ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያንን እንዴት እንደምንጠቀም


ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያንን እንዴት እንደምንጠቀም፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 ( እ.አ.አ)]

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያንን እንዴት እንደምንጠቀም፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ጥንዶች አብረው ሲያጠኑ

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያንን መጠቀም

ይህ ጽሁፍ ለማን ነው?

ይህ ጽሁፍ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን—በግለሰብ ደረጃ፣ እንደ ቤተሰብ እና በቤተክርስቲያን ክፍሎች ውስጥ ለማጥናት ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው ይሆናል። ከዚህ በፊት ቅዱሳት መጻህፍትን ዘወትር የማታጠኑ ከነበረ፣ ይህ ጽሁፍ እንድትጀምሩ ይረዳችኋል። ቀድሞውኑ በቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ጥሩ ልምድ ካላችሁ፣ ይህ ጽሁፍ የበለጠ ትርጉም ያለው ተሞክሮ እንዲኖራችሁ ይረዳል።

ግለሰቦች እና ቤተሰቦች በቤት

ከሁሉም የተሻለው ወንጌልን የመማሪያ ስፍራ ቤት ነው። በቤተክርስቲያን ያሉ አስተማሪዎቻችሁ ሊረዷችሁ ይችላሉ፣ እንዲሁም ከሌሎች የአጥቢያ አባላት ማበረታቻ ልታገኙ ትችላላችሁ። ሆኖም በመንፈሳዊነት ለመቀጠል፣ እያንዳንዳችን ዕለት ተዕለት “የእግዚአብሔርን መልካም ቃል” መመገብ ይኖርብናል፤(ሞሮኒ 6፥4 እንዲሁም ራስል ኤም. ኔልሰን“የመክፈቻ ንግግር፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 [እ.አ.አ] 6–8 ተመልከቱ)።

ይህንን ጽሁፍ እናንተን በሚረዳ በማንኛውም መንገድ ተጠቀሙበት። መዘርዝሮቹ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የሚገኙትን አንዳንድ ዘለአለማዊ እውነቶች ያጎላሉ። በተጨማሪም በግለሰብ ደረጃ፣ ከቤተሰባችሁ ወይም ከጓደኞቻችሁ ጋር ቅዱሳት መጻህፍትን ለማጥናት የሚረዱ ሃሳቦችን እና አክቲቪቲዎችን ይጠቁማሉ። በምታጠኑበት ጊዜ፣ ለእናንተ ትርጉም ያላቸውን ዘለአለማዊ እውነቶች እንድታገኙ የመንፈስን ምሪት ተከተሉ። እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን መልዕክት ፈልጉ እንዲሁም የምትቀበሏቸውን መነሳሳቶች ተከተሉ።

አስተማሪዎች እና ተማሪዎች በቤተክርስቲያን

የመጀመሪያ ክፍልን፣ የወጣቶች ወይም የጎልማሶች የሰንበት ትምህርት ክፍልን፣ የአሮናዊ ክህነት ቡድንን ወይም የወጣት ሴቶች ክፍልን የምታስተምሩ ከሆነ ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ያሉትን መዘርዝሮች እንድትጠቀሙ ትበረታታላችሁ። ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤታችሁ ስርዓተ ትምህርት ነው። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ያሉት የትምህርት ሃሳቦች በቤት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመማር የተዘጋጁ ናቸው። ለማስተማር ስትዘጋጁ፣ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የራሳችሁን ተሞክሮዎች በማግኘት ጀምሩ። እጅግ አስፈላጊው ዝግጅታችሁ የሚከናወነው ቅዱሳት መፃህፍትን ስትመረምሩ እና ከመንፈስ ቅዱስ የግል መነሳሳትን ስትሹ ነው። የምታስተምሯቸውን ሰዎች ፍላጎቶች በአዕምሯችሁ በመያዝ ልታጠኑም ትችላላችሁ። ዘለዓለማዊ እውነቶችን ፈልጉ። ኑ፣ ተከተሉኝ እነዚህን አንዳንድ እውነቶች እንድትለዩ እና ቅዱሳት መፃህፍትን እንዴት በህይወታችሁ ለመጠቀም እንደምትችሉ እንድትገነዘቡ ሊረዳችሁ ይቸላል።

ወንጌልን ለመማር ከሁሉም የተሻለው ቤትን ማዕከል ያደረገ እና በቤተክርስቲያን የተደገፈ ሲሆን እንደሆነ አስታውሱ፡፡ በሌላ አነጋገር የእናንተ ዋና ኃላፊነት የምታስተምሯቸው ሰዎች ወንጌልን በቤት ውስጥ ለመማር እና ለመኖር የሚያደርጉትን ጥረት መደገፍ ነው። በክፍል ውስጥ ለእነርሱ ስለምታቀርቡት የተለየ ይዘት አታስቡ። ከዚያ ይልቅ ልምዶቻቸውን፣ ሃሳቦቻቸውን እና በቤታቸው በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ስላነበቧቸው ምንባቦች ያሏቸውን ጥያቄዎች እንዲያካፍሉ እድሎችን ስጧቸው። ያገኟቸውን ዘለአለማዊ እውነቶች እንዲያጋሩ ጋብዟቸው። ይህ፣ የጽሁፍን የተወሰነ ክፍል ከመሸፈን የበለጠ አስፈላጊ ነው።

የወጣቶች እና የጎልማሶች የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍሎች

በሰንበት ትምህርት ቤት ክፍሎች የምንሰበሰብበት አንዱ ዋና ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል በምናደርገው ጥረት እርስ በርስ ለመደጋገፍ እና ለመበረታታት ነው። ይህንን ማድረግ የሚቻልበት ቀላሉ መንገድ “በዚህ ሳምንት ኑ፣ ተከተሉኝን በመጠቀም ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠኑ መንፈስ ቅዱስ ምን አስተማራችሁ?” የሚል ጥያቄን በመጠየቅ ነው። የዚህ ጥያቄ መልሶች በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ ላይ ያለን እምነት ወደሚገነባ ትርጉም ያለው ውይይት ሊያመራ ይችላል።

ከዚያም በኑ፣ ተከተሉኝ ውስጥ ባሉት የጥናት ሐሳቦች ላይ በመመርኮዝ ውይይት እንዲደረግ መጋበዝ ትችላላችሁ። ለምሳሌ አንድ የጥናት ሃሳብ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥15–20ን ማውጣትን እና አዳኙ ሥቃዩን እንዴት እንደገለፀ መፈለግን ሊጠቁም ይችላል። የክፍል አባላት የእርሱን ገለፃ ሲያነቡ እንዴት እንደተሰማቸው እንዲያካፍሉ ልትጠይቋቸው እንዲሁም ይህ ስለእርሱ በሚያስቡበት መንገድ ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንደሚያደርግ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ወይም ጊዜ ወስዳችሁ እነዚህን ጥቅሶች በክፍል ደረጃ በጋራ ልታጠኗቸው ትችላላችሁ።

የአሮናዊ ክህነት ቡድኖች እና የወጣት ሴቶች ክፍሎች

የአሮናዊ ክህነት ቡድኖች እና የወጣት ሴቶች ክፍሎች በየእሁዱ በሚገናኙበት ጊዜ፣ ዓላማቸው በተወሰነ መልኩ ከሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል የተለየ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመማር ረገድ እርስ በርስ ከመረዳዳት በተጨማሪ፣ በክፍል እና በቡድን አመራሮች በሚሰጠው መመሪያ መሰረት፣ እነዚህ ቡድኖች የመዳን እና በዘለአለም ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግ ስራን ስለማከናወን በጋራ ለመምከር ይገናኛሉ (አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል1.2 ተመልከቱ)።

በዚህ ምክንያት፣ አንድ የቡድን ወይም የክፍል አመራር አባል ስለጥረቶቻቸው ውይይትን በመምራት እያንዳንዱ የቡድን ወይም የክፍል ሥብሠባ መጀመር ይገባዋል። ለምሳሌ፣ ወንጌልን ስለመኖር፣ የተቸገሩ ሰዎችን ስለማገልገል፣ ወንጌልን ስለማካፈል ወይም በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ሥራ በመሳተፍ ረገድ ስለሚደረጉ ጥረቶች በጋራ ሊወያዩ ይችላሉ።

ከዚህ በጋራ ከሚመካከሩበት ጊዜ በኋላ፣ አንድ አስተማሪ ወንጌልን በአንድ ላይ በመማር ረገድ ክፍሉን ወይም ቡድኑን ይመራል። ጎልማሳ መሪዎች ወይንም የክፍል ወይንም የቡድን አባላት እንዲያስተምሩ ሊመደቡ ይችላሉ። የክፍል ወይንም የቡድን አመራር ከጎልማሳ መሪዎች ጋር በመመካከር እነዚህን ምደባዎች ያከናውናሉ።

እንዲያስተምሩ የሚመደቡ ሰዎች በኑ፣ ተከተሉኝ ሳምንታዊ መዘርዝር ውስጥ ያሉትን የመማር ሃሳቦች በመጠቀም መዘጋጀት አለባቸው። በእያንዳንዱ መዘርዝር ውስጥ ያለው ይህ ምልክት በተለይ ለወጣቶች የሚሆን እና በሴሚናሪ እየተማሩት ካለው ትምህርት ጋር የተስማማ አክቲቪቲ እንደሆነ ያሳያል። ሆኖም በመዘርዝሩ ውስጥ ያሉት ማንኛቸውም ሃሳቦች ለወጣቶች የትምህርት አክቲቪቲ በመሆን ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

ለቡድን ወይም ለክፍል ስብሰባዎች ናሙና አጀንዳ ለማግኘት አባሪ መን ተመልከቱ።

የመጀመሪያ ክፍል

የመጀመሪያ ክፍልን ለማስተማር የምታደርጉት ዝግጅት የሚጀምረው በግል እንዲሁም ከቤተሰባችሁ ጋር መጽሐፈ ሞርሞንን በምታጠኑበት ጊዜ ነው። ይህንን ስታደርጉ፣ በመጀመሪያ ክፍላችሁ ውስጥ ያሉትን ልጆች አስመልክቶ ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጡ መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን እና ሃሳቦችን ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ። በፀሎት መንፈስም ሁኑ። መንፈስ እነርሱን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲማሩ ትረዷቸው ዘንድ በሃሳቦች ሊያነሳሳችሁ ይችላል።

ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ፣ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ያሉትን የማስተማሪያ ሃሳቦች በማገላበጥ ተጨማሪ መነሳሳትን ልታገኙ ትችላላችሁ። በኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው እያንዳንዱ መዘርዘር “ልጆችን ለማስተማር የሚጠቅሙ ሃሳቦች” የሚል ክፍል አለው። እነዚህን ሀሳቦች መነሳሳት እንዲሰማችሁ እንደሚያደርጉ ጥቆማዎች ውሰዷቸው። በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ያሉትን ልጆች ታውቋችዋላችሁ—እንዲሁም ከእነርሱ ጋር በክፍል ውስጥ በምትገናኙበት ጊዜ የበለጠ ታውቋችዋላችሁ። እግዚአብሔርም ያውቃቸዋል፣ ስለዚህም እነርሱን ለማስተማር እና ለመባረክ በምትችሉባቸው ከሁሉም በተሻሉ መንገዶች ያነሳሳችኋል።

በክፍላችሁ ያሉ ልጆች በኑ፣ ተከተሉኝ ውስጥ ያሉትን አንዳንድ አክቲቪቲዎች አስቀድመው ሰርተው ሊሆን ይችላል። ያ መልካም ነው። መደጋገም ጥሩ ነው። ልጆቹ በቤት የተማሩትን አንዳቸው ለሌላቸው እንዲያካፍሉ መጋበዝን ግምት ውስጥ አስገቡ። ልጆቹ በቤት ውስጥ እየተማሩ ባይሆንም እንኳን ሊሳተፉ የሚችሉባቸውን መንገዶች ማቀድም አለባችሁ። ልጆች እነዚህን እውነቶች በተለያዩ አክቲቪቲዎች በተደጋጋሚ ሲማሩ የወንጌልን እውነቶች በላቀ ብቃት ይማራሉ። አንድ የመማሪያ አክቲቪቲ ለልጆቹ ውጤታማ ሆኖ ካገኛችሁት፣ በተለይ ትንንሽ ልጆችን እያስተማራችሁ ከሆነ በድጋሚ ማቅረብን ግምት ውስጥ አስገቡ።

አምስት እሁዶች ባሏቸው ወራት ውስጥ፣ የመጀመሪያ ክፍል አስተማሪዎች በአምስተኛው እሁድ መርሐ ግብር የተያዘለትን ኑ፣ ተከተሉኝ መዘርዝር በ“አባሪ ለ፦ ለመጀመሪያ ክፍል—ልጆችን ለእድሜልክ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ እንዲሆኑ ማዘጋጀ” ውስጥ ባሉት አንድ ወይም ከአንድ በላይ የትምህርት አክቲቪቲዎች እንዲተኳቸው ይበረታታሉ።

አትም