“ሐምሌ 21–27፦ ‘ብዙ ለተሰጠው ከእርሱ ብዙ ይጠበቅበታል’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81–83፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]
“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81–83፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 21–27፦ “ብዙ ለተሰጠው ከእርሱ ብዙ ይጠበቅበታል”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81–83
በመጋቢት 1832 (እ.አ.አ)፣ ጌታ፣ በሊቀ ካህን አመራር ውስጥ (አሁን ቀዳሚ አመራር ይባላል) የጆሴፍ ስሚዝ አማካሪ በመሆን እንዲያገለግል ጄሲ ጋውስን ጠራው። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81 ስለአዲሱ ጥሪ ለወንድም ጋውስ የተሰጠ ራዕይ ነው። ነገር ግን ጄሲ ጋውስ በታማኝነት አላገለገለም ስለዚህም ፍሬድሪክ ጂ. ዊልያምስ በእርሱ ምትክ ተጠራ። በራዕዩ ውስጥ የወንድም ጋውስ ስም በወንድም ዊሊያምስ ስም ተተካ።
ይህ አስፈላጊነቱ አነስተኛ የሆነ ዝርዝር ሊመስል ይችላል፣ ነገር ግን ትርጉም ያለው እውነታን ያመላክታል፦ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች የሚገኙ አብዛኛዎቹ ራዕዮች ስለተለዩ ሰዎች የሚናገሩ ናቸው፣ ነገር ግን ሁል ጊዜ ለእኛ የሚሆኑበትን መንገዶችን ልንፈልግ እንችላለን (1 ኔፊ 19፥23 ተመልከቱ)። ጌታ “የሰለሉትን ጉልበቶች አጠንክር” ሲል ለፍሬድሪክ ጂ. ዊልያምስ የሰጠውን ምክር ስናነብ ልናጠናክራቸው የምንችላቸውን ሰዎች ልናስባቸው እንችላለን (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥5)። ጌታ የቤተክርስቲያኗን ስጋዊ ፍላጎቶች ለማሟላት “በዚህ ቃል ኪዳን ራሳችሁን እንድታስተሳስረሩ“ ሲል ለተባበረው ድርጅት አባላት የሰጠውን ምክር ስናነብ የራሳችንን ቃል ኪዳኖች ማሰብ እንችላለን። “እኔ የምለውን ስታደርጉ በቃሌ እታሰራለሁ” በማለት የገባውን ቃል ኪዳን ልክ ከእኛ ጋር እየተነጋገረ እንዳለ አድርገን እናነበዋለን (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥10፣ 15)። ይህን ማድረግ እንችላለን፣ ምክንያቱም ጌታ ደግሞ እንደተናገረው፣ “ስለዚህ፣ ለአንዱ የምናገረው ለሁሉም የተናገርሁት ነው” (ቁጥር 5)።
“Newel K. Whitney and the United Firm፣” “Jesse Gause: Counselor to the Prophet፣” Revelations in Context 142–47፣ 155–57 ተመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥4–5፤ 82፥18–19
“ከሁሉም በላይ የሆነ መልካም ነገሮችን ለሠዎች ታደርጋለህ።”
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81–83 ውስጥ ብዙ ምንባቦች ጌታ በዙሪያችን ያሉትን የተቸገሩ ሠዎች እንድንረዳ ይጋብዘናል። ምንባቦቹን ስታገኟቸው በላያቸው ላይ ምልክት ማድረግን አስቡ። በጣም ገላጭ ከሆኑት ምሳሌዎች አንዱ በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥4–5 ውስጥ ይገኛል። በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ለማሰላሰል የሚረዷችሁ አንዳንድ ጥያቄዎች እነሆ፦
-
ሰው “ደካማ” ሊሆን የሚችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ምን ናቸው? እነርሱን “መደገፍ” ማለት ምን ማለት ነው? ድካም በተሰማኝ ጊዜ የሌሎች የክርስቶስ መሠል አገልግሎት የረዳኝ መቼ ነው?
-
የሰው እጆች በምሳሌያዊ ሁኔታ “የዛሉ“ የሚሆኑት በምን መነሻ ሊሆን ይችላል? እነዚያን እጆች “ማቅናት” የምንችለው እንዴት ነው?
-
“የሰለሉትን ጉልበቶች” ማለት ምን ማለት ሊሆን ይችላል? ሊጠናከሩ የሚችሉት እንዴት ነው?
አዳኙ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግላችሁ እንዴት ነው?
ምናልባት ይህንን ጥቅስ ማጥናት “ልትደግፉት፣” ”ቀና” ልታደርጉት፣ ወይም “ልታጠነክሩት” የምትችሉትን አንድ ሰው ወደ አእምሯችሁ አምጥቷል። ያንን ሰው ለማገልገል ምን ታደርጋላችሁ?
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82 ውስጥ ሌሎችን ስለማገልገል ምን ሌላ ነገር ትማራላችሁ? “Teachings of Thomas S. Monson: Rescuing Those in Need” የሚለውን ቪዲዮ (በወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ ልትመለከቱም ትችላላችሁ። የኤጲስ ቆጶስ ሞንሰን አጥቢያ አባላት እነዚህ ጥቅሶች የሚያስተምሩትን በምሳሌነት ያሳዩት እንዴት ነበር?
በተጨማሪም ያዕቆብ 2፥17–19፤ ሞዛያ 18፥8–9፤ “Works of God” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።
አዳኙ ብዙ ስለሠጠኝ ከእኔ ብዙ ይጠበቅብኛል።
ይህን ጥቅስ ማንበብ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ሥጋዊ እና መንፈሣዊ በረከቶች እንድትከልሱ ሊያነሳሳችሁ ይችላል። ቀሪውን ክፍል 85ን ስታነቡ ያንን በአእምሮአችሁ ያዙ። እግዚአብሔር ምን የሚጠብቅባችሁ ይመስላችኋል?
በተጨማሪም “Because I Have Been Given Much፣” መዝሙር፣ ቁጥር. 219 ተመልከቱ።
ትዕዛዛት እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር የሚያሳዩ ማስረጃዎች ናቸው።
እናንተ ወይም የምታውቁት ሌላ ሰው ጌታ ለምን በጣም ብዙ ትዕዛዛትን እንደሰጠ አስቦ የሚያውቅ ከሆነ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥8–10 ሊረዳ ይችላል። የጌታን ትዕዛዛት ለመከተል ለምን እንደመረጣችሁ ለአንድ ሠው ለማስረዳት ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የትኞቹ ግንዛቤዎች ሊረዷችሁ ይችላሉ? ትዕዛዛቱን ሊረዳችሁ ከሚችል ከምን ጋር ልታነፃፅሩ ትችላላችሁ? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥37–38፤ 130፥20–21 እና “Blessed and Happy Are Those Who Keep the Commandments of God” (የወንጌል ላይብረሪ) በተሰኘው ቪዲዮ ውስጥ ተጨማሪ ግንዛቤዎችን ማግኘት ትችላላችሁ። ትዕዛዛትን እንደ በረከቶች እንድትመለከቷቸው ያስተማሯችሁ የትኞቹ ተሞክሮዎች ናቸው?
እግዚአብሔር ስለሰጣችሁ ስለአንዳንድ ትዕዛዛት አስቡ። እነዚህ ትዕዛዛት ስለእርሱ እና ስለፈቃዱ ምን አስተምረዋችኋል? (ቁጥር 8ን ተመልከቱ)። እነዚህን ትዕዛዛት መጠበቃችሁ በህይወታችሁ ላይ ተፅዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው?
ከቁጥር 10 ስለጌታ ምን ትማራላችሁ? ጌታ “[ይታሰራል]” ሲባል ምን ማለት ይመስላችኋል? (በተጨማሪም (ቁጥር 15ን ተመልከቱ)።
ጌታ የገባውን ቃል በህይወታችሁ የፈፀመው እንዴት ነው? ተስፋ ያደረጋቸውን በረከቶች ባለማግኘቱ ምክንያት ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ ተነሳሽነት ለማይሰማው ሰው ምን ልትሉ ትችላላችሁ? በሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን “Our Relationship with God” በተሰኘ መልዕክት ውስጥ የሚረዱ ግንዛቤዎችን ታገኛላችሁን? (ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 78–80)።
በተጨማሪም Topics and Questions፣ “Commandments፣” የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።
ጌታ በራሱ አስደናቂ መንገድ ይባርከናል።
የቀድሞ የወጣት ሴቶች አጠቃላይ አመራር አባል የነበረችው እህት ቨርጂኒያ ኤች. ፒርስ፣ ትክክል ያልሆነ ምርጫ እያደረጉ በነበሩ ልጆችዋ ተስፋ በመቁረጥ ስለምትጨነቅ አንዲት ሴት ተናግራለች። ወደ ከባድ ጭንቀት በሚጠጋ ሥሜት ውስጥ በመሆን ስለእነርሱ የጌታን በረከቶች ለመሻት ልታስበው የምትችለውን ነገር ሁሉ ሞክራለች። ልባዊ ጸሎት ከማድረግ በተጨማሪ፣ የቤተመቅደስ ተሣትፎ ቁጥርን ከፍ የማድረግ ታላቅ ግብ አወጣች፤ በዚህም ጌታ የልጆቿን ልብ በመቀየር ይህንን ጉልህ መስዋዕትነት በአድናቆት እንደሚመለከትም እርግጠኝነት ተሰማት። ሴቲዮዋ እንዲህ ስትል ተናግራ ነበር፦
“ከአሥር ዓመታት በቁጥር ከፍ ያለ የቤተመቅደስ ተሣትፎ እና የማያቋርጥ ጸሎት በኋላ፣ የልጆቼ ምርጫዎች እንዳልተለወጡ ስናገር እያዘንኩኝ ነው። …
“እኔ ግን ተለውጫለሁ። “እኔ ሌላ ሴት ነኝ። … ለሥለስ ያለ ልብ አለኝ። በርህራሔ የተሞላሁኝ ነኝ። እንደ እውነቱ ከሆነ ይበልጥ መስራት እችላለሁ እንዲሁም ከፍርሃት፣ ከጭንቀት፣ ከጥፋተኝነት፣ ከነቀፋ እና ከፍርሃት ነጻ ነኝ። ያስቀመጥኳቸውን የጊዜ ገደቦች ትቻቸዋለሁኝ እንዲሁም ጌታን መጠበቅ እችላለሁ። በተጨማሪም የጌታ ሃይል መገለጫዎችን በተደጋጋሚ አያለሁ። ለእኔ እና ለልጆቼ ያለውን ፍቅር የሚያረጋግጡ ትናንሽ የደግነት መልዕክቶችን ይልካል። የምጠብቃቸው ነገሮች ተለውጠዋል። ልጆቼ እንዲለወጡ ከመጠበቅ ይልቅ፣ እነዚህን ተደጋጋሚ ደግነቶች እጠብቃለሁ እንዲሁም ስለእነሱ አመስጋኝ ነኝ።…
“ፀሎቶቼ ተለውጠዋል። ይበልጥ ፍቅርን እገልጻለሁ እንዲሁም የበለጠ አመስጋኝ ነኝ። ጌታ በሚያስደንቅ መንገድ ይሰራል፣ እንዲሁም በእውነት አእምሮን ሁሉ በሚያልፍ ሰላም ተሞልቻለሁ” (“Prayer: A Small and Simple Thing፣” At the Pulpit [2017 (እ.አ.አ)]፣ 288–89)።
“ባልቴቶች እና የሙት ልጆችም … ይረዳሉ።”
በሚያዝያ 1832 (እ.አ.አ)፣ በጌታ እንደታዘዘው፣ ጆሴፍ ስሚዝ በሚዙሪ የተሰባሰቡትን ቅዱሳን ለመጎብኘት 800 ማይልስ ተጓዘ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥9ን ተመልከቱ)። እዚያ በነበረበት ወቅት፣ ልጆቻቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ ብዙ መበለቶች ያሉበትን አንድ ማህበረሰብ ጎበኘ። ከእነርሱም ውስጥ ነቢዩ በግል የሚያውቃቸው ፊቢ ፔክ እና አና ሮጀርስ ይገኙበት ነበር። በ1830ዎቹ (እ.አ.አ) በሚዙሪ ግዛት በነበሩት ህጎች መበለቶች በሞቱ ባሎቻቸው ንብረት ላይ የነበራቸው መብት ውስን ነበር። ጌታ ለመበለቶች እና ለወላጅ አልባ ልጆች ስላለው ስሜት ከክፍል 83 ምን ትማራላችሁ? በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለ እናንተ ከምትሠጡት ፍቅር እና እንክብካቤ ሊጠቀም የሚችል ሰው ታውቃላችሁ? ያላችሁን ለመበለቶች፣ ለወላጅ አልባ ህፃናት፣ ለነጠላ እናቶች እና ለሌሎች እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ልታካፍሉ የምትችሉባቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ምን ናቸው?
በተጨማሪም ኢሳይያስ 1፥17፤ ያዕቆብ 1፥27 ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
“[ድምፄን አውጥቼ እናም በልቤ]” ወደ እግዚአብሔር መፀለይ እችላለሁ።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥3ን ከልጆቻችሁ ጋር ስታነቡ፣ “በዓለም ፊት” እና “በሥውር” መጸለይ የሚችሉባቸውን የተለያዩ ቦታዎች እንዲያስቡ እርዷቸው። እንዲሁም እንደ “Secret Prayer” (መዝሙር፣ ቁጥር 144) ያለ ስለ ፀሎት የሚያወሳ መዝሙር ከእነርሱ ጋር ልታዳምጡ ወይም ልትዘምሩም ትችላላችሁ። መዝሙሩ ስለጸሎት የሚያስተምረውን አንድ ጠቃሚ እውነት አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ። በተጨማሪም ከሰማይ አባት ጋር በጥልቅ አክብሮት ስለመነጋገር ማውራት ትችላላችሁ።
-
ልጆቻችሁ በልባቸው እንዲጸልዩ ለማበረታታት፣ ከወረቀት የተሰሩ ልቦችን ልትሰጧቸው እና ለሰማይ አባት በፀሎት ሊያሳውቁ የሚፈልጉትን ነገር እንዲሥሉ ወይም እንዲጽፉ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። የሰማይ አባት ምን እያሰብን እንዲሁም ምን እየተሰማን እንደሆነ እንደሚያውቅ እና ድምፅ አውጥተን ባንናገርም ፀሎታችንን እንደሚሰማ መስክሩ። በልባችሁ የፀለያችሁበትን እና የሰማይ አባት የሰማበትን አንድ ተሞክሮ ለእነርሱ ልታካፍሏቸው ትችላላችሁ።
ጌታ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን እንድረዳ ይፈልጋል።
-
ከልጆቻችሁ ጋር በመሆን የእጆችን እና የጉልበቶችን ምሥሎች ሣሉ፣ ከዚያም ልጆቻችሁ እነዚህን የሰውነት ክፍሎች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥5 ውስጥ እንዲፈልጉ ጠይቋቸው። በዚህ ጥቅስ ውስጥ ጌታ የሚጠይቀን ምን እንድናደርግ ነው? “ድካም” ወይም “መዛል” በተሰማችሁ ጊዜ ሰዎች እናንተን ያበረታቱበትን አንዳንድ መንገዶች አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። “Pass it on”(ChurchofJesusChrist.org) የተሰኘው ቪዲዮ ልጆቻችሁ ሌሎችን እንዴት ሊያገለግሉ እንደሚችሉ ሃሳብ ሊሰጣቸው ይችላል። እንደ “Have I Done Any Good?” የመሠለ ስለአገልግሎት የሚያወሳ መዝሙርን አብራችሁ ልትዘምሩም ትችላላችሁ (መዝሙር፣ ቁጥር 223)። ልጆቻችሁ በዚህ ሳምንት ቢያንስ አንድ የተቸገረን ሰው ለመርዳት እቅድ እንዲያወጡ መርዳትን አስቡ።
-
እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎችን እንዴት እንዳገለገለ የሚያወሱ ቀላል ታሪኮችን ለመናገር ሥዕሎችን ወይም ቪዲዮዎችን መጠቀም ችላላችሁ (በዚህ መዘርዝር ውስጥ ያሉትን ሥዕሎች፤ የወንጌል የአርት መፅሐፍ፣ ቁጥር. 41፣ 42፣ 46፣ 47፣ 55፤ ወይንም ከBible Videos አንዱን፣ በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ)። የአዳኙን ሌሎችን የመርዳት ምሳሌ እንዴት መከተል እንችላለን?
እርሱን ለመታዘዝ ሥጥር፣ የሰማይ አባት እንደሚባርከኝ ቃል ገብቷል።
-
“የሰማይ አባት ትዕዛዛትን የሚሰጠን ለምንድን ነው?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለሥ እናንተ እና ልጆቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥8–10 ውስጥ መልሶችን መፈለግ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ የእርሱን ትዕዛዛት ምሳሌዎች እንዲያስቡ ለመርዳት ትፈልጉ ይሆናል (ለምሣሌ፣ ዘፀዓት 20፥4–17፤ ማቴዎስ 22፥37–39፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥5–17 ተመልከቱ)። እናንተ እና ልጆቻችሁ አንዳንዶቹን ለመወከል የሚችሉ ሥዕሎችን ብታገኙ ወይም ብትስሉ ሊጠቅም ይችላል። የሰማይ አባት ትዕዛዛት እርሱ ለእኛ ያለውን ፍቅር የሚያሳዩት እንዴት ነው?
-
ምናልባት አንድ ቀላል ጨዋታ፣ ልጆቻችሁ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንደ ሸክም ሳይሆን እንደበረከት እንዲያዩዋቸው ሊረዳቸው ይችላል። አንድ ሠው፣ ዓይኑን የተሸፈነን ሌላ ሠው ሳንድዊች እንደ መሥራት ወይም ሥዕል እንደ መሳል የመሣሠሉ ሥራዎችን እንዲሠራ የሚረዳውን መመሪያ ሊሰጠው ይችላል። አስደሳች እና ፈጠራ የታከለበት ነገርን አስቡ። ከዚያም የእግዚአብሔር ትዕዛዛት እንዴት በጨዋታው ውስጥ እንዳሉት መመሪያዎች እንደሆኑ ተነጋገሩ።