የመመሪያ መጽሃፍ ጎላ ጎላ ያሉ ነጥቦች
ቡራኬያችሁን ተቀበሉ
የክህነት መሪዎች ወይም የቤተክርስቲያኗ አባላት “ቡራኬዎቻችሁን ለመቀበል ተዘጋጁ” ብለው ሲያበረታቱዋችሁ ሰምታችኋል? ምን እንደሆነ እያሰላሰላችሁ ይሆናል። የአጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ እንዲህ ያብራራል፦
“ቡራኬ የሚለው ቃል ትርጉም ‘ስጦታ’ ማለት ነው” ይላል አጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ። “የቤተመቅደስ ቡራኬ እግዚአብሔር ልጆቹን የሚባርክበት ከሱ የሆነ ስጦታ ነው።ቡራኬን መቀበል የሚቻለው በቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ ብቻ ነው።በቤተመቅደስ ቡራኬ አማካኝነት አባላት የሚቀበሉት አንዳንድ ስጦታዎች እነኚህን ያካትታሉ፦”
-
በጌታ አላማዎች አና ትምህርቶች ላይ የበለጠ እውቀት።
-
የሰማይ አባት ልጆቹ እንዲያደርጉ የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ሀይል።
-
ጌታን፣ ቤተሰባቸውን፣ እና ሌሎችን ሲያገለግሉ መለኮታዊ ምሪት።
-
የበለጠ ተስፋ፣ መጽናኛ፣ እና ሰላም።
ወደጥምቀታችሁ የአንደኛ አመት ክብረ በአል ስትቃረቡ ለቡራኬያችሁ ለመዘጋጀት ቀጣዮቹን ነገሮች እንድታረጉ አጠቃላይ መመሪያ መጽሐፉ ሀሳብ ይሰጣል።
በመጀመሪያ የቤተመቅደስ መዘጋጃ ክፍሎችን መሳተፍ ጀምሩ።
ሁለተኛ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ለመቀበል ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር ቃለመጠይቅ ለማድረግ ቀን አውጡ።
ሶስተኛ ቡራኬያችሁን ለመቀበል ከቤተመቅደሱ ጋር ቀን ወስኑ።
ቡራኬን መቀበል አዲስ እና አጓጊ የሆነ ልምድ ነው። ከመሄዳችሁ በፊት ጥያቄ ሊኖራችሁ ይችላል እናም ከሄዳችሁ በኋላ ምናልባት ተጨማሪ ሊኖራችሁ ይችላል።ብዙ ጊዜ ለሄዱ ግለሰቦች እንኳን የመማር ሂደት ነው።ወደ ቤተመቅደስ መመለሳችሁን ስትቀጥሉ ግንዛቤያችሁ ይጨምራል።