ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሰኔ 2–8፦ “መልካም ስራን በጉጉት ማከናወን“፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58–59


“ሰኔ 2–8፦‘መልካም ስራን በጉጉት ማከናወን’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58–59፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58–59፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ኢንድፔንደንስ፣ ሚዙሪ፣ በ1830ዎቹ (እ.አ.አ)

ኢንድፔንደንስ፣ ሚዙሪ፣ 1831 በአል ራውንድስ

ሰኔ 2–8፦ “መልካም ስራን በጉጉት ማከናወን“

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58–59

የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የፅዮን ከተማ ቦታ የሚሆነውን ቦታ—ኢንድፔንደንስ፣ ሚዙሪን—ሲመለከቱ እንደጠበቁት ሆኖ አላገኙትም። አንዳንዶች የበለጸገ ታታሪ ማህበረሰብ ያሉት ጠንካራ የቅዱሳን ቡድን እንደሚያገኙ አስበው ነበር። ከዚያ ይልቅ ብዙ ሰዎች ያልነበሩበት፣ የለመዱት ስልጣኔ የሌለበት እና በቅዱሳን ሣይሆን በአስቸጋሪ የድንበር ሰፋሪዎች የተያዘ ቦታ ሆኖ ነበር ያገኙት። ጌታ የጠየቃቸው ወደ ፅዮን እንዲመጡ ብቻ አልነበረም—ፅዮንን እንዲገነቧትም ፈልጎ ነበር።

ግምቶቻችን ከእውነታው ጋር በማይገናኙበት ጊዜ፣ ጌታችን በ1881 (እ.አ.አ) ለቅዱሳን የነገራቸውን ማስታወስ እንችላለን፦ “አምላካችሁ ያቀደውን እናም ብዙ መከራን ተከትሎ የሚመጣውን ክብር በዚህ ጊዜ በተፈጥሮ አይኖቻችሁ ልታዩ አትችሉም” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥3)። አዎን፣ ህይወት በፈተና፣ በክፋትም የተሞላ ነች፣ ነገር ግን “ብዙ ጽድቅንም መስራት [እንችላለን]፤ ሀይል [በእኛ] ውስጥ ነውና” (ቁጥር 27–28)።

በተጨማሪም Saints1፥127–33ን ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፣1–5 59፥23

“ከብዙ መከራ በኋላ በረከቶች ይመጣሉና።”

ቅዱሳን፣ ጃክሰን ካውንቲ በህይወት ዘመናቸው ሁሉም ሊሰበሰቡበት ወደሚችሉበት ወደ ፅዮን ያድጋል ብለው ተስፋ አደረጉ። ሆኖም፣ በጃክሰን ካውንቲ ያሳለፉት ጊዜ በመከራ የተሞላ ነበር። በጥቂት ዓመታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ እንዲሁም “የፅዮን[ን] ቤዛነት ለትንሽ ዘመን [እንዲ]ጠብቁ” ተገደው ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 105፥9)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፣1–5 ውስጥ ከሠፈሩት የጌታ ቃላት ስለመከራ ወይም ስለ ፈተናዎች ምን ትማራላችሁ? አንዳንድ በረከቶች ከመከራ በኋላ ብቻ የሚመጡት ለምን ይመስላችኋል? ከፈተናዎች በኋላ ምን በረከቶችን ተቀብላችኋል?

ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 59 ተሥፋን የሚያመጡላችሁ ምን ትማራላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥26–29

“በራሴ ነጻ ምርጫ” አማካኝነት “ብዙ ጽድቅንም መሥራት” እችላለሁ።

የእነዚህ ጥቅሶች የጥናት አካል በማድረግ “በጉጉት [የምታ]ከናውኗቸውን“ የተወሰኑ ነገሮች ዝርዝር ማዘጋጀት ትችሉ ይሆናል። ሁሉም “መልካም ስራ[ዎች]“ ናቸው? “ብዙ ጽድቅንም መሥራት” እንድትችሉ—እንዲሁም ይህንን ማድረግ የሚያስችሉ ግቦችን ማውጣትን ግምት ውስጥ እንድታስገቡ—ምን ልታደርጉ እንደምትችሉ አሰላስሉ።

ጌታ “ብዙ ነገሮችን [በራሳችሁ] ነፃ ምርጫ እንድታደርጉ“ የሚፈልገው ለምን ይመስላችኋል? “በሁሉም ነገር [ብትገደዱ]” ኖሮ ውጤቱ ምን ሊሆን ይችል ነበር? 2 ኔፊ 2፥27 በዚህ መርህ ላይ ባላችሁ ግንዛቤ ላይ ምን ይጨምራል?

በተጨማሪም ዴል ጂ. ረንለንድ፣ “በዛሬ ቀን ምረጡ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 104–6 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42–43

የሴሚናሪ ምልክት
ንስሐ ስገባ ጌታ ይቅር ይለኛል።

ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42 ውስጥ ንስሃ የገቡትን ሙሉ በሙሉ ይቅር እንደሚል የገባው ቃል፣ ምንም እንኳን ንሥሐ መግባት ማለት ምን ማለት ነው የሚል ጥያቄን የሚያስነሣ ቢሆንም የሚያነሣሣ ነው። ንስሐ እንደገባሁ እንዴት ማወቅ እችላለሁ? እንደ እድል ሆኖ፣ ጌታ “በዚህም … ታውቃላችሁ” ሲል ይቀጥላል (ቁጥር 43)።

አንዳንድ ጊዜ ሠዎች ስለንሥሐ የሚያነሷቸው የተወሰኑ ተጨማሪ ጥያቄዎች እነሆ። ከታች የቀረቡትን በጥቆማ የቀረቡ ግብዓቶች ስታጠኑ መንፈስ ምን ያስተምራችኋል?

ኃጢያቶቼን መናዘዝ ንሥሐ እንድገባ የሚረዳኝ እንዴት ነው? መዝሙር 32፥1–5ምሣሌ 28፥፣13ሞዛያ 27፥34–37አልማ 39፥12–13 ተመልከቱ።

ኃጢአቴን ለመተው እየሞከርኩኝ ነው፣ ሆኖም አሁንም ስህተቶችን እሰራለሁ። የምገባው ንሥሐ ተቀባይነት አለው? ብራድሊ አር. ዊልኮክስ፣ “Worthiness Is Not Flawlessness፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 61–67፤ “Daily Restoration” (ቪዲዮ)፣ በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

5:27

Daily Restoration

አዳኙ ይቅር እንዳለኝ እርግጠኛ መሆን የምችለው እንዴት ነው? ታድ አር. ካሊስተር፣ “The Atonement of Jesus Christ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 85–87፣ በተለይ “2. ኃጢያት” የሚል ርዕስ ያለውን ክፍል ተመልከቱ።

ንስሐ ስለመግባት “ጥያቄዎች እና መልሶች” በሚለው በለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ (ገፅ 8–9) ውስጥ ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።

በተጨማሪም Topics and Questions፣ “ንስሐ፣” የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59

ፖሊ ናይት ማን ነበረች?

ፖሊ ናይት እና ባለቤቷ ጆሴፍ ናይት፣ ቀዳማዊ ፣ የጆሴፍ ስሚዝ ነቢያዊ ጥሪ የመጀመሪያዎቹ አማኞች ነበሩ። ፖሊ እና ጆሴፍ መፅሐፈ ሞርሞንን በመተርጎም ስራ ላይ ለነቢዩ ወሳኝ ድጋፍ ሰጥተውታል። የናይት ቤተሰብ ኦሃዮ ውስጥ ከቅዱሳኑ ጋር ለመሰባሰብ ሲሉ ፣ ከኒው ዮርክ ከኮልቪል ወጡ ከዚያ በኋላም ወደ ጃክሰን ካውንቲ፣ ሚዙሪ እንዲሄዱ ታዘዙ። በሚጓዙበት ጊዜ የፖሊ ጤንነት ማሽቆልቆል ጀመረ፣ ነገር ግን ከመሞቷ በፊት ፅዮንን ለማየት ቆርጣ ነበር። ስትሞትም ሚዙሪ ውስጥ የነበረችው ለጥቂት ቀናት ብቻ ነበር (Saints1፥127–28132–33 ተመልከቱ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59 የመጣው እርሷ ያረፈች እለት ነበር፣ እናም ቁጥር 1 እና 2 በተለይ ስለ እርሷ የሚናገሩ ሊሆኑ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥4–19

ትዕዛዛት በረከቶች ናቸው።

በ“ትእዛዛት … አክሊል [ይቀበላሉ]“ ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? (ቁጥር 4)። (ቁጥር 5–19 ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ትዕዛዛት ለመታዘዝ ስትጥሩ ጌታ እንዴት እንደሚባርካችሁ አስቡ።

እየተማራችሁ ያላችሁትን አጋሩ። ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠኑ የምታገኟቸው መንፈሳዊ ግንዛቤዎች፣ በብዙ አጋጣሚዎች የቤተሰባችሁን፣ የጓደኞቻችሁን እና የአጥቢያ አባላትን እምነት ሊያጠናክር ይችላል። ልምዶቻችሁን፣ ስሜቶቻችሁን እንዲሁም ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ምስክርነቶች አካፍሏቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥9–19

ሰንበት የጌታ ቀን ነው።

ጌታ በፅዮን ውስጥ የሚገኙ ቅዱሳንን “ጥቂት ባልሆኑ ትዕዛዛት“ ለመባረክ ቃል ከገባ በኋላ፣ ለአንድ ትእዛዝ ለየት ያለ ትኩረት ሰጠ፦ የእርሱን “የተቀደሰ ቀን” የማክበር ትእዛዝ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥4 ፣9)። ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 59፥9–19ን ስታጠኑ፣ ፅዮንን ለመገንባት እየፈለጉ በነበሩበት ጊዜ ለእነዚህ ቅዱሳን ሰንበትን ማክበር እጅግ አሰፈላጊ የነበረው ለምን እንደሆነ አሰላስሉ። ለእናንተስ አሰፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

የሰንበትን ቀን ጌታ ባሰበው መንገድ እየተጠቀማችሁ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማሰላሰልም ትችላላችሁ። የሰንበትን ቀን ማክበር “ከአለም ነገሮች [ራሳችሁን] ንፁህ እና ነውር የሌለበት ለማድረግ“ የሚረዳችሁ እንዴት ነው? (ቁጥር 9)። “ለልዑል [አምልኮን ለመስጠት]“ ምን ማድረግ ትችላላችሁ? (ቁጥር 10)።

ቅዱስ ቁርባን

ጌታ ስለሰንበት ቀን ለማስተማር እንደ “ደስታ” “ደስተኛ” እና “ደስ የሚል” የመሳሰሉ ቃላትን እንደተጠቀመ ልታስተውሉ ትችላላችሁ። ሰንበትን ለእናንተ አስደሳች የሚያደርገው ምንድን ነው? የጌታን ቀን ለማክበር የመረጣችሁት ለምን እንደሆነ ለአንድ ሰው የምታስረዱት እንዴት ነው?

ስለሰንበት ዓላማዎች እና በረከቶች ከ“Gently Raise the Sacred Strain” (መዝሙር፣ ቁጥር 146) ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ዘፍጥረት 2፥2–3ኢሳይያስ 58፥13–14፤ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ሰንበት አስደሳች ነች፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 129–32 ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥26–28

የሰማይ አባት የመምረጥ ኃይል ሰጥቶኛል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥26–28ን በጋራ ማንበብ እናንተ እና ልጆቻችሁ መልካም ማድረግን እንድንመርጥ የሰማይ አባት ስለሰጠን ኃይል እንድትናገሩ ዕድል ሊሰጣችሁ ይችላል። ስላደረጋችኋቸው በርካታ ምርጫዎች እና ስላስከተሏቸው ውጤቶች አንዳችሁ ለሌላችሁ ልትነግሩ ትችላላችሁ። ምናልባት ልጆቻችሁ የነበሯችውን ተሞክሮዎች ሊሥሉ ይወዱ ይሆናል።

  • በአንድ ትንሽ ወረቀት ላይ በአንድ በኩል ምርጫ እንዲሁም በሌላኛው በኩል ውጤቶች ብላችሁ ልትፅፉ እና ይህን ወረቀት ምርጫዎች እና የሚያስከትሏቸው ውጤቶች የማይነጣጠሉ መሆናቸውን ለማሳየት ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ። ምናልባት ልጆቻችሁ የተወሰኑ ምርጫዎችን ሊዘረዝሩ እና በእነርሱ ምክንያት ስለሚመጡ ውጤቶች ሊናገሩ ይችላሉ። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥27–28ን አብራችሁ ልታነቡ እና “ብዙ ጽድቅን ” ወይም ጥሩ ውጤቶችን ስለሚያመጡ ምርጫዎች ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። መልካም ለማድረግ በምንጥርበት ጊዜ የሠማይ አባት እኛን “የሚሸልመን” ወይም የሚባርከን እንዴት ነው? (ቁጥር 28)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥7፣ 18–21

“ጌታ አምላክህን በሁሉም ነገሮች አመስግን።”

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ “… አይንና ልብን የሚያስደሰቱ” ነገሮችን እያያችሁ በእግር በምትጓዙበት ወይም ተፈጥሮን የሚያሳዩ ሥዕሎችን በምትመለከቱበት ጊዜ እነዚህን ጥቅሶች ማንበብን አስቡ (ቁጥር 18)። እንደ “My Heavenly Father Loves Me፣” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 228–29) ባሉ መዝሙሮች ውስጥ ተመሳሳይ ነገሮችን ልታስተውሉም ትችላላችሁ። ወይም ልጆቻችሁ አመስጋኝ ስለሆኑባቸው ነገሮች ሥዕሎችን እንዲሥሉ ልትጋብዟቸውና ስለሥዕሎቻቸው እንዲነግሯችሁ ልታደርጉ ትችላላችሁ። ለእነዚህ ነገሮች ያለንን ምስጋና ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ሃሚንግ በርድ እና አበቦች

ጌታ ለእኛ ደስታን እንዲሠጡን ብዙ የሚያምሩ ነገሮችን ፈጠረ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥9–12

ሰንበት የእግዚአብሔር ቀን ነው።

  • ጌታን ለማምለክ እና ደስታን ለማግኘት በእሁድ ቀን ምን ልናደርግ እንችላለን? ልጆቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥9–12 እና በዚህ ሣምንት የአክቲቪቲ ገፅ ውስጥ ሃሳቦችን እንዲፈልጉ እርዷቸው። ምናልባት በሰንበት ቀን የምናደርጋቸውን ነገሮች የሚወክሉ ምስሎችን ወይም ዕቃዎችን (ለምሳሌ በዚህ መዘርዝር ውስጥ እንዳሉት ዓይነት የቅዱስ ቁርባን ሥዕሎችን) ሊፈልጉ ይችላሉ። እነዚህ ነገሮች ወደ ሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደቀረብን እንዲሠማን የሚረዱን እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ቅዱስ ቁርባንን ለመውሰድ መዘጋጀት

ሥዕል በማርቲ ሜጀር

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ