ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሰኔ 23–29፦ “ከአለም ሁሉ ሀብቶች በላይ ታላቅ ዋጋ [አላቸው]”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67–70


“ሰኔ 23–29፦ ‘… ከአለም ሁሉ ሀብቶች በላይ ታላቅ ዋጋ [አላቸው]’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67–70፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67–70፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

የትዕዛዛት መፅሐፍ የመጀመሪያው የእጅ ፅሁፍ

ሰኔ 23–29፦ “… ከአለም ሁሉ ሀብቶች በላይ ታላቅ ዋጋ [አላቸው]”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67–70

ከ1828 እስከ 1831 (እ.አ.አ) ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለግለሰቦች የመጡ መለኮታዊ ምክሮችን፣ ቤተክርስቲያኗን የማስተዳደር መመሪያን፣ የኋለኛው ቀናትን የተመለከቱ ራዕዮችን ጨምሮ ብዙ የሚያነሳሱ ዘለዓለማዊ እውነቶችን ከጌታ ተቀብሏል። ነገር ግን ብዙዎቹ ቅዱሳን አላነበቧቸውም ነበር። ራዕዮቹ ገና አልታተሙም ነበር፣ እንዲሁም የነበሩት ጥቂት ቅጂዎች አባላት የሚቀባበሏቸው እና ሚስዮናውያን ይዘዋቸው የሚዞሩት በወረቀት ላይ በእጅ የተጻፉ ነበሩ።

ከዚያም በህዳር 1831 (እ.አ.አ)፣ ጆሴፍ ራዕዮቹን ስለማሳተም ለመወያት የቤተክርስቲያን መሪዎች ምክር ቤት ስብሰባን ጠራ። የጌታን ፈቃድ ከጠየቁ በኋላ፣ እነዚህ መሪዎች የትእዛዛት መፅሐፍን ለማሳተም አቀዱ—ለአሁኑ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መፅሐፍ መንገድ ከፋች ነበር። ወዲያው እያንዳንዱ ሰው በነቢዩ አማካኝነት የተገለጸውን የእግዚአብሔር ቃል ራሱ ለማንበብ ይችላል፤ ይህም “የአዳኛችን መንግስት ሚስጥር ቁልፎች እንደገና ለሰው በአደራ እንደተሰጡም ለማሳየት” ግልጽ ማስረጃ ነው። በእነዚህ እና በሌሎች በብዙ ምክንያቶች፣ ቅዱሳን ያኔ እና ዛሬ እነዚህ ራዕዮች “ከአለም ሁሉ ሃብቶች በላይ ታላቅ ዋጋ እንዳላቸው” ያስባሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 70፣ የክፍል መግቢያ)።

Saints1፥140–43ን ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67፥1–968፥3–6

የጌታ አገልጋዮች በመንፈስ ቅዱስ ሲነሳሱ የእርሱን ፈቃድ ይናገራሉ።

በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት የተገለጸውን ራዕይ ማሳተም ቀላል ይመስል ነበር፤ ነገር ግን አንዳንድ የመጀመሪያዎቹ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ጥሩ ሃሳብ ስለመሆኑ እርግጠኞች አልነበሩም። አንደኛው አሳሳቢ ነገር ጆሴፍ ስሚዝ ራዕዮቹን በፃፈበት መንገድ ከነበሩ ጉድለቶች ጋር ይያያዛል። በክፍል 67 ውስጥ ያለው ራዕይ የመጣው ለዚያ ስጋት ምላሽ ለመስጠት ነበር። ከቁጥር 1–9 ውስጥ ስለጌታ ነቢያት እና ስለራዕዮች ምን ትማራላችሁ? ከ68፥3–6 ውስጥ ምን ተጨማሪ ግንዛቤ ታገኛላችሁ?

እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚሰጣቸው ራዕዮች እውነት መሆናቸውን ያወቃችሁት እንዴት ነው? እንዲሁም ጌታ ከአገልጋዮቹ በአንዱ በኩል ሲያናግራችሁ በተሰማችሁ ጊዜ ስለነበሯችሁ ተሞክሮዎች ማሰላሰልም ትችላላችሁ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥4)። አንድ ነገር እንድትናገሩ “በመንፈስ ቅዱስ [መነሳሳት]” (ቁጥር 3) የተሰማችሁ መቼ ነው። ጌታ “ከጎናችሁ [የቆመው]” (ቁጥር 6) እንዴት ነው?

መፅሐፈ ትእዛዛት ከመታተሙ በፊት ብዙ የቤተክርስቲያን መሪዎች በመጽሃፉ ውስጥ ያሉት ራዕዮች ትክክል እንደሆኑ የሚገልጽ የጽሁፍ ምስክርነት ላይ ፈርመዋል። ምስክርነት የሰጡበትን ቅጂ ለማየት፣ “Testimony, circa 2 November 1831፣” Revelation Book 1፣ 121፣ josephsmithpapers.org ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67፥10–14

“በትዕግስት ፅኑ።”

ምቀኝነት፣ ፍርሃት፣ እና ኩራት ወደ ጌታ እንዳንቀርብ የሚያደርጉን እንዴት ነው? “[እርሱን] አይተን [እርሱ] እንዳለ እናውቅ ዘንድ” “የተፈጥሯዊውን ሰው” ወይም “ሥጋዊን አእምሮ” ማሸነፍ የምንችለው እንዴት ነው? (ቁጥር 12፤ በተጨማሪም ሞዛያ 3፥19 ተመልከቱ)። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “ፍጹም እስክትሆኑ ድረስ በትዕግስት [እንድትፀኑ]” (ቁጥር 13) የሚያነሳሷችሁ ምን ታገኛላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25–31

የሴሚናሪ ምልክት
ቤቴ ኢየሱስ ክርስቶስን ያማከለ እንዲሆን መርዳት እችላለሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25–31 ውስጥ ያለው የጌታ ቃል በተለይ ወላጆችን ይመለከታል፤ ነገር ግን ወላጅ ብትሆኑም ባትሆኑም፣ ቤታችሁ የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ያማከለ እንዲሆን ለማድረግ የራሳችሁን ድርሻ ለመወጣት፣ የእርሱን ምክር መጠቀም ትችላላችሁ። ጌታ በቤት ውስጥ በትምህርት መልክ መሠጠት አለባቸው ከሚላቸው መርሆዎች መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። አሁን የምትኖሩበት ቤት ወይም የወደፊት ቤታችሁ እነዚህ እያንዳንዳቸው ክርስቶስን ያማከለ ቤት መሠረት አካል እንዲሆኑ ማድረግ የምትችሉት እንዴት እንደሆነ አስቡ። የተሰጡት ግብዓቶች እና ጥያቄዎች ሊረዱ ይችላሉ።

  • ንሥሐአልማ 36፥17–20ን አጥኑ፤ ከዚያም አባቱ ስለአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ተልእኮ አስተምሮት የነበረ በመሆኑ ምክንያት አልማ በአስቸጋሪ ጊዜ እንዴት እንደተባረከ አስተውሉ። ቤተሰባችሁ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመለሱ እና ንስሀ እንዲገቡ ለማነሳሳት መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው? (በተጨማሪም 2 ኔፊ 25፥26 ተመልከቱ)።

  • በክርስቶስ ማመን፦ በ“ክርስቶስ ተነስቷል፤ በእርሱ ማመንም ተራራን ያነቃንቃል፣“ (ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 103) ውስጥ እምነት ለማዳበር የሚረዱ የፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን አምስት ጥቆማዎችን አንብቡ። እነዚህ ጥቆማዎች በቤተሰባችሁ ውስጥ የእምነት ባህል እንዴት ሊፈጥሩ እንደሚችሉ አሰላሥሉ።

  • ጥምቀት፦ በሞዛያ 18፥8–10፣ 13 ውስጥ የተገለፀውን የጥምቀት ቃል ኪዳን ከልሱ። ይህን ቃል ኪዳን ለመጠበቅ የምታደርጉት ጥረት ቤተሰባችሁን የሚያጠናክረው እንዴት ነው?

  • የመንፈሥ ቅዱስ ሥጦታ፦ በገጽ 17–19 ላይ በለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ ውስጥ ያሉትን ግብዣዎች አጥኑ። በቤታችሁ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን ተጽዕኖ ለመጋበዝ ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል?

  • ፀሎት፦ በ“Love Is Spoken Here” በሚለው መዝሙር ውሥጥ በቤት ውሥጥ የሚደረግ ፀሎት ስላለው ሃይል ምን ትማራላችሁ? (የልጆች መዝሙር መፅሀፍ 190–91)። አዳኙ በ3 ኔፊ 18፥15–21 ውስጥ ምን በረከቶችን ለመስጠት ቃል ገባ?

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25–31 ውስጥ የምታገኟቸው ሌሎች መርሆዎች፦

የቤተሰባቸው አባላት በክርስቶስ ላይ እምነት ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት ለማይደግፉላቸው ሰዎች ምን ምክር ትሰጣላችሁ?

በተጨማሪም “The Family: A Proclamation to the World፣” ወንጌል ላይብረሪ፤ Topics and Questions፣ “Parenting፣” ወንጌል ላይብረሪ፤ ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “Jesus Christ Is the Strength of Parents፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 55–59 ተመልከቱ።

ቤተሰብ በአንድነት እየተማሩ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 69፥1

“እውነተኛ እና ታማኝ የሆ[ኑ]” ጓደኞቼ ኢየሱስ ክርስቶስን እንድከተል ይረዱኛል።

በዚህ ጥቅስ ውስጥ በተገለጸው የሥራ ምደባ ላይ “እውነተኛ እና ታማኝ” የሆነ ሰው ከኦሊቨር ካውደሪ ጋር አብሮ መሄዱ “[በጌታ] ዘንድ ጥበብ [የሆነው]” ለምን ይመስላችኋል? እነዚህ መርሆዎች ለእናንተ ሊሆኑ የሚችሉት እንዴት ነው?

ተማሪዎች እርስ በርሳቸው እንዲረዳዱ አግዟቸው። በክፍላችሁ ወይም በቤተሰባችሁ ውስጥ ያሉ ሁሉም ግለሠቦች ወንጌልን በመኖር ረገድ የብዙ ምሥክርነት፣ ግንዛቤዎች እና ተሞክሮዎች ምንጮች ናቸው። ያገኟቸውን ዘለአለማዊ እውነቶች እንዲያጋሩ እና እርስ በርሳችወ እንዲረዳዱ ጋብዟቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 70፥1–4

ጌታ ለሰጣቸው ራዕዮች ኃላፊነት አለብኝ።

ጌታ ለተወሰኑ ሽማግሌዎች የራዕዮቹን ህትመት ስራ በበላይነት የመቆጣጠር ሃላፊነት ሰጠ። ምንም እንኳን ያ የተለየ ሃላፊነት ባይኖርባችሁም፣ “በራዕዮቹ እና [በ]ትዕዛዛቱ“ ላይ መጋቢ ልትሆኑ ወይም ኃላፊነት ልትወስዱ የምትችሉት በምን መንገድ ነው? (ቁጥር 3)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምረኛል።

  • የጆሴፍ ስሚዝ ራዕዮች በአንድ መጽሐፍ እንዴት እንደታተሙ ለልጆቻችሁ ንገሯቸው (“Chapter 23፦ The Doctrine and Covenants [ምዕራፍ 23፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች]፣” በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 90–92፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ)። በዚህ አመት እስካሁን ድረስ ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተማራችኋቸውን አንዳንድ ነገሮች እንዲያስታውሱ እርዷቸው። ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የምትወዷቸውን ጥቅሶች አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉም ትችላላችሁ።

    2:2

    Chapter 23: The Doctrine and Covenants: August–November 1831

  • እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን፣ መጽሐፈ ሞርሞንን፣ ትምህርትን እና ቃል ኪዳኖችን እና የታላቁ ዋጋ ዕንቁን ለልጆቻችሁ ልታሳዩዋቸውና ስለልዩነታቸው እንዲሁም ስለተመሳሳይነታቸው ከእነሱ ጋር ልትነጋገሩ ትችላላችሁ (የእነዚህን መፃህፍት መግለጫ በየቅዱሳት መፃህፍት መመሪያ ውስጥ ተመልከቱ)። ቅዱሳት መጻህፍት እውነት መሆናቸውን እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67፥49 ውስጥ ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ ስለሰጠው ራዕዮች ምን እንማራለን?

ልጆች ቅዱሳት መጻህፍትን እያነበቡ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25–31

ስምንት ዓመት ሲሞላኝ መጠመቅ እችላለሁ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥27 ውስጥ አንድ ሰው ለመጠመቅ ስንት ዓመት መሆን እንዳለበት ጌታ ገልጿል። ልጆቻችሁየተናገረውን እንዲያገኙ እርዷቸው። ኢየሱስ እንድንጠመቅ የሚፈልገው ለምንድን ነው? እንደ “Baptism፣” (የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 100–101) ያለ መዝሙር ሊረዳ ይችላል። ልጆች ሥዕሎችን ወይም ቁጥር 25–31ን (ወይም ሁለቱንም) ሲጠቀሙ ጌታ እንዲማሩ የሚፈልገውን ነገሮች እንዲያውቁ ይረዳቸዋል።

  • ጌታ ለኦሊቨር ካውድሪ ስለሰጠው የሥራ ምደባ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 69 የክፍል መግቢያ ውስጥ ከልጆቻችሁ ጋር አንብቡ። በቁጥር 1 ውስጥ ጌታ ምን አይነት ምክር ሰጥቷል? “እውነተኛ እና ታማኝ ከሚሆኑ” ሰዎች ጋር መሆን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ምናልባት ልጆቻችሁ “እውነተኛ እና ታማኝ” እንደሆነ ስለሚያውቁት ሰው ሊናገሩ ይችላሉ። እንደ “I’m Trying to Be like Jesus፣” (የልጆች መዝሙር መጽሐፍ፣ 78–79) ያለ ህፃናትልጆች እንደ አዳኙ እውነተኛ እና ታማኝ እንዲሆኑ የሚያበረታታ መዝሙር አብራችሁ ልትዘምሩም ትችላላችሁ። እውነተኛ እና ታማኝ መሆናችንን ለጌታ ማረጋገጥ የምንችለው እንዴት ነው? እውነተኛ እና ታማኝ በምንሆንበት ጊዜ፣ እርሱ ሌሎችን ለመባረክ ሊጠቀምብን የሚችለው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ማተሚያ

የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መንገድ ከፋች የነበረው መፅሐፈ ትእዛዛት የታተመው ይህን በመሠለ ማተሚያ ነበር።

የአክቲቪቲ ገጽ ለልጆች