ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሰኔ 30–ሐምሌ 6፦ “በእናንተ ላይ እንዳትበለጽጉ የሚከላከል መሳሪያ አይከናወንም“፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71–75


“ሰኔ 30–ሐምሌ 6፦ ‘በእናንተ ላይ እንዳትበለጽጉ የሚከላከል መሳሪያ አይከናወንም’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71–75፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71–75፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ሚስዮናውያን በእርሻ ውስጥ እየተራመዱ

I Will Remember the Covenant፣ በኤንሪክ ማኑዌል ጋርሲያ

ሰኔ 30–ሐምሌ 6፦ “በእናንተ ላይ እንዳትበለጽጉ የሚከላከል መሳሪያ አይከናወንም“

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71–75

ከልጅነቱ ጀምሮ የእግዚአብሔርን ስራ ለመስራት ሲሞክር፣ ጆሴፍ ስሚዝ ተቺዎች፣ እንዲሁም ጠላቶች ገጥመውታል። ነገር ግን በ1831 (እ.አ.አ) ዕዝራ ቡዝ ቤተክርስቲያኗን በይፋ ማውገዝ ሲጀምር፣ በተለይ ከባድ ሳይሆን አይቀርም፣ ምክንያቱም በዚህ ጊዜ ተቺው የቀድሞ አማኝ ስለነበረ ነው። ዕዝራ፣ ጆሴፍ ስሚዝ አንድን ሴት ለመፈወስ የእግዚአብሔርን ሃይል ሲጠቀም አይቶ ነበር። በሚዙሪ የሚገኘውን የጽዮን መሬት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቃኙ፣ ከጆሴፍ ጋር እንዲሄድ ተጋብዞ ነበር። ነገር ግን ከዚያን ጊዜ በኋላ እምነቱን አጥቶ ነበር፣ እናም የነቢዩን ክብር ለመንካት ባደረገው ጥረት በአንድ የኦሃዮ ጋዜጣ ላይ ተከታታይ ደብዳቤዎችን አሳትሟል። እናም ጥረቶቹ እየተሳኩ የመጡ ይመስሉ ነበር ምክንያቱም በአካባቢው “በቤተክርስቲያኗ ላይ … የጥላቻ ስሜት” አድጎ ነበር (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 71 የክፍል መግቢያ)። በእንደዚያ አይነት ሁኔታ ውስጥ አማኞች ምን ማድረግ አለባቸው? ለሁሉም ሁኔታዎች የሚሆን አንድ መልስ ባይኖርም፣ አብዛኛውን ጊዜ—በ1831 (እ.አ.አ) ለነበረው ሁኔታ ጨምሮ—የጌታ መልስ ክፍል “ወንጌ[ሉ]ን በማወጅ” (ቁጥር 1) እውነትን መናገር እና ሃሰትን ማረም ነበር። አዎን፣ የጌታ ስራ ሁል ጊዜ ተቺዎች ይኖሩታል፣ ነገር ግን በመጨረሻ “[በዚህ ላይ] እንዳይበለፅግ የሚከላከል መሳሪያ አይከናወንም” (ቁጥር 9)።

ዕዝራ ቡዝ እና አይዛክ ሞርሊ፣” Revelations in Context፣ 134 ውስጥ ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71

የሴሚናሪ ምልክት
የአዳኙን ወንጌል ሳውጅ መንፈሱ ይመራኛል።

ሰዎች በአዳኙ፣ በወንጌሉ ወይም በቤተክርስቲያኑ ላይ ያላችሁን እምነት ሲነቅፉ ወይም ሲሳለቁበት አስጨናቂ ሊሆን ይችላል። ያ በሚሆንበት ጊዜ ምን ታደርጋላችሁ? በ1831 (እ.አ.አ) በኦሃዮ ተመሳሳይ ነገር ተፈጥሮ ነበር (የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71 የክፍል መግቢያ ተመልከቱ)። ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥71 ውስጥ ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን ስለዚህ ጉዳይ ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው? ምናልባት ጌታ የሰጣቸውን መመሪያዎች እና ቃል የገባላቸውን በረከቶች ልትዘረዝሩ ትችላላችሁ።

ክፍል 71ን ከማጥናት በተጨማሪ፣ አዳኙ በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ለተቺዎቹ እንዴት ምላሽ እንደሰጠ መፈለግ ትችላላችሁ። የተወሰኑ ምሣሌዎች እነሆ፦ ማቴዎስ 22፥15–2226፥59–64ዮሐንስ 10፥37–38። ከእርሱ ምን ትማራላችሁ? ከማቴዎስ 18፥15ኤፌሶን 4፥31–322 ጢሞቴዎስ 3፥12ያዕቆብ 1፥19 ምን ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ታገኛላችሁ?

ምክሩ ዛሬ በሚያጋጥሟችሁ ሁኔታዎች ላይ እንዴት ተግባራዊ ሊሆን ይችላል? በራሳችሁ ቃላት ውሸትን በሰላማዊ መንገድ ማስተካከል የምትችሉባቸውን መንገዶች ታስቡ ይሆናል። ለምሳሌ፣ ለሌላው ሰው አመለካከት ያላችሁን አክብሮት በመግለጽ መጀመር ትችሉ ይሆናል፤ ከዚያም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስና ስለትምህርቶቹ የምታምኑባቸውን በትህትና እና በደግነት ልታካፍሉ ትችላላችሁ። ለእነዚህ አጋጣሚዎች ለመዘጋጀት፣ ምናልባት ይህን አቀራረብ ከጓደኞቻችሁ ወይም ከቤተሰብ አባላት ጋር ልትለማመዱ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም Topics and Questions፣ “Helping Others with Questions፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “Loving Others and Living with Differences፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2014 (እ.አ.አ)፣ 25–28፤ ዮርግ ክሌብንጋት፣ “Valiant Discipleship in the Latter Days፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 107–10 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 72

እንደ ኤጲስ ቆጶሳት ባሉ መሪዎች አገልግሎት ጌታ ይባርከኛል።

ኒወል ኬ.ዊትኒ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ እንዲያገለግል በተጠራ ጊዜ፤ የነበሩበት ሃላፊቶች ከአሁኖቹ ኤጲስ ቆጶሳት ሃላፊነቶት ትንሽ ለየት ይሉ ነበር። ለምሳሌ፣ ኤጲስ ቆጶስ ዊትኒ የንብረቶች ቅዱስ ስጦታን እና በሚዙሪ፣ በጽዮን መሬት ላይ ለመስፈር የሚሰጥን ፈቃድ በበላይነት ይቆጣጠር ነበር። ነገር ግን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 72 ውስጥ ስለጥሪው እና ስለሃላፊነቶቹ ስታነቡ፣ ኤጲስ ቆጶሳት ዛሬ ከሚሰሩት ጋር የተወሰነ ተያያዥነት እንዳላቸው ልታስተውሉ ትችላላችሁ—በዝርዝር ኃላፊነቶቻቸው ባይሆንም እንኳን ቢያንስ በመንፈስ።

ለምሳሌ፣ ለኤጲስ ቆጶሳችሁ “[የመጋቢነታችሁን] መግለጫ” የምታቀርቡት በምን መንገዶች ነው? (ቁጥር 5)። በእኛ ዘመን፣ “የጌታ ጎተራ” የአጥቢያ አባላት ልገሳዎችን፣ አገልግሎትን እና ክህሎቶችን ሊያካትት ይችላል (ቁጥር 10፣ 12ን ተመልከቱ). ለዚያ ጎተራ ልገሳ ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው?

ጌታ በኤጲስ ቆጶስ አገልግሎት አማካኝነት እናንተን እና ልጆቻችሁን የባረካችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም ክውንተን ኤል. ኩክ፣ “Bishops—Shepherds over the Lord’s Flock፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 56–60 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 73

የአዳኙን ወንጌል የማካፈል ብዙ አጋጣሚዎች አሉኝ።

ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን ከሚስዮናዊ የሥራ ምድባቸው ሲመለሱ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71 ተመልከቱ)፣ ጌታ መፅሐፍ ቅዱስን ወደ መተርጎሙ ሥራ እንዲመለሱ ነገራቸው (የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ.ስ.ት)” ወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ)። ያ ማለት ግን ወንጌልን ማካፈልን እንዲያቆሙ ይፈልጋል ማለት አልነበረም። ከሁሉም በላይ፣ የደቀመዝሙር የህይወት ክፍል ነውና።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 73ን ስታነቡ፣ ወንጌልን ማካፈልን ከሌሎች ሃላፊነቶቻችሁ ጋር እንዴት ቀጣይነት ያለው፣ “በተቻለ መጠን” (ቁጥር 4)—ወይም ተጨባጭ—የህይወታችሁ አካል ልታደርጉት እንደምትችሉ አስቡ።

ጓደኛማቾች ስለወንጌል እየተነጋገሩ

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማካፈል የተለመደ እና ተፈጥሯዊ ሊሆን ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 75፥1–16

“በአቅማችሁ ሁሉ … እውነትን [አውጁ።”

ክፍል 75 ላይ ያለው ራዕይ የተሠጠው “[የአዳኙን] ወንጌል ለመስበክ … ስማቸውን ለሰጡ” (ቁጥር 2) ሰዎች ነው። ይህንን ራዕይ የማጥኛው አንዱ መንገድ፣ ሁለት ዝርዝሮችን ማዘጋጀት ነው፦ (1) ወንጌሉን በብቃት እንዴት ማካፈል እንደሚቻል እና (2) ያንን ስናደርግ ጌታ እንዴት እንደሚባርከን እና እንደሚደግፈን።

ወንጌልን በማካፈል ረገድ “[መዘግየት]” ወይም “[ስራ መፍታት]” ምን ማለት ይመስላችኋል? “በአቅማችሁ ሁሉ [መሥራት]” ምን ይመስላል? (ቁጥር 3)።

በተጨማሪም፣ “I’ll Go Where You Want Me to Go፣” መዝሙር፣ ቁጥር 270 ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄት ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71

ምስክርነቴን በማካፈል እውነትን መከላከል እችላለሁ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 71ን የክፍል መግቢያ ወይም “Chapter 25: Joseph Smith and Sidney Rigdon Go on a Mission” የሚለውን (በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 96፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ በመጠቀም ክፍል 71ን ስላነሳሱት ሁኔታዎች ልጆቻችሁን ለማስተማር ትችላላችሁ። ከዚያም፣ ጆሴፍ እና ስድኒ በቤተክርስቲያኗ ላይ የነበረውን “የጥላቻ ሥሜትን” በተመለከተ ጌታ ምን እንዲያደርጉ እንደፈለገ በቁጥር 1 ውስጥ እንዲፈልጉ እርዷቸው። እረዳቸዋለሁ ያለው እንዴት ነበር? እንደ ጆሴፍ እና ስድኒ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

    0:45

    Chapter 25: Joseph Smith and Sidney Rigdon Go on a Mission: December 1831–January 1832

  • እንዲሁም ልጆቻችሁ ለአዳኙ ታማኝ እንዲሆኑ የሚያነሳሳ እንደ “Stand for the Right፣” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 159) ያለ መዝሙርን መዘመር ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያውቁትን እንዴት ማካፈል እንደሚችሉ እንዲለማመዱ እርዷቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 72፥2

ጌታ እኔን ለመርዳት ኤጲስ ቆጶስን ጠርቷል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 72፥2ን አንድ ላይ ማንበብ ጌታ ለምን ኤጲስ ቆጶሳትን እንደሰጠን ለመወያየት እድል ይፈጥራል (በተጨማሪም “Chapter 17: The First Bishops of the Church፣” በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 64–66፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ ተመልከቱ)። እናንተ እና ልጆቻችሁ የኤጲስ ቆጶስ ሀላፊነቶችን የሚወክሉ ሥዕሎችን ወይም እቃዎችን መፈለግ ትችላላችሁ። በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ያለው ምስል እና የአክቲቪቲ ገጽ የተወሰነ ሃሳብ ይሰጧችኋል። ከዚያም ስለምታውቋቸው ኤጲስ ቆጶሳት እና በአገልግሎታቸው አማካኝነት ጌታ ቤተሰባችሁን እንዴት እንደባረከ አብራችሁ መነጋገር ትችላላችሁ።

    1:45

    Chapter 17: The First Bishops of the Church: February and December 1831

ሁልጊዜ ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሩ፡፡ “ምንም እያስተማራችሁ ብትሆኑ በእርግጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም እንዴት እንደእርሱ መሆን እንደሚቻል እያስተማራችሁ መሆኑን አስታውሱ” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር6)። ለምሳሌ፣ ልጆቻችሁን ስለኤጲስ ቆጶሳት በምታስተምሩበት ጊዜ፣ ሥራውን እንዲሠሩ በእርሱ የተጠሩ የኢየሱስ ክርስቶስ ተወካዮች ስለመሆናቸው አጽንኦት ስጡ (1 ጴጥሮስ 2፥25 ተመልከቱ)፡፡

ምግብ እና አቅርቦቶች በጌታ ጎተራ ውስጥ

ኤጲስ ቆጶሳት እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሠዎች ይረዱ ዘንድ ጌታ ይጠይቃቸዋል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 75፥3

ማድረግ የሚቻለኝን ሁሉ ለጌታ መስጠት እችላለሁ።

  • “ስራ ፈት [በመሆን]” እና “በአቅማች[ን] ሁሉ በመስራት” መካከል ስላለው ልዩነት ለመናገር፣ ምናልባት አንዳንድ የአገልግሎት ተግባራትን ወይም የቤት ውስጥ ሥራዎችን ልትመርጡ እና ልጆቻችሁ ስራ መፍታትን ከዚያም በአቅማቸው ሁሉ መሥራትን እንዲያሳዩ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 75፥3 ውስጥ “ሥራ ሣትፈቱ” የሚለውን ስታነቡ፣ ልጆቻችሁ የቤት ውስጥ ሥራዎችን እንዴት በሥንፍና እንደሚሠሩ ማሳየት ይችላሉ። “በአቅማችሁ ሁሉ በመስራት” የሚለውን ስታነቡ እንዴት ጠንክረው እንደሚሠሩ ማሳየት ይችላሉ። ጌታን በምናገለግልበት ጊዜ የተቻለንን ሁሉ ማድረጋችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • Two Principles for Any Economy]” (ሊያሆና፣ ህዳር 2009 (እ.አ.አ)፣ 55–58)፣ በተሠኘው መልዕክታቸው ፕሬዚዳንት ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ ስለ ሥራ ሁለት ታሪኮችን ተናግረዋል። ምናልባት ለልጆቻችሁ ልታካፍሏቸውና ጠንክረን እንደሰራን እና የቻልነውን እንደሰራን ማወቃችን ምን ዓይነት ሥሜት እንደሚሰጥ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወጣት ልጅን እያማከረ

Recognizing the Tender Mercies in Your Life፣ በኬት ላርሰን

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ