉ ይዘግባሉ።

የናይሮቢ ኬንያ የአፐርሂል አጥቢያ አኔት ናንኩምባዎ በጀመሪያ ስለ ቢዋይዩ ፓዝዌይ ያወቀችው በኮትዲቯር ውስጥ ከሚስዮን ፕሬዘዳንቷ ነበር። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷ ዝቅተኛ ውጤት ሳቢያ የዩንቨርሲቲ ትምህርት ለመቀጠል ፈርታ ነበር። ከሚስዮን ከተመለሰች ከጥቂት ወራቶች በኋለ በፓዝዌይኮኔክት ለመመዝገብና የመጀመሪያ ድግሪ ለማግኘት ጉዞዋን ለመጀመር ወሰነች። ይህ ከቤተሰቧ የመጀመሪያዋ የዩኒቨርስቲ ተመራቂ ያረጋታል። “ፓዝዌይኮኔክት ትልቅ በረከት ሆኖኛል። በመጀመሪያ የወሰድኩት ኮርስ የእድገት አስተሳሰብ ስለመያዝ አስተምሮኛል። ከበፊቱ በተለየ አሁን ላይ ውድቀትን የምመለከተው እንደማደጊያ እድል ነው።” ብላለች።

አኔት በይበልጥ እንዲህ አብራርታለች “ቋሚ የሆነ አስተሳሰብ ያለው ሰው ውድቀትን ይፈራል፣ ነገሮች ከባድ ሲሆኑ ተስፋ ይቆርጣል፣ እና እራሳቸውን ጎብዝ እንዳልሆኑ አድርገው ያያሉ። በትምህርት መንገዴ ላይ በትኩረት ለመቆየት አወንታዊ መሆን አለብኝ እና ችግሮቹ ውስጥ እየመራ በሚረዳኝ የሰማይ አባቴ ማመን አለብኝ።” አኔት የተሻለ የፋይናንስ አስተዳደርም እንደተማረችና በትንሽ ቢዝነሷ ውስጥ እየረዳት እንደሆነ ትናገራለች። “የአስራት ክፍያን እንዳስቀድም ተምሬያለው፣ እና አሁን ይበልጥ በህይወቴ የአዳኙ ምሪት ይሰማኛል። በሳምታዊ አምልኮዎች እና የኢንስቲቲዩት ሀይማኖት ክፍሎች እየተነሳሳሁ ነው፤ ይህ ሁሉ ነገር በአዳኙ ላይ እምነቴን እንድጨምር እየረዳኝ ነው። ከባድ ነገሮችን ማሳካት እንደምችል አውቃለሁ!”

ፊኒያስ ኛምቢታ እና ባለቤቱ ካሮላይን የቢዋይዩ ፓዝዌይ ተማሪዎች ናቸው። ፊኒያሥ ከሚስዮኝ የተመለሰ ሚስዮናዊ ነው እና በዳሬሰላም ታንዛኒያ ቅርንጫፉ ውስጥ የቅርንጫፍ ፕሬዘዳንት ሆኖ ያገለግላል። በአፕላይድ ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ድግሪውን እያጠና ያለው ፊኒያስ እንዲህ ብሏል “ፕሮግራሙ ደስ ይለኛል ምክንያቱም ሙሉ ጊዜ እየሰራሁና ክፍሎቼን እየተካፈልኩ ነው። ባል እና አባት፣ የቤተክርስቲያን መሪ መሆን እና የተማሪነት ተጨማሪ ሀላፊነት መጨመር ከባድ ስሜት ሊኖረው ይችላል። ሆኖም በትልቅ ስኬት ሊሰራ እንደሚችል ተመልክቻለው።” ወደቻንጎንቤ ቅርንጫፍ እና ወደ ሌሎች ቦታዎች በመዞር ፊኒያስ ይህን ምክር ይሰጣል “ጌታ በዚህ ህይወት ስኬታማ እንድንሆን እንደሚፈልግ አውቃለው።

“ቢሆንም ግን በእምነት ካልሰራን ስኬት ላይመጣ ይችላል። እንደ አባቶች፣ እናቶች፣ መሪዎች፣ እና ወጣቶች ብዙ ነገሮች ሊኖሩብን ይችላል። ከእምነት እና ቅድሚያ አሰጣጥን ለመማር ካለን ፍላጎት ጋር ስኬታማ ልንሆን እችላለን። ወደፊት በሚመጡ እድሎች ውስጥ ስኬታማ ለመሆን መሰረትን ለመገንባት ትምህርታቸውን ወደፊት መግፋት ለሚፈልጉ ሁሉ ቢዋይዩ ፓዝዌይ ያግዛል።”

ካሮላይን የፓዝዌይኮኔክት የምስክር ወረቀት ይዛለች እናም ከጥቂት ወራቶች በፊት የሁለተኛ ልጃቸውን ለመውለድ ትምህርቷን ላጭር ጊዜ ማቆም ነበረባት። “መጪው መስከረም ላይ በድጋሚ እጀምራለሁ፣ ተመዝግቤያለው።” ብላለች። በፓዝዌይኮኔክት ውስጥ ጉዞዋን ወደኋላ በመመልከት ካሮላይን “ጉዞው ቀላል አልነበረም ምክንያቱም እንደእናቶች ብዙ መፈጸም ያሉብን ነገሮች አሉ። ነገርግን ከእምነትና ከቢዋይዩ ፓዝዌይ ትምህርቶች ጋር ወደፊት ቀጥዬ ፓዝዌይኮኔክትን ጨርሻለሁ። ወደፊት መግፋቴን ለመቀጠል ሳምንታዊ አምልኮዎች የየቀኑ መነሻሻዎቼ ነበሩ። እንደኔው ተማሪዎችን በሳምታዊ ስብሰባዎቻችን ማግኘትና የነሱን ልምድ ማዳመጥ ገንብቶኛል እናም አበረታቶኛል። ትምህርቴን እንድጨርስ ለእርዳታና ጥንካሬ የሰማይ አባቴን ተማጽኛለሁ።”

የፓዝዌይ ድግሪ መከታተል አንዳንድጊዜ ረጅምና ትግስት ጠያቂ ሂደት ነው። ዳዲ ካምፖይ ዴቪድ ልምዱን ያካፍላል። “ታዳጊ ቤተሰብ እና የሙሉ ጊዜ ስራ አለኝ። በዲአርሲ ባንዳሉንግዋ አጥቢያ እንደ መጀመሪያ አማካሪ አገለግላለሁ እናም በእንግሊሽኮኔክት ፕሮግራም ውስጥ አስተምራለው። ለማጥናት ያለኝ ሰአት በጣም ውስን ነው። ዲግሪዬን የጀመርኩት በ2020(እ.አ.አ) ነው እናም በ2024(እ.አ.አ) ለመጨረስ ተስፋ አደርጋለሁ። ለማጥናት፣ ቤተሰቤን ለመንከባከብ፣ ሙሉቀን ለመስራት፣ እና ማታ ቤት ከመመለሴ በፊት ለተወሰነ ሰአት ለማጥናት ለሊት 11 ሰአት እነሳለሁ። ከፈተና በፊት ለማጥናት የጥቂት ጊዜ እረፍት እወስዳለሁ። ይሄ ድግሪ እንደሰው እንዳድግ እና ለቤተሰቤ ይበልጥ የተረጋገጠ ህይወት እንድሰጣቸው እንደሚረዳኝ አውቃለሁ። ይሄ የሚከፈለው ዋጋ እንደሚገባው አውቃለው!”

ፕሬዘደንት ረስል ኤም. ኔልሰን ይህን ግብዣና ቃልኪዳን አሳልፈዋል፤ “አለም አቀፍ ቢዋይዩ ፓዝዌይ ለትምህርት አዲስ የፈጠራ ዘዴን ያመጣል። እያንዳንዱን ሰው ምንም እድሜ ላይ ቢሆኑ መማራቸውን እንዲቀጥሉ አበረታታለሁ። ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ የበለጠ ጠቃሚ የሚሆነውን ማንኛውም መንገድ ተከተሉ። ይህን ስታደርጉ ትባረካላችሁ። ትምህርታችሁን ለማጎልበት ስትሹ በትምህርት፣ በሙያችሁ፣ እና በመንፈሳዊ ታድጋላችሁ።”1

ቢዋይዩ ፓዝዌይ ለሁሉም ክፍት ነው። ትምህርታቸሁን ወደፊት ለመግፋት ፍላጎት ካላችሁ እባካችሁ www.byupathway.org ን ጎብኙ።

ማስታወሻዎች

  1. ፕሬዝዳንት ኔልሰን፣ አለምአቀፍ የቢዋይዩ ፓዝዌይ ምረቃ፣ 16 ህዳር 2017 (እ.አ.አ)።

አትም