ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሰኔ 9–15፦ “እነሆ፣ ዘወትር ከታማኙ ጋር ነኝ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60–63


“ሰኔ 9–15፦ ‘እነሆ፣ ዘወትር ከታማኙ ጋር ነኝ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60–63፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60–63፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ካምፋየር በሚዙሪ ወንዝ አጠገብ

ዝርዝር ከCampfire on the Missouri[ካምፋየር በሚዙሪ]፣ በብራያን ማርክ ቴይለር

ሰኔ 9–15፦ “እነሆ፣ ዘወትር ከታማኙ ጋር ነኝ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60–63

ነሐሴ 1831 (እ.አ.አ) መጀመሪያ ላይ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች “በጽዮን ምድር” አጭር ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ወደ ከርትላንድ ለመመለስ በዝግጅት ላይ ነበሩ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥3)። ጌታ በጉዟቸው ላይ ወንጌልን እንዲሰብኩ ፈልጎ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 52፥10) እናም አንዳንዶቹ ይህንኑ በትጋት አደረጉ። ሌሎች ግን አመንትተው ነበር። ጌታም፣ “ሰውን በመፍራት የሰጠኋቸውን ችሎታ ደብቀዋል” ሲል ተናግሯል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥2)። ብዙዎቻችን እነዚህ ሽማግሌዎች እንዴት ተሰምቷቸው እንደነበረ እናውቃለን። ለወንጌል ፍቅር ቢኖረንም ፍርሃት እና ጥርጣሬ ከማካፈል ሊገቱን ይችላሉ። ይሁንና ጌታ ይቅር ባይ ነው። “የሰውን ድክመት እና … እንዴት [እንደሚረዳን] ያውቃል” (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 62፥1)። ለቀደምት ሚስዮናውያን በተሰጠው በዚህ ራዕይ ውስጥ ፍርሃቶቻችንን እና ድክመቶቻችንን ለመቋቋም ሊረዱን የሚችሉ ማረጋገጫዎች ይገኛሉ፦ “ቅዱሳን አደርጋችሁ ዘንድ ይቻለኛልና”። “ሁሉም ስጋ በእጄ ነው።” “እነሆ፣ ዘወትር ከታማኙ ጋር ነኝ።” እንዲሁም “ታማኝ የሆነው እና የሚጸናውም አለምን ያሸንፋል።” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥761፥662፥963፥47።)

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፤ 62

ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝን ፍቅር እና ምስክርነት ማካፈል እችላለሁ።

የወንጌል ምስክርነታችሁ “የተፈጥሮ ስጦታ“ ወይም ከእግዚአብሔር የተሰጠ ሃብት የሆነው እንዴት ነው? አንዳንድ ጊዜ “ችሎታ[ችንን] [የምንደብቀው]” በምን ዓይነት መንገዶች ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥2፤ በተጨማሪም ማቴዎስ 25፥14–30 ተመልከቱ)።

ክፍል 60 እና 62 ውስጥ ከጌታ ምን አበረታች መልዕክቶችን ታገኛላችሁ? እነዚህ መልዕክቶች ወንጌልን በማካፈል ረገድ በራስ መተማመናችሁን የሚገነቡት እንዴት ነው? በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ ስታሰላስሉ፣ “I Want to Be a Missionary Now፣” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣168) የሚለውን መዝሙር መዘመርን ወይም ቃላቶቹን ማንበብን ልታስቡ ትችላላችሁ። ከዚህ የልጆች መዝሙር ውስጥ ወንጌልን ስለማካፈል ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም “የወንጌልን ማጋራት” ስብስቦችን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

ወንጌልን በአውቶቡስ ውስጥ ማካፈል።

በክርስቶስ ያለኝን እምነት ለማካፈል ግልፅ መሆን እችላለሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥2–461፥1–22036–3862፥1፣ 6

ቅዱሳት መጻህፍት ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምራሉ።

የእርሱን ሚስዮናውያን ባስተማራቸው ጊዜ፣ ጌታ ስለእራሱ ጠቃሚ እውነቶችን ገልጿል። እነዚህን እውነቶች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥2–461፥1–2፣ 20፣ 36–3862፥1፣ 6 ውስጥ ፈልጉ። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ያገኛችኋቸው የአዳኙን ሚናዎች እና ባህርያት የሚገልጹት የትኞቹ ዘገባዎች ናቸው? (ለምሳሌ፣ ዮሀንስ 8፥1–11ኤተር 2፥14–15 ተመልከቱ)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 62

ውሳኔዎቼ “በማመዛዘን እና መንፈስም [እንደመራኝ]” የተመጣጠኑ መሆን አለባቸው።

ጌታ ስለዘለዓለማዊ እውነቶች እና መርሆዎች መመሪያ ይሰጣል፣ ነገር ግን ብዙ ጊዜ እነዚህን መርሆዎች እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንዳለብን የሚመለከቱ የተለዩ ዝርዝሮችን እንድንወስን ለእኛ ይተውልናል። ይህ መርህ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 62 ውስጥ ተገልፆ የምታዩት እንዴት ነው? (በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥561፥22 ተመልከቱ)። ይህንን መርህ በህይወታችሁ ውስጥ ያያችሁት እንዴት ነው? እግዚአብሔር በትክክል ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲነግረን ሳንጠብቅ አንዳንድ ውሳኔዎችን ማድረጋችን ለእኛ ጥሩ የሚሆነው ለምንድን ነው?

በተጨማሪም ኤተር 2፥18–25ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥27–28 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥7–12

ምልክቶች የሚመጡት በእምነት እና በእግዚአብሔር ፍላጎት ነው።

በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ዕዝራ ቡዝን በጣም ያስደነቀ የተዓምር ምሳሌ ይገኛል፦ የኤልሳ ጆንሰን ክንድ በተዓምር ተፈውሶ ነበር። ያንን ካየ በኋላ ዕዝራ በጉጉት ተጠመቀ። ሆኖም በጥቂት ወራት ውስጥ ቡዝ እምነቱን አጣ እንዲሁም ነቢዩን የሚተች ሆነ። አይቶ የነበረውን ተዓምር ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥7–12ን ስታነቡ ይህንን አሰላስሉ። ስለምልክቶች እና ስለእምነት ምን እውነቶችን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ማቴዎስ 16፥1–4ዮሐንስ 12፥37ሞርሞን 9፥10–21ኤተር 12፥12፣ 18ን ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥16

የሴሚናሪ ምልክት
በሃሳቤ እና በድርጊቴ ንፁህ መሆን እችላለሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፦16 ውስጥ፣ አዳኙ በአዲስ ኪዳን ያስተማረውን በድጋሚ አረጋግጧል—የንፅህና ህግ ድርጊቶቻችንን ብቻ ሳይሆን ሀሳቦቻችንንም መምራት አለበት (ማቴዎስ 5፥27–28 ተመልከቱ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥16ን ስታነቡ፣ አዳኙ ስለምኞት ሃሳቦች የሰጣቸውን ማስጠንቀቂያዎች መዝግቡ። በእያንዳንዱ ማስጠንቀቂያ ተቃራኒ ላይ ማሰላሰልም ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ የፍርሐት ተቃራኒ የሆኑ አንዳንድ ቃላት እና ሐረጎች ምን ምን ናቸው? የንጹህ ሐሳቦች እና ድርጊቶች ባለቤት በመሆን ሌሎች ምን በረከቶች ይመጣሉ?

ብዙ ሰዎች የጌታ የሀሳብ እና የድርጊት የንጽህና መስፈርቶች ዘመን ያለፈባቸው አልፎ ተርፎም ጨቋኝ ናቸው ብለው ያስባሉ። የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በዚህ ህግ ለመኖር ቢጥሩ ኖሮ ምን ለውጥ ይመጣ ነበር? የዚህን ጥያቄ መልሶች ለማግኘት በሽማግሌ ዴቪድ ኤ ቤድናር “We Believe in Being Chaste”(ሊያሆና፣ ግንቦት 2013(እ.አ.አ)፣ 41–44) በሚለው መልዕክት ውስጥ ወይም “ሰውነታችሁ ቅዱስ ነው” (ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ፣ 23–26) ውስጥ ልትፈልጉ ትችላላችሁ። ምን የተስፋ መልዕክቶች ታገኛላችሁ?

በሐሳባችን እና በድርጊታችን ንጹህ በመሆን በረከቶች እንደሚመጡ እያወቅንም እንኳን ያ ቀላል ነው ማለት አይደለም። የአዳኙን የንጽህና መስፈርት መጠበቅን ምን አስቸጋሪ እንደሚያደርግባችሁ እንዲሁም ምን ቀላል እንደሚያደርግላችሁ ለማሰላሰል ትንሽ ጊዜ ልትመድቡ ትችላላችሁ። ብቁ ባልሆኑ ሀሳቦች ስትፈተኑ ማድረግ ስለሚገባችሁ ነገር ለሌሎች ምን ጠቃሚ ምክሮችን ልታካፍሉ ትችላላችሁ?

አንዳችሁ ለሌላችሁ ድጋፍ ስጡ። በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች እና በክፍሎች ውስጥ አንድ ላይ መሰብሰብ ከሚያስገኛቸው ታላቅ በረከቶች አንዱ አዳኙን ለመከተል በምናደርገው ጥረት ከቅዱሳን አጋሮቻችን ድጋፍ የማግኘት አጋጣሚን መፍጠሩ ነው። ብዙዎቻችን ተመሳሳይ ፈተናዎች ይገጥሙናል፣ እናም የጋራ ልምዶቻችን ትልቅ ጥንካሬ ሊሆኑን ይችላሉ። ፈተናዎች እንዳሉባችሁ መቀበልን አትፍሩ። የእግዚአብሔርን ህግጋት እንድትኖሩ እና ፈተናን እንድታሸንፉ የሚረዳችሁ ምን እንደሆነ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥45፤ Topics and Questions፣ “Virtue፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ “Standards: Sexual Purity and Modesty—True Confidence” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ፤ AddressingPornography.ChurchofJesusChrist.orgተመልከቱ።

3:58

Standards: Sexual Purity and Modesty - True Confidence

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥58–64

ቅዱስ ነገሮች በጥልቅ አክብሮት መያዝ አለባቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥58–64 ውስጥ ያሉት መርሆዎች የጌታን ስም በከንቱ ከመጠቀም በላይ የሚያመለክቱ ናቸው። “ከላይ” ወይም ከእግዚአብሔር የሚመጡ ሌሎች ቅዱስ ነገሮች የትኞቹ ናቸው? ስለእነዚህን ነገሮች “በጥንቃቄ” መናገር ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ግብዓቶች
የልጆች ክፍል ምልክት 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥461፥1–23662፥1

ቅዱሳት መጻህፍት ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምራሉ።

  • ምናልባት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥62 ውስጥ የሚገኙትን ስለአዳኙ የተነገሩትን አንዳንድ ቃላት በትንናሽ ወረቀቶች ላይ ልትፅፏቸው ትችላላችሁ። ከዚያም ልጆቻችሁ እነዚህን ቃላት በምድራዊ አገልግሎቱ ያሳያቸውን እነዚህን ባህርያት ከሚያሳዩ ከኢየሱስ ምስሎች (የወንጌል የአርት መፅሐፍቁጥር 34–61 ተመልከቱ) ጋር ማዛመድ ይችላሉ። ዛሬ እራሱን የሚያሳውቀን እንዴት ነው?

    Jesus Christ at age twelve in the temple at Jerusalem during the Feast of the Passover. A group of learned Jewish doctors are gathered around Christ. The doctors are expressing astonishment at the wisdom and understanding of the young Christ. (Luke 2:41-50)
ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ

ዝርዝር ከFor This Purpose [ለዚህ ዓላማ]፣ በዮንግሰንግ ኪም

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥761፥1–262፥1

ንስሐ ከገባሁ ጌታ ይቅር ይለኛል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 60፥761፥2ን ከልጆቻችሁ ጋር ስታነቡ፣ እነዚህ ጥቅሶች የያዟቸውን ተመሳሳይ ቃላት እንዲፈልጉ እርዷቸው። እነዚህ ራዕዮች ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች የተሰጡ እንደነበሩ አስታውሷቸው። ጌታ እንዲያውቁ የፈለገው ምንድን ነበር? ስህተት ስንሰራ አዳኙ ስለ እኛ እንዴት እንደሚሰማው እና ንስሐ መግባት ማለት ምን ማለት እንደሆነ መናገርም ትችላላችሁ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 62፥1 መሠረት፣ በምንፈተንበት ጊዜ ኢየሱስ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 62፥3፣ 9

ኢየሱስ ክርስቶስ የእርሱን ወንጌል እንዳካፍል ይፈልጋል።

  • አንድ ሰው ልጆቻችሁን ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለቤተክርስቲያኑ የሚወዱትን ነገር ቢጠይቃቸው ምን ይሉ እንደነበር ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። እንደ “I Want to Be a Missionary Now” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 168) ያሉ ወንጌልን ስለማካፈል የሚያወሱ መዝሙሮችን አንድ ላይ መዘመር ሃሳቦችን ሊሠጣቸው ይችላል። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 62፥3ን ልታነቡ እና ምስክርነታችንን በምናካፍልበት ጊዜ ስለሚሆነው ነገር እንዲያዳምጡ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ፍርሃት ከተሰማን በቁጥር 9 ውስጥ የተሠጠው ተስፋ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥64

ጥልቅ አክብሮት ያለኝ መሆን እችላለሁ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥64ን ለማስተዋወቅ እንደ “Reverence Is Love” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ ቁጥር. 31) ያሉ ስለጥልቅ አክብሮት የሚያወሱ መዝሙሮችን ከልጆቻችሁ ጋር መዘመር ትችላላችሁ። ከዚያም ለሰማይ አባት እና ለኢየሱስ ክርስቶስ አክብሮት ማሳየት ስለምትችሉባቸው የተለያዩ መንገዶች መናገር ትችላላችሁ።

  • ልጆቻችሁ ስለሚወዱት መጫወቻ፣ መጽሐፍ ወይም ብርድ ልብስ የመሠለ ለእነርሱ ልዩ ስለሆነ አንድ ነገር ከእነርሱ ጋር በመነጋገር ጥልቅ አክብሮት ምን እንደሆነ እንዲገነዘቡ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ለእነሱ ልዩ የሆኑ ነገሮችን እንዴት እንደሚንከባከቧቸው እና እንደሚጠብቋቸው ጠይቋቸው። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥64ን አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። ለሰማይ አባት ልዩ ወይም የተቀደሱ ነገሮች—ምን ምን ናቸው? (ለምሳሌ፣ ቁጥር 61 እና የዚህን ሣምንት የአክቲቪቲ ገፅ ተመልከቱ)። እነዚህን ነገሮች በቃላችን እና በድርጊታችን ልንይዛቸው የሚገባን እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ኤልሣ ጆንሰንን መፈወስ

የኤልሳ ጆንሰን ትከሻ መፈወስ፣ በሳም ላውሎር

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ